www.maledatimes.com ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ የሚፈታበት ጊዜ ቀረበ! - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ የሚፈታበት ጊዜ ቀረበ!

By   /   October 9, 2017  /   Comments Off on ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ የሚፈታበት ጊዜ ቀረበ!

    Print       Email
0 0
Read Time:1 Minute, 13 Second

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝን እንዴት እንቀበለው? ዳዊት ሰለሞን

Temesegen Dessalegn

=========
ከሞያው ጋር በተያያዘ በተፈበረከበት ክስ ፖለቲካዊ ውሳኔ ተላልፎበት ያለፉትን ሶስት ዓመታት በወህኒ ቤት ያሳለፈው ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በቀጣዮቹ ጥቂት ቀናቶች የወህኒ ቤት ቆይታውን በማጠናቀቅ ቤተሰቦቹን፣አድናቂዎቹንና የሞያ አጋሮቹን በሰፊው እስር ቤት ይቀላቀላል፡፡
ተመስገን በወህኒ ቤት በጨለማ ክፍል ውስጥ፣ከሌሎች እስረኞች እንዳይገናኝ ተደርጎ፣ህክምና ተከልክሎና ለሚበዙ ጊዜያትም ቤተሰቦቹ ጭምር እንዳይጠይቁት ተደርጎ መቆየቱ አይዘነጋም፡፡ሐሳቡን ያለምንም ፍርሃት በመግለጹና መንግስትን በመተቸቱ እንደ ጠላት የተቆጠረው ተመስገን ከወህኒ ቤት ሲወጣ ለከፈለው መስዋዕትነት ክብርና ቦታ የሚሰጥ ወገን እንዳለው ማሳየት ከወህኒ ቤት ውጪ የሚገኙ ሰዎች ግዴታም ውዴታም ይመስለኛል፡፡
ለምሳሌ
በማህበራዊ ሚዲያዎች የተመስገንን ፎቶ ግራፍ የፕሮፋይል ፒክቸር በማድረግና ስለእርሱና በወህኒ ቤት እስካሁን ድረስ ዋጋ እየከፈሉ የሚገኙ የሞያ አጋሮቹን የተመለከቱ ዘገባዎችን በመጻፍ ተመስገንን እንኳን ወደ ዞን ዘጠኝ መጣህ ልንለው እንችላለን፡፡
ቤተሰቦቹን በተመለከተም

የተመስገን ወላጅ እናት ለጠቅላይ ሚንስትሩ ደብዳቤ እስከመጻፍ መድረሳቸው አይዘነጋም(ሐማደ ደብዳቤውን ውጠው ቢቀሩም)፡፡በሽምልግና ዕድሜያቸው ወህኒ ቤት ድረስ እየተመላለሱ ልጃቸውን እንዳያዩ የተደረጉበት አጋጣሚም ሰፋ ያለ ነው፡፡እኚህን እናት ‹‹እንኳን ደስ አልዎት ማለትና ሌሎች የኢትዮጵያ እናቶች እየከፈሉ የሚገኙትን ተመሳሳይ መስዋዕትነት መዘከር ይኖርብን ይመስለኛል፡፡
ታሪኩ ደሳለኝ

የተመስገን ደሳለኝ እስር የወንድሙን የታሪኩን ደሳለኝን አቅም እንድንመለከት አድርጎናል፡፡ታሪኩ በወንድሙ መታሰር ሰበብ ብዙ ነገሮችን ለማጤን መቻሉን በየጊዜው በሚለቃቸው የማህበራዊ ድረ ገጽ ፅሁፎቹ መረዳት አያስቸግርም፡፡
ታሪኩ ለታላቅ ወንድሙ የከፈለው መስዋዕትነት በወንድሙ መፈታት እንዳይቆም ምናልባትም ታሪኩ የጀመረውን ሐሳቡን አቀናጅቶ የመግለጽ አቅሙን አጠናክሮ እንዲቀጥል ልንወተውተውም እንችላለን፡፡
ታሪኩ እንኳን ደስ አለህ ሊባል የሚገባው እውነተኛ ወንድም (አለኝታ)መሆኑን ለብዙዎቻችን በተፈተነ ተግባሩ ማሳየቱን የምንመሰክርበት አጋጠሚም ይሆንልናል የሚል እምነት አለኝ፡፡
እስኪ ሌሎች ሐሳቦችን አፍልቁና ተመስገን እንበል፡፡

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar