www.maledatimes.com የደርግ መቶ አለቃ እሸቱ እና ዘ ሄግ የፍርድ ውሳኔ ክትትል - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

የደርግ መቶ አለቃ እሸቱ እና ዘ ሄግ የፍርድ ውሳኔ ክትትል

By   /   November 3, 2017  /   Comments Off on የደርግ መቶ አለቃ እሸቱ እና ዘ ሄግ የፍርድ ውሳኔ ክትትል

    Print       Email
0 0
Read Time:4 Minute, 4 Second

ክንፉ አሰፋ (ዘ ሄግ)

ለ25 ዓመታት በኔዘርላንድ ውስጥ ሲኖር ሰብዓዊነት ማለት ምን እንደሆነ በደንብ የተረዳ ይመስላል። ምዕራባውያን ለሰብዓዊ ፍጡርየሚሰጡትን ዋጋ ሳይገነዘብ አልቀረም። አምላክ በአምሳሉ የፈጠረውየሰው ልጅ ህይወት ቀርቶ ለእንሰሶች ህይወት የሚሰጠውን ክብር ሌትተቀን እያየ የአመለካከት ለውጥ አያደርግም ብሎ ለመናገር ይከብዳል። እዚህ ሰብአዊ ፍጡርን በፖለቲካ አመለካከቱ መግደል ከቶውንምአይታሰብም።  መግደል አይደለም የሰው ልጅ ላይ እጁን የሚያነሳ፣ ጸያፍስድብ ከአንደበቱ የሚያወጣ እንኳ ባለስልጣን ቢኖር ዋጋ ይከፍላል።

መቶ አለቃ እሸቱ  በዚህ ሕብረተሰብ ውስጥ ለ25 ዓመታትዘልቋል።   ከ25 ዓመት በፊት የነበረውን ትውስታ ሁሉ አጭንቅላቱ ሰርዞአዲስ የስነልቦና ተክለሰውነት ይዞ እየኖረ ነው። በሌላ አገላለጽ ከ30 ዓማታት በፊት የተከሰተውን ሁሉ እንዳያስታውስ ሜሞሪው ሙሉ በሙሉ ታጥቧል።    ‘ወጣቱ የደርግ አባል’ ተብሎ ይጠራ የነበረው መቶ አለቃእሸቱ አለሙ ዜግነቱ ወደ ሆላንዳዊነት ሲቀየር በሱ አመለካከት ሁለ ነገሩ ተቀይሯል።  ከዚያን ግዜ በኋላ  እያቆራረጠ መተንፈስን አቆሞ የነጻነት አየር ያገኘ መስሎት ነበር።  እንደማንኛውም የደች ዜጋ ይኖራል፣ይዝናናል፣  የዜግነት መብቱን ያስከብራል።

“የተሳሳተ ሰው ነው የያዛችሁት” ነበር ያለው መቶ አለቃ እሸቱዓለሙ በዘ-ሄግ ከተማ የዓለም አቀፍ ወንጀል ችሎት ላይ ቀርቦ ቃሉንሲሰጥ። እርግጥ ነው። አሁን “ነጻ ሰው ነኝ” ብሎ ራስን ላሳመነ ሰውከዳይኖሰር የገዘፈ ወንጀል ከላይ ሲጫንበት ማስደንገጡአያስገርምም።  “አቃብያነ-ሕግ በምን እንደከሰሱኝ ስሰማ እጅግተደናግጫለሁ”  በማለት ለፍርድ ቤቱ የተናገረው ቃል ይህንኑያረጋግጥልናል።

ወንጀሉ ከበድ ይላል። በሆላንድ ሃገር (ዓለማቀፉን ችሎት ሳይጨምር)  እንዲህ አይነት የወንጀል ጉዳይ ሲቀርብ የመጀመርያው መሆኑን ነው መገናኛ ብዙሃን የሚነግሩን።   75 ወጣት እስረኞችን መግደል፣  9 እሰረኞችን ማሰቃየት፣  240 እስረኞች ላይ ከባድ ግፍ መፈጸም፣ … ከተዘረዘሩት ክሶች ዋነኞቹ ናቸው።  በሆላንድ የሰብአዊነት አስተሳሰብና ስነልቦና ውስጥ ለሚገኝ ሰው ይህንን ዱብ እዳ በአንድ ግዜ መቀበል ቢከብድም ምላሹ ግን ያስደነግጣል።  “ጎጃም ውስጥ እስር ቤቶች አይቼ አላውቅም!” ብሏል እሸቱ።  የሚደብር አካካድ። መካድ ካልቀረ በደንብ አድርጎ መሸምጠት ነበረበት።   “እኔ መቶ አለቃ እሸቱ አለሙ አይደለሁም። ተሳስታችኋል!” ቢል ነበር ጥሩ ክህደት የሚሆነው።  ከጉዳዩ ባያመልጥም!  “ላታመልጪኝ አታሯሩጭኝ”  ይል የለ ያገሬ ሰው።

በስልጣን ስካር ውስጥ በነበረበት ግዜ ያደረገው የነበረውነገር  ሁሉ ላይታወሰው ይችላል።  በወቅቱ አይኖቹ ሁሉ ተጋርደው  የሚታየው ከፍ ብሎ የወጣበት የስልጣን ማማ  እና በዜጋው ላይሊፈርድ የተቀመጠበት ወንበር ብቻ ነው።  ቀይ ሽብርን ደርሼ በአይኔባላየውም በታሪክ አንብቤያለሁ።  የወጣቱ ደም እንደ ጎርፍ መፍሰስ  በወታደሮቹ  እንደጀብድ የሚታይበት ግዜ ነበር።  በስልጣን ለመቆየትሲሉ ብቻ አንድን ትውልድ እንደዋዛ አጠፉት።  የሚገርመው የአሁኖቹባለተራዎች ከዚህ ያለመማራቸው ነው። እነሱም ደም ማፍሰሱንአላቆሙትም።  ስልት ቀየሩ እንጂ  ትውልዱን  አሁንም እየፈጁት ይገኛሉ።የቤተ መንግስቱን ቁልፍ በእጃቸው ሲያስገቡ የሚታወሩበት አዚም ግራይገባል። ሌላው ቀርቶ የሚያንማርዋ መሪ ኡን ሳን ሱ ቺ – ተቃዋሚሳለች  የኖቤል የሰላም ተሸላሚ ጀግና ነበረች።  ቤተ መንግስት ስትገባ  በአለም አንደኛዋ የተባለው የዘር ማጥፋት ወንጀል ውስጥ ተዘፍቃእየዋኘች ትገኛለች።

ልብ ያለው ልብ ይበል። በህይወት ዘመናቸው ክቡሩን ህይወት የቀጠፉ ሁሉ ደም ይጠራቸዋል። ግዜው ሊቀርብም ሊርቅም ይሽላል።  በመጨረሻ ግን… ማንም ከፍትህ አያመልጥም።  የሰው ደም አይለቅቅም!

እነሆ የ63 አመቱ  እሸቱ አለሙን በሆላንዱ ፍርድ ቆሞ አየሁት። ይህንን ሰው ከዚህ ቀደም አንድ ግዜ ብቻ በአካል አግኝቼ እንዳነጋገርኩት ትዝ ይለኛል። ቀደም ሲል በሆላንድ ላይ “ኢትዮጵያ ወዴት?” በሚል ርዕስ ተዘጋጅቶ በነበር ትልቅ ስብሰባ ላይ ሃሳብ ሲሰጥ በቪድዮ አይቼዋለሁ። ስለ ፍትህ እና ዲሞክራሲ ግንባታ ሲናገር በጣም ያስደምማል።  በእሸቱ ንግግር የተመሰጡት ፕሮፌሰር ጌታቸው ሃይሌ “… አነጋገርርህን  ስሰማ ስልጣኑን ለደርግ መልሰህ ስጥ ስጥ አለኝ” ሲሉ በዚያው ስብሰባ ላይ የተናገሩት የምጸት ቃልም ታወሰኝ።  ከዚያን  ግዜ ወዲህ  እሸቱ በኢትዮጵኖች ስብስብ ላይ ታይቶ አይታወቅም።

ባለፈው ሃሙስ ተጠቂዎች  በ ዘሄግ ፍርድ ቤት ቀርበው ቃልሲሰጡ በስፍራው የነበረው ስሜት የተለየ ነበር። ሰውን  ሁሉ ስሜታዊያደረገው  የተጎጂ ወገኖች ምስክርነት ከተሰማ በኋላ፣  መቶ አለቃ እሼቱ30 ዓመት ወደኋላ በትውስታ ተጉዞ ወደ አእምሮው  የተመለሰይመስላል።     እንባ እየተናነቀውም፣    “በወቅቱ እጅግ አስከፊ ነገርተፈጽሟል።  ይህ ስርዓት ለፈጸመው በደል ሁሉ በጉልበቴ ተንበርክኬይቅርታ እጠይቃለሁ። ”  ሲል ተናገረ። በዚህ ግን አላበቃም።  ወዲያውአንድ ነገር ትዝ አለውና እንዲህ አለ።

“የሚነገረውን ወንጀል ሁሉ ግን  እኔ አላውቀውም!”

ይቅርታው እና ክህደቱ ትንሽ ግራ ያጋባሉ። ድርጊቱንአልፈጸምኩም ካለ – ሰው ራሱ ላልሰራው ወንጀል እንዴት ይቅርታይጠይቃል? ወይንስ  በውክልና  ይቅርታ እንዲጠይቅ ደርግ ሃላፊነትተሰጥቶታል?

እ.ኤ.አ. ጥቅምት 16 ቀን 2018  የሆላንድ ፖሊሶች  የፍርድቤት ማዘዣ  በመያዝ  አምስተልቪን በሚገኘው መኖርያው እሸቱ አለሙንእስካገቱት ድረስ ድምጹም ተሰምቶ አያውቅም።     በደርግ ዘመን  በጎጃም ክፍለ ሃገር ዜጎችን በመግደል፣ በማሰርና በማሰቃየት ተከስሶበወያኔ የሞት ፍርድ የተበየነበት መቶ አለቃ እሸቱ አለሙ  በፖሊስቁጥጥር ስር ከዋለ ሁለት አመት ሞላው።

እሸቱ አለሙን ለፍርድ የማቅረብ ሂደቱ የተጀመረው ከዛሬ 18 አመት ገደማ  ነበር።  በወቅቱ ከገዥው ፓርቲ ደህንነት ሃላፊ የነበሩት አቶክንፈ ገብረመድህን ሆላንድ ሃገር ባሉ ተወካዮቻቸው አማካይነትእንቅስቃሴ ተጀመረና  ግፊቱ ወደ ሆላንድ የኢትዮጵያውያን ማህበርጽህፈት ቤት ደረሰ። በወቅቱ የነበሩት የኢትዮጵያ ማህበር አመራሮችጉዳዩን ከግምት ውስጥ አላስገቡትም ነበር። ለዚህም በቂ ምክንያትነበራቸው።   በስልጣን ላይ ያለው መንግስት ከደርግ የባሰ ወንጀልእየፈጸመ ነበርና።

ወያኔ በቀጥታ የሆላንድ መንግስትን መጠየቅ ሲችል ለምንበዚህ መንገድ መጣ የሚለው ጥያቄ በወቅቱ በእምሮዬ መጣ።  ሁለትምክንያት አለው።   አንደኛው ሁለቱ ሃገራት ወንጀለኛን አሳልፎ የመስጠትስምምነት ስለሌላቸው እና በሁለተኛ ደረጃ ደግሞ የኢትዮጵያ ወንጀለኛመቅጫ ህግ የሞት  ቅጣትን ስላካተተ ነው።

  በወቅቱ የነበረው የማህበሩ አመራር፣  “ግለሰቡ መዳኘትካለባቸው ዘ ሄግ ያለው አለም አቀፉ ፍርድ ቤት ነው” ሲል ጥያቄውንውድቅ ማድረጉ ይታወሳል።

እ.ኤ.አ. በ1998 ዩዲት ኑሪንክ የምትባል ታዋቂ የሆላንድ ጋዜጠኛ  ቢሮዋ ጠርታ ስለዚህ ጉዳይ  አነጋገረችኝ። እሸቱ አለሙ የጎጃም ነዋሪ ወጣቶች እንዲገደሉ እና እንዲታስሩ የፈረመበት ክምር ዶሴ በእጅዋ ነበር።  እንደ ጋዜጠኛ ሃላፊዋነትዋን ብቻ መወጣት እንደሚገባት ተነጋግረን ተለያየን። ጋዜጠኛ  ዩዲት – የኢትዮጵያ ማህበር አመራሮችን  (ጸጋ ታክሉን እና ወንድም አስረስን) እያጣቀሰች መረጃውን በአንድ ተነባቢ መጽሄት ላይ ለቀቀችው። …  ከዚያም ጉዳዩ በሆላንድ የአለማቀፍ ወንጀሎች ምርመራ ቡድን አይን ውስጥ ሊገባ ቻለ።

የሆላንዱ ፍርድ ሂደት ለእሸቱ አለሙ ህልም ሊመስልይችላል።  የሚወዱትን ለተነጠቁት ለሟች ቤተሰቦች ግን እውን ነው።  እሸቱ አለሙን በባእድ ሃገር ፍርድ ቤት ብቻውን ቆሙ ለሚያየው ሰውእጅግ ያሳዝናል።    ከጎኑ አንዳች ሰው የለም።

 በአይኑ ሳይሆን በልቦናው አትኩሮ ለሚመለከተው ሁሉየሚነግረን መልእክት ግን አለ። … “እኔን ያየህ ተቀጣ!”

ይቀጥላል….   የፍርድ ሂደቱ ማክሰኞ ይቀጥላል።  ካቻልኩበምስል ለማቅረብ እሞክራለሁ!

ማለዳ ታይምስ ተባባሪ ከሆላንድ

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar