www.maledatimes.com በዓለማችን ታሪክ ከፍተኛ የሆነው የገንዘብ በጀት ኢትዮጵያ ላይ ተመድቦዋል! ለምን ሚስጥሩን ዳንኤል ቶማስ እንዲህ አስናድቶታል። - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Addis Admas  >  Current Article

በዓለማችን ታሪክ ከፍተኛ የሆነው የገንዘብ በጀት ኢትዮጵያ ላይ ተመድቦዋል! ለምን ሚስጥሩን ዳንኤል ቶማስ እንዲህ አስናድቶታል።

By   /   August 23, 2018  /   Comments Off on በዓለማችን ታሪክ ከፍተኛ የሆነው የገንዘብ በጀት ኢትዮጵያ ላይ ተመድቦዋል! ለምን ሚስጥሩን ዳንኤል ቶማስ እንዲህ አስናድቶታል።

    Print       Email
0 0
Read Time:6 Minute, 1 Second

አስተዋይ ኢትዮጵያውያን ሆይ!አስተውሉ!
ኢትዮጵያ ብታድግና ብትሰለጥን የሚጠላ ዜጋ አይኖርም።ከዚህ አንጻር የዓለም መንግስታትና የዓለማችን ቢሊየነሮች ይህን ከፍተኛ ገንዘብ ኢትዮጵያ ውስጥ ለሚሰሩት ስራ በመመደባቸው ሊደሰት የሚችል ኢትዮጵያዊ በርካታ ሊሆን ቢችል አይገርምም!ሆኖም በዚህ የገንዘብ በጀት ከመደሰት ይልቅ መደንገጥ የሚቀድማቸው አስተዋይ ዜጎች ብዙም ባይሆኑ እንዳሉ አውቃለሁ።ምንም ይሁን፤ለምን?እንዴት?ብሎ መጠየቅን ማስቀደም ተገቢ ነው።
ትናንት ይፋ ከሆነው ዜና ጀምሮ ከወራት በፊት ለጥናት ብቻ ከተመደበው ገንዘብ ጋር የተባበሩት መንግስታትና አሜሪካ እንዲሁም ሌሎች የሃያል አገራት መንግስታት በጋራ በመሆን አጠቃላይ 40 ቢሊዮን ዶላር መድበዋል!የትናንቱን 20 ቢሊዮን ዶላር ጉዳይ በስተመጨረሻ የምናየው ይሁንና፤በቅድሚያ 16.5 ቢሊዮን ዶላር “ለጥናት ብቻ”ስለወጣበት ታሪክ ጥቂት መረጃዎችን ልስጣችሁ።
የህንዱ ማሂንድራ ኮንሰልታንት ከወራት በፊት በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የገንዘብ በጀት ኢትዮጵያ ውስጥ በአራቱም ክልልሎች ለኢንደስትሪ ፓርክ(እንደ እውነቱ ለጦር ካምፕ) የሚሆኑ ቦታዎችን አጥንቶ ለተባበሩት መንግስታት ድርጅትና ለሃያል አገራት እንዲሁም ለዓለማችን ቢሊየነሮች ጥናቱን እንዲያቀርብ ይታዘዛል።
ከኒውክለር ግንባታና ከስፔስ ሳይንስ ጋር በተያያዘ ጥናት የሚያደርገውና እግረመንገዱንም የከባድ ኢንስትሪ ቦታዎችን የሚያጠናው የስፔስ ሳይንስ ጠበብት በሆኑ ሰራተኞች የተሞላው ማሂንድራም ለጥናቱ የጠየቀው ገንዘብ 16.5 ቢሊዮን ዶላር ነበር!እናም ተፈቅዶለት ኢትዮጵያን በረቀቀ የ ጂፒኤስ ቴክኖሎጅ ታግዞ በወራት ውስጥ አጥንቶ ጨርሶ አስረከበ።በዓለማችን የጨረታ ታሪክ ተደርጎ በማይታወቅ ሁኔታም ለጥናት ብቻ የጠየቀውን 16.5 ቢሊዮን ዶላር አምና በ2009 ዓ.ም ተከፈለው።ስለዚህ አጥኝው ቡድን ጥናቱን ጨርሶ ገንዘቡንም ተቀብሎ ወደአገሩ ተመልሶዋል።ይህ ጥናትም ለኢትዮጵያውያውያን “በሚመጥን” መልኩ ወደ አማርኛ ተተርጉሞ ለሚመለከታቸው ቅድመ ስራውን ማስጀመር ለሚችሉ አካላት ይፋ ሆነ።
ይህን ጥናት በፎቶ መልክ ስካን አድርጌ ከስር ስለለጠፍኩላችሁ እያንዳንዱን ገጽ እየከፈታችሁ ማንበብ ትችላላችሁ።
እንግዲህ ከስር እንደምታዩት በ16.5 ቢሊዮን ዶላር፤ማለትም 400 ቢሊዮን ብር አካባቢ የሚደርስ ገንዘብ ለጥናት ብቻ ከተመደበ ለዋናው ስራ ወይም ለዋናው ዓላማ ምን ያህል ገንዘብ ሊመድቡ ነው?የሚለውን ማሰብ አይከብድም!
በዓለማችን ይህን ያህል ከፍተኛ ገንዘብ ለጥናት ብቻ የመደበ አይደለም፤ ይህን ያህል የገንዘብ መጠን በአንድ ጊዜ ኢንቨስት ተደርጎበት የተሰራ ስራ የለም!የተባበሩት መንግስታት ድርጅትም ይህን ያህል ገንዘብ ለአንድ አገር የመደበበት ታሪካዊ አጋጣሚ የለም!በመሆኑም ኢትዮጵያ የመጀመሪያዋ ናት!
አስታውሱ!ኢትዮጵያ ከንጉሱ ዘመን ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ የተበደረችው ገንዘብና አጠቃላይ ያለባት እዳ 22 ቢሊዮን ዶላር አካባቢ ነው!ይህ ሁሉ ህንጻ መንገድ አየር መንገድ ፕሌኑም ተሽከርካሪውም ለጦርነት የወደመው ለልማት የዋለው በባለስልጣን የተዘረፈው ወዘተ ሀሉም ለማለት በሚቻል ሁኔታ በብድርናና በእርዳታ የሆነ ነው።እናም አገሪቱ ላለፊት መቶ አመታት የተበደረችውን 22 ቢሊዮን ዶላር ጨርሶ መክፈል የማትችል አገር ሆና የምትገኝ ናት!እነሱ ግን ለጥናት ብቻ የእዳዋን ያህል ገንዘብ ኢንቨስት አድርጋለች!በዚህ ገንዘብ የሚሰራው ስራ ደግሞ ለኛ ሳይሆን ለእነሱ ጥቅም የሚውል ነው።
ለምሳሌ ለጥናት ይህን ያህል ገንዘብ ከመደቡልን በሁዋላ የኢትዮጵያ መንግስት ተጠንቶ በተሰጠው ቦታ በሁሉም ክልልሎች ቦታዎችን አጥሮ ሰፋ ያሉ ቤቶችን ይሰራል።ሰርቶ ከጨረሰ በሁዋላ በውሉ መሰረት የውጭ ባለሃብቶችን ይጋብዛል!እነዚያ ቢሊየነሮችም ወደ ኢትዮጵያ መጥተው የመረጡትን ቦታ ይረከቡና የየራሳቸውን ማሽን ይዘው ይገባሉ።ለምሳሌ በአማራ ክልል በቡሬ ብቻ 10 ኪ.ሜ ካሬ ቦታ ተከልሎ አጥሩ በ63 ሚሊዮን ብር ከታጠረ በሁዋላ ተራ ኤልሸፕ ቤቶች እየተሰሩ ነው።በቅርቡ ሲያልቁ የሚጠብቁት መራጩን ባለሃብት ነው።ያ ባለሃብት ከፈለገ በጨርቃጨርቅ ከፈለገ በሽቶ ዘርፍ ተሰማርቶ ስራውን ይሰራል ነው።የቶሚ ሄልፋየር የናይክ የወዘተ ካምፓኒ ድርጅቶች ናቸው የሚመጡት።በዚህ ሂደት ኢትዮጵያ የውጭ ምንዛሬ ታገኛለች የሚለውን ብቻ ነው ተዋዋዮቹ የኛ ባለስልጣናት የሚያውቁት።
እስካሁን እንደሚመጡ ቃል የገቡት የአሜሪካ፣የፈረንሳይ፣ የእንግሊዝ እና የቻይና ቢሊየነሮች ሲሆኑ፤ሁሉም በጨርቃ ጨርቅ ዘርፍ ሊሰማሩ ነው ያቀዱት።ፈረንሳይ በጂንስ ፋሽን እና በሽቶ፣ሌሎች ያው በጨርቃጨርቅ ሆኖ በጂንስ በምናምን ነው።እነዚህ ትልልቅ ዓለም አቀፍ ድርጅቶችና ባለሃብቶች ጥሬ እቃውን ከየራሳቸው አገር የሚያስመጡና ኢትዮጵያ አምርተው ለውጭ ገበያ የሚያቀርቡ ናቸው።ምክንያቱም ኢትዮጵያ እነሱ ላሰቡት የሚበቃ የጥጥም ሆነ የሌላ ጥሬ እቃ አቅርቦትን መሸፈን አትችልም።በመሆኑም እነሱ የሚፈልጉት ሰፋፊ ቦታዎችን በውላቸው መሰረት በባለቤትነት ለመያዝ እንጂ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያንን ለማገዝ፣ በንግድ ለማስተሳሰር፣የውጭ ምንዛሬ አስገኝቶ ለመርዳት አይደለም፤ሊሆንም አይችልም!በጥናቱ መሰረት በኢትዮጵያ በአራቱም አቅጣጫ ባሉ ዋና ዋና ክልሎች እየተመሰረቱ ያሉት እንዳሉ ሆነው፤በኢትዮጵያ በየ መቶ ኪሎ ሜትሩ ተመሳሳይ ሰፋፊ ካምፕ እንዲኖራቸው ያዛል!እነዚህ በብዙ ሺ ሄክታር የሚገመቱ ቦታዎች ባለቤትነቱ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ንብረት እንጂ የማንም ሊሆኑ አይችሉም!ምክንያቱም ማንኛውም ባለሃብት ቦታውን ከተረከበ በሁዋላ የመረጠውን ዘርፍ መስራት ጀምሮ ባሻው ጊዜ ማቁዋረጥ ይችላል።ተገቢውን የመሬት ግብር እየከፈለ ለዘለቄታው በባለቤትነት ይዞ መቀጠል ይችላል።የኢትዮጵያ መንግስት “ስራችሁን ባግባቡ አልሰራችሁምና ለቃችሁ ውጡ” የማለት መብትም ሆነ “ምን እየሰራችሁ ነው?” ብሎ መጠየቅ አይችልም!ያን ካለ የግድ በስምምነት ሰነዱ ላይ የፈረመበትን ለጥናቱ ብቻ የተመደበውን 16.5 ቢሊዮን ዶላር መመለስ ወይም ማወራረድ ግድ ይለዋል!እስካሁን የሰራችሁት በቂ ነውና…..ብሎ መሞገትም አይችልም!ምክንያቱም ምንም አይነት ሱሪና ቀሚስ ቢመረት ይህን ያህል ገንዘብ በሁለት ጄኔሬሽን ዘመን እንኩዋን ለማትረፍ ስለማይቻል ነው!ይህ ብቻ አይደለም፤የቤቶቹን አሰራርም ሆነ አጠቃላይ ግንባታውን በፈለጉት ዲዛይን የማሻሻል አፍርሶ የመስራት መብቱም ሆነ የስራ ዘርፉን የመለዋወጥ ሙሉ መብት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ስልጣን እንጂ የማንም አይደለም።ኢትዮጵያዊ ኢንጅነሮችም ሆኑ ተራ ሰራተኞች ስለ ግራውንዱ የማወቅም የመጠየቅም የማየትም ስልጣን የላቸውም!ልብ በሉ!ይህ ገንዘብ በብድር ወይም በእርዳታ ወይም በስጦታ መልክ ለኢትዮጵያ በይፋ የተሰጠ አይደለም!ስለዚህ ስልጣኑ የሌሎች ሃያላን እንጂ የኢትዮጵያውያውያን ሊሆን አይችልም!ይህ ብቻ አይደለም፤ለፈራሚ ባለስልጣኖችም ሆነ ለኢትዮጵያ ህዝብ ግልጽ ያልሆነ ሰፋ ያለ ውስብስብ ነገር ነው ያለው።
ይህ ዘመቻ ኢትዮጵያን ወደ ኢንደስትሪ ዘርፍ ለማሸጋገርና የውጭ ምንዛሬ ለማስገኘት ሲባል፤ በየዋሃን ረጂዎቻችን የተደረገ ነው ብለን አቅልለን የማናይበት ብዙ ምክንያት አለ።እንዲያ ቢሆን ኖሮ የኢትዮጵያን ብቻ ሳይሆን የምስራቅ አፍሪካን ዘርፈ ብዙ ችግር እስከወድያኛው ሊፈታ የሚችልን ግዙፍ ገንዘብ ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያውያንን ሊጠቅም በሚችል መልኩ በይፋ ይለግሱ ነበር እንጂ ይህን ሁሉ ገንዘብ ለጥናት ብቻ ሊመድቡት አይችሉም ነበር!ለኢንደስትሪ ፓርክ የሚሆኑ ቦታዎችን ለማጥናትና ለመምረጥም ይህን ያህል ገንዘብ ሊመደብ አይችልም!ያውም ለጨርቃጨርቅና ፋሽን ልብሶችን ለማምረት ምቹ የሆነን ቦታ ለማጥናት 16.5 ቢሊዮን ዶላር!ወይም 400 ቢሊዮን ብር!ለዚህ ነው እነሱም፤”This investments will be much higher as well as give security and assurance to foreign investors.”ብለው በድፍረት የተናገሩት!
ስለዚህ መደሰት ብቻ ሳይሆን፤ለምን?እንዴት?ብሎ መጠየቅ ከአስተዋይ ኢትዮጵያውያን ይጠበቃል!
በነገራችን ላይ ይህ የቻይናዎቹን አያካትትም።ለምሳሌ በደቡብ ክልል ዋናውና ግዙፉ ካምፕ ይርጋለም ላይ የተከለለው ነው።ስለዚህ የአዋሳው ቀላሉና በአንድ አገር በቻይና ብቻ ታቅዶ የተሰራ ነው።ሌሎች በአዲስ አበባና በዙሪያዋ እንዲሁም በሌሎች ወረዳዎች ያሉትን ጥናቱ አያካትታቸውም።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ደግሞ በትናትናው እለት የዓለምን የበጀት ሪከርድ የሰበረ ሌላ አስደንጋጭ ገንዘብ በአሜሪካ ተመደበ!
በጭስ አባይ ዙሪያ ለሚሰራው የቴክኖለጂ መንደር ብቻ ዓለምን ጉድ ባሰኘ መልኩ 20 ቢሊዮን ዶላር ነው የተመደበው!ግማሽ ቲሪሊየን ብር መሆኑ ነው!መጀመሪያ ካየነው ለጥናት ከወጣው ገንዘብ ጋር ሲደመር 1 ትሪሊየን ብር ከምናምን ሚሊዮን መሆኑ ነው።ይህን ዜና ያልሰማ ካለ ዜናውን እንደወረደ ላካተውና ተጣምሮ ይታይ፤ይገናዘብ።
“በአማራ ክልል በ20 ቢሊየን ዶላር የቴክኖሎጂ ከተማ ሊገነባ ነው፡፡
ባሕር ዳር፡ነሀሴ 12/2010 ዓ.ም (አብመድ)በአማራ ክልል ባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር -ጭስ አባይ ከተማ በ20 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር ወጭ የመጀመሪያው የኢትዮጵያ የቴክኖሎጂ ከተማ ሊገነባ ነው፡፡
የቴክኖሎጂ ከተማው ሀብ ሲቲ ላይቭ ኢትዮጵያ በተሰኘ ፕሮጀክት ነው የሚገነባው፡፡ የአማራ ክልል መንግስት ቦታውን ከወዲሁ አቅርቧል፡፡
የኢትዮጵያ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶክተር ኢንጅነር ጌታሁን መኩሪያ ዛሬ በተካሄደው የመርሃ ግብር ትውውቅ እንዳሉት የቴክኖሎጂ ከተማው የኢትዮጵያን የቴክኖሎጂ ልህቀት ያፋጥናል፡፡የቴክኖሎጂ ሽግግሩንም ወደፊት ያስጉዛል ብለዋል፡፡
የቴክኖሎጂ ከተማው ዋና ስራ አስፈጻሚ ሚካኤል ካሚል “ኢትዮጵያ ቀደምት የቴክኖሎጂ ሀገር እና ለቴክኖሎጂ ቅርበት ባለው አባይ ላይ መገኘቷ የቴክኖሎጂ ከተማዋን ለመገንባት ያነሳሳን ጉዳይ ነው ብለዋል፡፡
“ፕሮጀክቱንም በ7 ዓመታት ውስጥ እናጠናቅቃለን።ከዚያም በብላክ ፓንተር ፊልም ያለችውን የ‹‹ዋካንዳ›› ከተማን በባሕር ዳር እውን እናደርገታለን” ብለዋል፡፡”ይላል ዜናው።ፕላኑም ይፋ ሆኖዋልና ከስር ፎቶውን ከፍታችሁ እዩት።
Technology Hub City ማለት ምን ማለት ነው?
“Ethiopia is the Real WAKANDA”ሲሉስ ምን ማለታቸው ነው?ለምንስ ጭስ ዓባይን መረጡ?አሜሪካስ ይህን ያህል ገንዘብ ለምን በጣና ዘሪያ ብቻ መደበች?የሚለውን፤ከሌላኛው በቻይና በኩል በብዙ ትሪሊየን ዶላር በጣና ዙሪያ ሊገነባ ከታቀደውና፤ባለፈው ዓመት ከክልሉ ባለስልጣናት ጋር በግራንድ ሆቴል ከቻይናው ግዙፍ ኩባንያ ልዑካን ጋር በኢኮ ዞኑ ምስረታ ተስማምተው ከተፈራረሙበት ሌላ ታሪክ ጋር እንመለስበታለን!እስከዚያው ግን ጭስ ዓባይና ጣና ሊለማልን ነው ብላችሁ የተደሰታችሁ የዋህ ዜጎች ፤ጣናን ስለዋጠውና ምንነቱ ስላልተለየው አረም፤ የሚያግዝ አገርና የሚረዳን ወገን ጠፍቶ ሃይቁን እያጠፋው ስለሚገኘው እንቦጭ እያሰባችሁ ጠብቁኝ!

No automatic alt text available.
No automatic alt text available.
Image may contain: textImage may contain: text
Image may contain: textImage may contain: textImage may contain: textImage may contain: text
Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

♦ “ ትክክለኛ ፍትሕ አይሰጡም” የተባሉት የጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኛ ከችሎት እንዲነሱ ተጠየቀ !

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar