www.maledatimes.com የሃገራችን የኢኮኖሚ ጉዞ እና የአሊባባ ከፍተኛ ፍላጎት - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

የሃገራችን የኢኮኖሚ ጉዞ እና የአሊባባ ከፍተኛ ፍላጎት

By   /   August 23, 2018  /   Comments Off on የሃገራችን የኢኮኖሚ ጉዞ እና የአሊባባ ከፍተኛ ፍላጎት

    Print       Email
0 0
Read Time:6 Minute, 22 Second

እርግጥ ነው በአሁኑ ሰዓት “አንዳች ነገር” ውስጥ ስላለን እንዲህ አይነት እውነት ለማስተዋልና ለመመርመር ዝግጁም ፈቃደኛም ላንሆን እንችል ይሆናል።ሆኖም ሌላ ጊዜ መለስ ብለን ልናስተውለው እንችላለንና ይህን መረጃ በወቅቱ መለጠፍን መርጫለሁ።
“አሊባባ ግሩፕ” የዓለማችን ትልቁ የንግድ ተቁዋም ነው።
ባለቤቱም ከዓለማችን ቢሊየነሮች ውስጥ አንዱ የሆነው ቻይናዊው ጃክ ማ ነው።

Jack Ma

የ Jack Ma ‘Alibaba group” የዓለማችን ግዙፉ የኢንተርኔት ገበያ ድርጅት ሲሆን፤በስሩም ዘርፈ ብዙ ኩባንያዎች ያሉት ነው።ባለቤቱ Jack Ma ም የዓለማችን ዋነኛ ተጽእኖ ፈጣሪ ባለሃብት ነው።
በአንድ ሰዓት 3.9 ቢሊዮን ዶላር ሽያጭ የሚያከናውነው የአሊባባ ግሩፕ ባለቤት ጃክ ማ ባሁኑ ወቅት የተጣራ ሀብቱ ማለትም ጥሬ ገንዘቡ ብቻ 43 ቢሊዮን ዶላር ሲሆን፤ከጥሬ ገንዘቡ ውጭ ያሉት ንብረቶች ወደ ገንዘብ ቢለወጡ የዓለማችን አንደኛው ትሪሊየነር መሆን የሚችል ነው።
የ አሊባባ ግሩፕ መስራችና ባለቤት የሆነው ጃክ ማ በኢትዮጵያ ከፍተኛ መዋእለ ንዋይ በመመደብ እንደነሱ አገላለጽ በሞባይል ፋይናንስ ዘርፍ ተሰማርቶ ኢትዮጵያ ውስጥ ስራውን ሊጀምር ነው።
ከቀናት በፊት የአሊባባ ኩባንያ ስራ አስኪያጅ ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ ከኢፊዲሪ ፕሬዘዳንት ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ ጋር ተገናኝቶ ስራውን ለመጀመር የሚያስችለውን ስምምነት ተፈራርሞ ፈቃድም አግኝቶ የተመለሰ ሲሆን፤ስራውን በቅርቡ እንደሚጀምርም ተገልጾዋል።
ዓለም አቀፉ የፋይናንስ ትብብር ምክትል ፕሬዘዳንትም በእለቱ አብረው በብሄራዊ ቤተ መንግስት ተገኝተው በኢትዮጵያ የገንዘብ ተቁዋም ለመመስረት የሚያስችላቸውን የጋራ ስምምነት ተፈራርመዋል።
ዓለም አቀፉ የፋይናንስ ትብብር ማለት የዓለም ባንክ አንዱ አካል ሲሆን፤ድርጅቱ ለምስራቅ አፍሪካ አገራት ብቻ 260 ቢሊዮን ዶላር የሚደርስ የገንዘብ መጠን ለመመደብ የተዘጋጀ ነው።ይህ ይቆየንና በ አሊባባው እቅድ ዙሪያ ጥቂት ነገሮችን በማንሳት ጃክ ማ ማነው?የድርጅቱ እቅድና ዓላማስ ምን ይመስላል?የሚሉትን ነጥቦች ባጭሩ እንይ።ዝርዝር ሃተታውን ደግሞ ከስር ባስቀመጥኩላችሁ ሊንኮች እየገባችሁ ማረጋገጥ ትችላላችሁ።
ጃክ ማ “በዓለማችን ላይ መመስረት ያለበት”Gay Impair”/የግብረሰዶማውያን ግዛት/ ነው!”የሚል አቁዋም ያለው ሲሆን፤ይህንንም በየጊዜው በየመድረኩ በየአገራቱ ደጋግሞ ከመናገርና ከመቀስቀስ ተቆጥቦ አያውቅም።
ጃክ ማ ሌላም ራእይ አለው።”ገዥያችን ቴክኖለጂ እንጂ ሰው ሊሆን አይገባውም”የሚል እምነትና አቁዋም ያለው ሲሆን፤ለዚህም ተፈጻሚነት በድርጅቱ ስር ተግባራዊ እንቅስቃሴ እያደረገ የሚገኝ ነው።
“ከ30 እና።ከ 40 ዓመት በሁዋላ 80% ቱ የዓለም ህዝብ በቴኖለጅ ቁጥጥር ስር ይውላል”በማለትም በቅርቡ ለ ዴይሊ ቻይና ይፋ አድርጎዋል።
ጃክ ማ ቻይና ውስጥ የግብረሰዶማውያን የጋብቻ ህግ እንዲጸድቅ በቻይና መንግስት ላይ ከፍተኛ ጫና እየፈጠረና እየተሙዋገተ ያለ ነው።ለግብረሰዶማውያንም በቢሊዮን የሚቆጠር የገንዘብ በጀት በየዓመቱ ይመድባል።ቻይና በአሁኑ ጊዜ ጾታ የመቀየር እንጂ ጋብቻን ህጋዊ አላደረገችምና ጃክ ማ ቻይና ውስጥ ያሉ ግብረሰዶማውያንን ወደ አሜሪካ ሄደው ህጋዊ ጋብቻቸውን ፈጽመው የሚመለሱበትን ሁኔታ የሚያመቻች ሰው ነው።
ለአብነት ያህል በ April 2015 ላይ በርከት ያሉ ጥንዶችን ወደካሊፎርኒያ ሄደው ህጋዊ ጋብቻቸውን እንዲፈጽሙና የጫጉላ ሽርሽራቸውን እዚያው አሜሪካ ውስጥ እንዲያደርጉ ራሱ ስፓንሰር ሆኖ በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠር ዶላር መድቦ ተጋብተው እንዲመጡ የላከ ሰው ነው።እነሱም ወደ አሜሪካ ሄደው ህጋዊ ጋብቻቸውን በቤተክርስቲያን ፈጽመው ተመልሰዋል።
ጃክ ማ ግብረሰዶማውያንን በይፋ ከመርዳትና ተስፋ ከመስጠት አልፎ፤ የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻ ባልጸደቀባቸው አገራት የሚኖሩ ጥንዶችንም አገርና አህጉር ሳይገድበው በተመሳሳይ ያግዛቸዋል፤ወጪያቸውንም ይሸፍናል።የጋብቻ ህጉ ባልጸደቀባቸው አገራት ለሚኖሩ ግብረሰዶማውያንም በየጊዜው፤
“…Today is hard, tomorrow will be worse, but the day after tomorrow will be sunshine…”በሚል ንግግር ያጽናናቸዋል፤ አሁን ድረስም እየተሙዋገተላቸው ይገኛል።
ይህ ብቻ አይደለም፤ጃክ ማ ግብረሰዶማውያኑ በነጻነት የሚገናኙበትን ነጻ ዌብሳይት ፈጥሮ በነጻ እንዲገናኙና የልምድ ልውውጥ እንዲያደርጉ፤እርስ በርስ እንዲረዳዱ፣ ለመብታቸው እንዲነሱ፣ዛሬ ድረስ በመቀስቀስ ላይ የሚገኝ ሰው ነው።ለእነሱ የሚሆን ሽልማት አዘጋጅቶም የህይወት ታሪካቸውንና የፍቅር ታሪካቸውን እያዘጋጁ ቪዲዮውን እንዱልኩና ከፍ ያለ ሽልማት እንዲያገኙ እድሉን አመቻችቶላቸዋል።በየዓመቱም 75ሺ ቪዲዮ የሚደርሰው ሲሆን፤እያወዳደረ እየሸለመ፤የሚደርሱትን የብልግና ታሪክ የያዙ ቪዲዮዎችንም ለሌሎች ግብረሰዶማውያን እያካፈለ፤እየሸጠ እየለወጠ ደንበኞችንም እያበዛ ይገኛል።
የጃክ ማ እርኩስ ተግባር በዚህ ብቻ የተወሰነ አይደለም።የስነልቦና ጫና ደርሶብናል ለሚሉ ግብረሰዶማውያን በመቆርቆርና “ባል አጣን” “ሚስት አጣን” ለሚሉ ግብረሰዶማውያን በስሩ ባሉ ድርጅቶች አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ በሚባለው ዘዴ ሮቦት የሆኑ ሰዎችን እያመረተ ያቀርብላቸዋል።በእሱ የሮቦቲክስ ካምፓኒ ስር የሚሰሩ ሁለመናቸው ሰው የመሰለና የሚያወሩ፣የሚንቀሳቀሱ፣ ስሜት ቀስቃሽ የሆኑ ቃላቶችንና እንቅስቃሴዎችን የሚያደርጉ፣የተፈጥሮ የመሰለ ሙሉ አካል ያላቸውና ፍጹም በሰው አምሳል የሚሰሩ ሮቦቶችን እያመረተ ያቀርብላቸዋል።አቅም ያለው ይገዛል፤አቅም የሌለው ግብረሰዶማዊ ድህነቱን አስመስክሮ በነጻ እንዲያገኝ ያደርጋል።
ጃክ ማ ስለ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ማለትም ስለ ሮቦት አውርቶ አይጠግብም።ትራምፕንም ሆነ ቤኒያሚ ኔታኒያሁን እንዲሁም ሌሎችን የሃያል አገራት መሪዎች ሲያገኛቸውም ሆነ ከትልልቅ ቢሊየነሮችና ከየቴክኖለጂ ባለቤቶች ጋር ሲገናኝ ቅድሚያ የሚያብራራውና የሚሰብከው ስለዚሁ ስለ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስና ስለ ሮቦት ጥቅም ነው።
“ሰው ሊሰራው የማይችለውን ነገር ሮቦት ይሰራዋል”በሚል ሰበብና መነሻ፤እንዲሁም ቁልፍ ማህበራዊ ችግሮችን ለመፍታት፣ ሰዎች ከበሽታ ራሳቸውን ነጻ ለማድረግና በጋብቻ ችግር ለሚሰቃዩ፣በሃብት ክፍፍል ምክንያት ማግባትን ለሚጠሉ ወዘተ መፍትሄው የሮቦት ቴክኖለጂ ነው”በማለት ለዘርፉ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ የሚገኝ ሰው ነው።በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ አማካኝነትም የሰውን እድሜ ማርዘም እስከሚቻልበት ደረጃ ልንደርስ እንችላለን የሚል እቅድ ያለው የዓለማችን ተጽእኖ ፈጣሪ ባለሃብት ነው።
በዓለም ላይ የጌይ ኢምፓየር መመስረት እንዳለበትም ያምናል ይደግፋል።እርግጥ ነው ብቻውን አይደለም፤የሃያል አገራት መሪዎችና የዓለማችን ቢሊየነሮች፣የተባበሩት መንግስታት ድርጅት፣ኢሮፒያን ዩንየን፣ወዘተ…ሁሉም ዓለማችን የሚዘውሩ ድርጅቶች፣ ተቁዋማትና መንግስታት፤እንዲሁም ጃክ ማን የመሳሰሉ ቢሊየነሮች በጋራ እየተረባረቡለት ያለው ጉዳይ ነው።የጃክ ማ አስተዋጽኦና ግፊት እንዲሁም ተግባራዊ እንቅስቃሴ ግን ለየትና ጠንከር ያለ ነው።ይህ ሰው ነው በኢትዮጵያ የሞባይል ፋይናንስ ዘርፍ ሊሰማራ የተፈራረመው!
እርግጥ ነው የአሊባባ ግሩፕ ለጊዜው እሰማራበታለሁ ብሎ የጠየቀውና ተፈቅዶለት የተፈራረመበት ዘርፍ “የሞባይል ፋይናንስ”ዘርፍ ነው።
ይህ ቴክኖለጂ ደግሞ እንግዳ ያልሆነና የተለመደ፤አሁንም በየአገራቱ እየተሰራበት ያለ ዘርፍ ነው።
በተለይም በምስራቅ አፍሪካ በኬንያና በውጋንዳ ይህ አይነቱ አሰራር ተግባራዊ ከሆነ አስር አመት ሞልቶታል።
ለምሳሌ በኬንያ ኤም ፔሳ በመባል የሚታወቀው የስልክ ግብይት ለፈጣን የገንዘብ ልውውጥ ጠቃሚ ሆኖ ተገኝቶዋል።ሆኖም አገልግሎቱን ተግባራዊ እንዲሆን ያደረገው አንድ ወጣት ኬንያዊ ተማሪ ነው።ለዚህ ፈጠራውም ከሳፋሪ ኮም(ከቴሌ) 1ሚሊዮን ሽልንግ ነው የተሰጠው።እንጂ ይህ አይነቱ ሲስተም በዓለም ቢሊየነሮች በእነ አሊባባ ደረጃ የተሰራና ከፍተኛ መዋእለ ንዋይ የጠየቀ አይደለም።
የሞባይል ፋይናንስ ማለት ማንኛውም ሲም ካርድ ያለው ሰው ያለምንም ኢንተርኔት በስልክ ቁጥሩ ተመዝግቦ ልክ ካርድ እንደምንላላከው የገንዘቡን መጠን ነግሮ፣የራሱን የቁጥር ኮድ ሞልቶ መላክና መቀበል፤በየሱቁ ሄዶም በጥሬ ገንዘብ መለወጥና ሳይለውጥም ከስልክ ወደስልክ ልኮ የሚፈልገውን ሸቀጥ መሸመት የሚችልበት ዘዴ ነው።
በየመንደሩ የ ኤም ፔሳ ወኪል የሆኑ ሱቆች ስላሉ በስልክ የተላከላቸውን የገንዘብ መጠን ወደስልካቸው መግባቱን ካረጋገጡ በሁዋላ እዚያው በዚያው ጥሬ ገንዘቡን ለተገልጋዩ ቆጥረው ይሰጣሉ።ከተገልጋዩም ትንሽ ሳንቲም የአገልግሎት ይቆርጣሉ።በዚህ አይነት በስልክ ብቻ ቤታቸው ሆነው የውሃ የመብራት የወዘተ ክፍያዎችን ይፈጽማሉ።
ስለዚህ ይህ የሞባይል ፋይናንስ ግብይት ሲስተም የተለመደና እንግዳ ያልሆነ ከመሆኑም በላይ፤ከቴሌኮምና ከባንክ ጋር በሚኖር ግንኙነት ብቻ በቀላሉ ግልጋሎቱን መስጠትና ተገልጋዩም አገልግሎቱን ማግኘት የሚችልበት ዘዴ ነው።እንዲያውም እንደእኛው አገር ኤም ብር መጀመሪያ ከባንክ ጋር ግንኙነት መመስረትና በጥሬ ገንዘብ አካውንት ከፍቶ ማስቀመጥ አያስፈልግም።
ሲም ካርዱን ብቻ ለ ኤምፔሳ አክቲቭ በማድረግ የራስን የኮድ ቁጥር መቀበልና የአገልግሎቱ ተጠቃሚ መሆን ይቻላል።ሲም ካርዱን አክቲቭ ከሆነና የራሳችን የኮድ ቁጥር ከያዝን በሁዋላ ሌላ ተጠቃሚ ወደስልካችን ገንዘብ መላክ ይችላል።ያን ገንዘብም በየሱቁ ወደጥሬ ገንዘብ ለውጦ መጠቀም ለሌሎችም መላክ…እያለ የሚቀጥል ነው።ስለዚህ ይህ ሲስተም ቀላልና የተለመደ እንጂ እንግዳ ያልሆነ ነገር ነው ማለት ነው።
ነገር ግን ጃክ ማን በዚህ ዘርፍ ሲሰማራ፣ የሞባይል ፋይናንስን ይዞ ሲመጣ፣ ራሱ ጃክ ማ እና ዓላማው ወደ ኢትዮጵያ መግባታቸውን መገንዘብ ያስፈልጋል!ጃክ ማ ደግሞ ዓላማው ግልጽ ነው።በአምላክ አምሳል የተፈጠረውን የሰው ልጅ በቴክኖለጂ አሳስቦ፣ በቴክኖለጂ ክብ ውስጥ አስገብቶ፣ ሰውን እንደ እቃ ማድረግና በቀላሉ መቆጣጠር መቻል ነው።ለዚህ ደግሞ ቅድመ ስራ አለው።ጃክ ማ ቅድመ ስራውን መጀመሩ ነው።ቅድመ ስራውም አገባቡን ማሳመርና ማቅለል ስለሆነ እሱኑ እያደረገ እንዳለ መቁጠር አጉል ተጠራጣሪነት መሆን ማለት አይደለም።
እኔ ይህን የምለው ለመቃወም ወይም ለማስቆም አይደለም።ወይም መንግስት የመጡትን ሁሉ ዓለም አቀፍ ባለሃብቶች ፈቃድ መስጠት የለበትም እያልኩም አይደለም።ፊልተር እየተደረጉ፣ ባክግራውንዳቸው እየተፈተሸ በየዘርፉ ይሰማሩ ለማለት አይደለም።የአገር ሉአላዊነት ቅድሚያ ሊሰጠው ይገባልና መንግስት ይጠንቀቅ፣ያስቁምልን፣ ለማለትም አይደለም።ይህን ብሎ ማስቆምም አይቻልም።እነሱም እሽ ብለው አይቆሙም፤ የዘመኑ መንግስትም ማገዝና ማመቻቸት እንጂ በተቃውሞ መግታት አይችልም።ይህ ለብዙዎቻችን ግልጽ ነው።ሆኖም ግን በግለሰብ ደረጃ መዘናጋት እንዳይኖርና ቢያንስ እያወቅን ብናልቅ የተሻለ ስለሚሆን ነገሮችን በየግላችን እንመርምር ለማለት ነው።ምርጫችን በየግላችን ይሆን ዘንድ ቢያንስ ማወቅ አለብን ለማለት ነው።ቴክኖለጂና ዘመናዊነት እንዲሁም ቀልጣፋ አሰራር ሁሉ ለክፋት ተግባር የሚውል ነው ለማለትም አይደለም።ቴክኖለጂ ሁሉ ለቅን ተግባር ብቻ የሚውል በቅን ባለሃብቶች ለቅን ዓላማ ብቻ የሚዘጋጅ እንዳልሆነ ለመጠቆም ነው።ምን እየተከናወነ እንዳለ ለማወቅ ይረዳን ዘንድ ነው።ሁሉም ነገር ለሰዎች ጥቅም ብቻ ታስቦ ከተቆርቁዋሪ ሰዎች በኩል እየተበረከተልን አድርገን ከመውሰድ ይልቅ ለምንና ለማን ዓላማ እየዋለ እንደሆነ ማሰብን እንለማመድ ዘንድ ዘንድ ነው!
የአምላክ ትእዛዝና የበላይነት በቴክኖለጂ የበላይነት እየተሸረሸረ፣እየከሰመ፣እየጠፋ፣መሄዱን መገንዘብና መጠንቀቅንም እንዳንዘነጋ በሚል ነው።
በዲሞክራሲ ስም የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻ የምድር መንግስታት ህግ እንደሆነው ሁሉ፤በቴክኖለጂ ስምም ነብስን እስከመስጠት ደረጃ የሚደርስ አሰራር ሊዘረጋ እንደሚችል ብቻ ሳይሆን አየተዘረ እንዳለ ለመጠቆምና ለማንቃት ያህል ነው።ስለዚህ አስተዋዮች አስተውሉ!!!

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar