www.maledatimes.com ከጥላሁን ገሰሰ ኢትዮጵያ እስከ መሃሙድ ሰላም ….ኢትዮጵያ ልተገባ ዝግጅቱን አጠናቀቀች ፣ አቦነሽ አደነው በዝማሬ ሸኘቻት!! - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

ከጥላሁን ገሰሰ ኢትዮጵያ እስከ መሃሙድ ሰላም ….ኢትዮጵያ ልተገባ ዝግጅቱን አጠናቀቀች ፣ አቦነሽ አደነው በዝማሬ ሸኘቻት!!

By   /   August 25, 2018  /   Comments Off on ከጥላሁን ገሰሰ ኢትዮጵያ እስከ መሃሙድ ሰላም ….ኢትዮጵያ ልተገባ ዝግጅቱን አጠናቀቀች ፣ አቦነሽ አደነው በዝማሬ ሸኘቻት!!

    Print       Email
0 0
Read Time:2 Minute, 23 Second

ሁለገብ የኪነጥበብ ባለሙያዋ ዓለም ጸሐይ ወዳጆ በሐገሯ ውስጥ በነበራት እድሜ ለሐገራችን ያበረከተችውን አስተዋጽኦ ከሐገሯም ከራቀች በኋላ የኢትዮጵያን ታሪክ ባህል እና ኪነጥበብ ለማስተዋወቅ ላደረገችው ትጋት ለማመስገን እንዲሁም ልምዷን እና ሙያዋን የምታካፍልበት ባለሙያዎች እና የጥበብ አድናቂዎችም እውቀት የምናተርፍበት መድረኮች እየተመቻቹ ነው፡፡
ይሄ መድረክ ሲዘጋጅ በቅድሚያ ዓለምጻሐይን ለማያውቃት ሆኖም ግን የምን ግዜም ምርጥ ከሆኑት የፈጠራ ስራዎቿ ጋር አብረን የኖርን የጥላሁን ገሰሰን “ኢትዮጵያ”ን በየመድረኩ ያቀነቀነን፣ “ሰላም” የተሰኘው መሓሙድ አህመድ የተጫወተውን ተወዳጅ ዘፈን የምንወድ ስለ ዓለም ሰላም የሚነሱ ሃሳቦች እና የሚፈጸሙ የሰላም ስምምነቶች በ ‹‹ሰላም›› ሙዚቃ ሲታጀብ ሐሳባችንን የሚያጎለብትልን ፣ ለሰላም ስንጨባበጥ ስሜትን ከውስጥ ፈንቅሎ እጅ ለእጅ የሚያያይዘን፣ በደስታ የሚያስነባን፣ የሚያስተቃቅፈን ዘመን ተሻጋሪ የሆነው ድንቅ ግጥም እና ሌሎችም በርካታ ስራዎች ፈጣሪ ዓለምጸሐይ ወዳጆ መሆኗን ለማናውቅ በስራዎቿ ማስተዋወቅ እና ማስታወስ ተገቢ በመሆኑ ነው፡፡
ዓለም ጸሐይ ባለፈው ጽሑፌ ዘርዘር አድርጌ የጠቀስኳቸውን በርካታ ስራዎች ከመስራቷም በተጨማሪ ከ27 ዓመታት በኋላ ወደ ናፈቀቻት ሐገሯ ስትመለስም ባዶ እጇን አይደለም፡፡ ግጥሞችን፣ ወጎችን፣ ለዘመናት በኢትዮጵያ ላይ ሆኖ ለማየት የጓጓችበት የለፋችበትን አሁን እውን ለማድረግ የተነሳችበትን ታላቅ ሐሳብ፣ ከዜማ ሊዋሃዱ በድምጻዊያን ሊቀነቀኑ የተሰናዱ በርካታ የዘፈን ግጥሞችንም ይዛ ነው፡፡
ዓለም ፀሐይ ለ27 ዓመታት በአካል ከተለየቻቸው ቤተሰብ እና ወዳጆቿ ጋር ልትገናኝ ነው፡፡ በተፈጥሮ የምንታደለውን ዜግነት እና ሐገር ተነጥቆ በስደት መኖር ብዙ ህመም አለው፡፡ ይሄን የዜግነት በረከት ማነው የሚነጥቀው? ማነውስ የሚመልሰው? የሚፈጠረው ህመምስ እንዴት ያለ ነው? የሚለውን ለመግለጽ ከወራት በፊት በደራው ጨዋታ ፕሮግራም ላይ ዓለም አቀፍ ታዋቂነት ያተረፈችው የደበቡ አፍሪካዊቷን ሚሪያም ማኬባን ታሪክ እንደምሳሌነት በመጥቀስ በሷ የስደት ህይወት ታሪክ ውስጥ ከሐገር ተሰደው በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያኖችን ህመም ለማሳየት በማሰብ ሚሪያም ማኬባ ለአንድ መጽሔት የሰጠችውን ቃለመጠይቅ ተርጉመን በደራው ጨዋታ ፕሮግራም ላይ አቅርበነው ከነበረው እና ሚሪያም ማኬባ ስለስደት ከተናገረቸው ጥቂቱን እናካፍላችሁ፡፡
– ሚሪያም ማኬባ ፡- ‹‹ ሐገር በችግር ውስጥ በነበረችበት ጊዜ በስደት ውጪ ሐገር ኖሮ ሁኔታዎች ሲስተካከሉ ወደ ሐገር ተመልሶ ሰዎች ላይ ይፈጸም የነበረውን ማየት እና መስማት ያማል፡፡ አቅመቢስነት እና አንዳንዴም የጥፋተኝነት ስሜት ነበር የሚሰማኝ፡፡ ሐገር ለመግባት እንዳልችል መታገዴ በጣም ከባድ ህመም ነው፡፡ ሆኖም ግን ሐገሬ ከወገኖቼ ጋር ችግሩን ተካፍዬ፣ አብሬያቸው ሆኜ አንድ ነገር እንኳን አለማድረጌ ድንጋይ እንኳን አለመወርወሬ ከሐገሬ ውጭ ተቀምጬ ሁሉም ሆኖ ሁሉም ተቀየሮ ማየት ከባድ ህመም አለው፡፡ አንዳንዴ ከሐገር ቤት ለቤተክርስቲያን ዝማሬ ፣ ለአገልግሎት ወይም ለሌሎች ጉዳይ ወገኖቼ ወዳለሁበት ሐገር ይመጣሉ የመጡበትን ጉዳይ ጨርሰው ወደ ሐገርቤት ሲመለሱ አየር ማረፊያ ድረስ ሄጄ እሸኛቸዋለሁ፡፡ እጆቼን እያውለበለብኩ ከተሰናበትኳቸው በኋላ መኪናዬ ውስጥ ገብቼ አለቅሳለሁ… አልቅሼ አልቅሼ ሲደክመኝ እራሴን ለማጽናናት አንድ ቀን እኔም ወደሐገሬ እመለሳለሁ ብዬ አስባለሁ መልሶ ግን ሃሳቤ በጥቁር ጭጋግ ሽፍን ይልብኝና ምንድነው የማወራው ምናልባትም መቼም መቼም ሐገሬን አላያት ይሆናል ብዬ ተስፋ እቆርጣለሁ፡፡ ለእኔ እጅግ ከባድ የነበረው አሁንም ድረስ ሳስበው የሚያመኝ እናቴ ስትሞት በቀብሯ ላይ ተገኝቼ አፈር አለማልበሴ ነው፡፡ እናቴን አልቀበርኳትም፡፡››
ዓለምጸሐይ ወዳጆም ወላጅ እናቷን ፣ ወላጅ አባቷን፣ የትዳር አጋሯን እና የልጆቿን አባት ቆማ ለመቅበር አልታደለችም፡፡ እርሟን ልታወጣ ፣ ከ27 ዓመታት በኋላ ከወገን ከቤተሰቦቿ ጋር በዓይነስጋ ልትተያይ፣ ልምዷን እና እውቀቷን በአካል ተገኝታ ልታካፍል ለሐገሯ ያሰበችውን ያለመችውን ልትፈጽም ማክሰኞ ነሐሴ 22/2010 ዓ.ም ከጠዋቱ በአንድ ሰዓት ወደ እናት ሐገሯ ልትመጣ ነው፡፡
በሰላም ለሐገርሽ ያብቃሽ
አዜብ ወርቁ

በትላንትናው እለት በዋሽንግተን ዲሲ የአለም ጸሃይ ወዳጆ ሽኝት ፕሮግርም ላይ በተሳተፉ ሰዎች መካከል የቀድሞዋ የሙዚቃ ባለሙያ የአሁኗ ዘማሪ አቦነሽ አድነው በሽኝት ፕሮግራሙ ላይ በመታደም እግዚአብሄር ላደረገልን እንዘምራለን እናመሰግነዋለን ስትል አዜማለች።

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 6 years ago on August 25, 2018
  • By:
  • Last Modified: August 25, 2018 @ 1:10 pm
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar