www.maledatimes.com ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ የምህረት አዋጁ ኮ/ል መንግስቱ ሃይለማርያምን አይመለከትም አሉ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ የምህረት አዋጁ ኮ/ል መንግስቱ ሃይለማርያምን አይመለከትም አሉ

By   /   August 25, 2018  /   Comments Off on ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ የምህረት አዋጁ ኮ/ል መንግስቱ ሃይለማርያምን አይመለከትም አሉ

    Print       Email
0 0
Read Time:1 Minute, 47 Second

by: Zehabesha

(ዘ-ሐበሻ) ዶ/ር አብይ አህመድ ከአንድ መቶ ሃያ በላይ ጋዜጠኞች ጋር ዛሬ ጠቅላይ ሚኒስተር ከሆኖ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ አድረጉ:: በዚህ ቃለምልልስ የተለያዩ ጥያቄዎችን ያስተናገዱት ዶ/ር አብይ “በሁሉም ዘነድ ቅቡልነት ያለው የምርጫ ተቋም እንዲፈጠር እንሰራለን፡፡” ብለዋል::

የምህረት አዋጁን ተከትሎ “ኮ/ል መንግስቱ ሀ/ማርያም በምህረት አዋጁ መሰረት ይቅርታ ተደርጎላቸው ሊመለሱ ይችላሉ?” በሚል ለቀረበላቸው ጥያቄ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሲመልሱ ” የቀይ ሽብር ወንጀል በምህረት አዋጁ አይካተትም። ይህ በህገ- መንግስቱም ያለ ነው ስለዚህ አሁን ባለው ሁኔታ አይመጡም። ህገ- መንግስቱ ወደፊት የሚሻሻል ከሆነ ግን የእሳቸው ጉዳይም በእዛው የሚታይ ይሆናል።” በማለት አሁን ያለው የምህረት አዋጅ የቀድሞውን የኢትዮጵያ ፕሬዚዳንት እንደማይመለከት ተናገረዋል::

በኢህ አዴግ ውስጥ ልዩነት አለ ስለሚባለው ለተጠየቁት ጥያቄ “ኢህአዴግ በቅርቡ ባካህሄደውደው ጉባኤ ይዟቸው በገባቸው አጀንዳዎች ላይ በመግባባት ነው የተለያየው፡፡ልዩነት አለ የሚባው መሰረት የለውም፤ ልዩነት ቢኖር እንኳን መሰል ድምፆች እንዲደመጡ ነው የምንፈልገው፡፡ ኢህአዴግ ከላይኛው አመራሩ ሙሉ ለሙሉ ታድሷል ማለት አይቻልም፡፡ጅምሩን አጠናክሮ ለመሄድ እየጣርን ነው፡፡” ብለዋል::

“ወንጀል ሰርተው ማህበረሰቡ ውስጥ የተደበቁ ባለስልጣናት ጊዜው ይረዝማል እንጂ ከመጠየቅ አይድኑም፡፡የተሟላ ማስረጃ ሲገኝ ወደ አደባባይ ይወጣሉ፡፡” ያሉት ዶ/ር አብይ ቀጣዩን ምርጫ ኢህ አዴግ ሊያራዝመው ይችላል ወይ በሚል ለቀረበላቸው ጥያቄም “ኢህአዴግ ቀጣዩን የምርጫ ጊዜ የማራዘም ሀሳብ የለውም፡፡ስለማራዘምም አልተወያየም፡፡ ሆኖም ግን ምርጫው ያለምርጫ ኮረጆ በዘመናዊ የኤሌክትሮኒክ መንገድ በተያዘው ጊዜው እንዲካሄድ ነው ፍላጎታችን፡፡ የኢትዮጵያን ህዝብ መምራት የምፈልገው በምርጫ ካሸነፍኩ በሁዋላ ነው።” ብለዋል::

አንድ ሰው ከተገደለ በኋላ ምንም ማስረጃ ሳይኖር በነጋታው ይኼ ነው የገደለው ተብሎ እንደማይነገር የገለጹት ዶ/ር አብይ ” የኢ/ር ስመኘው ሞት እኔ በቀደም ካደረግኩት ንግግር ጋር ይገናኛል መባሉን አልቀበልም። በቅርቡ በግድቡ ላፕ የወሰንንነው ውሳኔ ኢ/ር ስመኘውን የሚደግፍ ነበር። የኢንጅነር ስመኘው ሞት የሚያሳዝን ነው፤ ስለአሟሟቱ ጥብቅ ክትትል ተደርጓል፡፡ ይህም ጉዳይ በምስራቁ የአገሪቱ ክፍል በተከሰተው አለመረጋጋት የምርመራ ውጤቱ ገለፃ ዘግይቷል:: በቅርቡ ባለሙያዎቹ የደረሱበትን ውጤት ለህዝብ ያሳውቃሉ፡፡ የሰኔ 16ቱ ጥቃት በሚመለከት ውጤት በሚመለከት ባለሙያዎች የደረሱበትን ማስረጃ ለህዝብ ያሳውቃሉ፡፡ የምርመራ ውጤቱ ገለፃ የዘገየው የተጣራ መረጃ ለህዝብ ለማቅረብ ሲባል ነው፡፡” ብለዋል::

“አሁን ያለውን ለውጥ አለመገንዘብ ከባድ እንደሆነ የሚገልጹት ዶ/ር አብይ ከለውጡ በፊት እኮ አዲስ አበባ ተከባ እንደነበር ገልጸዋል:: የትግራይ ከፍተኛ አመራሮች ለውጥ እንደሚፈልጉ ሆኖም ግን አንዳንድ ከስልጣን የወረዱ እና በጡረታ የተሰናበቱ ግን ቅሬታ ሊኖራቸው እንደሚችል ገልጸው ኢህአዴግ አይዲዮሎጂ ለውጥ ንግግር እስካሁን እንዳላደረገና ያለው ስርአት እንደሚቀጥል ተናግረዋል::

ጠቅላይ ሚኒስተሩ ከጋዜጠኞች ጋር ከ2:30 በላይ ተወያይተዋል ሙሉውን ውይይት በዘ-ሐበሻ ኦፊሻል ዩቱብ ገጽ ይዘን እንቀርባለን::

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 6 years ago on August 25, 2018
  • By:
  • Last Modified: August 25, 2018 @ 12:31 pm
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar