www.maledatimes.com ለመጀመሪያ ጊዜ የኢትዮጵያን ቀን በሚኖሶታ በደመቀ ሁኔታ ተከበረ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

ለመጀመሪያ ጊዜ የኢትዮጵያን ቀን በሚኖሶታ በደመቀ ሁኔታ ተከበረ

By   /   September 3, 2018  /   Comments Off on ለመጀመሪያ ጊዜ የኢትዮጵያን ቀን በሚኖሶታ በደመቀ ሁኔታ ተከበረ

    Print       Email
0 0
Read Time:1 Minute, 37 Second

በትላንትናው እለት በሚኖሶታ ግዛት ለመጀመሪያ ጊዜ የተዘጋጀው የኢትዮጵያን ቀን ከተለያዩ ስቴቶች እና ከካናዳ የመጡ ኢትዮጵያኖች በክብር እና በድምቀት ተከብሯል ። ከካናዳ ዊኒፒንግ፣ ችካጎ ፣ ሳውዝ ዳኮታ ፣ ዊስካንሰን ፣አይዋ እና ኖርዝ ዳኮታ የመጡ ኢትዮጵያውያኖች ከሚኖሶታ ነዋሪዎች ጋር በመሆን በጋራ በድምቀት አክብረዋል።

በዚህ የመጀመሪያው የኢትዮጵያውያኖች በአንድነት የመደመር እና በአዲስ አመት አዲስ ቀንን በማስመልከት የኢትዮጵያኖች ቀን ተሰይሞ መከበር መጀመሩ አስደሳች ነው ሲሉ ብዙሃኖች ገልጸዋል።

ከአዘጋጆች መካከል ከነበሩት ውስጥ የዘሃበሻ ዋና አዘጋጅ የሆኑትን አቶ ሄኖክ አለማየሁን ለምን እንደጀመሩ ስንጠይቃቸው በሚኖሶታ ብዙ ኢትዮጵያውያኖች ቢኖሩም በተለያዩ የፖለቲካ አመለካከታቸው መሰረትን በማድረግ የተራራቁ የነበሩ ሲሆን ዛሬ ግን ሁላችንም ይህንን ልዩነቶቻችንን አጥብብበን በአንድነት በጋራ መስራት እና መተባበር በጋራ የተጎዳ ሰው ካለ በመርዳት የተቸገረን በማገዝ እንዲሁም ለሃገራችን በጋራ በመቆም በበአሎቻችን በድምቀት ማክበር ግዴታችን ስለሆነ ኢትዮጵያኖችን ማገናኘት የእኛ ተግባር መሆን አለብን ብለን እንጠብቃለን ሲሉ ገልጠዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ በችካጎ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኮሙኒቲ አሶሴሽን ኦፍ ሽካጎ እና ሌሎች ከተመሰረተ ከሰላሳ አራት አመታት በላይ ቢቆይም በኢትዮጵያን ቀን አከባበር ላይም ግንባር ቀደሙን ቦታ ይዞ በከተማዋ እምብርት ላይ ለሶስት አስርተ አመታት የኢትዮጵያን ባንዲራ በየአመቱ መስቀሉ ለህዝቦቿ ክብር ሲያግጎናጽፍ ፣ለልጆቻቸው ባህሉን እና እሴቱን ሳያስተምር ቆይቷል፣ታዲያ ይህንን ትልቅ በአል በሚኖሶታ በዘሃበሻ ሚዲያ ይህንን በአል ማዘጋጀቱ በህዝቦቹ ዘንድ ሊከበረ እና ሊመሰገን ይገባዋል። 

እንደ ዘሃበሻ አዘጋጅ አገላለጽ ከሆነ ከዛሬ ጀምሮ በየአመቱ በሚኖሶታ የኢትዮጵያን ቀን  ይከበራል እና ቀጣይነቱ ከሁሉም ኢትዮጵያን ህዝቦች ጋር ፣በጋራ ሆነን እናከብራለን ሲል ገልጾአል።

ማለዳ ታይምስ መረጃ ማእከል ከስፍራው ሆኖ ይህንን ዘገባ ሲዘግብ እና ሲከታተል መቆየቱ ነበር በታርጌት ሴንተር ተደርጎ የነበረውን አልባሌ ተግባር በፍቅር ለማሳየት እና ኢትዮጵያዊነት ትርጉም እንዳለው ዘሃበሻ ክፍተኛውን ድርሻ እንደተወጣ ለማወቅ ተችሎአል።

በዚህ ትልቅ ዝግጅት ላይ የኢትዮጵያን ታላላቅ ድምጻውያን የተገኙ ሲሆን ድምጻዊ ስለሽ ደምሴ፣ ብርሃኑ ተዘራ ፣ ዮሃንስ ጦና ፣ ገነት አባተ ፣ተሾመ ወልዴ ፣የህያ አደም፣ አሸብር እና ሌሎችም የኪነጥበብ ባለሙያዎች ተገኝተዋል፣ የኢትዮጵያ እና ኤርትራውያን ዳንሰኞችም በስፍራው ላይ ትእይንታቸውን አቅረዋል በሌላም በኩል ደግሞ የኢትዮጵያውያን እና ኤርትራውያን የወንድማማችነት እግርኳስ ጨዋታ ፣ኢትዮጵያውያን እና ኤርትራውያን ለመጀመሪያ ጊዜ ከ ፳፯ አመታት በኋላ በመጫወት ሚኖሶታወች ታሪክ ሰርተዋል። በጨዋታው የሚኖሶታው ኒያላ ቡድን የኤርትራውን ደንደን ከለብ ጋር በአደረገው ፍልሚያ ኒያላ አሸናፊ እንደነበር ለማወቅ ተችሏል። ማለዳ ታይምስ መረጃ ማእከል።

Ethiopia Fest in MN Maleda Times Media Group

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 6 years ago on September 3, 2018
  • By:
  • Last Modified: September 3, 2018 @ 1:09 pm
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar