www.maledatimes.com 9 የጋሞ አካባቢ ወረዳዎች በአዲስ አበባ አካባቢ እና በኦሮሚያ ልዩ ዞን ለተፈናቀሉ የጋሞ ተወላጆች የ5 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረጉ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

9 የጋሞ አካባቢ ወረዳዎች በአዲስ አበባ አካባቢ እና በኦሮሚያ ልዩ ዞን ለተፈናቀሉ የጋሞ ተወላጆች የ5 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረጉ

By   /   September 20, 2018  /   Comments Off on 9 የጋሞ አካባቢ ወረዳዎች በአዲስ አበባ አካባቢ እና በኦሮሚያ ልዩ ዞን ለተፈናቀሉ የጋሞ ተወላጆች የ5 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረጉ

    Print       Email
0 0
Read Time:1 Minute, 0 Second

በዛሬው ዕለት ከጋሞ ጎፋ ዞን አስተዳደር ማዕከል ፣ ከ9 ወረዳዎች እና አርባምንጭ ከተማ አስተዳደር የመንግሥት ስራ ኃላፊዎች ፣ የሕዝብ ተወካዮች ፣ የሀገር ሽማግሌዎች እና ወጣቶች በመገኘት የተፈናቀሉ ወገኖችን ጄነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ፣ መድኃኔአለም መሰናዶ ት/ቤት ፣ አስኮ ቃሌ 1ኛ ደረጃ ት/ቤት ፣ አስኮ ፊ/ ሀብተጊዮርጊስ መጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ፣ አስኮ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ፣ ፊሊጶስ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት እና በሌሎች ት/ቤቶች ያሉ የተፈናቀሉ የጋሞ ተወላጆችን ጎብኝተዋል ።

 የጋሞ አካባቢ ወረዳዎች በአዲስ አበባ አካባቢ እና በኦሮሚያ ልዩ ዞን ለተፈናቀሉ የጋሞ ተወላጆች የ5 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረጉ

ተፈናቃዮችን በጠየቁበት ወቅት የዞኑ አስተዳዳሪ አቶ እሳያስ እንድሪያስ እንደገለፁት የጋሞ ብሔር ትጉህ ሠራተኛ ፣ የሰው የማይነካ እና ለበቀል የማይነሳሳ ባህሉን አክባሪ ሕዝብ መሆኑን ጠቅሰው በዚህ ሕዝብ ላይ ኢ- ሰብዓዊ ድርጊት የፈፀሙ አካላት ለሕግ ቀርበው ውሳኔ እንዲያገኙ ለመንግሥት ጥሪ አቅርበዋል ።

የዞኑ አስተዳደር ፣ 9ኙ የጋሞ አካባቢ ወረዳዎች እና የዞኑ ልማት ማህበር የ5 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ማድረጋቸውን አቶ እሳያስ ገልፀዋል ።

የጋሞ ሀገር ሽማግሌዎችም በብሔሩ ባህል መሠረት ጋሞ እርጥብ ሣር ነጭቶ ፀብን ወደ ሠላም ጥልን ወደ እርቅ የሚለውጥ ኩሩ ባህል ያለው በመሆኑ ወጣቶች በስሜት ተነሳስተው ወዳልተፈለገ ግጭት ውስጥ እንዳይገቡ አሳስበዋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች እና ወጣቶች ከተጎጂዎች ጎን ሆነው ላደረጉት በጎነት ምስጋና አቅርበዋል ።

ሚዲያዎችም በዜጎች ላይ የደረሰውን ጉዳት እና የሚደርሰውን ችግር እውነታውን በመዘገብ እነዚህ ወገኖች የሚረዱበትን ሁኔታ እንዲያመቻቹ ጥሪ ቀርቦላቸዋል፡፡

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 6 years ago on September 20, 2018
  • By:
  • Last Modified: September 20, 2018 @ 12:24 pm
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar