www.maledatimes.com 40 በመቶ እናቶች ከጤና ተቋም ውጪ ይወልዳሉ ተባለ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

40 በመቶ እናቶች ከጤና ተቋም ውጪ ይወልዳሉ ተባለ

By   /   January 29, 2019  /   Comments Off on 40 በመቶ እናቶች ከጤና ተቋም ውጪ ይወልዳሉ ተባለ

    Print       Email
0 0
Read Time:37 Second

በኢትዮጵያ በጤና ተቋም መውለድ ከነበረባቸው እናቶች 40 በመቶዎቹ ከጤና ተቋማት ውጪ መውለዳቸውን ጤና ሚኒስቴር ገለጸ።

ሚንስትሩ ዶክተር አሚር አማን ማክሰኞ፣ ጥር 14 ለተወካዮች ምክር ቤት የመስሪያ ቤታቸውን የስድስት ወራት አፈፃፀም ባቀረቡበት ወቅት ነው፤ ይህን የተናገሩት።

ሚንስትሩ እንዳሉት በሰለጠነ ባለሙያ የሚሰጥን የወሊድ አገልግሎት ማግኘት ይጠበቅባቸው ከነበሩት አንድ ነጥብ አራት ሚሊዮን ነፍሰ ጡር እናቶች መካከል በጤና ተቋማት የወለዱት 800 ሺህዎቹ (60 በመቶ) ናቸው። ይህም 600 ሺህ (40 በመቶዎቹ) አገልግሎቱን አላገኙም ማለት ነው።

ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር በጤና ተቋማት የሚወልዱ እናቶች ቁጥር በአንድ በመቶ ቀንሷል። ስለዚህ ጉዳይ ከምክር ቤቱ ጥያቄ የቀረበላቸው ዶክተር አሚር የመረጃ ቋት ስርዓታቸውን እየቀየሩ መሆኑን ተከትሎ ትክክለኛ መረጃ ላይመዘገብ ይችላል ብለው እንደሚያስቡ አንስተዋል። በመረጃው ላይ የተካተተው አኃዝ የአምስት ወር መሆኑም ቁጥሩ ዝቅ እንዲል ምክንያት ይሆናል ብለዋል። ክልሎችም ትክክለኛ መረጃ እያቀበሉ እንዳልሆነ በመግለጽ ኮንነዋል።

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 5 years ago on January 29, 2019
  • By:
  • Last Modified: January 29, 2019 @ 3:25 pm
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar