www.maledatimes.com የመረጃ ዘጋቢን ያስደበደቡት ፖሊሶች ናቸው !! የለገጣፎ 04 ቀበሌ ሊቀመንበር አቶ ነጋሽ ወርቁ ለጠፋው እና ለተጎዱት ወገኖች ተጠያቂ ናቸው - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

የመረጃ ዘጋቢን ያስደበደቡት ፖሊሶች ናቸው !! የለገጣፎ 04 ቀበሌ ሊቀመንበር አቶ ነጋሽ ወርቁ ለጠፋው እና ለተጎዱት ወገኖች ተጠያቂ ናቸው

By   /   February 23, 2019  /   Comments Off on የመረጃ ዘጋቢን ያስደበደቡት ፖሊሶች ናቸው !! የለገጣፎ 04 ቀበሌ ሊቀመንበር አቶ ነጋሽ ወርቁ ለጠፋው እና ለተጎዱት ወገኖች ተጠያቂ ናቸው

    Print       Email
0 0
Read Time:1 Minute, 3 Second

የመረጃ ዘጋቢ ወደ ለገጣፎ ያቀናው ዛሬ ማለዳ ከሌሎች ባልደረቦቹ ጋር ሲሆን በቦታው እንደደረሱ ፖሊሶች አፍሰዋቸው ወደ ፖሊስ ጣቢያ በር ላይ እንዳመጧቸው ከስፍራው የደረሰን መረጃ ያመለክታል ።

ደብዳቢዎቹም በፖሊስ መኪና መጥተው ነው የደበደቧቸው ። ኢንስፔክተር ግርማ የከንቲባዋ ደጋፊ በመሆኑ ይህንን አይነት ህገ ወጥ ስራ የሰሩት ። አስር ሰዎች ከሶማሌ ተፈናቃይ የነበሩትን ሰብስበው ይዘው እንደመጡና ጋዜጠኞቹን ከበው እንደደበደቧቸው ገልጠዋል ። ነዋሪዎቹ አመራሮቹን ለምን መደብደብ አስፈለገ በለው በተደጋጋሚ ሲጠይቁ ኢሳት የተባለው የቴሌቪዝን ድርጅት «ዘርን ያማከለ ጥቃት እያደረሰ ስለሆነ ጋዜጠኞች መደብደብ አለባቸው ሲሉ አቶ ወርቁ ደጋግመው ሲናገሩ መስማታቸውን ገልጠዋል።»

ጋዜጠኞቹን ያፈኗቸው እና ያስደበደቡት ፖሊሶች ናቸው ያሉት እማኝ ምንጮቻችን ከተደብዳቢዎቹ አንዱ በዚህ ምስል ላይ የምትመለከቱት ፣ የጓደኛዬን ነው የምፈልገው እያለ ደሙ የፈሰሰ ሳለ ፣ ካሜራውን ቀምተውታል ፣ልጁን ወደ ጤና ጣቢያ ሲወስዱት በእግሩ እንደሆነ ገልጠዋል።

የለገጣፎ ዞእሮ አራት ሊቀመንበር የሆኑት ነጋሽ ወርቁ የውሸት ጋዜጠኞች ናቸው መጥተው እየዘገቡ ነው ያሉት ዘረኝነትን እና ጥላቻን እንጂ እውነተኛ መረጃን አይደለም የሚዘግቡት በማለት በሃገሪቱ ያሉትን የመገናኛ ብዙሃን አጥላልተዋል ። ትንሹ ትራምፕ ሲሏቸውም ነበር ።

ለገጣፎ ፖሊስ ጣቢያ በር ላይ ይሄው ጋዜጠኛ በአሁን ሰአት ከጓደኞቹ ጭምር ያለበት ሁኔታ ባይታወቅም የአካባቢው ነዋሪዎች በፖሊስ መኪና ትራንስፖርት አምጥታችሁ ካወራድችኋቸው በኋላ እንዴት እንዴት ይደበደባሉ ብለን ስንጠይቅ ዘረኝነትን እየዘገቡ ስለሆነ ይደበደባሉ በማለት ሊቀመንበሩ መልሷል ። ይህ የጋዜጠኝነትን ስነ ምግባር እና የመገናኛ ብዙሃንን ህልውና የሚጋፋ ከመሆኑም በላይ እኝህ የቀበሌ አስተዳደር (አቶ ነጋሽ ወርቁ) በህግ ሊጠየቁ ይገባል ፣የስም ማጥፋት ወንጀል በመገናኛ ብዙሃን ላይ መስርተዋል ሲሉ አንዳንድ ነዋሪዎች ጠቁመዋል።

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 5 years ago on February 23, 2019
  • By:
  • Last Modified: February 23, 2019 @ 1:01 pm
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar