www.maledatimes.com ከንግድ መርከቦች ግዥ ጋር በተያያዘ በሜቴክ የቀድሞ ኃላፊዎች ላይ ብይን ተሰጠ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

ከንግድ መርከቦች ግዥ ጋር በተያያዘ በሜቴክ የቀድሞ ኃላፊዎች ላይ ብይን ተሰጠ

By   /   March 16, 2019  /   Comments Off on ከንግድ መርከቦች ግዥ ጋር በተያያዘ በሜቴክ የቀድሞ ኃላፊዎች ላይ ብይን ተሰጠ

    Print       Email
0 0
Read Time:1 Minute, 20 Second

እነ ሜጀር ጄኔራል ክንፈ ዳኘው የእምነት ክህደት ቃላቸውን ሰጡ

የብረታ ብረት ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) የግዥ መመርያን በመተላለፍ ኮርፖሬሽኑ ከተቋቋመበት ዓላማ ውጪ ሁለት መርከቦችን በመግዛት፣ ከ544 ሚሊዮን ብር በላይ በሕዝብና በመንግሥት ላይ ጉዳት አድርሰዋል በማለት ዓቃቤ ሕግ ክስ በመሠረተባቸው በእነ ሜጀር ጄኔራል ክንፈ ዳኘው (14 ሰዎች) ላይ ብይን ተሰጠ፡፡

የሜቴክ የቀድሞ ዋና ዳይሬክተር ሜጀር ጄኔራል ክንፈ ዳኘውን ጨምሮ ክስ የተመሠረተባቸው የኮርፖሬሽኑ የተለያዩ ክፍል ኃላፊዎች በክሱ ላይ ያቀረቡትን የክስ መቃወሚያ ውድቅ በማድረግ፣ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 15ኛ ወንጀል ችሎት ብይን ሰጥቷል፡፡

ፍርድ ቤቱ ዓቃቤ ሕግ በሁለተኛ ክሱ ላይ ያቀረበው የክስ ሀተታ በአንደኛ ክሱ ላይ የዘረዘረውን በመነጣጠል መሆኑን ገልጿል፡፡ በአንደኛ ክስ ላይ ዋና ዳይሬክተሩ የወንጀል ሕግ አንቀጽ 407 በመተላለፍ ሥልጣናቸውን ያላግባብ በመጠቀም ጉዳት እንዲደርስ ማድረጋቸውን ገልጾ ሳለ፣ በሁለተኛ ክሱ ደግሞ የወንጀል ሕግ አንቀጽ 411 በመተላለፍ ‹‹የመንግሥት ሥራ በማያመች አኳኋን መምራት›› በማለት ያቀረበውን ክስ ፍርድ ቤቱ ውድቅ አድርጎታል፡፡ በመሆኑም ዓቃቤ ሕግ ሁለቱን ክሶች በማጣመር አሻሽሎ እንዲያቀርብም ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡

ተከሳሾቹ በዋናነት የተመሠረተባቸው ክስ የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ንብረት የነበሩና የአገልግሎት ጊዜያቸውን የጨረሱ ሁለት መርከቦችን ለመሸጥ ያወጣውን ጨረታ፣ ሜቴክ ለስክራፕ እንደሚፈልጋቸው በመግለጽ በ3.3 ሚሊዮን ዶላር መግዛቱን ዓቃቤ ሕግ በክሱ አስፍሯል፡፡ ሜቴክ መርከቦቹን ከገዛ በኋላ በ7.3 ሚሊዮን ዶላር ወጪ በማደስ አገልግሎት ላይ እንዲውሉ በማድረጉ ከገዛበት ዋጋ በላይ ለማሳደሻ ከማውጣቱም በላይ፣ ለአስተዳደርና ለተለያዩ ወጪዎች 544,702,623 ብር ጉዳት እንዲደርስ ማድረጋቸውን መዘገባችን ይታወሳል፡፡

ፍርድ ቤቱ እንዲሻሻል ትዕዛዝ የሰጠበትን ክስ ለመጠባበቅ ለመጋቢት 13 ቀን 2011 ዓ.ም. ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

እነ ሜጀር ጄኔራል ክንፈ ዳኘው (አራት ሰዎች) በሌላ መዝገብ ከትራክተር ግዥ ጋር በተያያዘ በተመሠረተባቸው ክስ ላይ የዕምነት ክህደት ቃላቸውን ሰጥተዋል፡፡ ድርጊቱን አለመፈጸማቸውንና ጥፋተኛም እንዳልሆኑ በመግለጻቸው፣ ዓቃቤ ሕግ ምስክሮቹን ከግንቦት 1 እስከ 13 ቀን 2011 ዓ.ም. ድረስ እንዲያሰማ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡  

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 5 years ago on March 16, 2019
  • By:
  • Last Modified: March 16, 2019 @ 9:46 pm
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar