www.maledatimes.com የሜቴክ የቀድሞ ኃላፊዎች ሰጥተዋል በተባሉበት ሐሰተኛ የማስተርስና የዶክትሬት ዲግሪ ክስ ላይ የእምነት ክህደት ቃል ሰጡ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

የሜቴክ የቀድሞ ኃላፊዎች ሰጥተዋል በተባሉበት ሐሰተኛ የማስተርስና የዶክትሬት ዲግሪ ክስ ላይ የእምነት ክህደት ቃል ሰጡ

By   /   March 23, 2019  /   Comments Off on የሜቴክ የቀድሞ ኃላፊዎች ሰጥተዋል በተባሉበት ሐሰተኛ የማስተርስና የዶክትሬት ዲግሪ ክስ ላይ የእምነት ክህደት ቃል ሰጡ

    Print       Email
0 0
Read Time:1 Minute, 21 Second

አሜሪካ ከሚገኘውና ታዋቂ ከሆነው ‹‹ካሊፎርኒያ ኢንስቲትዩት ኦፍ ቴክኖሎጂ›› ከሚባለው የትምህርት ተቋም ጋር ተቀራራቢ ስም ያለው ‹‹ካሊፎርኒያ ኢንተርናሽናል ኢንስቲትዩት ኦፍ ቴክኖሎጂ›› የሚል ሐሰተኛ የፈጠራ ተቋም ስም የተዘጋጀ፣ ሁለተኛ ዲግሪ (ማስተርስ) እና ሦስተኛ ዲግሪ (ዶክትሬት) ሰጥተዋል ተብለው ክስ የተመሠረተባቸው የሜቴክ የቀድሞ ኃላፊዎች የእምነት ክህደት ቃላቸውን ሰጡ፡፡

ሰኞ መጋቢት 9 ቀን 2011 ዓ.ም. በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 15ኛ ወንጀል ችሎት ‹‹እንደ ክሱ ድርጊቱን አልፈጸምኩም፣ ጥፋተኛም አይደለሁም፤›› በማለት በተመሳሳይ ሁኔታ የእምነት ክህደት ቃላቸውን የሰጡት ሜጀር ጄኔራል ክንፈ ዳኘው፣ ብርጋዴር ጄኔራል ጥጋቡ ፈትለ፣ ሻለቃ ገብረ ሥላሴ ገብረ ጊዮርጊስ፣ መቶ አለቃ ቶማስ ደረሰና አቶ ወሰንየለህ ኃይለ ሚካኤል ናቸው፡፡ ዋናው የወንጀሉ ተዋናይ ናቸው የተባሉት  መኮንን ገብረ ሚካኤል (ዶ/ር)፣ ሀድአት ወልደ ተንሳይና ሻለቃ ፋሲል አበራ ክሳቸው የሚታየው በሌሉበት ነው፡፡ 

ተከሳሾቹ ከሐሰተኛውና የፈጠራው የትምህርት ተቋም ጋር በጥቅም በመመሳጠር ከሜቴክ ጋር ከፍተኛ ትምህርት ለማስተማር የውል ስምምነት እንዲፈጸምና ድርጊቱ በኢትዮጵያ መንግሥት እንዳይታወቅ፣ ክፍያውን በውጭ ምንዛሪ ማድረጋቸውንም ዓቃቤ ሕግ በክሱ ዘርዝሮ አቅርቧል፡፡ አስተማሪ ናቸው የተባሉ ግለሰቦች ከውጭ አገር በቱሪስት ቪዛ ወደ አገር ውስጥ እንዲገቡ በማድረግ፣ አስተማሪ ያልሆኑ ሰዎችን በመጠቀም ተማሪዎቹ ሳይማሩ ሁለተኛ ዲግሪና ዶክተሬት እንዲሰጣቸው ማድረጋቸውንም አክሏል፡፡

 ከተቋሙም አራት የተለያዩ ውሎችን በመዋዋል በአጠቃላይ 3,901,140 ዶላር ወይም 75,114,030 ብር በአሜሪካ በሐሰተኛው ተቋም ስም በተከፈተ ሒሳብ ገቢ መደረጉንም ዓቃቤ ሕግ አብራርቶ ማቅረቡ ይታወሳል፡፡

ሜጀር ጄኔራል ክንፈ ዳኘውም ለራሳቸው ጥቅም ለማግኘትና ማርዳ መለስ ለተባለች ግለሰብ ጥቅም ለማስገኘት በማሰብ፣ ሕጋዊ ምክንያት ሳይኖራቸው ‹‹ኮርፖሬሽኑ ወስኗል›› በማለት አሜሪካ በሚገኝ ግለሰብ ስም በተከፈተ ሒሳብ ሁለት ጊዜ በመላክ፣ በአጠቃላይ 75,600 ዶላር ወይም 1,250,886 ብር እንዲከፈል በማድረጋቸው ሥልጣናቸውን ያላግባብ መገልገል ወንጀል ፈጽመዋል በማለት ዓቃቤ ሕግ ክስ መመሥረቱን መዘገባችን አይዘነጋም፡፡

ተከሳሹ ክደው በመከራከራቸው ዓቃቤ ሕግ ምስክሮቹን ከግንቦት 19 ቀን 2011 ዓ.ም. ጀምሮ እንዲያሰማ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡   

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 5 years ago on March 23, 2019
  • By:
  • Last Modified: March 23, 2019 @ 9:16 am
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar