www.maledatimes.com የኢትዮ ቴሌኮም የቀድሞ ዳይሬክተር ላይ ቀርቦ የነበረው ክስ ተሻሻለ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

የኢትዮ ቴሌኮም የቀድሞ ዳይሬክተር ላይ ቀርቦ የነበረው ክስ ተሻሻለ

By   /   March 23, 2019  /   Comments Off on የኢትዮ ቴሌኮም የቀድሞ ዳይሬክተር ላይ ቀርቦ የነበረው ክስ ተሻሻለ

    Print       Email
0 0
Read Time:58 Second

የፌዴራል ዓቃቤ ሕግ በመንግሥትና በሕዝብ ላይ ከ768.7 ሚሊዮን ብር በላይ ጉዳት አድርሰዋል በማለት በቀድሞ የኢትዮ ቴሌኮም የቀድሞ ኤንጂፒኦ ዳይሬክተር ላይ አቅርቦ የነበረውን ክስ አሻሽሎ አቀረበ፡፡

ዓቃቤ ሕግ ክሱን ያሻሻለው ክስ የተመሠረተባቸው አቶ ኢሳያስ ዳኘው ቀደም ብሎ በቀረበባቸው ክስ ላይ ያቀረቡትን የቅድመ ክስ መቃወሚያ፣ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 15ኛ ወንጀል ችሎት በመቀበሉና ክሱ እንዲሻሻል ትዕዛዝ በመስጠቱ ነው፡፡

ዓቃቤ ሕግ በመጀመርያ ክሱ ላይ አቶ ኢሳያስ የወንጀል ሕግ አንቀጽ 33 እና 411 በመተላለፍ፣ በልዩ ወንጀል ተካፋይ በመሆንና የመንግሥትን ሥራ በማያመች መንገድ መርተዋል በማለት ሁለተኛ ክስ አድርጎ አቅርቦባቸው ነበር፡፡

ነገር ግን ፍርድ ቤቱ እንዲያሻሽል በሰጠው ትዕዛዝ ‹‹ከግብረ አበሮቻቸው ጋር በመሆን›› የሚለውንም በመተውና አንቀጹንም ወደ ወንጀል ሕግ አንቀጽ 32 እና 407 በመቀየር፣ ሥልጣንን ያላግባብ መገልገል ወንጀል በማለት አሻሽሎ አቅርቧል፡፡

በመሆኑም አቶ ኢሳያስ ሥልጣናቸውን ያላግባብ በመጠቀም፣ ራሳቸውን ለመጥቀምና ዜድቲኢ የተባለውን የቻይና ቴሌኮም ኩባንያ ለመጥቀም ግዥ እንዲፈጽም ማድረጋቸውን አካቶ ቀርቧል፡፡

ለዩኒቨርሲቲዎች የኔትወርክ ግንባታ አገልግሎት ያለ ጨረታና ከተቋሙ የግዥ መመርያ ውጪ የ44,510,971 ዶላር ወይም 768,704,469 ብር ግዥ እንዲፈጸም በማድረግ፣ በተቋሙ ላይ ጉዳት አድርሰዋል በማለት ክስ ዓቃቤ ሕግ ማቅረቡን መዘገባችን ይታወሳል፡፡

የተሻሻለውን ክስ የተቀበለው ፍርድ ቤቱ ለተከሳሹ እንዲደርሳቸው ካደረገ በኋላ፣ በተሻሻለው ክስ ላይ አስተያየት ካላቸው ለመጠባበቅ ለሐሙስ መጋቢት 12 ቀን 2011 ዓ.ም. ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 5 years ago on March 23, 2019
  • By:
  • Last Modified: March 23, 2019 @ 9:18 am
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar