www.maledatimes.com አብን የአማራ፣ የጉራጌና የቅማንት ሕዝብ ˝የቁጥር ዘር ማጥፋት ወንጀል ተፈጽሞበታል˝ አለ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

አብን የአማራ፣ የጉራጌና የቅማንት ሕዝብ ˝የቁጥር ዘር ማጥፋት ወንጀል ተፈጽሞበታል˝ አለ

By   /   March 31, 2019  /   Comments Off on አብን የአማራ፣ የጉራጌና የቅማንት ሕዝብ ˝የቁጥር ዘር ማጥፋት ወንጀል ተፈጽሞበታል˝ አለ

    Print       Email
0 0
Read Time:1 Minute, 45 Second

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) በ1999 በተካሔደው የሕዝብና ቤቶች ቆጠራ የአማራ፣ የጉራጌና የቅማንት ሕዝብ ላይ ˝የቁጥር ዘር ማጥፋት ወንጀል ተፈጽሟል˝ ሲል መንግሥትን ወቀሰ። በቆጠራው የተሳተፉ ባለሙያዎችና ባለሥልጣናት ተጠያቂ እንዲሆኑ የሚል አቋም እንዳለውም አሳውቆም፣ በቆጠራው ለተፈጠረው ስህተት መንግሥት ካሳ ሊከፍል ገባል ሲል ጠይቋል።

በ1999ኙ ሦስተኛው የሕዝብና ቤቶች ቆጠራ ወቅት ከስድስት ሚሊዮን በላይ የአማራ ብሔር ተወላጆች ባለመቆጠር ወይም ቢቆጠርም ሪፖርት ባለመደረጉ ምክንያት፣ የሕዝብ ቁጥሩና የክልሉ በጀት መመጣጠን አልቻለም ሲልም ከሷል። በዚህም የመምህራን ደመወዝ መክፈል ያቃታቸው በርካታ የአማራ ክልል ወረዳዎች መኖራቸውን የአብን የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ክርስቲያን ታደለ ለአዲስ ማለዳ ገልጸዋል። የአማራ ክልል በቆጠራው በተፈፀመው ስህተት ምክንያት አንድ ቢሊዮን ብር አጥቷል ያሉት ክርስቲያን፣ በዚህም ምክንያት የአገልግሎት ጥራት ጫና እየፈጠረ መሆኑን ተናግረዋል።

አብን 4ኛው የሕዝብና ቤቶች ቆጠራ መራዘሙ ተገቢ ቢሆንም፣ በሦስተኛው የሕዝብና ቤቶች ቆጠራ የተሳተፉ አመራሮች እንዲጠየቁ፣ መንግሥት ይቅርታ እንዲጠይቅ፣ ውጤቱም በይፋ እንዲሰረዝ እና ካሳ ለሚገባቸውም እንዲከፈል ሲል ማክሰኞ፣ መጋቢት 10 በሰጠው መግለጫ ጠይቋል።

ፓርቲው በሦስተኛው የሕዝብ እና ቤቶች ቆጠራ ወቅት በአማራ፣ በጉራጌ እና በቅማንት ሕዝቦች ላይ ፖለቲካዊ የሆነ ሕዝብን ያለመቁጥር፣ የተቆጠረውንም ያለማሳወቅ ወንጀል ተሰርቷል ብሎ እንደሚያምንም ገልጿል።

በጉዳዩ ዙሪያ ያነጋገርናቸው የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የሕግ ትምህርት ክፍል መምህር ታደለ ፈረደ (ዶ/ር)፣ የሕገ መንግሥቱን አንቀጽ 32 በመጥቀስ፣ በሕገ መንግሥቱም ይሁን በዓለም ዐቀፍ የሰብኣዊ መብት ሰነዶች መሰረት መንግሥት ቢያንስ በሦስት ምድቦች ሥር የሚካተቱ ግዴታዎች እንዳሉበት ያስረዳሉ። እነዚህም የማክበር፣ የማስከበርና የማሟላት ግዴታዎች ናቸው። ይህም የዜጎችን እንደ አገር ዜግነት የመቆጠር መብትን ያካትታል ሲሉም ለአዲስ ማለዳ አስረድተዋል።

በሕጉ መንግሥት በተለያዩ ዕርከን ላይ የሚገኙ ተቋማቱም ይሁን ባለሥልጣናት ወይም ሠራተኞች የሌላን ሰው መብት በመጣሳቸው ምክንያት ጉዳት ከደረሰ እንደ ሁኔታው የፖለቲካ፣ የወንጀል፣ የፍትሐ ብሔር ወይም የአስተዳደራዊ ዕርምጃ መውሰድ እንደሚጠበቅበት ግድ መሆኑን መምህሩ ያክላሉ።

ከላይ በተጠቀሱት ግዴታዎች ማዕቀፍ ሥር የሚወድቁ፣ የተለያዩ መብቶችን መንግሥት ማክበር፣ ማስከበር ወይም ማሟላት ባለመቻሉ ምክንያት ዜጎች ላይ ጉዳት በሚደርስበት ወቅት ተጎጂዎቹ የፍትሐ ብሔር መብት እንደሚኖራቸውም ታደለ አስረድተዋል።

ስለጉዳዩ የጠየቅናቸው የማዕከላዊ ስታቲስቲክስ ኤጀንሲ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ሳፊ ገመዲ፣ ˝ፖለቲካዊ ይዘት ባላቸው ነገሮች ላይ መልስ መስጠት አልችልም፤ ነገር ግን በ1999ኙ ቆጠራ የአማራን ክልል ጨምሮ በርካታ ክልሎች ያቀረቡትን አቤቱታ መሰረት ተደርጎ በተሠራው የማጣራት ሥራ መጠነኛ ማስተካከያ መደረጉን አስታውሳለሁ˝ ብለዋል።

በሌላ በኩል አብን በአዲስ አበባ እና አካባቢው ስለታማ ነገሮችን በመያዝ ከሕግ አግባብ ውጭ እየተንቀሳቀሱ እና ሕዝብን እያሸበሩ ባሉ አካላት ላይ የኦሮሞ ፖለቲካ ኃይሎች ዝምታ ተገቢ አይደለም ሲልም በመግለጫው አንስቷል። መንግሥትም ሕግን እንዲያስከብር ጠይቋል።

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 5 years ago on March 31, 2019
  • By:
  • Last Modified: March 31, 2019 @ 1:18 pm
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar