www.maledatimes.com በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ የኦነግ ታጣቂዎች ህዝብን እየገደሉ ነው! ቤተክርስቲያንም ተቃጠለ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ የኦነግ ታጣቂዎች ህዝብን እየገደሉ ነው! ቤተክርስቲያንም ተቃጠለ

By   /   April 7, 2019  /   Comments Off on በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ የኦነግ ታጣቂዎች ህዝብን እየገደሉ ነው! ቤተክርስቲያንም ተቃጠለ

    Print       Email
0 0
Read Time:1 Minute, 26 Second

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ ፣ በአጣዬ (ኤፌሶን) ፣ ካራቆሬ ፣ ቆሪ ሜዳ እና ማጀቴ ላይ የኦሮሞ አሸባሪ ቡድን በንጹሃን ዜጎች ላይ ከፍተኛ የሆነ ጦርነት ከፍቷል ፣ በአሁን ሰአትም ከአስር ሰው በላይ በይፋ ህይወታቸው እንዳለፈ የተጠቆመ ሲሆን ብዙሃንን ሴቶችን እና ህጻናትን አስገድዶ መድፈር ላይ እንደሚገኙ ከአካባቢው ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

በትላንትናው እለት ከሰአት በኋላ በአጣዬ ከተማ ውስጥ የተነሳው የተኩስ ጦርነት አዳሩን የቀጠለ እና ውሎውንም የዋለ ሲሆን የመከላከያ ሰራዊንም ምንም አይነት እርምጃ ሳይወስድ እንዳለ ነዋሪዎቹ ገልጸዋል፡፤ ከጠቅላይ ሚንስትሩ መስሪያ ቤት ትእዛዝ ካልተሰጠን በስተቀር ምንም አይነት እርምጃ አልወስድም ሲል የመከላከያ ሰራዊት አመራር አካላቶች ለህዝቦቹ ገልጸዋል።

በሌላም በኩል በአካባቢው በተፈጠረው የኔትወርክ ችግር ምክንያት ምንም አይነት መረጃ ለውጭ ላሉትም ሆነ ለመንግስት አካላት መግለጽ አለመቻሉን ነዋሪዎች ገልጸዋል።

የማለዳ ታይምስ ዘጋቢ ለማጣራት እንደሞከረው ከሆነ ሰሞኑን በአካባቢያችን ከፍተኛ ውጥረት ከመንገሱም ባሻገር ወጣት ወንዶች ጫካ ገብተዋል ፣ ሴቶች፣ አዛውንቶች እና ህጻናት አስገድደው ደፍረዋቸዋል በማለት ነዋሪዎቹም ገልጸዋል። የአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቤተ ክርስቲያንም መቃጠሉንም ከስፍራው የማለዳ ሪፖርተሮች ካነጋገሯቸው እማኞች ለማወቅ ተችሏል። መስፍን ሰለሞን የተባለው ግለሰብ እንደገለጸው ከሆነ ”
ዘላኑ ኦነግ ቆሬ አቡነ ገ/መ/ቅዱስ ቤ/ንን እንዲህ አቃጥሏል፤እስካፍንጫው በታጠቀው ሀይል ንጹሀን እየተገደሉ ነው፤ወንዶች መከላከል ሥላልቻሉ ጫካ ገብተዋል።ሴቶችና ህጻናት እየተደፈሩ ቤቶችም እየተዘረፉ ነው። ዘላኑ ኦነግ አሁን አቅጣጫውን ወደ ሀይማኖት ያዞረ ቢመሥልም መላው የአገራችን ህዝብ የዘላኑን አካሄድ ጠንቅቆ ይረዳዋል። እውነታው ዘላኑ እሥከዛሬም ከወለጋ እና ኢሉባቡር ጾም በሆዳቸው ይዘው በቁም ያረዳቸው ሙሥሊም ወሎየዎች ያጠፉት ቢኖር አማራ ሆነው መገኘታቸው ነው።ሙሥሊምና ክርሥቲያን ወገኖቻችን ከመቸውም ጊዜ በበለጠ አንድነታችንን አሥጠብቀን ጭፍጨፋውን እንከላከላለን!! “

ባሳለፍነው ሳምንት በደቡብ ወሎ ከሚሴ በኦነግ ታጣቂዎች በተጀመረ የተኩስ ልውውጥ ብዙ ዜጎች ማለፋቸው ይታወሳል ።

በሌላም በኩል ከአጣዬ አካባቢ የደረሰን መረጃ እንደሚገልጸው ከሆነ ህዝቦች በተለያየ አቅጣጫ የአድኑን ጥሪ ቢያሰሙም መንግስት ግን ጆሮ ዳባ ልበስ ብሎናል ይላሉ ።

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 5 years ago on April 7, 2019
  • By:
  • Last Modified: April 7, 2019 @ 1:35 pm
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar