www.maledatimes.com ህወሃት ኢህአዴግ የአየር ሃይል አዛዥ የሆኑትን ሜጀር ጄኔራል ሞላ ሃይለማርያምን ከስልጣን አነሳ ! - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

ህወሃት ኢህአዴግ የአየር ሃይል አዛዥ የሆኑትን ሜጀር ጄኔራል ሞላ ሃይለማርያምን ከስልጣን አነሳ !

By   /   November 2, 2012  /   2 Comments

    Print       Email
0 0
Read Time:4 Minute, 16 Second

ህወሃት ኢህአዴግ የአየር ሃይል አዛዥ የሆኑትን ሜጀር ጄኔራል ሞላ ሃይለማርያምን ከስልጣን አነሳ !
ሜጀር ጄኔራል ሞላ ከስልጣን መውረድ ህወሃት ውስጥ ከተፈጠረው መከፋፈል ጋር የተያያዘ ነው :: ሜጀር ጄኔራል ሞላ የአየር ሃይሉ አዛዥነትን ስልጣን ጨብጠው ከነበሩት አራት የህወሃት አባላት ማለትም ከጄኔራል አበበ ተክለሃይማኖት( ጆቤ) ጄኔራል መሃሪ ዘውዴ (ወዲ ዘውዴ) እና ጄኔራል አለምሸት ደግፌ አንዱ ነበረ ::
ባሁኑ ጊዜ የቀድሞው አየር ሃይል አዛዥና የህወሃት አባል የሆነው እንዲሁም በዚህ አመት መጀመሪያ ላይ ጠቅላይ ሚንስትር በሌለበትና ፓርላማ ባልመከረበት ሁኔታ የወታደራዊ ማዕረግ እድገት ከተደረገላቸው የመከላከያ አባላት አንዱ የሆኑት ሜጄር ጄኔራል መሃሪ ዘውዴ (ወዲ ዘወዴ) አየር ሃይሉን ባዛዥነት እየመሩ እንደሆነ ታውቋል::

በዚህ አመት ውስጥ ብዙ ባለስልታናቶች ከስልጣናቸው እንደሚነሱ የሚጠቁመው የውስጥ ምንጫችን ሌሎችም በቁልፍ ቦታ ላይ ያሉ ባለስልጣናቶች  መነሳታቸው አይቀርም ሲሉ ይናገራሎ  ሆኖም ግን ማንነታቸውን ከመግለጽ ተቆጥበዋል  በአጠቃላይ ህወሃት የሚያደርገው የስልጣን ሽግሽግ አሁንም ተጠናክሮ የሚቀጥል ሲሆን ከላይ የሚያስቀምጣቸው ከተለያዩ የህወሃት አጋር ድርጅቶች የተመረጡ ባለስልታናትን ብቻ ሲሆን ከዚያ ውጭ ከስር በመሆን የማስተዳደሩን ስራ ሲተገብሩ ይኖራሉ በማለት ምንጫችን ይገልጻሉ ። አጠቃላይ የወያኔ አስተዳደር ከቀድሞው ሊቀመንበሩ አቶ መለስ ዜናዊ ስርአተ ሞት በኋላ የመንሸራተት እና ከፍ ዝቅ የማለት እይታ ይታይበታል። አቶ ጁነዲን ሳዶን ከውጭ አገር ህክምና ካገደ በኋላም ሌሎችን ባለስልጣናትን ጨምሮ የቁም እስረኛ አድርጎ ያስቀመጣቸው ሰዎች እንዳሉ የማለዳ ታይምስ የውስጥ መረጃ ያመለክታል ።በዚህ አመት ውስጥ በወያኔ ኢሃዴግ ከተሰሩት ስህተቶች ውስጥ ያለ ጠቅላይ ሚንስትሩ የመኮንኞች ሹመት ማጽደቁ ፓርላማውን እና እንዲሁም አስተዳደሩንም ያስገመተም ከመሆኑም በላይ የራሱን አካላቶች በከፍተኛ ቦታ ላይ ለማስቀመጥ ያደረገውን ዝግጅቱን ለማሳየት በቂ መረጃ ነው ሲሉ መረጃዎቻችን አብራርተዋል 

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 11 years ago on November 2, 2012
  • By:
  • Last Modified: November 2, 2012 @ 1:58 pm
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%

2 thoughts on “ህወሃት ኢህአዴግ የአየር ሃይል አዛዥ የሆኑትን ሜጀር ጄኔራል ሞላ ሃይለማርያምን ከስልጣን አነሳ !

  1. ay weyane manesat masqemet new seraw ! min yidereg
    ageritu befashishetawi ye aparthied agezaz 21 amet
    alefat, betigre yebelayinet ageritun eyezerefu new.
    Tewuledum feri ena sedeten yemiwed telekasha hone,
    bebaher lay eyeteneteletel ye asa erat mehonen mertowal, yetewared tewuled.God Pless Ethiopia.

    1. @yagersew,
      If you got the motive then show us and confront weyane and you will be called a hero, as of Tunisian Boaziz who sets himself to fire and start public gathering and turmoil which end up changing the country’s ruling party and become prototype to the whole arab spring. If you do this you will be remembered for centuries in the minds of ethiopian people otherwise shut your fccking mouth.

Comments are closed.

<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar