www.maledatimes.com በመከላከያ የጄኔራሎች ፍጥጫ ከኢየሩሳሌም አርአያ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

በመከላከያ የጄኔራሎች ፍጥጫ ከኢየሩሳሌም አርአያ

By   /   November 3, 2012  /   Comments Off on በመከላከያ የጄኔራሎች ፍጥጫ ከኢየሩሳሌም አርአያ

    Print       Email
0 0
Read Time:10 Minute, 17 Second

በመከላከያ ያለው ሽኩቻ እየበረታ ሄዶዋል። በጄ/ል ሳሞራ ትዕዛዝ የአየር ሓይል አዛዥ የነበሩት ጄ/ል ሞላ ሃ/ማሪያም ከሃላፊነት እንዲነሱ ተደርጎዋል። በምትካቸው ደግሞ ጄ/ል መሃሪ ዘውዴ እንደሚቀመጡ ታውቓል። በቅርቡ የሜ/ጄኔራልነት ሹመት ያገኙት እና ወዲ ዘውዴ በሚል የሚጠሩት ጄ/ል መሃሪ ዘውዴ ከበረሃ አንስቶ ከሳሞራ ጋር የጠበቀ ወዳጅነት እንዳላቸው ከዚህ ቀደም ጠቁሜ ነበር። የሹመታቸው ምስጢሩ ሳሞራ ናቸው። ካኤርትራ የሚወለዱት ወዲ ዘውዴ ከሳሞራ ባለፈ ለመለስ ታማኝ አገልጋይ የነበሩ ናችው። በኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት « ፈሪ» ተብለው እንደተገመገሙ ታማኝ ምንጮች አስታውሰዋል።

 በአንጻሩ ጄ/ል ሞላ ወደ አየር ሃይል አዛዥነት ከመምጣታቸው በፊት የላቀ ጀብዱ እንደፈጸሙ ምንጮች ጠቁመዋል። በሻእቢያ ጦርነት ወቅት ኰ/ል ማእረግ የነበራቸው ሞላ በባድመ፡ አስመራ፡ ተሰኔ….በመሳሰሉ ከባድ ውጊያዎች ላይ የጦር ጄቶችን በማብረር ሻእቢያን ድባቅ የመቱ ኢትዮጵያዊ ጀግና ናቸው።
ጄ/ል ሞላ ለአቶ መለስና ለሳሞራ ከፍተኛ ተቃውሞ እንደነበራቸው ሲታወቅ በተለይ በጦርነቱ የተፈጥጸመው ሴራ፡ አሰብ ወደብን ለመያዝ የተነደፈው ፕላን መኮላሽትን ጨምሮ ባድመን እንስጥ የሚለውን ባለ 5 ነጥብ የክህደት አጀንዳና ሌሎች የነመለስ – ሳሞራ ሕገ ወጥ አካሔዶችን አጥብቀው ያወግዙ እንደነበረ ተጠቁሞል። « በራሱ እምነት የሚጉዝ ጠንካራ ሰው» ተብለው በባልደረቦቻቸው የሚሞካሹት ጄ/ል ሞላ ያራምዱት በነበረው አቁዋም በነመለስ- በረከት ጥርስ ተነክሶባቸው ቆይቶዋል። ከዚያም ባለፈ « የአንጃ ደጋፊ» በሚል ተገምግመዋል። ቢሆንም ግን ከአቖማቸው ዝንፍ ሳይሉ ቖይተዋል።
ከጄ/ል ሞላ ጋር የቅርብ ወዳጅ የነበሩትና የአየር ሃይል ባልደረባ የነበሩት ኰ/ል ክብሮም በ1996á‹“.ም የመለስን – ባድመን አሳልፎ የመስጠት አጀንዳ በመቃወም ሰራዊቱን ሰብስበው እንዲያወግዝ የማነሳሳት ጥሪ በማድረጋቸው አንዲባረሩ ተደርጎዋል። በ1999 á‹“.ም ማእረጋቸው ተገፎ እንዲባረሩ የተደረጉት የቀድሞ የአየር ሃይል አዛዥ ጄ/ል አለምሽት ደግፌ ፡ መጀመሪያ ያራምዱት የነበረውን – መለስን የመደገፍ አቁዋም በመተው መቃወም በመጀመራቸው ውሳኔው ሊተላለፍባቸው ችሎዋል። ጄ/ል አለምሽት ከስልጣን ከመነሳታቸው በፊት አንድ አስገራሚ ነገር ሰርተዋል፤ በ1993 á‹“.ም የአቶ መለስን ተሃድሶ በማውገዝ ጥለው የወጡት ጄ/ል ታደሰ በርሄ (ጋውና) እና ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ « መታሰር አለባቸው » ሲሉ በወቅቱ የተከራከሩት ጄ/ል አለምሽት ከጊዜ በሁዋላ ለሁለቱም የቀድሞ ባለስልጣናት ስልክ ደውለው ይቅርታ መጠየቃቸው ነበር። « በናንተ ላይ ሳራምድ የነበረው ተግባር አሳዝኖኛል፤ የመለስን አካሄድ ያወቅኩት ዘግይቶ ነው። ይቅርታ አድርጉልኝ።» እንዳሉዋቸው ታማኝ ምንጮች አረጋግጠዋል። በነገራችን ላይ አለምሽት ቦሌ አካባቢ በየእለቱ መጠጥ ሲጎነጩና ሲበሳጩ ይታያሉ።
በአለምሽት ቦታ የተተኩት ጄ/ል ሞላ ለ4 አመት አየር ሃይልን ሲመሩ ከቆዩ በሁላ መነሳታቸው ከጀርባ ያለውን ከባድ የፖለቲካ ሽኩቻ ወደከፋ ጫፍ እንደሚያሽጋግረው የቅርብ ምንጮች ስጋታቸውን አስቀምጠዋል። ጄ/ል ሞላ በአየር ሃይልና በመከላከያ በርካታ ደጋፊዎች እንዳላቸው ምንጮቹ ጠቁመዋል።
በሌላም በኩል ጄ/ል መሃሪ ዘውዴ በአንድ የአየር ሃይል አንጋፋ መኮንን ላይ የፈጸሙት አሳዛኝ ድርጊት ይገኛል። መ/አ ለማ ይባላሉ፤ የኦሮሞ ተወላጅ ናቸው። ለ25 አመታት በአየር ሃይል አገልግለዋል። በኢትዮጵያ በግራውንድ ስኩል እንዲሁም በሩሲያ ከፍተኛ ስልጠና ወስደዋል። ኤል-39 የመለማመጃ አውሮፕላን ሴፍቲ ሃላፊ ነበሩ። ከተግባርድ ጀርባ ኪራይ ቤቶች በሰጣቸው መኖሪያ ተከራይተው ይኖሩ ነበር። በ1996ዓ.ም ለውሽማቸው  ቤቱን መስጠት የፈለጉት ጄ/ል መሃሪ መ/አ ለማን ቤቱን ይጠይቃቸዋል፤ « ለምን እለቃለው?» በማለት እምቢ ይላሉ። ጄ/ል ወዲ ዘውዴ ለማስፈራራት ይሞክራሉ። ለማ ግን አልተበገሩም። ጄኔራሉ የአየር ሃይል ኤር-ፖሊሶችን በማሰማራት መ/አ ለማ በመኖሪያ ቤታቸው በምሽት ያስደበድባሉ። በአጋጣሚ ፓትሮል የሚዞሩ ፌደራል ፖሊሶች ደርሰው ያስጥሉኣቸዋል።
መ/አ ለማ ለደታ ፍ/ቤት ይከሳሉ፤ ደብዳቢዎቹ ፍ/ቤት ቀርበው ሲጠየቁ « ወዲ ዘውዴ ነው የላከን » ይላሉ። ከዚያም ጄ/ሉ ተከሰሱ፤ በአስገራሚ ሁኔታ ፍ/ቤቱ ክሱን በማቓረጥ «ጉዳዪ በወታደራዊ ፍ/ቤት ነው መታየት ያለበት» አለ። መ/አ ለማ በደረሰባቸው ከባድ ድብደባ አንድ ጆሮቸው አይሰማም፤ኩላሊታቸውና እግራቸው ክፉኛ ተጎድቶ ስለነበረ፤ የሃኪሞች ቦርድ « መስራት እንደማይችሉ በመግለጽ ቦርድ እንዲወጡ ወሰነ።
ይህን ተከትሎ ጄ/ል ወዲ ዘውዴ ባሳለፉት ቀጭን ትእዛዝ መ/አ ለማ እስር ቤት ተወረወሩ፤በየቀኑ ከፍተኛ ድብደባ ይፈጸምባቸው ነበር። ክእስር ቤት በተደጋጋሚ ደብዳቤ ጽፈዋል፤ በወቅቱ የመከላከያ ሚ/ር ለነበሩት አባዱላ ገመዳ ጭምር የአቤቱታ ጥሪ አሰምተዋል። ሰሚ ግን አላገኙም።
መጀመሪያ በአየር ሃይል ከዛም በታጠቅና ናዝሬት እስርቤቶች የታሰሩትና ከፍተኛ ግፍና ሰቆቃ የተፈራረቀባቸው መ/አ ለማ መጨረሻቸው ምን እንደሆነ አይታወቅም።
Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 12 years ago on November 3, 2012
  • By:
  • Last Modified: November 3, 2012 @ 12:11 pm
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar