www.maledatimes.com የጋዜጠኞች መታሰር ለፕሬሱ አደጋ ነው ተባለ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

የጋዜጠኞች መታሰር ለፕሬሱ አደጋ ነው ተባለ

By   /   August 5, 2019  /   Comments Off on የጋዜጠኞች መታሰር ለፕሬሱ አደጋ ነው ተባለ

    Print       Email
0 0
Read Time:5 Minute, 31 Second

ድንበር የለሽ ዘጋቢዎች የተሰኘው የጋዜጠኞች መብት ተቆርቋሪ ቡድን ይፋ እንዳደረገው የዚህ ዓመት የዓለም የጋዜጠኞችና ሃሳብን የመግለፅ ይዞታ ዘገባ ኢትዮጵያን በፕሬስ ነፃነት እርከን ከ180 የዓለም ሃገራት 150ኛ ላይ ሲያስቀምጣት፤ ኤርትራ ደግሞ ሰሜን ኮሪያን ቀድማ 179ኛ ደረጃ ላይ መቀመጧን አመልክቶ ነበር። ዓለም አቀፉ ድርጅት በያዝነዉ ዓመት አጋማሽ፣ ጥር ላይ ባወጣዉ የፕረስ ነፃነት መዘርዝር ኢትዮጵያ አምና ከነበረችበት አርባ ደረጃ ቀንሳለች፡፡

ይህም በበርካታ አለም አቀፍ ተቋማት ምስጋና እንዲቸራት ምክንያት ሆነ፡፡ ይሁን እንጂ እንደ ድርጅቱ ገለጻ፣ ውደሳው መቆየት የቻለው ለአራት ወራት ያህል ብቻ ነበር፡፡ ሰኔ ወር ላይ አራት ጋዜጠኞች መታሰራቸውን ተከትሎ፣ የኢትዮጵያ መንግሥት ባለፈው ዓመት በመገናኛ ብዙኃን ነጻነት ላይ ባደረገው ከፍተኛ መሻሻል የኋሊት የመቀልበስ አደጋ ተጋርጦበታል ሲል የዓለም አቀፉ የመብት ተሟጋች ድርጅት ሃምሌ 17/2011 መግለጫ አወጣ።

ሰሞኑን በምስራቅ አፍሪካ የአምንስቲ ኢንተርናሽናል ዋና ተጠሪ ጆአን ንያንዩኪ እስሩና የመክሰስ ዛቻዉ ጠ/ሚ ዐብይ አሕመድ ወደ ስልጣን ከመጡ ወዲህ በኢትዮጵያ የታየዉን የፕሬስ ነፃነት የሚደፈጥጥ፣ ሃገሪቱንም ወደ አልተፈለገ አቅጣጫ የሚያመራት እንደሆነ አመልክተዋል። የድርጅቱ ዋና ተጠሪ የታሰሩ ጋዜጠኞች ሁሉ መፈታት አለባቸዉ፤ የተመሰረተባቸዉ ክስም ዉድቅ መሆን አለበት ሲሉ አሳስበዋል።

አምንስቲ እንዳለዉ የኢትዮጵያ መንግሥት መፈንቅለ መንግሥት ካለዉ የባለስልጣናት ግድያ በኋላ ሦስት ጋዜጠኞች ታስረዋል። ከሦስቱ ሁለቱ በአሸባሪነት ተከስሰዋል። በእስር ላይ ያሉ እንዲሁም ታስረው ከተፈቱ ጋዜጠኞች መካከል የአሃዱ ጋዜጠኞች ሊዲያ አበበ፣ ሱራፌል ዘላለም እና ታምራት አበራ እንዲሁም ደግሞ የሬድዮ ጣቢያው ሥራ አስከያጅ ጥበቡ በለጠ ድርጅቱን ወክለው ክስ ተመስርቶባቸው እንደነበር ይታወሳል፡፡

ጋዜጠኞቹ ከዚህ ቀደም በአሃዱ ሬድዮ ሰንዳፋ አካባቢ የሚገኝ፣ ባለቤትነቱ የሌላ ግለሰብ የሆነ ንብረትን ሐሰተኛ መታወቂያ በማዘጋጀት እና ንብረቱ የእነሱ እንደሆነ በማስመሰል ንብረቱን ሕገወጥ በሆነ መልኩ ተወሰዷል ሲል ዘገባ አቅርቧል።

ሥሜ ጠፍቷል ያለው ፍርድ ቤትም ጋዜጠኞቹ ሕዝብ በመንግሥት ላይ እንዲያምፅ አድርገዋል እና ሚዛናዊ ያልሆነና አድሏዊ ዜና አቅርበዋል በሚል በሰኔ 4/2011 በበረክ ወረዳ ፍርድ ቤት ክስ ተመስርቶባቸው በእስር ላይ የነበሩ ቢሆንም ራሳቸውን ለመከላከል በቀረቡበት ቀጠሮ ሐምሌ 12/2011 ቀን የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የተከሰሱበት ክስ በድጋሜ መጣራት አለበት የሚል ትዕዛዝ በመስጠቱ ክስ መቋረጡ ይታወሳል፡፡

በተጨማሪም የባልደራስ ዋና ጸሐፊ እንዲሁም የቀድሞ ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ ዐቃቢ ህግ ከዚህ ቀደም በባህር ዳር ከተማ ከተፈጠረው ችግር ላይ እጠረጥረዋለው ስለዚህ ጉዳዩን የበለጠ ለማጣራት 28 ቀን ይፈቀድልኝ በማለቱ ፍርድ ቤቱ በእስር ላይ እንዲቆይ ወስኖ እንደነበር ይታወቃል፡፡

የበረራ ጋዜጣ እንዲሁም የአስራት ቴሌቪዥን ጋዜጠኛ በሪሁን አደራ፣ የአማራ ሚዲያ ኔትዎርክ ጋዜጠኛ ታስሮ መለቀቅና የሲዳማ ሚዲያ ኔትዎርክ ጋዜጠኛ መታሰር በዋቢነት ከሚጠቀሱት መካከል ናቸው፡፡ በፈረንሳይኛ ምሕፃሩ RSF ተብሎ የሚጠራዉ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ድርጅትም በተመሳሳይ፣ ሰሞኑን ባወጣዉ መግለጫዉ እንዳለዉ፣ መንግሥት የወሰዳቸዉ እርምጃዎች ባለፈዉ አንድ ዓመት ብዙ ተስፋ የተጣለበትን የፕረስ ነፃነት ላይ አደጋ የሚያጋልጥ ነዉ። ፖለቲከኛው ሙሼ ሰሙ በበኩላቸው፣ በጋዜጠኞች ላይ የሚታዩት ማዋከቦችና ዛቻዎች አሁንም ቀጥለዋል፡፡

የማይመለከተው አካል ተነስቶ በጋዜጠኞች ላይ መግለጫ ይሰጣል ያሉት ሙሼ፣ ለምሳሌ መከላከያ ሚኒስትር “በመከላከያው ላይ በተሰሩት ዘገባዎች ዙሪያ በፍትህ መጽሄት ላይ ክስ እመሰርታለሁ” ሲል የሰጠው መግለጫ ተገቢነት የሌለውና ሙያተኛውን የሚያሸማቅቅ ሲሉ ለአዲስ ማለዳ አስታውቀዋል፡፡ ሚዲያውና ባለሙያው ስህተት ቢሰራ እንኳን ያንን በህጋዊ መንገድ መጠየቅ እንጂ፣ ማንም ተነስቶ በፈለገው ሰአት መግለጫ ሊሰጥ አይገባም ሲሉ አክለዋል። የኢትዮጵያ ነጻ ጋዜጠኞች ማህበር ፕሬዚደንት ወንደሰን መኮንን፣ በሙሼ ሃሳብ ይስማማሉ።

ጋዜጠኞች በሚሰሩት ስራ ከስ ሲመሰረትባቸው ህጉን መሰረት ባደረገ መልኩ መሆኑን የሚያወሱት ወንደሰን፣ ከዚህ ባለፈ መልኩ ማንም እየተነሳ ቢሮ እየከበበና እያዋከበ ጋዜጠኛውንና ሙያውን ማዳከም እንደሌለበት ለአዲስ ማለዳ ገልጸዋል፡፡ በመጀመርያ የወንጀል ህጉ ሚዲያ ላይ ጠንከር ያለ ነው የሚሉት የህግ ባለሙያው ስሜነህ ኪሮስ፣ አሁን ያለው የወንጀል ህግ የሚዲያ ነፃነትን የሚያስከብር አይደለም ሲሉ ለአዲስ ማለዳ አስታውቀዋል፡፡

ምክንያቱንም ሲያስረዱ፣ በአፄ ሀይለ ስላሴ ዘመነ መንግስት ወቶ የነበረው የወንጀል ህግ አሁንም ድረስ የፀና ነው፡፡ ነፃ ሆኖ የመገመት መብትን ይጣረሳል፡፡ በወንጀል ህጉ አንቀፅ 43 ወይም 45፣ ወንጀል የተባለው ተግባር ወደ ህትመቱ የገባው በዋና አዘጋጁ እውቀት እንደሆነ ግምት ይወሰዳል፡፡ ግምት ከወሰደም በኃላ ተቃራኒ ማስረጃን ማቅረብ ይከለክላል፡፡ ይሄ ደግሞ ነፃ ሆኖ የመገመት መብትን በግልፅ የሚጣረስ ነው ሲሉ የህጉን ክፍተት ያሳያሉ፡፡

በሚዲያ ተፈፀመ የሚባልን ወንጀል አንደኛ ወንጀል የሚያደርገው ምድነው፣ የሚቀጣውስ ምንድነው የሚለውን እንደገና አተኩሮ ማየት ያስፈልጋል ባይ ናቸው፡፡ የጋዜጠኞቹ ይዞታ ሰላማዊ ተቃዋሚዎች ከባሕር ዳሩ ክስተት ጋር ግንኙነት የላቸውም የሚሉት ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ፣ ጋዜጠኞቹ በየእስር ቤቱ የተያዙበት ሁኔታም እጅግ የሚያሳዝን ነዉ ይላሉ፤ ከህወሃት ዘመን የሚብስ እንጂ የሚስተካከል አይደለም ሲሉ ሃምሌ 17/2011 በሰጡት መግለጫ ያስታወቁት እስክንድር፣ ወንድሞቻችን እጅግ አስቸጋሪ በሆነ ሁኔታ ላይ ነዉ የሚገኙት፤ እጅግ ጠባብ በሆነ ፤ ምንም ብርሃን በሌለበት ጨለማ እና ቀዝቃዛ ክፍል፤ ከፈነዳ መፃዳጃ ቤት የሚወጣ ሽታን እየተነፈሱ፤ ኢ- ሰብዓዊ በሆነ ሁኔታ ላይ ነዉ የሚገኙት» ሲሉም ታሳሪዎቹ ይገኙበታል ያሉትን ሁኔታ ዘርዝረዋል። «ሁኔታውም ለሀገራችን የኋልዮሽ ጉዞ ነው» ብለዋል።

ፍርድ ቤቶችም ችግር እንዳለባቸዉ ከወዲሁ ምልክት እያየን ነዉ የሚሉት እስክንድር «ንፁሐን ዜጎች ሽብር በሌለበት ሀገር በሽብር ተጠርጥረዋል ተብለዉ የአቃቤ ሕግን ጥያቄ ተከትሎ ፍርድ ቤት ሲቀርቡ፤ ሙሉ ማስረጃ እንኳ ሳይሆን አመላካች ማስረጃ አላችሁ ብሎ እንኳ ሳይጠይቅ በደፈናዉ እየተቀበለ ነዉ» ሲሉ ገልጸዋል።

ሙሼ፣ ባለፉት 12 ወራት ውስጥ የታዩትን ለውጦች ከዚህ ቀደምም መንግሥታት ሲለወጡ እንመለከተ የነበረው አይነት ለውጥ ነው ይላሉ። ‘’ከዚህ ቀደም ከነበረን ታሪክ እንደምረዳው መንግሥታት ሲቀየሩ፤ አዲስ መንግሥት ሲመጣ ሚዲያውን የመክፈት ባህሪ አላቸው። ሚዲያዎች አዲስ የመጣውን መንግሥት ማጀገን፤ ያለፈውን ደግሞ ማሳጣት ሥራዬ ብለው ይያያዙታል። መንግሥትም ሚዲያዎቹ ፊታቸውን ወደእሱ እስኪያዞሩ ድረስ በይሁንታ ይዘልቃል’’ ሲል ሃሳባቸውን ያስቀምጣሉ።

ሙሼ ጨምረው የጠቅላይ ሚንስትሩ አስተዳደርም ለሚዲያዎች ምን ያክል ክፍት መሆኑ የሚፈተነው ከአሁን በኋላ በሚኖሩ ሁነቶች ነው ይላሉ። አክለውም ‘’የሚዲያ ፍልስፍና ስለመኖሩ ከመንግሥት በግልጽ አልተነገረንም፤ ከዚህ ቀደም የነበረው ኢህአዴግ ባህሪው ሚዲያ ጠል ነበረ። ይህም ከሚከተለው ‘ፖለቲካዊ-ኢኮኖሚ ርዕዮተ አለም’ ጋር አብሮ ይሄዳል። አሁን ለውጡ ስርዓታዊ መሆን ይኖርበታል።’’

በማለት ይናገራሉ። በአሁኑ ወቅት ጋዜጠኞች የታሰሩበት ሁኔታ አሳሳቢ መሆኑን እየሰማን ነው የሚሉት ሙሼ፣ እጅግ ጠባብ በሆነ ፤ ምንም ብርሃን በሌለበት ጨለማ እና ቀዝቃዛ ክፍል፤ ከፈነዳ መፃዳጃ ቤት በሚወጣ ሽታ እየተፈተኑ መሆኑ ሲነገር መስማት በራሱ አሳፋሪ ነው ብለዋል፡፡ እንደመፍትሄ ስሜነህ፣ ጋዜጠኛ መታሰር አለበት የለበትም ለሚለው ህጉ ራሱ የሚመልሰው ጉዳይ ነው ይላሉ፡፡

አክለውም፣ አሁን ልናየው የሚገባው ህጉን እንዴት ማሻሻል ይቻላል የሚለውን ነው፡፡ ማንኛውም ነገር ላይ ጋዜጠኞች አስተያያት መስጠት ይችላሉ፡፡ ፍርድ ቤቱ ሚስጥር ነው ብሎ በዝግ ችሎት ሳያደርግ በግልፅ ችሎት ውሳኔ የሚሰጥ ከሆነ ጋዜጠኛውን በሚድያ መዘገብ፣ እንዲሁም ደግሞ አስተያያት መስጠት ወንጀለኛ የሚስብለው ድንጋጌ የለም ብለዋል፡፡ የፍርድ ውሳኔው ስህተት ከሆነ አስተያያት ሰጥቶ ማብጠልጠል ይቻላል የሚሉት ስሜነህ፣ እዚህ ሀገር ትልቁ ችግር ፍርዱ ስህተት ነው ብሎ መናገር ክልክል መሆኑ ነው፡፡ የተለየ አስያየት እንደ ጦር የሚፈራበት ዘመን ላይ ነው ያለነው፡፡

ህዝቡ በህዝቡ ላይ እንዲነሳ አድርጋችዋል በሚል ታስረው የተፈቱ ብዙ ሰዎችን ማየት እንችላለን፡፡ በሚገርም ሁኔታ ግን ክስ የሚመሰረተው ዛሬ፣ ፍርድ የሚሰጠው ከሁለት ዓመት ባኃላ ሊሆን ይችላል፡፡ ሲሉ ክፍተት አለበት ያሉት የፍትህ ስርአት መስተካከል እንዳለበት ይመክራሉ፡፡

፣ አሁን ልናየው የሚገባው ህጉን እንዴት ማሻሻል ይቻላል የሚለውን ነው፡፡ ማንኛውም ነገር ላይ ጋዜጠኞች አስተያያት መስጠት ይችላሉ፡፡ ፍርድ ቤቱ ሚስጥር ነው ብሎ በዝግ ችሎት ሳያደርግ በግልፅ ችሎት ውሳኔ የሚሰጥ ከሆነ ጋዜጠኛውን በሚድያ መዘገብ፣ እንዲሁም ደግሞ አስተያያት መስጠት ወንጀለኛ የሚስብለው ድንጋጌ የለም ብለዋል፡፡ የፍርድ ውሳኔው ስህተት ከሆነ አስተያያት ሰጥቶ ማብጠልጠል ይቻላል የሚሉት ስሜነህ፣ እዚህ ሀገር ትልቁ ችግር ፍርዱ ስህተት ነው ብሎ መናገር ክልክል መሆኑ ነው፡፡ የተለየ አስያየት እንደ ጦር የሚፈራበት ዘመን ላይ ነው ያለነው፡፡

ህዝቡ በህዝቡ ላይ እንዲነሳ አድርጋችዋል በሚል ታስረው የተፈቱ ብዙ ሰዎችን ማየት እንችላለን፡፡ በሚገርም ሁኔታ ግን ክስ የሚመሰረተው ዛሬ፣ ፍርድ የሚሰጠው ከሁለት ዓመት ባኃላ ሊሆን ይችላል፡፡ ሲሉ ክፍተት አለበት ያሉት የፍትህ ስርአት መስተካከል እንዳለበት ይመክራሉ፡፡

ሙሼ በበኩላቸው መንግስት ራሱን መፈተሽ አለበት ብለዋል። የመናገርና የመጻፍ ነጻነት ከተገፈፉና ሰዎች ያለምክንያት መታሰር ከጀመሩ አገርን
እንደሃገር ለማስቀጠል ከባድ ስለሚሆን መንግስት ራሱን ማረም እንዳለበት ይመክራሉ፡፡
ወንደሰንም የሙሼን ሃሳብ ይጋራሉ። ጋዜጠኛን በማስፈራራትና በማሰር ነገሮችን ማስተካከል እንደማይቻል ባለፉት ስርአቶች አይተናል፤ ስለዚህ
ከዛ ብዙ መማር ይኖርብናል ብለዋል፡፡

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 5 years ago on August 5, 2019
  • By:
  • Last Modified: August 5, 2019 @ 9:11 am
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar