www.maledatimes.com የታጠቁ አካላት በኤፍራታና ግድም ወረዳ ተኩስ ከፍተው አካባቢውን ለመረበሽ ያደረጉት ሙከራ መክሸፉን የወረዳው አስተዳድርና ፀጥታ ጽህፈት ቤት አስታወቀ! - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

የታጠቁ አካላት በኤፍራታና ግድም ወረዳ ተኩስ ከፍተው አካባቢውን ለመረበሽ ያደረጉት ሙከራ መክሸፉን የወረዳው አስተዳድርና ፀጥታ ጽህፈት ቤት አስታወቀ!

By   /   October 5, 2019  /   Comments Off on የታጠቁ አካላት በኤፍራታና ግድም ወረዳ ተኩስ ከፍተው አካባቢውን ለመረበሽ ያደረጉት ሙከራ መክሸፉን የወረዳው አስተዳድርና ፀጥታ ጽህፈት ቤት አስታወቀ!

    Print       Email
0 0
Read Time:42 Second

ለጊዜው ማንነታቸው ያልታወቁ የታጠቁ ኃይሎች በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታና ግድም ወረዳ ከተራራ ሥፍራ በመሆን ወደ አጣዬ ከተማ በመተኮስ የአካባቢውን ሰላም እየረበሹ መሆኑን የወረዳው አስተዳድርና ፀጥታ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ጌታቸው የሽጥላ ገልፀዋል።

አቶ ጌታቸው እንዳስታወቁት ከተራራ ወደ ከተማዋው በተከፈተው ተኩስ ስጋት የአጣዬ ቅዳሜ ገበያ ተበትኗል፤ ነዋሪውም እየተረበሸ ነው።

የአማራ ክልል ልዩ ኃይልና የመከላከያ ሠራዊት ሕዝቡን ለማረጋጋት እየሠሩ እንደሆነም ኃላፊው አስታውቀዋል። የታጠቁ ኃይሎቹ በርከት ያሉ መሆናቸውንና በብዙ አቅጣጫ እንደሚተኩሱ ከመግለጻቸው ባለፈ ማንነታቸውና በሰው ላይ ያደረሱት ጉዳት ስለመኖሩ አልተገለጸም።

የሰሜን ሸዋ ዞን የሠላምና ደኅንነት ግንባታ መምሪያ ኃላፊ አቶ ካሳሁን እምቢያለ ግን የታጠቁ ቡድኖቹ በልዩ ኃይል ላይ ጥቃት ሊፈጽሙ መሞከራቸውንና በአጸፋው ከጥፋት ኃይሎቹ አንዱ መገደሉን አስታውቀዋል። መምሪያው ሁኔታው ወደ መረጋጋት መመለሡንም አስታውቋል። አካባቢውን ልዩ ኃይል፣ ፌዴራል ፖሊስና መከላከያ ሠራዊት መቆጣጠሩም ተብራርቷል።

በኤፍራታና ግድም የተከሰተው ሁኔታ ከሰሞኑ በምንጃር ሸንኮራ ወረዳ አጋጥሞ እንደነበር ከተገለጸው ክስተት ጋር የማይገናኝ ስለመሆኑም የመምሪያው ኃላፊ አስታውቀዋል።

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 5 years ago on October 5, 2019
  • By:
  • Last Modified: October 5, 2019 @ 10:54 am
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar