www.maledatimes.com ሰበር ዜና ሕወሓት ልዩ ሀይሉን ወደ አላማጣ እያስገባ ነው የሰሜን እዝ ጥንቃቄ እንዲያደርግ ተጠየቀ! - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

ሰበር ዜና ሕወሓት ልዩ ሀይሉን ወደ አላማጣ እያስገባ ነው የሰሜን እዝ ጥንቃቄ እንዲያደርግ ተጠየቀ!

By   /   October 21, 2019  /   Comments Off on ሰበር ዜና ሕወሓት ልዩ ሀይሉን ወደ አላማጣ እያስገባ ነው የሰሜን እዝ ጥንቃቄ እንዲያደርግ ተጠየቀ!

    Print       Email
0 0
Read Time:52 Second

የሕወሓትን ወታደራዊ እንቅስቃሴ በቅርብ እየተከታተለ ይፋ የሚያደርገው ከራያ ማንነት ኮሚቴ የሕዝብ ግንኙነት ሀላፊው አቶ ደጀኔ አሰፋ እንደገለጸው የጦርነት እንቅስቃሴ ለማድረግ ሰፊ ዝግጅት ሲያደርግ የቆየው ሕወሓት ዛሬ ጥቅምት 9/2012 ልዩ ሀይሉን ወደ አላማጣ እያስገባ መሆኑን እና የሰሜን ዕዝ ይህ ተስፋ የቆረጠ ሀይል ሕዝብ ላይ ጉዳት እንዳይደርስ ጥንቃቄ እንዲወስድ ጥሪ አቀረበ።

Image may contain: sky, outdoor and nature

“ዛሬ መስከረም 9/2012 በዚህ ሰዓት ከግራካህሱ ወደ ራያ አላማጣ ከተማ እየገባ ያለ የትህነግ ልዩ ሃይል ነው። ይህ ተስፋ የቆረጠ ድርጅት አጥፍቶ በመጥፋት የመጨረሻ በቀሉን በህዝባችን ላይ እንዳይፈፅም መረጃው ለመከላከያ ሰራዊት በተለይም ለሰሜን እዝ እንዲደርስ እንሻለን።” ሲል የራያ ማንነት ኮሚቴ የሕዝብ ግንኙነት ሀላፊው ጥሪ አድርጉዋል።

ሰሞኑን ሕወሓት በጉልበት ወደ አካለለው ራያ ተገኝቶ ለአካባቢው ሚሊሻዎች በነፍስ ወከፍ ጥይት፣ቃሬዛ፣አካፋና ዶማ ጭምር ማከፋፈሉን መዘገባችን አይዘነጋም።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ትላንት በሚሊኒየም አዳራሽ መደመር የተሰኘውን አዲሱ የገዢው ፓርቲ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ፖሊሲ ይሆናል የተባለ መጽሐፋቸውን ሲያስመርቁ ጦርነት እንደማያስፈልግ ልዩነትን በሰለጠነ እና ሰላማዊ መንገድ ብቻ መፍታት እንደሚገባ አንስተው በስም አይጥቀሱ እንጂ መቀሌ ከመሸጉ በሁዋላ ሆቴል ተቀምጠው ውስኪ ሲራጩ የሚኖሩትን ጠንከር አድርገው መውቀሳቸው አይዘነጋም።

የሕወሓትን የጦርነት ነጋሪት የታከለበት መግለጫ ተከትሎ ከኢህአዴግ እና ኦዴፓ ጠንከር ያለ መግለጫ ማውጣታቸው አይዘነጋም።

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 5 years ago on October 21, 2019
  • By:
  • Last Modified: October 21, 2019 @ 12:47 pm
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar