www.maledatimes.com የዘመናዊ ስናይፐር የጦር መሣሪያ ተጓዳኝ ዕቃዎች በኤርፖርት ፍተሻ ተያዙ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

የዘመናዊ ስናይፐር የጦር መሣሪያ ተጓዳኝ ዕቃዎች በኤርፖርት ፍተሻ ተያዙ

By   /   November 7, 2019  /   Comments Off on የዘመናዊ ስናይፐር የጦር መሣሪያ ተጓዳኝ ዕቃዎች በኤርፖርት ፍተሻ ተያዙ

    Print       Email
0 0
Read Time:44 Second

በጋዜጣዉ ሪፓርተር

ማክሰኞ ጥቅምት 25 ቀን 2012 ዓ.ም. ከቀትር በኋላ በአዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት፣ የዘመናዊ ስናይፐር የጦር መሣሪያ ተጓዳኝ ዕቃዎች (Accessories) በቁጥጥር ሥር ዋሉ፡፡

የገቢዎች ሚኒስቴር ማምሻውን እንዳስታወቀው፣ በአዲስ አበባ ኤርፖርት ጉምሩክ የግል መገልገያ ዕቃዎችን ሽፋን በማድረግ በዓረቢያን መጅሊስ ውስጥ በሕገወጥ መንገድ ተደብቀው በግለሰብ ስም የመጡ የተለያዩ የስናይፐር የጦር መሣሪያ ተጓዳኝ ዕቃዎች ተይዘዋል፡፡

በኤክስሬይና በዕቃ ፍተሻ ኦፊሰሮች አማካይነት የስናይፐር ጦር መሣሪያ ተጓዳኝ ዕቃዎች በቁጥጥር ሥር ሲውሉ፣ ስሙና ማንነቱ ያልተገለጸ ተጠርጣሪም አብሮ መያዙን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

የጦር መሣሪያው ተጓዳኝ ዕቃዎች ከየት እንደመጡና በየትኛው አየር መንገድ እንደተጓጓዙ ግን አልተገለጸም፡፡ የተጓዳኝ ዕቃዎቹ ሥሪት የት እንደሆነም አልታወቀም፡፡

በኢትዮጵያ ሕገወጥ የጦር መሣሪያዎች ዝውውር በመስፋፋቱ ምክንያት፣ እንዲህ ያለው የጦር መሣሪያ ተጓዳኝ ዕቃዎች በኤርፖርት በኩል ሊገቡ ሲሉ መያዛቸው መደናገር መፍጠሩን ለማወቅ ተችሏል፡፡

እጅግ ዘመናዊ ለሆነ ስናይፐር የጦር መሣሪያ በተጓዳኝነት የሚያገለግሉ ዕቃዎች በኤርፖርት በኩል ወደ አገር ውስጥ ሊገቡ ሲሉ መያዛቸው፣ የጦር መሣሪያ ዝውውሩ ምን ያህል አደገኛ እየሆነ እንደመጣ ማመላከቻ ነው ተብሏል፡፡

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 5 years ago on November 7, 2019
  • By:
  • Last Modified: November 7, 2019 @ 10:56 am
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar