www.maledatimes.com ኒውክሌር ጤፍ ማሻሻሻ ዘዴ ሊሆን እንደሚችል ተጠቆመ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

ኒውክሌር ጤፍ ማሻሻሻ ዘዴ ሊሆን እንደሚችል ተጠቆመ

By   /   November 11, 2019  /   Comments Off on ኒውክሌር ጤፍ ማሻሻሻ ዘዴ ሊሆን እንደሚችል ተጠቆመ

    Print       Email
0 0
Read Time:1 Minute, 50 Second

በኢትዮጵያ የግብርንናና ምርት ተቋም ደብረዘይት የሚገኘው የእርሻ ምርምር ተቋም ለሰላሳ ስድስት ወራት ሲከናወን የነበረው የጥናት አጀንዳ የአቶሞክ ነጸብራቅ የጤፍ ምርትን ሊያሳድግ እንደሚችል ጠቁሟል ። የዘር ምርቱንም ሃይል ያለው የእድገት ብቃት ሊኖረው እንደሚችል አሳውቋል።

በሶሎሞን ጫንያለው (ዶ/ር) የሚመራው እና አራት ባለሞያዎችን አሳትፎ በኢትዮጵያ መንግሥት ሙሉ የፋይናንስ ድጋፍ የሚደረግለት ይህ ምርምር፣ የኒኩሌር ጨረርን በመጠቀም የጤፉን ዘረመን በማሻሻል የተሻለ ዘርን ለማግኘት ተስፋ ሰጪ ምልክቶች መታየታቸውን ለመታዘብ ተችሏል። በቁመቱ ያጠረ እንዲሁም በአጭር ጊዜ በመድረስ የአየር ንብረት ለውጥን የሚቋቋም ምርጥ ዘር ላማግኘት የተለያየ መጠን ያለው የኒኩሌር ጨረርን በመጠቀም ሙከራ እየተደረገ እንደሆነ ተመራማሪው ለማለዳ ተናግረዋል።

‹‹ከተለያዩ ዝርያዎች የተወሰዱ የጤፍ ዝርዎች ላይ የተለያየ የጨረር መጠንን በመጠቀም የጤፉን ዘረመን በማሻሻል ከፍተኛ የፕሮቲን መጠን ያለው፣ በጥቂት ውሃ በአጭር ጊዜ የሚደርስ ሰብል ለማምረት የሚስችሉ ምልክቶችን ተመልክተናል›› ሲሉ ተናግረዋል። ‹‹በተያዘው ዓመት ምርቱን ወደ መስክ ወስደነዋል፣ የጤፍ ተክል ቁመቱ ሲረዝም የመውደቅ አዝማሚያ ስለሚኖረው የምርታማነት አቅሙ የሚቀንስ ሲሆን በቁመቱ ያጠረ እና በአጭር ጊዜ የሚደርስ ዝርያን በመፍጠር ድርቅን የሚቋቋም ምርት እናገኛለን ብለን እናምናለን›› ሲሉ ሶሎሞን ተናግረዋል።

ከዚህ ቀደም የተለያዩ ኬሚካሎችን በመጠቀም ምርጥ ዘሮችን ሲያዘጋጅ የቆያው ተቋሙ፣ የኒኩሌር ቴክኖሎጂን በመጠቀም ተመሳሳይ ጥናት ሲያካሒድ የመጀመሪያው ነው። በኢትዮጵያ ውስጥ ሦስት ሚሊዮን ሄክታር መሬት በጤፍ ምርት የሚለማ ሲሆን በየ ዓመቱ ስድስት ሚሊዮን አርሶ አደሮች ተሳታፊ ናቸው። ተመራማሪዎቹ ከኤክስ ሬይ ጋር ሲነፃፀር ከ10 እስከ 100 ሚሊዮን እጥፍ የሚበልጥ ጨረርን እንደሚጠቀሙ ለማወቅ ተችሏል።

ዓለም ዐቀፉ የአቶሚክ ኢነርጂ ተቋምም፣ ለጥናቱ የቴክኒክ እና ሥልጠና ድጋፎችን ያካሔደ ሲሆን በተመሳሳይም የጥንቃቄ እርምጃ ላይ ድጋፍ ማድረጉን ይፋ አድርጓል። ‹‹የምንጠቀምበት የኒኩሌር ጨረርን የሚሰጠን መሣሪያ ከፍተኛ ጥንቃቄ ይደረግበታል። በጥንቃቄ ካልተያዘ የሽብር ጥቃትን ጨምሮ ለተለያዩ እኩይ ተግባራት ሊውል ስለሚችል ለሦስተኛ ወገን እንዳይተላለፍ ከፍተኛ ቁጥጥር በኢትዮጵያዊያን ባለሞያዎች አምስተኛው የአፍሪካ የጨርቃ ጨርቅ የቆዳ እና የፋሽን ሳምንት በአዲስ አበባ ሊካሔድ ነው ሲሉ እኝሁ ግለሰብ ገልጸዋል።

ጤፍ በዓለማቀፍ ደረጃ ተፈላጊነቱ እየጨመረ መምጣቱን ተከትሎ፣ ዘሩን በማሻሻል የምግብ አቅርቦት እንዲሁም የኢኮኖሚ ጥቅሞችን እንዲያመጣ ለማድረግ የሚያስችል መሆኑንም ተመራማሪው ተናግረዋል። መደበኛ የኤክስሬይ ማሽን ከሚጠቀመው ከ10 እስከ 100 ሚሊዮን ጊዜ የሚልቅ የጨረር ኀይል የሚጠቀመው ይህ ምርምር፣ የኒኩሌር ቴክኖሎጂው ለሌላ ዓላማ እንዳይውል ጥብቅ ቁጥጥር እንደሚደረግበትም ታውቋል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተለያዩ ጥናቶች ግሉቲን የተባለውን የፕሮቲን አይነት መጠቀም የሚያመጣውን የጎንዮሽ ጉዳቶች በመሸሽ እንደ ጤፍ ያሉ ከግሉቲን ነጻ የሆኑ ጥራ ጥሬዎችን መጠቀም ተመራጭ እየሆነ መጥቷል። ይህም በኢትዮጰያ እና በኤርትራውያን ዘንድ ብቻ በሰፊው ሲዘወተር የቆየውን የጤፍ ምርት በዓለማቀፍ ደረጃ እንዲጨምር አድርጎታል። ምርምሩ ተጠናቆ ምርጥ ዘሩ ይፋ እስኪደረግ ከአራት እስከ አምስት ዓመት ጊዜያትን የጥናት ጊዜው ሊቆይ እንደሚችልም ሶሎሞን ተናግረዋል።

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 5 years ago on November 11, 2019
  • By:
  • Last Modified: November 11, 2019 @ 12:59 pm
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar