www.maledatimes.com በአዲስ አበባ 1.7 ቢሊዮን ብር ብድር ያለ ዋስትና ተሰጠ !! - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

በአዲስ አበባ 1.7 ቢሊዮን ብር ብድር ያለ ዋስትና ተሰጠ !!

By   /   November 11, 2019  /   Comments Off on በአዲስ አበባ 1.7 ቢሊዮን ብር ብድር ያለ ዋስትና ተሰጠ !!

    Print       Email
0 0
Read Time:2 Minute, 48 Second

ለብድሩ መያዣነት የሚመሠረተው ማህበር ሆኖ ይቀጥላል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በ2012 የበጀት ዓመት ከመደበው የወጣቶች የብድር ፈንድ ውስጥ 1.7 ቢሊዮን ብሩን በስድስት ወር ውስጥ ያከፋፈለ ሲሆን ለብድሩ መያዣነትም የተመሰረቱት ኢንተርፕራይዞች ራሳቸው እንጂ የማስተማመኛ ንብረት እንደሌለ አዲስ ማለዳ አረጋግጣለች። አዲስ ብድር እና ቁጠባ ተቋም ለሰባት ሺሕ ኢንተርፕራይዞች ብድሩን ያከፋፈለ ሲሆን፣ በዚህ ውስጥም ከ 21 ሺሕ በላይ ወጣቶች ተደራጅተዋል።

በግንባታው ዘርፍ እና በአምራችነት ለተሰማሩ ዘርፎች ቅድሚያ ተሰጥቷል። ወጣቶቹ እንደየ ተሰማሩበት የሥራ ዘርፍ አዋጭነት እና በአጭር ጊዜ ትርፍ የማስገኛት አቅም ከ አንድ ወር ጀምሮ እስከ 4 ወር የሚደርስ የእፎይታ ጊዜ እንደሚሰጣቸው ተገልጿል። የተበደሩትን ገንዘብም እንደተሰማሩበት የሥራ መስክ አዋጭነት ከ አንድ ዓመት እስከ አራት ዓመታት በሚደርስ ጊዜ ውስጥ እንዲመልሱ ውል ገብተዋል።

በአዲስ አበባ በሚገኙ በሁሉም ክፍለ ከተማዎች እና ወረዳዎች ለሚገኙ ወጣቶች ብድሩ እንደቀረበም አዲስ ብድርና ቁጠባ አስታውቋል። የተዘዋዋሪ ፈንዱ ተጠቃሚ ለመሆን የሚያመለክቱ ወጣቶችን የንግድ ሥራ ሃሳብ በማወዳደር እንደየ ንግድ ሥራ ሐሳባቸው ብድሩ የተከፋፈለ ሲሆን፣ አመላለሱን በተመለከተም በተቀመጠላቸው ጊዜ በማይመልሱ ወጣቶች ላይ ተገቢው ሕጋዊ እርምጃ እንደሚወሰድ አዲስ ብድር እና ቁጠባ ተቋም ገበያ ልማት ኀላፊ መስፍን ፊጤ ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል። የሥራ እድል ፈጠራ እና ምግብ ዋስትና ኤጀንሲ በበኩሉ ወጣቶችን በማደራጀት ለሚሰማሩበት ሥራ ዘርፍ ሥልጠና በመስጠት እና በማማከር እየተሳተፈ የሚገኛ ሲሆን፣ ሌሎች በርካታ ኢንተርፕራይዞች በመደራጀት ከተዘዋወሪ ፈንዱ ተጠቃሚ ለመሆን እየተጠባበቁ እንደሚገኙ ገልጿል። ሆኖም አንዳንድ ኢንተርፕራይዞች ብድር ካገኙ በኋላ ወደ ሥራ ሳይገቡ እንደሚጠፉ እና ወደ ሥራ በሚገቡበት ወቅት የቤት ኪራይ አዲስ ብድር እና ቁጠባ ተቋም መክፈሉን ተከትሎ ከሦስት እስከ ስድስት ወራት የሚሆን ገንዘብ በመቀበል እንደሚጠፉ በኤጀንሲው የኢንተርፕራይዞች ልማት ድጋፍ እና ክትትል ኀላፊ የሺጥላ ክፍሌ ተናግረዋል።

ይህንንም ችግር ለማስቀረት ኢንተርፕራይዞቹ በራሳቸው ገንዘብ ቤት ተከራይተው ብድሩን እንዲጠባበቁ የሚያደርግ አሠራር መተግበሩን የገለጹ ሲሆን፣ ይህም በርካታ ወጣቶችን ለችግር ከመዳረጉም በላይ አንዳንድ ኢንተርፕራይዞች ግን ግማሽ ብድር በመውሰድ ወደ ሥራ ሳይሰማሩ እንደሚጠፉ ገልጸዋል። ‹‹ብድሩ ቡድንን ዋስትና ባደረገ ማስያዣ መስጠቱ አንድ እርምጃ ሲሆን ገንዘቡን በማይመልሱ ኢንተርፕራይዞች ላይ ከሚመለከታቸው የሕግ አካላት ጋር በመሆን ተገቢውን ሕጋዊ እርምጃ ለመውሰድ አዲስ ብድርና ቁጠባ ዝግጁ ነው›› ሲሉ መስፍን ተናግረዋል።

ወጣቶች ይህንን ብድር በአግባቡ ሰርተው በመመለስ ሌሎች በሥራ አጥነት ውስጥ ለሚገኙ ዜጎች ዳግም በማበደር የሥራ እድል ለመፍጠር በሚደረገው ጥረት ወስጥ ወጣቶች እምነትን መሰረት ባደረገ መልኩ የወሰዱትን ብድር ሊመልሱ እንደሚገባ ተናግረዋል። አክለውም ከተዘዋዋሪ ፈንዱ ውጪ በመደበኛው አሰራር ተመሳሳይ ቡድንን ዋስትና ያደረገ የብድር አሰጣጣ መኖሩን እና ብድሩ የማይመለስበት አግባብ አለመኖሩን ገልጸዋል። በጉዳዩ ላይ አዲስ ማለዳ ነጋገረቻቸው ምጣኔ ሃብት ባለሙያ ጌታቸው ተክለማርያም የወጣቶች ተዘዋዋሪ ፈንዱ በአዲስ አበባ ብቻ ሳይሆን በመላው ሀገሪቱ በተቀደደ ጣሳ ላይ ውሃ እንደመጨመር ይቆጠራል ሲሉ ይገልፃሉ፡፡ በምክኒያትነትም ከዚህ ቀደም የተሰጠውን ገንዘብ በአግባቡ መሰብሰብ እንኳን ሳይቻል በስድስት ወራት ውስጥ የዚህን ያህል ገንዘብ ማሰራጨት ካለው ኢኮኖሚያዊ መነሻ እና ፋይዳ ይልቅ ፖለቲካዊ አላማው ያመዝናል ሲሉ ገልጸዋል፡፡

አክለውም በከተማ ውስጥ በአሁኑ ወቅት ያለወ ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ የዚህን ያህል ገንዘብ በብድር ለመስጠት የሚያስችል አይደለም ያሉ ሲሆን ተዘዋዋሪ ፈንዱ እንደስጦታ የሚቆጠር እና የመመለስ ሁኔታውም በአበዳሪዎቹ ሳይቀር የማይታመንበት ነው ብለዋል፡፡ በተጨማሪም ወጣቶች ለተሰማሩበት እና የንግድ ሀሳባቸውን ላቀረቡበት ስራ ዘርፍ እየተሰጠ መሆኑ ጥያቄ የሚያስነሳ ነው ብለዋል፡፡ ኢትዮጵያትቃቅን እና አነስተኛ ተቋማትን ከ ቴክኒክ እና ሙያ ትምህርት ቤቶች ጋር ለማገናኘት እያደረገችው ያለው ጥረት ከሌሎች ሀገራት ተለየ እና ሊበረታታ የሚገባው ነው የሚሉት ጌታቸው የጥቃቅን እና አነስተኛ መወቅሩ በድጋሚ ሊታይ የሚገባው እና የመዋቅረ ለውጥ ሊደረግበት ይገባል ይላሉ፡፡ በተጨማሪም ለተቋማቱን ከመመስረት እና ብደር ከመስጠት በላይ የሙያ ማሻሻያ ድገፎች ማድረግ እና በጥልቀት መከታተል ተገቢ ነው ብለዋል፡፡

4/8 አዲስ ብድር እና ቁጠባ ተቋም በ2012 በጀት ዓመት በመደበኛ ብድር አገልግሎት ኹለት ነጥብ ኹለት ቢሊዮን ብር፣ እንዲሁም በወጣቶች ተዘዋዋሪ ብድር ፈንድ አንድ ነጥብ ስምንት ቢሊዮን ብር፤ በድምሩ አራት ቢሊዮን ብር ለ 44 ሺሕ ተጠቃሚዎች የብድር አገልግሎት ለመስጠት ያቀደ ሲሆን አገልግሎቱን የበለጠ ቀልጣፋ ለማድረግ በከተማዋ በሁሉም ክፍለ ከተሞች ከተከፈቱት ቅርንጫፎች በተጨማሪ በያዝነው ዓመት 15 አዳዲስ ቅርንጫፎችን ለመክፈት ማቀዱን ገልጸዋል።

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 5 years ago on November 11, 2019
  • By:
  • Last Modified: November 11, 2019 @ 5:57 pm
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar