www.maledatimes.com በራስ አሉላ ስም የተሰየመው ት/ቤት በመለስ ተቀየረ ከኢየሩሳሌም አርአያ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

በራስ አሉላ ስም የተሰየመው ት/ቤት በመለስ ተቀየረ ከኢየሩሳሌም አርአያ

By   /   November 26, 2012  /   Comments Off on በራስ አሉላ ስም የተሰየመው ት/ቤት በመለስ ተቀየረ ከኢየሩሳሌም አርአያ

    Print       Email
0 0
Read Time:7 Minute, 15 Second

www.maledatimes.com

በትግራይ ተምቤን – አብዪአዲ የሚገኘውና በጀግናው ራስ አሉላ አባነጋ ስም ተሰይሞ የቆየው የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ስያሜው ተቀይሮ በመለስ ዜናዊ ስም እንዲሰየም መወሰኑን ታማኝ ምንጮች አስታወቁ።
በደርግ ዘመን የተሰራውና በራስ አሉላ ስም ተሰይሞ የ 9 – 10ኛ ክፍል ተማሪዎችን ተቀብሎ ሲያስተምር ከቆየ በሑላ ከ2002 ዓ.ም ጀምሮ የት/ቤቱን አቅም ለማሳደግ በሚል የ11-12ኛ መመሪያ ክፍሎችን ለመገንባት በአገር ውስጥና በውጭ አገራት የሚገኙ የአካባቢው ተወላጆች ገንዘብ አዋጥተው ስራው መከናወኑን ምንጮቹ ጠቁመዋል። ግንባታው ተጠናቆ ባለፈው ነሃሴ ወር ለማስመረቅ በዝግጅት ላይ እንዳለ አቶ መለስ በማለፋቸው ፕሮግራሙ መሰረዙን ሲታወቅ; ከሁለት ሳምንት በፊት በተከናወነው የምረቃ ስነ-ስርአት የክልሉ ከፍተኛ ባለስልጣናት በስፍራው እንደተገኙ ማወቅ ተችሎዋል።
ከምረቃው ጋር በተያያዘ  የራስ አሉላ ስም ተሰርዞ « መለስ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት » ተብሎ መሰየሙን ባለስልጣናቱ በይፋ እንደገለጹ ምንጮች አረጋግጠዋል። በት/ቤቱ በይፋ የመለስ ስም ተፅፎ መለጠፉ ተጠቁሞዋል። በህዝብ ገንዘብ መዋጮ የተገነባን ት/ቤት በጡንቻና በማን አለብኝነት ህዝብን በመናቅ የተፈጸመ ተግባር ነው ሲሉ የአካባቢው ተወላጆች ማውገዛቸው ታውቁዋል።
 www.maledatimes.com
በተለይ በአውስትራሊያ፡ ጀርመን፡ ኖርዌይ፡ አሜሪካ፡ ካናዳና… ሌሎች አገራት የሚኖሩ የአካባቢው ተወላጆች ባካሄዱት ቴሌ ኮንፈረንስ ከፍተኛ ተቃውሞ ማሰማታቸውን ተሳታፊዎቹ ገልጸዋል። ተሳታፊዎቹ እንዳሉት « የአፄ ምንሊክን፡ የሰማዕቱ አቡነ ጴጥሮስን ሃውልት ለማፍረስ የተጀመረው አፍራሽ እንቅስቃሴ ወደ ራስ አሉላ ተሻግሮዋል። ይህ የሚያመለክተው የቆየውን የኢትዮጲያን ታሪክ ለማጥፋት ቆርጠው መነሳታቸውን ነው። ይህ ትውልድ ታሪኩን አስጠብቆ የማቆየትና የተጀመረው አደገኛ አፍራሽ እንቅስቃሴ ከማውገዝ ባለፈ ለትግል መነሳሳት አለበት።ኢትዮጲያዊያን እጅ ለእጅ መያያዝ አለብን፤» ብለዋል። አክለውም « የኢትዮጲያዊነት ጉልህ መታወቂያና መገለጫ የሆኑ አኩሪ ታሪኰችንና ታሪክ ሰሪ ጀግኖችን ለማጥፋት ኤርትራዊው ቴውድሮስ ሃጎስ፡ በረከት ስሞንና ስብሃት ነጋ የሚመሩት አካል በአገራችን ላይ የጥፋት ዘመቻ ከፍተዋል» ሲሉ አንድ ተሳታፊ ተናግረዋል። « የዶጋሊ ዘመቻ » በሚል በየአመቱ ራስ አሉላ የሚዘከሩበት ታሪካዊ ቀን እንደነበረና ሕወሓት ወደ ስልጣን ከመጣ በሑዋላ ግን ይህ እንዲቀር መደረጉን እነዚሁ ወገኖች ያስታውሳሉ።
በሌላም በኩል በመቀሌ ከተማ ፒያሳ አካባቢ የአፄ ዮሃንስን መታሰቢያ ሃውልት ለማቆም ተጀምሮ የነበረው እንቀስቃሴ እንዲቆም መደረጉን የቅርብ ምንጮች አጋልጠዋል። ባለፈው አመት ከህዝብ በተዋጣ ገንዘብ ሓውልቱን ለማቆም የመሰረት ድንጋይ ተጥሎ እንደነበር ጠቁመው፤ በሁላ ግን « ከአንድ ሃይማኖት ተከታዮች ተቃውሞ በመቅረቡ ሃውልቱን ማቆም (መስራት) አይቻልም» በማለት እነ ቴውድሮስ ሃጎስ መወሰናቸውን ምንጮቹ ገልፀው፦ « አሳፋሪና ተቀባይነት የሌለው ተራ ምክንያት» ሲሉ ሁኔታውን በቅርብ የተከታተሉት ምንጮች አጣጥለውታል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ በአድዋ ከተማ አደባባይ ላይ ተሰቅሎ የነበረ የመለስ ፖስተር ተቀዳዶ መጣሉን ምንጮች ጠቆሙ። የክልሉ ካድሬዎች « የመድረክ ተለጣፊ የሆነው አረና ፓርቲ ነው ይህን የፈፀመው » በማለት ያልተጨበጠ የፈጠራ ወሬ እያሰራጩና እየዛቱ ነው ያሉት ምንጮች አክለውም ድርጊቱን የፈፀመው የአካባቢው ህዝብ እንጂ የትኛውም ተቃዋሚ ፓርቲ አይደለም ብለዋል።    www.maledatimes.com
Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 11 years ago on November 26, 2012
  • By:
  • Last Modified: November 26, 2012 @ 8:20 pm
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar