www.maledatimes.com 33ቱ ፓርቲዎች የምክትል ጠ/ሚኒስትሮቹን ሹመት ተቃወመ ኢራፓ “ስርአቱ ይስተካከል እንጂ ሹመቱን አልቃወምም” ብሏል (ሠላም ገረመው) - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

33ቱ ፓርቲዎች የምክትል ጠ/ሚኒስትሮቹን ሹመት ተቃወመ ኢራፓ “ስርአቱ ይስተካከል እንጂ ሹመቱን አልቃወምም” ብሏል (ሠላም ገረመው)

By   /   December 8, 2012  /   Comments Off on 33ቱ ፓርቲዎች የምክትል ጠ/ሚኒስትሮቹን ሹመት ተቃወመ ኢራፓ “ስርአቱ ይስተካከል እንጂ ሹመቱን አልቃወምም” ብሏል (ሠላም ገረመው)

    Print       Email
0 0
Read Time:6 Minute, 17 Second

በቅርቡ በአገሪቱ ጠ/ሚኒስትር በአቶ ኃይለማርያም  ደሳለኝ በፓርላማ ቀርቦ የፀደቀው የሁለት ምክትል ጠ/ሚኒስትሮች ሹመት ህገመንግስቱን የሚፃረር ነው ሲሉ በአዳማ ከተማ ፔቲሽን ተፈራርመው ለምርጫ ቦርድ ጥያቄዎቻቸውን ያቀረቡ 33 ፓርቲዎች ተቃወሙ፡፡ ኢራፓ በበኩሉ የኢህአዴግ ስርዓት ይስተካከል እንጂ ከህገመንግስት ውጭ ቢሆንም ለአገር እስከጠቀመ ድረስ ሹመቱን አልቃወምም ብሏል፡፡
የአገሪቱ ጠ/ሚኒስትር ሁለት ባለስልጣናትን በምክትል ጠ/ሚኒስትርነት ማዕረግ ለፓርላማ አቅርበው ማፀደቃቸው ህገመንግስቱን የጣሰ ተግባር ነው ብለዋል – ፓርቲዎቹ፡፡ ባለፉት ጊዜያትም
በጥድፊያና ከህገመንግስቱ ጋር በሚፃረር መልኩ የወጡት የፀረሙስና የመያዶች የፕሬስና የፀረ ሽብር አዋጆች ሁኔታው ቀጣይ እንጂ አዲስ ነገር አለመሆኑን ያሳያል ብለዋል – በመግለጫቸው፡፡ “የአጀንዳው
አቀራረብም ሆነ የሹመቱ አፀዳደቅ ከፓርላማው 33ቱ ፓርቲዎች የምክትል ጠ/ሚኒስትሮቹን ሹመት ተቃወመ ኢራፓ “ስርአቱ ይስተካከል እንጂ ሹመቱን አልቃወምም” ብሏል የአሰራር ስነስርዓት ጋር ያልተጣጣመና በተለመደው ጥድፊያ የተከናወነ ነው አጀንዳው ለፓርላማ አባላት በተለመደው አሰራር መሰረት ያልተሰራጨ ከመሆኑም በላይ በሚመለከተው ቋሚ ኮሚቴ ከህገመንግስቱ አንፃር ሳይመረመርና ሳይታይ መፅደቁ ይህን ያረጋግጣል” ብለዋል ፓርቲዎቹ፡፡የህዝብ ተወካዮች ም/ቤትም በተለያዩ ጊዜያት የህገመንግስቱን ድንጋጌዎች የሚጥሱ አምዶችን ተቀብሎ ማፅደቁን ፓርቲዎቹ ጠቁመው፤ አሁንም
ከዚህ ድርጊቱ ሳይቆጠብ በህገ መንግስቱ አንቀፆች 74፣ 75 እና 76 ሀገሪቱ አንድ ምክትል ጠ/ሚኒስትር እንደሚኖራትበግልጽ ቢቀመጥም ከህገመንግስቱ ውጪ ሌሎች ሹመቶችን ተቀብሎ ማጽደቁ
ህገመንግስቱን መጣስ ነው ሲሉ ተችተዋል፡፡
ገዢው ፓርቲና መንግስት ለተፈጠረው ኢ-ህገመንግስታዊ ድርጊት “የተሾሙት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሮች ሳይሆኑ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርነት ማዕረግ የሚሰሩ ኃላፊዎች ናቸው” በማለት የሰጠው ማስተባበያ የቃላት ጨዋታ ከመሆን አያልፍም ያለው የፓርቲዎቹ መግለጫ” ተሿሚዎቹ የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርነት ማዕረግ ሳይሰጣቸው በሚኒስትርነት ማዕረግ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የየዘርፎቹ
አማካሪዎች መሆን ይችሉ እንደነበር ገልጿል፡፡ ፓርቲዎቹ ህገመንግስቱን አክብረው የማስከበር ኃላፊነት አለባቸው ያሏቸውን አስፈፃሚ አካሉና ፓርላማው የተፈጠረውን ህገመንግስታዊ አካሄድ
በአስቸኳይ እንዲያርሙ ጠይቀዋል፡፡
የኢትዮጵያ ራዕይ ፓርቲ በበኩሉ፤ የኢህአዴግ ስርዓት ይስተካከል እንጂ ሹመቱ ከህገመንግስት ውጭ ቢሆንም ለአገር እስከጠቀመ ድረስ እንደማይቃወም ገልጿል፡፡የፓርቲው ፕሬዚዳንት አቶ ተሻለ ሰብሮ
ሰሞኑን በሰጡት መግለጫ “ኢህአዴግ የፈለገውን ሲያደርግና ሲሠራ የቆየ ቢሆንም መልካም ጐኖችን እንዳሉት መካድ የለብንም” በማለት ኢህአዴግ በተሻለ  መንገድና በአብሮነት በመጓዝ ከሠራና ለአገር እድገትና
ለውጥ በአንድነት ከተራመድን ከህገመንግስቱ ውጪ የሚሠሩትን አገራዊ ጥቅሞች በሙሉ ፓርቲያቸው እንደሚደግፍ አስታውቀዋል፡፡addmass radio

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 11 years ago on December 8, 2012
  • By:
  • Last Modified: December 8, 2012 @ 1:30 pm
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar