www.maledatimes.com ‹‹ከእስረኞች ሁሉ ህገ-መንግስታዊ መብቴ ተጥሶ ዘመድ አዝማድ እና ጓደኛ እንዳይጠይቀኝ የተደረኩት እኔ ነኝ›› አንዷለም አራጌ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

‹‹ከእስረኞች ሁሉ ህገ-መንግስታዊ መብቴ ተጥሶ ዘመድ አዝማድ እና ጓደኛ እንዳይጠይቀኝ የተደረኩት እኔ ነኝ›› አንዷለም አራጌ

By   /   January 8, 2013  /   Comments Off on ‹‹ከእስረኞች ሁሉ ህገ-መንግስታዊ መብቴ ተጥሶ ዘመድ አዝማድ እና ጓደኛ እንዳይጠይቀኝ የተደረኩት እኔ ነኝ›› አንዷለም አራጌ

    Print       Email
0 0
Read Time:5 Minute, 45 Second

 

የአንድነት ፓርቲ አመራሮችና አባላት ከአንዷለም አራጌ ጋር ተገናኙ

 

‹‹በፍቅርና በመተሳሰብ የምንኖርባት ኢትዮጵያ ትናፍቀኛለች››

 

‹‹ከእስረኞች ሁሉ ህገ-መንግስታዊ መብቴ ተጥሶ ዘመድ አዝማድ እና ጓደኛ እንዳይጠይቀኝ የተደረኩት እኔ ነኝ››

 

 

                                                            አንዷለም  አራጌ

           የገናን በዓል ምክንያት በማድረግ የአንድነት ፓርቲ ከፍተኛ አመራር የነበረውንና በሽብርተኝነት ሰበብ ለእስር ተዳርጎ የሚገኘውን ወጣቱን ፖለቲከኛ አንዷለም አራጌን ከአንድነት ከፍተኛ አመራሮችና አባላት የተውጣጡ ሰዎች ጠይቀውት መመለሳቸውን የሕዝብ  ግንኙነት መረጃ ይጠቁማል፡፡ በዋናው መጠየቂያ በር አትገቡም ከተባለ በኋላ ወደ ማረሚያ ቤቱ አስተዳዳሪ የቀረቡት ጠያቂዎቹ ስም ዝርዝራቸው ከተመዘገበ በሁዋላ ሊፈቀድላቸው የቻለ ሲሆን ከወጣቱ ፖለቲከኛ አንዷለም አራጌ ጋር የማረሚያ ቤቱ ጠባቂዎች አጠገብ ቢኖሩም ውይይት አካሂደዋል፡፡

 

ከአንድነት ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች መካከል ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ፣ የተከበሩ አቶ ግርማ ሰይፉ፣ አቶ ተመስጌን ዘውዴ፣ አቶ ዘካርያስ የማነብርሃን፣ አቶ ዳንኤል ተፈራ እና አቶ  ሙላት ጣሰው እና ከአስር በላይ የሚሆኑ አባላትም በመገኘት የአንዷለም የጤና ሁኔታና የእስር አያያዝ ምን እንደሚመስል ጠይቀዋል፡፡

 

አቶ አንዷለም በበኩሉ ከራሱ ይልቅ የገዥው ፓርቲ አፈናና ጭቆና እንዲሁም በዚህ ሁኔታ እየታገሉ ያሉ ባልደረቦቹ ጉዳይ እንደሚያሳስበው ገልጦ በእሱ በኩል እንደቀረበበት ክስ በማንም ላይ በክፋት ባለመነሳቱ የህሊና ሰላም እንደሚሰማው ተናግሯል፡፡ አሁንም ግን ኢትዮጵያና ፖለቲከኞቿ ስለፍቅርና መተሳሰብ ሊገባቸው እንዳልቻለና በፍቅር ተሳስቦ መኖር የሚባለውን  እንደሚፈሩት ይሄም ነገር ክፉኛ እንደሚያሳስበው ተናግሯል፡፡

 

በተያያዘም በቃሊቲ ከሚገኙ እስረኞች በተለየ 6 ሰው በሚያድርባት ጠባብ ክፍል የታሰረና እንደማንኛውም እስረኛ ዘመድ አዝማድ ጓደኛ እንዳይጠይቀው የተደረገ ብቸኛ ግለሰብ መሆኑን የማረሚያ ቤቱ ኃላፊ በተገኙበት ፊት ለፊት ተናግሯል፡፡

 

ለእኛ ቀርቶብን ለልጆቻችን እንኳን የተሻለ ማረሚያ ቤት ማስተላለፍ አለብን ያለው አንዷለም እሱ ላይ ብቻ ያነጣጠረው የመብት ገፈፋ ተገቢ እንዳልሆነ  ፊት ለፊት ገልጧል፡፡ በዚህ ሃቅ የተበሳጩት ኃላፊው ‹‹ተነስ ግባ!› የሚል ዘለፋ የአንድነት አመራር አባላት በተገኙበት ፊት በብስጭት ተናግረዋል፡፡

የአንድነት አመራርና አባላትም የተጀመረው ትግል ግቡን እስኪመታና በፍቅርና መተሳሰብ የምንኖርባት ኢትዮጵያ እስከምትፈጠር ከትግሉ ሜዳ እንደማያፈገፍጉ አረጋግጠውለታል፡፡

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 11 years ago on January 8, 2013
  • By:
  • Last Modified: January 8, 2013 @ 10:02 pm
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar