www.maledatimes.com ዛፍ በፍሬው ይታወቃል - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

ዛፍ በፍሬው ይታወቃል

By   /   January 17, 2013  /   Comments Off on ዛፍ በፍሬው ይታወቃል

    Print       Email
0 0
Read Time:10 Minute, 21 Second

ዛፍ በፍሬው ይታወቃል

በዳዊት መላኩ (ጀርመን)

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ያስተላለፈው ውሳኔ ሀገራችንና ህዝባችን ምን ያክል አስከፊ ሁኔታ ውስጥ እንደገቡ ያሳያል፡፡ሲኖዶሱ በመንፈስ ቅዱስ ይመራል ቢባልም አንዴ ዶ/ር ሽፈራው ተክለማሪያም፤ አንዴ አቶ አባይ ጸሀዮ ፤ሲያስፈልግም አቦይ ስብሃት እና  አቶ በረከት  ስምኦን እየተፈራረቁ በቤተክርስቲያኒቱ ላይ የጥፋት በትራቸውን እያሳረፉበት ይገኛሉ፡፡እንግዲህ የመንግስት ሰዎች በዚህ መልኩ እየተፈራረቁ ተጽዕኖቸውን ሲያሳርፉ በውስጡ የተሰገሰጉት የወያኔ ወኪል አባቶች ደግሞ ህዝቡ ተደራጅቶ መብቱን እንዳያስከብር ጊዜ ለማግኘትና ውስጥ ውስጡን ለሰላም የቆሙ በመምሰል በሽምግልና እና በጸሎት አማካይነት ይስተካከላል እያሉ ሲያታልሉ ቢቆዩም ዛሬ የመንግስትን አቋም ለማስፈጽም መቆማቸውን በግልጽ አሳይተዋል፡፡

የመግለጫው ይዘት ስናየው  ለማደናገሪያ ያክል በውስጡ አንዳንድ የመጽሃፍ ቅዱስ ጥቅሶችና የግዕዝ ቃላቶች ከመግባታቸው በስተቀር  ወያኔ   በየሦስት ወሩ እያሳተመ ለአባላቶቹ ከሚያሰራጨው የአብዮታዊ ዲሞክራሲ ውዳሴ መጽሔት  ከሆነችው የአዲስ ራዕይ መጽሔት፤ በበረከት ሰምኦን በኩል ከሚለቀቀው የመንግስትን አቋም የሚተነትን ተብሎ በመሰለ ገብረህይወት እየተነበበ በኢትዮጵያ ቴሌቭዥን  ከሚቀርበው ፕሮፖጋንዳ የተለየ አደለም፡፡ከዚህ መገመት የሚቻለው መንግስት አስቀድሞ ተዘጋጅቶበት መግለጫው በሲኖዶስ እንዲነበብ መደረጉን ነው፡፡ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሪወስ በ1984 ዓ.ም በአቶ ታምራት ላይኔ ፊርማ በተጻፈ ደብዳቤ መባረራቸው ያደባባይ ሚስጢር ሁኖ ሳለ ዛሬም በተለመደው ቅጥፈታቸው በገንዛ ፈቃዳቸው ጥለው ሸሽተዋል፣ስልጣኑን ለፈለጋችሁት ስጡት ብለዋል ተብሎ የተጻፈን ጽሁፍ የሲኖዶስ ውሳኔ ነው ብሎ ማውጣት ምን ያክል አሳፋሪ ተግባር ነው፡፡ጳጳሱ ወታደር ያላቸው ይመስል የቅድስተ- ማሪያምን ቤተክርስቲይን በታንክና በመትረጌስ አስከብበው የተወሰኑ ካድሬ የቤተክርስቲያን አገልጋይ  ተብየዎች የተቃውሞ ሰልፍ እንዲያዘጋጁ  ተደርጎ በተቀነባበረ ሴራ እንደተባረሩ እየታወቀ በገዛ ፈቃዳቸው ለቀቁ ሲባል  በተለይ አለም በቃን ካሉ መነኮሳት መስማት  ምን ያክል አሳፋሪ ተግባር ነው፡፡

ማቴ.7፤16-20 ” ጥሩ ዛፍ መጥፎ ፍሬ አያፈራም፡፡እንዲሁም መጥፎ ዛፍ ጥሩ ፍሬ አያፈራም፡፡ዛፍ ሁሉ በፍሬው ያታወቃል፡፡” ባለፉት 38 ዓመታት ወያኔ ያፈራቸው  የክህደት ፍሬዎች እንዳይናቸው ብሌን እንዲንከባከቡ ከእግዚያብሄር የተረከቡዋቸውን የመንፈስ ልጆቻቸውን በመበተን ይህን አሳፋሪ ተግባር አሜን ብለው ተቀብለዋል፡፡ዛሬም ቢመሽም ቅሉ ፈጽሞ አልጨለመምና በተለያዩ ዛቻና ማስፈራሪያ ምክንያት ያላመናችሁበትን የፈጸማችሁ አባቶች የእግዚያብሔርን ቃል አስታውሱ፡፡ከቤተ-ክርስቲያንና ከምእምናን ጎን በመሰለፍ የእስልምና እምነት ተከታይ የሀይማኖት መሪዎች እንዳደረጉት እንንተም ለእምነታችሁ መከበርና ለቤተክርሰቲያናችሁ አንድነት ነገቢውን ዋግ ክፈሉ፡፡

ማቴ.10፤26-28  “ እንግዲህ ሰዎችን አትፍሩ፤ምክንያቱም የተሸፈን መገለጡ አይቀርም፤ተሰወረም መታወቁ አይቀርም፤በሹክሹክታ የሰማችሁትንም በከፍታ ቦታ ላይ በይፋ  አስተምሩ፡፡ለእናንተ  ለወዳጆቼ እንዲህ እላችኋለሁ፤ስጋን ከመግደል አልፈው ነፍስን መግደል የማይችሉትን ሰዎች አትፍሩ፤ ይልቁን ነፍስን እና ስጋን በገሀነም ሊያጠፋ ሚችለውን  እግዚያብሄርን ፍሩ፡፡” ይላል የእግዚያብሄር ቃል፡፡

ሉቃ.13፤6-7 “አንድ ሰው በአትክልቱ ውስጥ የተተከለች አንዲት የበለስ ዛፍ ነበረችው፡፡ከዚያችም የበለስ ዛፍ  ፍሬ አገኛለፉ ብሎ በተለያዩ ጊዜያት እየሄደ ቢሞክርም ምንም ፍሬ ሳያገኝ ቀረ፡፡ስለዚህ አትክልተኛውን ጠርቶ ከዚች ዛፍ ፍሬ ለማግኘት ሦስት አመት ሙሉ ተመላለስኩ፤ ግን ምንም ፍሬ አላገኘሁባትም፤አሁን ቁረጣት ስለምን የአትክልቱን ቦታ በከንቱ ይዛ ታበላሻለች አለው”፡፡ እንግዲህ ከዚህ ምሳሌ መረዳት ሚቻለው ባለፉት 21 አመታት ፍሬ ያልሰጡትን አቡነ ጳውሎስን እና አቶ መለስ ዜናዊን የአትክልቱ ቦታ ባለቤት በቁጣ ቢነቅላቸውም ከትፋጣቸው መማር የማይችሉት ደቀ- መዛሙርቶቻቸው እነ አቶ አባይ ጸሀዬ እና አቦይ ስብሀት አንዲሁም ሌሎች  የወያኔ  ቡችሎች በጥፋታቸው ቀጥለውበታል፡፡ይባስ ብሎ በእነሱ ግፍና መከራ በስደት ኑሮዋቸውን መግፋት ሳያናሳቸው ሽብርተኛ በመሆናቸው አቡነ መርቆሪወስ ለፍርድ ሊቀርቡ ይገባል ሲሉ “አቫይ ጸሀዬ” ነግረውናል፡፡ወያኔዎች መልካም ፍሬ ለማፈራት የማይችሉ ተሰጣቸውን ሀገርን የማስተዳደር ትልቅ ሀላፊነት በተጠናወታቸው የዘር ልክፍት ምክንያት ህዝቡን ለብጥብጥ፣ ለሞት፣ለችግር እና ለስደት ከመዳረግ በቀር ሌላ ነገር የለም፡፡ውድ ኢትዮጵያውያን የእግዚያብሄርም ቃል የሚነግረን ፍሬ የማያፈሩትን ዛፎች ቆርጦ መጣል እንደሚገባ ነው፡፡የሌሌች ሀገሮችም ተሞክሮ የሚያሳየን ያለ ሀይል አልለቅም ብሎ በግድ የተጣበቀብንን ካናሰር በኃይል ቆርጦ መጣልና ነጻነታችንን ማስመለስ ነው፡፡

 

About Post Author

Abby

Internet reporter, freelancer and webmaster.
Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 11 years ago on January 17, 2013
  • By:
  • Last Modified: January 17, 2013 @ 8:45 pm
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

About the author

Internet reporter, freelancer and webmaster.

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar