www.maledatimes.com ሕወሓት እንደፓርቲ-ግብጽ እንደአገር-የሙስሊሞች ጥያቄ /ክፍል አንድ/ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

ሕወሓት እንደፓርቲ-ግብጽ እንደአገር-የሙስሊሞች ጥያቄ /ክፍል አንድ/

By   /   March 12, 2013  /   Comments Off on ሕወሓት እንደፓርቲ-ግብጽ እንደአገር-የሙስሊሞች ጥያቄ /ክፍል አንድ/

    Print       Email
0 0
Read Time:11 Minute, 1 Second

ይህ የምታዩት ምስል በወያኔ ደጋፊ ድህረገጽ TIGRAY ONLINE የተለቀቀ ነው ሰፋ ያሉ ሃገራዊ ጉዳዮችንአያየን ምስጢሮችን እየገለጥን የህወሓት አና የጠላቶቻችንን ሴራ አንዳስስበታለን :: ምንሊክ ሳልሳዊ ሕወሓት እንደ ፓርቲ-ግብጽ እንደአገር:- ሕዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ መሰረቱን በማርኪሲስታዊ ፍልስፍና ላይ አድርጎ በዘረኝነት ታጥሮ የተመሰረተ እና ትግራይን ነጻ ለማውጣት የታገለ ድርጅት መሆኑ እደተጠበቀ ሆኖ የያዘው መርዘኛ አላማን ለማሳካት በወቕቱ ሻእቢያ ሲፈበርከው እየተነሳ እንዲሽመደመድ ቢሆንም ይህ አፈበራረክ እንደገና ሞደሬት እንዲሆን በተደረገው መሰረት የቀድሞ የኢሕኣፓ አባላትን አቅፎ ራሱን ሃገር በቅል ማድረጉ ለዚህ የስልጣን ድል አብቅቶታል:: በሱዳን ከሰላ አከባቢ የተለያዩ ጥናቶች በተደረጉበት የትግሉ አመታቶች እንደሚጠቁሙት ወያኔ በኣረብ አገራት ዙሪያ እና በሃይማኖት ዙሪያ ያለውን አቋም ፈትሾበት ነበር::ድሎት እና ምቾት ይዞዋቸው ካረሱት በስተቀር ሲደርግ የነበረው እና ሲሯሯጡበት የነበረው ጉዳይ አሁን ላለው ችግር መሰረት ከመጣሉም አልፎ የመብት እና የነጻነት ጥያቄ እንዲነሳ ሆኗል:: በወቅቱ የጦርመሳሪያ እና የገንዘብ የቁሳቁስ ድጋፍ ለማግኘት ሱዳን እና ግብጥን መርገጫ ተደርጎ ከተለያዩ የአረብ መንግስታት ጋር የነበሩ ግንኙነቶችንን እና ቃለመሃላዎችን ዛሬ ላይ ተቀምጦ ትላንትን መፈተሽ ዋና የወያኔ ስራ መሆን አለበት::ባለፉት ጥቂት አመታት ስንናገር የነበረውን ይህንን ነው:; ወያኔ እንደፓርቲ እንጂ እንደሃገር ሆኖ መናገር እንደማይችል በተቀመጥንበት የካይሮ አደራሾች ተነጋግረናል:: እንግዲህ የወያኔ የደህንነት አባላት እና የግብጥ የደህንነት አባላት እንሱ ሃገራቸውን ወክለው ሲናገሩ ሕወሓት ግን እንደፓርቲ ሃገርን ወክሎ መናገር እንዴት እንደሚችል ተጠይቆ የሰጠው መልስ ኢትዮጵያ ውስጥ የፖለቲካ ዲፕሎማሲ ብስለት ያላቸው ሰዎች የሉም እኛ ከትግል እና ሃገር ከማስተዳደር ያገኘነው ልምድ ወክለን ለመናገር ሙሉ የሞራል ብቃት አለን ነው የሉት :: ይህ የሚያሳየው እንግዲህ የሃገርን ጥቅም በጥቂት ወገኖች ለመሸጥ እየተስማማ መሆኑን ነው:: በአሁኑ ሰአት የተቋረጠው እና በተከታታይ እስካለፈው አመት አጋማሽ ድረስ ሲደረጉ የነበሩት ስብሰባዎች እንደሚያሳዩት ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያውያን ተከራካሪ ያጡበት እደምታ እናስታውላለን :: የሃገር ልማት እና የሃይማኖት ጉዳዮችን በተመለከተ የወያኔ ሰዎች እየወሰዱ ያለው አቋም አስደንጋጭ መሆኑን ልናሰምርበት ይገባል:; ወያኔ በበረሃው ወቅት ለግብጾች የገባችውን ቃል ማጠፏ እና ዳግም ደሞ እየተናገረች ያለችውን ተስፋ ግብጾች በአንክሮ መከታተላቸው አጣብቂኝ ውስጥ እንድትገባ አድርጓታል:: በቅርብ ግዜ በዲፕሎማሲ ስም ሃገራችንን ጎበኙ የተባሉት እና በኢትዮጵያ የግብጥ እምባሲ ይመደባሉ የተባሉት እነዚህ ወጣቶች በዲፕሎማሲ ስም ስለላ የሚያደርጉ ናቸው ስልተናቸውም የህ ነው ብለን ሃገር ቤት ሳይገቡ በፊት ለወያኔ ጁናታ አሳውቀን ነበር የሚሰማን ስናጣ በማህበራዊ ድህረ ገጾች ጮህን:: ይህን እንዳደረግን የተናገርነው ከምላሳችን ሳያልቅ ሰላዮቹ በዲፕሎማቲ ጉብኝት ስም አገር ቤት መግባታቸውን በይፋ ሰማን:ይባስ ተብሎ የወያኔ የበረሃ ቃል ኪዳን የማያውቁት ባለስልጣን እንኳን ወደ 2ኛ ቤታችሁ መጣቹህ ሲሉ እንሱ ያበጠ ይፈንዳ ብለው ነው መሰል ወያኔያዊ ተስፋቸውን …ወደቤታችን ነው የመጣነው…ሲሉ አፈነዱት ልብ ያለው የዲፕሎማሲ ሽሙጡን ያስበው:; ግብጥ እንደሃገር ሃገራዊ ጥቅምዋን በምታስከብርበት በዚህ ወቅት ባልተጠና እና ባልተከለሰ የኋላቀር የፖለቲካ ጉዞ ላይ ያለው ሕወሓት ግብጥን ከኢትዮጵያ ሙስሊሞች ጀርባ እንዳለች አድርጎ በትግሪኛ በሚሰብካቸው ድህረገጾቹ ላይ እያንበለበለ ነው::በአሁኑ ሰአት በመሞት አጣብቂኝ ገደል አፋፍ ላይ ያለው ሕወሃት የፖለቲካው ነገር የተዘበራረቀበት ሲሆን የአባይ ግድብ እንዲገነባ የደረገበት ቦታ ከሱዳን ድንበር 12 ኪሎሜትር ላይ መሆኑ ደሞ ዳግም ጥያቄ ፈጥሮበታል:; በርግጥ ከግድቡ ግንባታ ፕሮጀክቶች 65% ያህን በገንዘብ እጥረት ቆመው ባሉበት ባሁኑ ወቅት እንዲሁም ከግብጥ እና ከአበዳሪዎቹ ጋር በጋራ በምስጢር ስምምነት ለአባይ ግድብ የሚሰጡ እርዳታዎች እና ብድሮች እንዲቆሙ ያደረገው የወያኔ ጁንታ የግድቡ በጠላቶች በተፈለገው ሰኣት እንዲመታ አስፈላጊው መረጃ እንዲሰለል ሲል በድንበሩ ቅርብ እርቀት ላይ ማስቀመጡ ከስልጡኑ የወያኔ አባላት ጥያቄዎች እያስነሱ ነው:: እንዲሁም የወያኔ የቀድሞ ታጋዮች በበረሃ ትግል ወቅት ቤታቸው በነበረችው ሱዳን ያከማቹት ሃብት እና ንብረት እንዳይወረስባቸው ስለሚፈሩ ሱዳንን ለነገሮች ሁሉ አስፈላጊ አድርገው ይመለከቷታል የሱዳንም ዝምታ የወያኔን የተስፋ ቃላቶች ስለምታውቅ ነው:: ግብጥ የሃገርዋን ጥቅም ለማስከበር የማትቆፍረው ጓድጓድ እንደማይኖር ወያኔ ሳይረዳው ቀርቶት ሳይሆን እንደአዲስ ለመንግስት ጋር ለመደራደር ያቀረበው ጥያቄ ተቀባይነት ቢያገኝም የኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ጥያቀ ደግሞ ጥያቄቸው አድርገው የተነሱ ግብጣውያን ለመንግስታቸው አቤቱታ አሰምተዋል:;በምንሰጣቸው መረጃ መሰረት ለመንግስታቸው ጥቆማውን ያደረሱት እነዚህ ወዳጆቻችን የሆኑ የግብጽ መንግስት አባላት በኢትዮጵያውያን ወንድሞቻችን ላይ ያለው የመብት አፈና እንዲቆም አስፈላጊውን እንቅስቃሴ እያደረጉ ነው:; ይቀጥላል::

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 12 years ago on March 12, 2013
  • By:
  • Last Modified: March 12, 2013 @ 7:48 pm
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar