www.maledatimes.com ኮሚተዎቻችን ይፈቱ!!ሲሉ የስዊዲን ኢትዮጵያዊ ዲያስፖራዎች ጠየቁ:: - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

ኮሚተዎቻችን ይፈቱ!!ሲሉ የስዊዲን ኢትዮጵያዊ ዲያስፖራዎች ጠየቁ::

By   /   March 19, 2013  /   Comments Off on ኮሚተዎቻችን ይፈቱ!!ሲሉ የስዊዲን ኢትዮጵያዊ ዲያስፖራዎች ጠየቁ::

    Print       Email
0 0
Read Time:2 Minute, 18 Second
በስቶኮልም ሲዊድን የኢትዮጵያ ኤምባሲ ፊት ለፊት ደማቅ የተቃውሞ ሰልፍ መካሄዱን የሰልፍ አስተባባሪዎች ለፍኖተ ነፃነት ገለፁ፡፡

ባለፈው ቅዳሜ መጋቢት 7 ቀን 2005 ዓ.ም የተደረገው የተዋውሞ ሰልፍ አላማ በኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ላይ መንግስት እያደረሰ ያለውን በደል ለመቃወም መሆኑን የገለፁት የሰልፉ አስተባባሪዎች በተቃውሞ ሰልፉ ላይ ከ 200 በላይ በስቶኮልምና በአካባቢው የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን መገኘታቸውንም አረጋግጠዋል፡፡

ሰልፉን ያስተባበሩት በስዊዲን የሚገኙ ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ከሌሎች ሀገር ወዳድ ዜጎች ጋር በመተባበር ሲሆን ሰልፉን የክርስትና እምነት ተከታዮችም በርከት ብለው በመታደም አጋርነታቸውን ገልፀውበታል፡፡

በስቶኮልም የኢትዮጵያ ኤምባሲ ፊት ለፊት በተደረገው በዚሁ ሰላማዊ ሰልፍ ላይ “ድምጻችን ይሰማ በስቶኮልም ከተማ”፣ “ሀገር በህግ እንጂ በሀሰት ፊልም አይመራም”፣ “ኢትዮጵያ የሁላችንም ሀገር ናት”፣ “ኮሚቴዎቻችን ህጋዊ ናቸው፤ እነሱን አሸባሪ ማለት ሁሉንም የኢትዮጵያ ሙስሊም አሸባሪ ማለት ነው” የሚሉና የተለያዩ መፈክሮችም ተስተጋብተዋል፡፡

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 11 years ago on March 19, 2013
  • By:
  • Last Modified: March 19, 2013 @ 9:26 am
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar