www.maledatimes.com በኦሮሚያ ክልል ሁለት ተጨማሪ የቱሪስት መዳረሻዎች ተከፈቱ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

በኦሮሚያ ክልል ሁለት ተጨማሪ የቱሪስት መዳረሻዎች ተከፈቱ

By   /   March 27, 2013  /   Comments Off on በኦሮሚያ ክልል ሁለት ተጨማሪ የቱሪስት መዳረሻዎች ተከፈቱ

    Print       Email
0 0
Read Time:3 Minute, 31 Second

በመስከረም አያሌው

በኦሮሚያ ክልል ዝዋይ ማህበረሰብ ተኮር የቱሪዝም ስፍራዎች ተከፈቱ። የአሜሪካ ኤምባሲ በላከው ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳስታወቀው፣ ዝዋይ እና ለፌስ የተባሉት አዲሶቹ የቱሪዝም ስፍራዎች የተገነቡት ከአሜሪካ ፕሬዝዳንት አስቸኳይ የኤድስ እርዳታ እቅድ በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ ሲሆን፣ ስፍራዎቹም በአይነታቸው የመጀመሪያ እና የስድስት ማህበረሰብ የአካባቢ ጥበቃ መረብ አካል ናቸው። እነዚህ ሁለት ስፍራዎች ባህላዊ ጎጆ ቤቶችን፣ የለፊስ ፏፏቴን፣ የወፍ እይታን፣ የቱሉ ጊዶ ደሴት እና በአካባቢው ባለሞያዎች የተዘጋጀ የእደ ጥበብ ውጤቶች እይታን እንዲሁም ከአካባቢው የሚጠመድ ትኩስ የተጠበሰ አሳ መስተንግዶን ያካትታል።

ተመርቀው ስራ የጀመሩት ስፍራዎች 40ሺ ያህል የአካባቢው ማህበረሰብን ይጠቅማሉ ተብሎ የታሰበ ሲሆን፤ የኢኮ ቱሪዝም እድሎችን መፈጠር ይችላሉ ተብሏል። የዩ ኤስ ኤ አይ ዲ ኢትዮጵያ የግብርና ሃላፊ ኩለን ሁነስ በምርቃት ስነ ስርዓቱ ላይ እንደገለፁትም እነዚህ ሁለት ስፍራዎች ተመርቀው ስራ መጀመር መቻላቸው ሁሉን አቀፍ የልማት አቀራረብ ለቱሪዝም እድገት ምቹ ሁኔታን እንዲፈጥር እና ለጎብኚዎችም ስለ ኢትዮጵያ እውነተኛ ገፅታ የማየት አጋጣሚን ይፈጥራል።

በካውንተርፓርቲ ኢንተርናሽናል አማካይነት የሚተገበረው ይህ የኢትዮጵያ ቀጣይነት ያለው የቱሪዝም ጥምረት ፕሮጀክት የአምስት አመት ፕሮጀክት ሲሆን ሰባት ሚሊዮን ዶላር የተመደበለት መሆኑም ተገልጿል። ለፕሮግራሙ ድጋፍ እስከ አሁን ድረስም ቀጣይነት ያለው የገቢ ምንጭ ማግኛና ብዝሃ ህይወት ጥበቃን ለመደገፍ በኢትዮጵያ በመካከለኛው እና ደቡብ ስምጥ ሸለቆዎች 34 ማህበራት ተመስረተዋል።

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 11 years ago on March 27, 2013
  • By:
  • Last Modified: March 27, 2013 @ 1:43 am
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar