www.maledatimes.com ታሪኬን አጠፉብኝ {ለአቡነ ጴጥሮስ } - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

ታሪኬን አጠፉብኝ {ለአቡነ ጴጥሮስ }

By   /   May 2, 2013  /   Comments Off on ታሪኬን አጠፉብኝ {ለአቡነ ጴጥሮስ }

    Print       Email
0 0
Read Time:2 Minute, 53 Second

ጦማር እንዳልጦምር ታሪክም የለኝም
ማንነቴን ሳላውቅ አንተ ማነህ ቢሎኝ
ቢጠይቀኝ ሰው ማንነት የለኝም
የታሪኬ ምንጩ በእንጭጩ ደርቆብኝ
ዛሬ ከትላንቱ ማየቱ ተስኖኝ
የነበረኝ ታሪክ ፈርሶ ፈራርሶብኝ
ብሎም ተቆራርሶ ሁሉም ተነካክሶ
ዘር ከዘር ተባልቶ በሃይማኖቱ ሞቶ
ማንነቱ ጠፍቶ ውሎ ተቋጥሮብኝ
መፍታቱ አቅቶኝ
እንደ እንዝርት አለላ መንገዱ ቀጥኖብኝ
መፍትሄ ስፈልግ የታሪኬን መስመር
ሳላገኘው ዋልኩ ዘመናት ቆጠርኩኝ
ታሪኬም ጠፋብኝ
ስውር ብሎ ጠፍቶ
ማንነቱን ክዶ
እራሱን እረስቶ
ታሪክን ታሪክ ቶቶ
በዘመናት ጊዜ ላልይመለስ ሽሮ
እራሱን አውድሞ
ነበረ የቆየኝ
የቀረው ታሪኬን እጠብቀዋለሁ ስል
ይሄው ሳይታሰብ ውሉን አጠፉብኝ
ዛሬም ደገሙብኝ
ታዲያ` ዘመኑ እውነት ፍርድ ላይፈርድ
ወይ ወያኔ ተብሎ ልክ እንዳልተወደሰ
ያ` ዘመን በሚያስብል ዘመን ላይ ደረሰ
ባውላላ አውድማ ታሪኩም ፈረሰ
የታሪክ አሻራ ዉሉን አጠፉብኝ
የጦር ጋሻ ጀግና ሞተው ካረፉበት
ደግመው ደጋግመው ይሄው ቀበሩብኝ
የታሪኬን ምንጩን ስሩን ነቃቀሉት
የኛነታችን ስር የፍሬአችን ግንድ
የጥንት ብቅለታችን
የጥቁር ዘር ታሪክ የጥቁር ሰው ትውልድ
የማንነቴን ምንጭ ይሄው አጠፉብኝ
ካባይ ከውልደቱ
ከሰሃራ ግለቱ ከታሪክ ሃውልቱ

ይሄው አጠፉብኝ ስሩን ነቀሉብኝ
ጸሃይቱም ጠልቃ ብርሃኗም ሞቶ
ዳው በላብኝ እኔን እኔነቴም ጠፍቶ
መታሰቢያነቱ ለአቡነ ጴጥሮስ ትሁንልኝ ዘላለም ገብሬ  923102_10200568936140160_941735044_n923102_10200568936140160_941735044_n
Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar