www.maledatimes.com ጉዞዓችን ወደተግባር ወይንስ ወሬ እስከመቼ ? - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

ጉዞዓችን ወደተግባር ወይንስ ወሬ እስከመቼ ?

By   /   May 3, 2013  /   Comments Off on ጉዞዓችን ወደተግባር ወይንስ ወሬ እስከመቼ ?

    Print       Email
0 0
Read Time:10 Minute, 19 Second

በኢሳ አብድሰመድ / by Issa Abdusemed

ህወሃት/ኢህአዴግ ጠባብና ዘረኛ የፖለቲካ አላማዉን ከግብ ለማድረስ ላለፉት 21 አመታት በመንግስት ስልጣን ላይ ተቀምጦ በፈፀማቸዉና ዛሬም በሚፈፅማቸዉ መንግስታዊ የሽብር ተግባሮች ምክንያት የአገሪቱ፤……

አንድነትና ሉኣላዊነት እንደተንኮታኮተ፤ ሀብትና፤ ታሪካዊ ቅርሶቿ  እያወደመና አላግባብ እየተዘረፍን፤ ዜጎቿ እስራት፤ እንግልት፤ ድብደባ፤ ሰቆቃና ግድያ እንደደረሰባቸዉ አለም አቀፍ የመረጃ ምንጮች በየጊዜዉ ይፋ ያደረጉት ሃቅ ነዉ።

በሃሰት ክስ ወንጀለኛ ለማድረግ የሚፈፀመዉ የተሳሳተ ተግባር የዜጎች በጋራ አብሮ የመኖርና፡ የመከባበር መሰረት በሆነዉ ፍትህና ዳኝነት ላይ ይቅር የማይባል ከፍተኛ ወንጀል እየፈፀመ መሆኑ በእጅጉ ያሳዝናል።

ዛሬ በሀሰት የወንጀል ክስ የተሰየሙት ዳኞችና አቃቢያነ ህጎች ብይን፤ የፈፀሙትን ተግባር በየ አጋጣሚዉ እያነሳ የራሳቸዉ ህሊና ዳኝነት እየሰጠ ሰላም እንደሚነሳቸዉ ግልፅ ነዉ።

ከህሊና ነፃነት ይልቅ ባርነትን፤ ከሞራል ፅናት ይልቅ ዉድቀትን የመረጡ የህግ ባለሙያዎች ለፍትህ ስርዓታችን ዘብ መቆም አልቻሉም። በሰብአዊ መብቶች መከበርና ጥበቃ ዙሪያ የሚሰሩ እንደ ሂዩማን ራይትስ ዎች፣

አመነስቲ ኢንተርናሽናልና በሌሎች ተመሳሳይ ተቋማት የሚወጡ ሪፖርቶች እንደሚያሳዩት ሀገራችን ያለው የሰብአዊ መብት አያያዝ እስከፊ ሁኔታ ላይ እንዳሉ የሚያሳዩ ናቸው፡፡

የመናገር፣ የመሰብሰብ፣ የመፃፍና  መብቶች የተጠበቁ ናቸው የሚለውን የአገሪቱን ሕገ መንግሥት በሚቃረን መልኩ መንግሥት የተቃዋሚ ኃይሎችን፣ ጋዜጠኞችንና የመንግስትን አቋም እንዲሁም  በኃይማኖታችን መንግስት ጣልቃ አይግባ የሚሉትን የሀይማኖት መሪዎች  አብዝተው የሚተቹና የሚጽፉ ሰዎችን ባሻው ጊዜ ያስፈራራል፣ ያስራል፡ይገድላል ቶርቸር ያደርጋል ይሁንና ብዙሀኑ የሙስሊም ማህበረሰብ አባላት፤ የማይወክላቸውን ‘መጂሊስ’እና የማይቀበሉትን  አህባሽየተባለ አስተምህሮ ፤

ከእምነትና ፍላጎታቸው ውጪ እየጫነባቸው ያለው ራሱ መንግስት እንደሆነ፤ ከኣመት በላይ በዘለቀው የተቃውሞ ሰልፋቸው በመግለጽ ላይ ይገኛሉ።

ሁሌም ግን እኔን የሚያስጨንቀኝ አንድ ነገር አለ  ሁሌም የምናየዉ በ መቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሙስሊም ወንድሞቻችን ሰላማዊ ትግል ያደርጋሉ

መንግስት ጥቂቶች ናቸዉ በማለት ሰላማዊ ትግላቸውን በአሸባሪነት ፈርጆአቸዋል  ታድያ ልማታዊዉ አህባሽ ብዙሀኑ ለምንድነዉ አንድም ቀን  እንደ ጥቂቶቹ ኢትዮዽያዊዉ ኢስላም ወቶ የማይታየዉ ? 

መንግስት በአሁኑ ወቅት በሀገራችን ውስጥ በእስልምና ኃይማኖት ሽፋን ተጨባጭነት የሌለው የሀሰት ፕሮፓጋንዳ በማሰራጨት ሁከትና ብጥብጥን ለማስፈን የሚጥሩ ኃይሎችን ህዝበ ሙስሊሙ  ህብረተሰብ ነቅቶ በመጠበቅ ኃይማኖታዊ ተልእኮውን መወጣት አለበት በማለት  ፕሮፓአጋንዳዉን ይነፋል >.> 

በአንዋር መስጊድ እና በሌሎችም አካባቢዎች ‹‹ድምጻችን ይሰማ›› እያለ መፈክር የሚያሰማን ሰላማዊ ህዝብ እና የሶማሊያ ታጣቂዎችን የአንድ ሳንቲም ሁለት ገፅታ ናቸው ብሎ ማቅረቡም መንግስት ለህዝበ ሙስሊሙ ያለውን ንቀት ትንሽም ለመደበቅ አለመፈለጉን በግልጽ አሳይቶናል

እኔ እንደሚገባኝ ከሆነ የህዝበ ሙስሊሙም ሆነ የንፁሀኑ ኢትዮጵያን ጠላት ዘረኛዉ እና ነብሰበላዉ ወያኔ መሆኑ ነዉ

ሙስሊሙ ህብረሰብ በአሁኑ ሰዓት ከመቼውም ጊዜ በከፋ ሁኔታ ትልቅ መስቀለኛ መንገድ ላይ መንግስትን አስገብቶት  ይገኛል፡

መንግስት ኢትዮዽያዊዉ ሙስሊም ከቢጫዉ ካርድ በዉሀላ ምን ሊያሳየዉ እንደሚችል አጭር እና ግልፅ ነዉ

በሽብርተኝነት ተጠርጥረው  ከታሰሩና ክሳቸውን በማረሚያ ቤት ሆነው ከሚከታተሉት ስምንት ተከሳሾች አንዱ የሆነው ለሀገር ፍቅር የሚሞት ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ እንኴአን በኢትዮጵያም ሰላማዊና ዲሞክራሲያዊ ሒደት  እንዲካሄድ ፍላጐቱ እንደነበር የተናገረው እስክንድር፣ በስብሰባዎቹ ይዘት ዓላማና ግብ ላይ አጥልቶ የነበረው ድባብ ቀጥተኛ አንድምታና ተፅዕኖ እንደነበረው የገለጸው ይኼ እምነት የእሱ ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵያ ሕዝብ ሁሉ መሆኑን በመጠቆም፣ የአሸባሪነት ስም ተሰቶት በግርፋትና በድብደባ በማሰቃየት በመጨረሻም የህሊና እስረኛ ለመሆን ያበቃው ይኼው መሆኑን ይታወቃል

  ከመንግሥት ጋር የነበረው  ሰላማዊ ትግል  በርካታ ዓመታትን ቢያስቆጥርም፣ በ2003 ዓ.ም. በግብፅ አገር በተካሄደው የስኬት አብዮት የተደናገጠው የወያኔ ኢሃዲግ  መንግሥት ‹እስክንድር ነጋን ‹ እርምጃ እንወስድብሀለን እንዳሉት ተናግሯል፡

እንዳለዉም የወያኔ መንግስ በእስክንድር ነጋ ላይም ሆነ በሌሎች እህትና ወንድሞቻችን ላይ እየደረሰ ያለው ግፍ እና መከራ ይህ ነው የማይባል ነው ብዙ ብዙ ነገር ተደርገናል የቀረን ነገር ያለ አይመስለኝም

ከአንግዲህ፣የወሬስልቻሁነንመቅረት፣የማንፈልግከሆነ፣ደግሞ፣ዛሬ ነገ ሳንልወደማይቀረው፣

የድርጊት፣እርምጃናዘመንየግድዛሬ፣መራመድ፣፣ይኖርብናልወሬውግንወንድሞቼይበቃናል።

ድል ለኢትዯዽያ ህዝብ

About Post Author

Abby

Internet reporter, freelancer and webmaster.
Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 11 years ago on May 3, 2013
  • By:
  • Last Modified: May 3, 2013 @ 12:34 pm
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

About the author

Internet reporter, freelancer and webmaster.

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar