www.maledatimes.com የፓትርያሪክ አቡነ ጳውሎስ በዓለ ሢመት – በሼራተን አዲስ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

የፓትርያሪክ አቡነ ጳውሎስ በዓለ ሢመት – በሼራተን አዲስ

By   /   July 26, 2012  /   Comments Off on የፓትርያሪክ አቡነ ጳውሎስ በዓለ ሢመት – በሼራተን አዲስ

    Print       Email
0 0
Read Time:8 Minute, 43 Second
(ደጀ ሰላም፤ ሐምሌ 19/2004 ዓ.ም፤ ጁላይ 26/ 2012/ READ THIS NEWS IN PDF)፦ የአቡነ ጳውሎስ ኻያኛ ዓመት በዓለ ሢመት ሐምሌ አምስት ቀን 2004 ዓ.ም በጠቅላይ ቤተ ክህነት የስብከተ ወንጌል አዳራሽ ተከብሯል፡፡ ሐምሌ 16 ቀን 2004 ዓ.ም ምሽት በሼራተን አዲስ ለሁለተኛ ጊዜ የተካሄደውና የመንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣናትን፣ አምባሳደሮችንና ታዋቂ ሰዎችን ጨምሮ ከ500 ያላነሱ ሰዎች የታደሙበት የራት ግብዣ በፓትርያሪኩ ልዩ ጽ/ቤት እና “ራእይ ለትውልድ” በተባለ አካል የተዘጋጀ መኾኑ ተገልጧል፡፡

 ለበዓለ ሢመቱ የኅትመቶች፣ ቲ- ሸርት፣ ፖስተሮች፣ ራት ግብዣ ዝግጅቶች ፓትርያሪኩን ጨምሮ ግለሰቦችከስፖንሰር ሽፕ እና በዚሁ ሰበብ ከአጥቢያ አብያተ ክርስቲያን ከሚሰበሰበው ገንዘብ ሕገ ወጥ ጥቅም እያጋበሱበት መኾኑ የበዓሉን ምንነትና ፋይዳ አደናጋሪ መልክ አስይዞታል፡፡ ከዚህ ጉዳይ ጋራ በተገናኘ አቡነ ጳውሎስ በሕገ ቤተ ክርስቲያን በማይታወቀው የልዩ ጽ/ቤታቸው መዋቅር፣ በእጅጋየሁ በየነ እና እንደ ዶ/ር አግደው ረዴ /ልማትና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን ኮሚሽነር/፣ ቀሲስ ግሩም መልአክ ታዬ /ትንሣኤ ዘጉባኤ ማተሚያ ቤት/፣ ሊቀ ኅሩያን ዳዊት ታደሰ /አዲስ አበባ ሀገረ ስብከት/ እና ተመስገን ዮሐንስ /አ.አ.ዩ/ በመሳሰሉት ግለሰቦች አማካይነት “ራእይ ለትውልድ” /Vision For Generation/ ከተባለው አካል ጋራ ፈጥረውት የቆዩት፣ በዚሁ በዓል አከባበርም ገሃድ የኾነው እውነታ እያነጋገረ ይገኛል፡፡
በዚሁ ዝግጅት ላይ ም/ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኀይለ ማርያም ደሳለኝ እና ዶ/ር ቴዎድሮስ አድኀኖም የራት ምሽቱ የክብር እንግዶች የነበሩ ሲሆን በአቡነ ጳውሎስ ስም የተሰየመ የኤድስ፣ ቲቢ እና ካንሰር ሕሙማን ማገገሚያ ማእከል በ200 ሚሊዮን ብር ወጪ እንደሚገነባና የግንባታ ሥፍራውን የማፈላለግ ሥራ እየተሠራ መኾኑ ተገልጧል። የጤና ጥበቃ ሚኒስትሩ የማእከሉን ግንባታ በበላይነት እንዲቆጣጠሩ አቡነ ጳውሎስ ሾመዋቸዋል። የአቡነ ጳውሎስን ሥራዎች ይዘክራል የተባለ የኻያ አምስት ደቂቃ ሥዕላዊ ፊልምም ታይቷል።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ኀይለ ማርያም ደሳለኝ “ክቡርነታቸው [ቅዱስነታቸው] በሀገራችን የልማት ጉዳይ ከመንግሥት ጋራ እየሠሩ መኾኑን እንገልጻለን፤ . . . የአክራሪነትን አደጋ በተመለከተ መንግሥታችን እዚህ ከተገኙትም ካልተገኙትም የሃይማኖት ተቋማት ጋራ አብሮ ይሠራል” ማለታቸውም ተዘግቧል።
ከወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ኅብረት የመጡት ቄስ ደረጀ ጀንበሩ በበኩላቸው “የሃይማኖት አባቶች ተመካክረው እንዲሠሩ ጥረት አድርገዋል፤ ቤተ ክርስቲያናችን የእርስዎን ታላቅ አባትነት ያከብራል” ሲሉ “እንዳዛሬው ደክመው በሚታዩበት ኹኔታ ሳይሆን ቀድሞ በተለይ ለኢትዮጵያ እና ኤርትራ ሰላም ለማስገኘት አብረን ሠርተናል፤ ቅዱስነታቸው ዘወትር ሲናገሩ አንድን ሃይማኖት ሳይሆን መላው የኢትዮጵያን ሕዝብ በመወከል ነው” ያሉት ደግሞ ሼኽ ኤልያስ ሬድዋን ናቸው።
በተያያዘ ዜና ከኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን በዝግጅቱ ላይ የተወከሉት አባ ብርሃነ ኢየሱስ ሱራፌልም “በኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ባልዎት የሊቀ መንበርነት ሓላፊነት ለሰላም አብረን መሥራታችንን እንቀጥላለን” ብለዋል። የ“ራእይ ለትውልድ” የተሰኘው ተቋም ተወካይም “ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ የኦርቶዶክሳውያን ብቻ ሳይሆን የመላው ኢትዮጵያውያን አባት ናቸው፤ በስማቸው የኤድስ፣ ካንሰር እና ቲቢ ማገገሚያ ማእከል ለመገንባት የዲዛየን ሥራው ተጠናቋል” ካሉ በኋላ በ200 ሚልዮን ብር ማእከሉን እንደሚገነባና ለመሠረት ሥራው ብቻ አምስት መቶ ሺሕ እንደሚያስፈልግ ሲገልጹ ማዕከሉን እንዲመሩ በፓትርያርኩ የተሾሙት ዶ/ር ቴዎድሮስ አድኀኖምም “የተሰጠኝን ሓላፊነት አልቀበልም አልልም፣ እቀበላለኹ፤ ከራእይ ለትውልድ ጋራ አብሬ እሠራለኹ፡፡” ብለዋል።
ማዕከሉን አስመልክቶ አቡነ ጳውሎስ ሲናገሩ “በስማችን የተሰየመው ማእከል ለመገንባት መነሣቱ የሚመሰገን ነው፤ ማእከሉን ሁላችንም እንደምንጠቀምበት ማሰብ አለብን፤ እግዚአብሔር አምላክ ለመልካም ሥራ ሁሉ እንድንተባበር አዞናል፤ በስሜ ለተሰየመው ማእከል ግንባታ የበላይ ተቆጣጣሪ እንዲኾኑ ዶ/ር ቴዎድሮስ ተሾመዋል” ብለዋል።
ቸር ወሬ ያሰማን፣
አሜን
Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar