www.maledatimes.com ፅንስም ከሆነ ይገፋል… - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

ፅንስም ከሆነ ይገፋል…

By   /   July 27, 2012  /   Comments Off on ፅንስም ከሆነ ይገፋል…

    Print       Email
0 0
Read Time:11 Minute, 5 Second

ከይኸነው አንተሁነኝ
የጎጠኛው መለስ ዜናዊን ሰሞንኛ ሁኔታ አስመልክቶ የሚባሉ፣ የሚተረኩና የሚጻፉ የተለያዩ አመለካከቶችንም ሆነ መላምቶችን ጨምሮ የደጋፊና የተቃዋሚ ምኞቶችን ያካተቱ መረጃዎች ይወጣሉ። መረጃዎች አንደኛው ከሌላኛው የመደጋገፋቸውን ያህል በዚያው ልክ ፈጽሞ የተራራቁ፣ የማይዛመዱና ከዚያም ሲያልፍ በፊት የተጻፉትን የሚቃወሙና የሚተቹ ቁጥራቸው ጥቂት ባለመሆኑ፤ የሆነውን ትክክለኛ ነገር ለማወቅ ለሚፈልገው የኢትዮጵያ ህዝብና አንባቢ ግራ አጋቢ ሁኔታን ፈጥሯል። ይህ እንዴት ሊሆን ቻለ ያልን እንደሆነ የወያኔ ድብቅ ተፈጥሮ ያመጣው መሆኑን እንረዳለን። ማንኛውንም ነገር ከህዝብ ደብቆ የራስ የግል ሚስጥር አድርጎ የመያዝ አባዜ። ”ፅንስም ከሆነ ይገፋል..” እንደሚባለው እውነቱን ሳይውል ሳያድር በቅርብ የምናውቀው ይሆናል።
በአቶ መለስ ሰሞንኛ ሁኔታ ላይ ከመንግስትም ሆነ ውስጥ አዋቂ ነን ከሚሉ ወያኔዎች የሚሰጠው መግለጫም ሆነ ማስተባበያ እውነታውን ባይቀይረውም ሁኔታው ግን ከዚህ በፊት በዘረኛው መለስና በወያኔዎች የተደረገ አንድ ታላቅ ታሪክ ያስታውሰኛል። ወቅቱ የኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት መነሻ አካባቢ ነበር። በጊዜው በሻቢያ አማካኝነት በኢትዮጵያ ድንበር አካባቢ ተደጋጋሚ ጠብ አጫሪ ድርጊቶች የሚደረጉበት ወቅት ነበር። ድርጊቱ ያሰጋቸው በትግራይ አካባቢ የሚኖሩ ተቆርቋሪ ግለሰቦች፣ በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚንቀሳቀሱ ጉዳዩ የሚመለከታቸው ተቋማት፣ በግልም ሆነ በስራ ወደ አካባቢው ተጉዘው የነበሩ ግለሰቦች፣ የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎችና አባላት እንዲሁም ታሪክ ጸሐፊዎችና ፖለቲካ ተንታኞች ኤርትራ ኢትዮጵያን ልታጠቃ ትችላለች እና ጥንቃቄ ይደረግ ከሚለው ጀምሮ መንግስት በዚህ ጉዳይ ላይ ምን እያደረገ እንደሆነ ለህዝብ ይፋ ያድርግ እስከሚለው ድረስ ቢጠይቁም መንግስት ግን መዋሸትን ነበር የመረጠው። ኤርትራ ኢትዮጵያን ልታጠቃ ትችላለች ብሎ ማሰብ የጤንነት እንዳልሆነ በመግለጽ ነበር ከጎጠኛው መለስ ጀምሮ ወያኔዎች በየተራ እየወጡ ሲሳለቁብን የነበረው። በድንበር አካባቢ የሚያጋጥሙ ግጭቶችም ቢሆኑ ነፍጠኛ ጦርነት ናፋቂዎች የሚያስወሩት እንጅ በየትኛውም የዓለም ዙሪያ በሚገኙ ሁለት ተጎራባች ሀገሮች ድንበር አካባቢ የሚኖሩ ህዝቦች ከሚያጋጥማቸው ቀላልና የተለመደ ግጭት የተለየ አይደለም እያሉ ነበር የዋሹን። የህዝብን መረጃ የማግኘት መብት በመገደብ ውስጥ ለውስት ሚስጥር አድርገው ሲያሹት ቢቆዩም ”ፅንስም ከሆነ ይገፋል…” ነውና ሁላችንም የምናውቀው አሳዛኙና አሰቃቂው እልቂት ተፈጸመ። ቀድሞም ቢሆን ከህዝብ ያልተመከረበትና በቂ ዝግጅት ያልተደረገበት ነበርና መስዋትነቱም እጅግ ግዙፍ ኪሳራውም ለመገመት የሚያዳግት ሆነ። የጦርነቱ መረጃና ጦርነቱ ባንድ ላይ ነበርና የተከሰቱት ሁኔታውን ለመቀበል ለህዝባችን በጣም አስቸጋሪ ነበር። ዛሬም በተለመደው መረጃን የማፈንና የግል ሚስጥር አድርጎ የመያዝ አባዜያቸው የተነሳ የወያኔውን ቁንጮ መለሰ ዜናዊ እጣ ፈንታ ለመግለጽ ተቸግረዋል።
በእርግጥ ወያኔወች እንደሚሉት ቀለል ያለ በሽታ ከሆነ ምነው ባልጋ ላይ እንዳለም ሆነ ተቀምጦ እንደተለመደው ቃላትን እየረገጠና እየቆጠረ ትናጋው እስኪሰፋ ያው የምናውቀውን ማስፈራሪያውን ፉከራ መፎከሩ ቢቀር እንኳ ተሽሎኛል፤ ከቀናት በሗላ እመጣላችሗለሁ ማለት ባይችል እንኳ እመጣባችሗለሁ ቢለን፤ አሃ በሂዎት አለ እንዴ ለማለት ይረዳን ነበር። ግን ምንም ነገር አላለም፤ እኛ ደግሞ ከዚህ በመነሳት የሉም እያልን ነው። ወያኔዎች መኖራቸውን የሚያረጋግጥ መረጃ ማቅረብ አልቻሉማ።
የሆነው ሆኖ ገንጣዩ መለስ ዜናዊ ሞተም ዳነ ከወዲህም ሆነ ከወዲያ (ከተቃዋሚም ሆነ ደጋፊ ለማለት ነው) የሚወረወሩት መላምቶችም ሆኑ ድጋፍና ተቃውሞዎች እንደጉድ እየተጻፉ ባሉበት ባሁኑ ወቅት ወያኔን ለመጣል እያደረግን ከነበረው እና እያደረግን ካለው ትግል ጎን ለጎን መሰረታዊ ስራዎች መሰራት አለባቸው። ኢትዮጵያዊ ነኝ የምንልና ኢትዮጵያን የምንወድ ዜጋዎች በሙሉ ከዚህ በሗላ ለሀገራችን ዲሞከረሲያዊ ያልሆነ ሰርአት በቃ ልንል ይገባል። የህዝቦች መብት የማይከበርባት፣ የተለያዩ ብሄር ብሄረሰቦች እና ሃይማኖቶች እኩል የማይታዩባት፣ የሃብት ክፍፍልና የቴክኖሎጂ ሽግግር ለሁሉም ዜጋ እኩል የማይዳረስባት፣ በጥቅሉ መልካም አስተዳደርና የህግ የበላይነት የማይከበርባትን ኢትዮጵያ ላለማየት መወሰን ይኖርብናል።
ይህም ብቻ አይደለም፤ ቀጣዩ በሀገራችን የሚገነባው ስርአት ዲሞክራሲያዊ እንዲሆን የዳር ተመልካችነትን በመሰልቸት ከጎጠኞችና እና ከከፋፋዮች በመራቅ እራሳችንን ከአንድነት ሃይሎች ጋር በማቀናጀት ነገ ዛሬ ሳንል ፍሬ ያለው ስራ ለመስራት እንነሳ። ”ፅንስም ከሆነ ይገፋል ቦርጭም ከሆነ ይጠፋል” እንደሚባለው ዛሬ ባይሆን ነገ የከፋፋዩን መለስ ዜናዊን ዜና እረፍትም ሆነ የወያኔን ውድቀት እንሰማለን ታዲያ ያኔ ሱሪ ባንገት እንዳይሆን ዛሬም አልዘገየንምና እራሳችንን ከሃገር አንድነት ሃይሎች ጋር እናሰልፍ። የሚሆነውን በንቃት እንከታተል፤ ወቅታዊና ደረጃውን የጠበቀ ውሳኔ በመስጠት የህዝብ ወገንተኝነታችንን እናስመስክር። ሀገራችንን ኢትዮጵያን የሚያስቀድም፣ ጥቅሟን የሚያስጠብቅና አንድነቷን የሚያስከብር አቅምን ያገናዘበ ማንኛውንም አይነት እገዛ ለምናምንባቸው የአንድነት ሃይሎች በመስጠት ከታሪክ ተጠያቂነትና ከህሊና ወቀሳ እንዳን እላለሁ።

About Post Author

Abby

Internet reporter, freelancer and webmaster.
Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email

About the author

Internet reporter, freelancer and webmaster.

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar