www.maledatimes.com ገዳዩ ሞቶ ተገኘ (ማንነቱ እያነጋገረ ነው!) - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

ገዳዩ ሞቶ ተገኘ (ማንነቱ እያነጋገረ ነው!)

By   /   May 14, 2013  /   Comments Off on ገዳዩ ሞቶ ተገኘ (ማንነቱ እያነጋገረ ነው!)

    Print       Email
0 0
Read Time:4 Minute, 3 Second

(ኢ.ኤም.ኤፍ) ከትላንት በስትያ፤ ምሽት ላይ ከ12 ሰዎች በላይ የገደለው የፌዴራል ፖሊስ አባል አባይ ወንዝ ውስጥ ሞቶ ተገኝቷል። የፖሊሱ ማንነት በውል ባይታወቅም በባህር ዳር ከተማ በሰፊው እየተነገረ ያለው፤ ግለሰቡ የህወሃት አባል እንደሆነና ድርጊቱን የፈጸመው፤ ሆን ብሎ በአማራ ህዝብ ላይ ያለውን ጥላቻ ለመግለጽ ነው፤ የሚለው ወሬ በሰፊው እየተናፈሰ ይገኛል። ከዚሁ ጋር ተያይዞ በፌዴራል ፖሊስ ሰበብ በከተማው በሚገኙት የሌላ ብሄር ተወላጆች ላይ ህዝቡ ቁጣውን እየገለጸ ነው። ይህንን የህዝብ ስሜት ለማብረድ እና ለማባበል በሚመስል መልኩም የፌዴራል ፖሊስ በተደጋጋሚ ይቅርታ እየጠየቀ ነው።

ገዳዩ የፌዴራል ፖሊስ ከአባይ ወንዝ ውስጥ ሞቶ ተገኝቷል

ገዳዩ የፌዴራል ፖሊስ ከአባይ ወንዝ ውስጥ ሞቶ ተገኝቷል
ከትላንት በስትያ ምሽት 2 ሰዓት ከ45 ላይ በተፈፀመው ድርጊት ከሞቱት መካከል ሴቶች ፣ ህፃናትና  አዛውንቶች ይገኙበታል ። ከተገደሉት ግለሰቦች መካከልም የሰባቱ የቀብር ስነ ስርዓት በደብረ አባይ ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስትያን በጋራ  ተፈፅሟል ።
በቀብር ስነ ስርዓቱ ላይ  የተገኙት የአማራ  ክልል  ርእሰ መስተዳድር  አቶ አያሌው ጎበዜ የክልሉ መንግስት የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን በመግለፅ ለሟች ቤተሰቦች መፅናናትን ተመኝተዋል ።
የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን  በበኩሉ በግለሰቡ ድርጊት ህይወታቸውን ባጡ ዜጎች  ህልፈት የተሰማውን ሀዘን ገልጿል ፡፡

 

በእንዲዚህ አይነቱ  ወንጀልም በህብረተሰቡና በፖሊስ መካከል ለዓመታት የቆየው መልካም ግንኙነትም አይሻክርም ብሏል በመግለጫው፡፡

የፖሊስነት ሙያዊ ዲስፕሊን  በጎደላቸው መሰል ፖሊሶችም ይህ አይነት ክስተት ደግም እንዳይፈጠር ጥረት እንደሚያደርግ ገልጿል። ይህ ሁሉ የፌዴራል ፖሊስ ልመና ግን ለህዝቡ እምብዛም የተዋጠለት አይመስልም። ይልቁንም ሰሞኑን በህወሃት ውስጥ የተፈጠረው ሽኩቻ ያበሳጨው ሰው መሆኑ ነው በሰፊው የሚወራው። ፖሊስም ይህንን የህዝቡን ቁጣ ላለማባባስ ሲል፤ የገዳዩን ስም እና ማንነት ከመግለጽ ተቆጥቧል፡፡

About Post Author

Abby

Internet reporter, freelancer and webmaster.
Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email

About the author

Internet reporter, freelancer and webmaster.

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar