ከተበላሸ ወተት ጥሩ እርጎ አይገኝምና ተተኪዉን ትዉልድ ሀገር ወዳድ አድርገን እናሳድጋቸው!

በኢሳ አብድሰመድ/by Issa Abdusemed/

22ኛ ዓመቱን ሊደፍን የተቃረበው የወያኔ ስርዓት ከቅድመ ዓያቶቻችን  የተረከብናት ሃገር አሁንም በመልካም አስተዳደር እጦትና
ብልሹነት ተውጣ የፍትህ ስርዓቷ በተረጋጋና በተደላደለ መሠረት ላይ የሚያቆሙ ተቋማት አልተዘረጉላትም፡፡
በዚህም ሀሳብን በነጻ የመግለጽ የመጻፍና የመናገር እንዲሁም በህግ ፊት እኩል የመቆም መብቶች እየተዳፈኑ ይገኛሉ…
በእርግጥ ያ ከ 21 ዓመት በፊት የነበረው ትውልድ  ከዚህ ውጭ አርአያ መሆን የሚችልባቸው
በርካታ ተሰጥኦዎች እንዳሉት መካድ አይቻልም። ለምሳሌ ላመነበት አላማ እፍኝ የማትሞላ ቆሎ ቆርጥሞ
ጦር ሜዳ ለመዋል አንዳች አለማመንታቱን ከትውልዳችን ጋር ብናነፃፅረው የመለኮት እንጂ የሰው ጽናት ላይመስለን ይችላል።
ይሄኔም ነው ያ ትውልድ እና ይሄ ትውልድ የመንፈስ ተወራራሽነት እንደሌላቸው በግልፅ የሚገባን፡፡
ለአገር ነፃነት መልካም ምግባር፣በጎነት፣ቆራጥና ደፋር ልብን ይፈልጋል። አገር ያለነፃነት አገር አይሆንም።
ነፃነት ሕያው የሕይውት ዋስትና መሰረትና አብይ ጉዳይ፣ የአገር ፍቅርና የክብር እሴት ሃብት ነው።ነፃነት
ዋጋ አለው። ይህውም ውድ የሆነ የሕይወት መሰዋዕትነት ደም ነው።ኢትዮጵያ ለብዙ ሺህ ዘመናት በነፃነት
ተጠብቃ የቆየችው የኛ ቀደምት ትውልድ በከፈሉት ቆራጥነት የደም ዋጋ ኃይል የአንድነት መሳሪያነት
ነው።በዚህም የኢትዮጵያ ሕዝብ ቆራጥነትና ፅናት አገርን በነፃነት መጠበቅ በዓለም ፊት ትልቅ ምሳሌነትን
ያተረፈ፣ ዛሬ ለአለነውና ለመጭውም ትውልድ የሚኰራበት ሕያው የታሪክ አለኝታ መመኪና ክብር፣
የዘላለም አገር ወራሽነት ሃብታችን በመሆኑ ጠብቀንና አስከብረን ለተተኪው ትውልድ ለማስረከብ
ኃላፊነቱ ከእጅግ ብርቱ ግደታ ጋር ነው።ለዚህም ነው “አገር አትሞትም ምንጊዜም ጠባቂ ትውልድ አላት”
የሚባለው። ይህን አምኖና ተቀብሎ አገርን በነፃነት የማይጠብቅ፣ወራሽ ትውልድ በኢትዮጵያ ሊኖር ከቶ
አይችልም። ከዚህ ያነሰ መስዋዕትነት ሆነ ኢትዮጵያዊነት የጐደለው ትውልድ፣ ከንቱ ትውልድ፣አገር
አልባነት፣ እፍረት፣ወራዳነት የቁም ሞት ነው። ሰው መሆን ይጠበቅብሃል።
አገርህ በባንዳዎች ወያኔ/ኢህአድግ  ሸፍጥና ተንኰል ተተብትቦ ከደደቢት ጀምሮ እስከ አሁኑ ወቅት ድረስ
በአሀዳዊት እናት አገር ኢትዮጵያ ላይ የማጥፋት ዘመቻ እተካሄደና እየተፈጸመባት ትገኛለች።ሉዓላዊነቷ
በክህደት ተንቆና ተደፍሮ አገር ለሁለት ተከፍላ፣ የቀረው በጎጥ ወንጀል በቋንቋ ክፍፍል ተመድቦ፣ የአገር
ሕልውና የውሃ፣የአየር፣ የየብስ ዳር ድንበር ክልሏ ተደፍሮ፣ ተጥሶና ተዋርዳ አለች።በአምባገነንነት
በጠበንጃ ኃይል፣ በሕገ_ ወጥ ሕግ፣በሃሰት ሕገ_ መንግሥት፣በማጭበርበሪያ ዴሞክራሲ፣ በውሸት ሽፍጥና
ተንኰል ሕዝብ ሰብዓዊ መብቱን ተነጥቆ፣ዜግነቱን አጥቶ፣ ብሔራዊ ሃብትና ንብረቱን እየተዘረፈ፣ የአገሩ
ለም መሬት እየተሸጠ፣እየተነጠቀና እየተባረረ፣ የሽብርተኛ ሕገ ወጥ ሕግ ወጥቶለት እየታሰረ፣እየተገረፈ ፣
ቶርች እየተደረገ፣እየተገደለና እየሞተ፣ እየተፈናቀለና እየተሰደደ፣እንዲሁም እየተሸጠ የአረብ አገር ባሪያ
እየሆነ በግፍና በጭቆና ማነቆ ተጠፍሮ በጥፋት ላይ በመሆኑ አንተ የኢትዮጵያ ወጣት ይህን በጽኑ ኅሊና
ተገንዝበህ በአስቸኳይ ልታጠፋው  የሚገባህ የባንዳ ሥርዓትን ነው።
ኢትዮጵያዊ ብሔራዊ ነፃነት ያነሰውና የጐደለው፣ዜግነትና አገራዊ ስሜትህን ተነፍገህ፣ በአደባባይ
ተዋርደህና ዝቅ ተደርገህ፣ ስብዕናና መብት ተነፍጐህ፣ኅብረተሰባዊ አንድነትህ፣ክብርና ኩራትህ ተንቆ
የአገሪቱ ሀብት እና ንብረት  ባለቤትነትህ ተነጥቆ፣ በባንዳ ወያኔ በአጉል ጠባብ ጎጠኛ አቀንቃኝነት በቋንቋ
ልዩነት ክፍፍል ኢትዮጵያዊ አንድነትህ ከታሪክ ምዕራፍ አውጥቶ ሲያስትህ በውሸት ፕሮፓጋንዳ
ሳታውቀው እየቆሰልክ እና እየደማህ፣  እየጠፋህና እየሞትህ እንደሆነ ልብ በል ። ዳሩግን ልብ
ከአጣህ ቆየህ ።
አንተ ዛሬ ወጣት በትምህርት ገበታ ላይ ነገ ደግሞ በሥራ ለአገር እድገት የምትሰለፍ
የመጭው ትውልድ መሰረት የሚጣልብህ ኃላፊነቱ እጅግ የላቀ ከፍተኛ የኅብረተሰብ ክፍል ነህ ብዬ
እገምታለሁ።
ይህ ከዚህ በላይ የተዘረዘሩት ግፍና ጭቆና በአገርና ሕዝብ በአንተ በዛሬው አበባ በነገው
ፍሬና ዘር ላይ የተተበተበና የታሰረ ማንነትን፣ጥቅምና ደህነትን፣ አለኝታን የነጠቀና ያሳጣ በባንዳ ወያኔና
በሆዳም አድርባይ ባንዳዎች የማያባራ ፀረ_ኢትዮጵያ፣ ኢትዮጵያዊነትና ሰንደቅ ዓላማችን ላይ ያነጻጸር
የጥፋት ሴራ አጀንዳ ነው።
ይህን የጠላት አመጣጥና አረማመድ በዓይነ_ኅሊና ልታይና ልትገነዘብ በተገባህ ነበር። ነገር ግን ዘንግተሃል እያንቀላፋህ ነው።
“ባለቤቱን ካልናቁ አህያውን አይጭኑም፣ወይም አይመቱም” እንደተባለው  አነጋገር ቤተሰብህ እጅ
በመስጠቱ በአንተ በታዳጊው ላይ ብዙ ጥፋትና በደል እየተሰራብህ ነው።
ወያኔ የአንተን አእምሮ አደንዝዞና ሰልቦ፣በማደንቆር ማንነትህን አሳጥቶ ቅል እራስ ሆነህ ወያኔ/ኢህአድግ
በአጠመደልህ ወጥመድ ዓይንህን ጨፍነህ፣ ጆሮህን አደንቁረህ ሰተት ብለህ በመግባት እራስህን፣ አገርና
ኅብረተሰብን የምትጐዳና የምትገድል ተልካሻ ትውልድ ሆነሃል።
በዚህም ክስተት ማንነትህን፣ የአገር ወገን የወደፊት ትውልድ ኃላፊነትና ግደታ ዘንግተህ ወያኔን አፍቃሪ፣
አክባሪ፣ እንድሁም ፈርተህና ተሸማቀህ አጐብድደህ ከመኖር በስተቀረ ወያኔ/ኢህአድግ ጠላትና አጥፊነቱ
ገዳይህም መሆኑን በፍጹም መረዳት አልቻልክም።
ተደስትህ የምትመካና የምትኰራ ትውልድ ሆነህ ወያኔዎች ሲሞቱ ታለቅሳለህ ፣ መሬት ትወግራለህ።
ይህ እጅግ ወራዳነትና የሚያሳፍር፣ ተራና ዝቅ ያለ እራስን በራስ የማጥፋት ከንቱ የኅረብተሰብ ዝቃጭነት ነው።
ይህ ሰው መሆንን ዘንግቶ የነገሩትን ብቻ የሚያስተጋባ ወይም የውሻ ጩህት ነው።
በዚህ ኅሊና ቢስነት ማንነትን ያላገናዘበ፣ያልተረዳና ያላወቀ ተግባር ትውልድን ሁሉ ያሳፈረ፣
ታሪክን የዘነጋና ያራከሰ እጅግ የሚያሳፍርና የሚጐዳ  ቁስል ነው።
በአገርና ሕዝብ ላይ የወያኔ አረመኔዊ ጭካኔና ክህደት ፣ጥፋት፣ሽፍጥና ተንኰል የሚደርስውና እያደረሰ ያለው
ከጣሊያን ፍሽስት ወረራ ጊዜ እጅግ የከፋና የመረረ ነው።
ወያኔ ፀጉረ_ልውጥ አይምሰልህ እንጂ፤ድሮም በአገር ክህደት ባንዳዎች የነበሩ እነዚህ የባንዳ ልጆች ወያኔዎች
የአገር ጠላ
አገር ተደፍሮና ተዋርዶ፣ታሪክ እየተበወዘ፣ አንድነት እየተናጋ፣ሕዝብ እየታመስ፣የአንተ ዜግነትና መብት
በሕገ ወጥ ሥርዓት ታፍኖና እየተረገጥህ፣ እየታሰርህ ማንነትህ እየጠፋና እየሞትክ ሲሆን፤ የአገርህ ለም መሬት
ደግሞ ከአንተ የአገሪቱ ተወላጅ፣ዜጋና ባለታሪክ ባለቤት፣አያት፣ ቅድመ አያትህ የሞቱላትን አጽመ_ርስት ሃብትን ተነፍገህና
እየተቀማህ ለውጭ አገሮች ለቻይና፣ ለህንድ፣ለአረብና ሌሎችም በርካሽና ለረዥም ጊዜ እየተሸጠ፣ እየተቸረቸረ ወያኔዎች
እየበለጸጉ፣ የአገርን ሃብት ወራሪ አንተን የማይመስሉ አጥፊዎች ናቸው።
ት እያወጡና እያሸሹት አንተ እየተቸገርህና እየደኽየህ በረሃብ እየተሰቃየህና ከአገር
እየተባረርክ እየተሰደድክህ ትገኛለህ። ይህ ሊያስቆጣህ፣ሊያናድድህና ጥርስ ሊያስነክስ በቻለ ነበር።
የወያኔ/ኢህአድግ እድሜ ለማሳጠር የተለመደው ሕዝባዊ ድጋፍ ተጠናክሮ እንዲቀጥል መላው ነፃነት ናፋቂና ሀገር
ወዳድ ኢትዮጵያዊያን ሀገራዊ መልዕክቴን አስተላልፏለዉ።

ኢትዮዽያ ለዘላለም ትኑር

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar