www.maledatimes.com የኢሳት ወይም የግንቦት ሰባት ሁለገብ ጋዜጠኞች ክሽፈት በኮረኔል ታደሰ እና ሌሎች ጉዳዮች ከያሬድ ኃይለማርያም - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

የኢሳት ወይም የግንቦት ሰባት ሁለገብ ጋዜጠኞች ክሽፈት በኮረኔል ታደሰ እና ሌሎች ጉዳዮች ከያሬድ ኃይለማርያም

By   /   July 22, 2013  /   Comments Off on የኢሳት ወይም የግንቦት ሰባት ሁለገብ ጋዜጠኞች ክሽፈት በኮረኔል ታደሰ እና ሌሎች ጉዳዮች ከያሬድ ኃይለማርያም

    Print       Email
0 0
Read Time:51 Minute, 9 Second

ሐምሌ 21፣ 2013 
ቀደም ሲል በሚያዝያ ወር 2005 ዓ.ም. ፕ/ር መስፍን ወልደ ማርያም ኢሳትን በማስመልከት በድህረ ገጻቸው ላይ “ደፋርና ፟ጭስ መውጫ አያጣም! የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዢንና ራዲዮ” በሚል ርዕስ ባስነበቡን ተከታታይ ጽሁፍ ክፍል አራት ላይ በመንተራስ የራሴን ትዝብትና ኢሳትን የሚመለከቱ አስተያየቶችን “የወያኔን ስሕተትና ወንጀል ሌላው ኃይል ሲፈጽመው ትክክልና ሕጋዊ ሊሆን
አይችልም” በሚል ርዕስ ሰንዝሬ ነበር። በዚያም ጽሑፌ ላይ ኢሳት ነጻና ገለልተኛ የሆነ ወይም ለእውነት፣ ለፍትሕ፣ ለሰብአዊ መብቶች እና ለዴሞክራሲያዊ መርሆዎች በሙሉ ልቡ የቆመ ሚዲያ አለመሆኑን አጠንክሬ በመግለጽ ወደፊት በዝርዝር እንደምመለስበት ቃል ገብቼ ነበር። በገባሁት ቃል መሰረት ምንም እንኳን ጊዜው ቢረዝምም የምንወያይበት ጉዳይ እልባት ያለገኘና እንደውም ችግሮቹ አፍጥጠው እየወጡ በመምጣታቸው መወያየቱ ሳይበጅ አይቀርም በሚል ሃሳቤን ለማካፈል ወድጃለሁ።
ባለፈውም ጽሑፌም ላይ በግልጽ እንዳስቀመጥኩት አገራችን ከተተበተበችበት አሳሳቢና ስር የሰደዱ ውጥንቅጥ ችግሮች፤ እንዲሁም በማኅበረሰባችን ውስጥ በሚታየው ግራ መጋባት እና መሰረታዊ በሆኑ የፍትሕ፣ የሰብአዊ መብቶች እና የዲሞክራሲ መርሆዎች ዙሪያ ከሚታየው ጥልቅ የሆነ የግንዛቤ ማነስ ወይም የተሳሳት ምልከታ መያዝ በመነሳት እንደ ኢሳት ያሉ የመገናኛ ብዙሃን ሊያበረክቱት የሚችሉትን አስተዋጽዎም ሆነ የሚኖራቸውን ቁልፍ ሚናን አሁንም አበክሬ ለመግለጽ እወዳለሁ። ይህን አቋሜን
ደግሜ መግለጽ የፈለኩት እርስ በርስ መተራረም፣ መገማገም እና አንዱ ያንዱን ድክመትና ጥንካሬ ከስሜት በጸዳና በቅን መንፈስ ላይ ተመርኩሶ የማሳየትና የመቀበል የፖለቲካ ባህል በማኀበረሰባችን ውስጥ ስላልዳበረ በርካታ የኢሳት ወይም የግንቦት ሰባት አፍቃሪዎች በኢሳት አካሄድ ላይ የተለየ አስተያየት የሚሰጡ ወገኖችን ጥላሸት ሲቀቡና የስድብ ናዳ ሲያወርዱባቸው በተደጋጋሚ ስለታዘብኩ
ነው። ለዚህም ከላይ የጠቀስኩትን የፕ/ር መስፍን ጽሁፎችና ተያይዘው የተሰጡ የአንባቢያን አስተያየቶችን መቃኘት ይበቃል።
እነኚህ ኢሳትን (ግንቦት ሰባትን) ወይም ሌሎች የሚደግፏቸውን ግልሰቦችና የፖለቲካ ድርጅቶች አትንኩብን ስለሚሉት ሰዎች አንድ ነገር ልበልና ወድ ዋናው ፍሬ ጉዳይ አመራለሁ። እነኚህን ወገኖች በሁለት ከፍዬ ባስቀምጣቸው ሳይሻል አይቀርም። የመጀመሪያዎቹ ቁጥራቸ እጅግ በርከት ያለ እና አገራቸውን ከመውደድና የአገራችን ጉዳይ ያሳስበናል ከሚል ስሜት ተነስተው ኢትዮጵያ ውስጥ
የፖለቲካ ለውጥ ለማምጣት የሚደረገውን ማናቸውንም ትግል ሁሉ በቅን መንፈስ የሚደግፉና ትግሉ እንዳይደናቀፍ የሚሰጉ ናቸው። ካላቸውም ጥልቅ ስጋት በመነጭ አዕምሮዋቸው የተለያዩ ሃሳቦችን እንዳያይቀበል እና እንዳይመራመር እንኳ ጥርቅም አድርገው በመዝጋት የማመዛዘን ሚዛኑን አስተው በሚደግፉት አካል ላይ ያላቸው ምልከታ ከደጋፊነት አልፎ አምላኪነት ደረጃ ላይ የደረሰ ነው። እነኚህ
ወገኖች በሚሰነዝሩዋቸው አስተያየቶች ላይ ሁሉ የሚንጸባረቀው እነሱ ከሚያራምዱት አስተሳሰብ ወይም ከሚደግፉት ሃሳብ ወይም ተቋም ውጪ ያለው አማራጭ ገደል ወይም ሞት ብቻ መሆኑን ነው፡ “ኢሳት ወይም ሞት!”፣ “ግንቦት ሰባት ወይም ሞት!”፣ ወዘተ … እንዲህ አይነት አቋም ካላቸው ወገኖች ጋር ክርክርም ሆነ ውይይት ማድረግ እጅግ አታካችና አሰልቺ ነው። ለመማማርም ሆነ ከስህተት ለመታረም ዝግጁ አይደሉም። ሙግታቸውም በእውቀት ላይ ወይም በሕገ-ኅልዮት ላይ የተመሰረተ አይደለም። በውይይት ላይ ‘ፍሬውን ትቶ ገለባውን የመውቀጥ’ ችግር ባልተማረውም የማኅበረሰባችን ክፍል ብቻ ሳይወሰን በተማረው የኅብረተሰብ ክፍልም ውስጥ ተዘውትሮ መታየቱ ግራ የሚያገባ እና ያለንበትንም ችግር ደረጃ በግልጽ የሚያሳይ ነው።
ሁለተኛው እና የሃሳብ ልዩነቶችን እንደጦር የሚፈራው ክፍል ከላይ ከጠቀስኳቸው ሰዎች የተለዩ ሰዎች ያሉበት ነው። ልዩነታቸው ከላይ የጠቀስኳቸው ሰዎች ከግንዛቤ ማነስም ይሁን ከቅን ልቦና በመነጨ ስሜት ለለውጥ ካላቸው ጉጉት ተነስተው ሲሆን እኒዚህኞቹ ግን ይህን አይነቱን አንድ ወጥ አስተሳሰብ ወይም አንድን አካል የበላይ ወይም ገዢ ሆኖ እንዲወጣ ማድረግን አቅደውና ይህንንም እንደ አንድ
የፖለቲካ ስልት ነድፈው የሚንቀሳቀሱ ኃይሎች መሆናቸው ነው። እነኚህ ኃይሎች ከቅን ልቦና እጅግ በራቀ መልኩ ልክ ገዥው የወያኔ ሥርዓት እንደሚያደርገው እነሱም ባሰመሩት አንድ ወጥ የሆነ የፖለቲካ አስተሳሰብ እና የትግል ስልት እንድንቆርብና ከላይ የጠቀስኩዋቸውን ደጋፊዎቻቸውን አጥር በማድረግ የፖለቲካ ተልኳቸውን ለማሳካት የሚዳክሩ ናቸው። እነኚህ አካላት ሁሉም ሰው በአንድ ከረጢት ውስጥ ሆኖ እንዲያስብ እና ከእነሱ ኋላም ተሰልፎ እንደተሰገረ በቅሎ ግራ ቀኙን ሳያያ ተከትሏቸው ገደልም ሲገቡ አብሮ ድንዲገባ የሚደክሙ ናቸው። እነዚህ አካላት ከወያኔ ጋር የሚመሳሰሉበት እና የሚጋሩት ብዙ ባህሪያት አሏቸው። ለዚህም ኢሳትን የመሰረተው እና በባለቤትነት
የሚያስተዳደረው ግንቦት ሰባት ግንባር ቀደም ተጠቃሽ ነው። ልክ ወያኔ የመገናና ብዙሃንን፣ ጋዜጠኞችን፣ የሲቪክ ማህበራትን፣ የሙያ ማኅበራትን፣ በውጭ አገር የሚገኙ ኮሚኒቲዎችን፣ አርቲስቶችን፣ የዜና ማሰራጫ ድህረ-ገጾችን፣ ምሁራንና የተለያዩ የመዋያያ መድረኮችን፤ በተለይም ፓልቶክን ለመቆጣጠር እና የድርጅቱን አቋም ብቻ እንዲያንጸባርቁና ሌሎች የድርጅቱን አቋም የሚነቅፉ ወይም የተለየ አስተሳሰብ ያላቸው አካላት እንዲዳከሙ ወይም እንዲሸማቀቁ ባርካታ ጥረቶችን ሲያደርግ ቆይቷል። ዝርዝሩን ወደፊት በማቀርባቸው ጽሑፎች እመለስበታለው። ለጊዜው ትኩረቴን የጽሑፌ መነሻ ወደሆነው እና የዚሁ ድርጅት ጥንስስ እና ሰለባ ወደሆነው የኢሳት ጉዳይ
ልመልስ።
ኢሳት የማነው የሚለው ክርክር ጊዜ ያለፈበት ስለሆነ በሱ ላይ ጊዜዬን ለማጥፋት አልፈልግም። ኢሳት የማንም ቢሆን እንደ አንድ ኃላፊነት የሚሰማው ሚዲያ ለእውነት ወግኖ እየሰራ ነው ወይም አይደለም የሚለውን ጭብጥ ግን ላልፈው አልችልም። የኢሳት ባለቤት የሆኑት የግንቦት ሰባት ባለስልጣናት እና በኢሳት ውስጥ በማገልገል ላይ ያሉ ጋዜጠኞች ባደባባይ ውጥተው ሥራችንን በአግባቡ እየሰራን ነው
ለሚለው ሚዛን የማይደፋ የመከላከያ ሙግታቸው ግን መልስ ለመስጠት እወዳለሁ። ነገሬን ፈር ለማስያዝ በኢሳት ላይ ያለኝን ትዝብት በሁለት መልኩ ባስቀምጠው ለአንባቢያንም እራሴን ግልጽ ለማድረግ ይቀለኛል። ይህውም ኢሳት ለእውነት፣ ለፍትሕ፣ ለሰብአዊ መብቶች፣ ለዴሞክራሲ የወገነ የሚዲያ ተቋም ነው ወይ? ሁለተኛ ኢሳት በሚያስተላልፋቸ ዘገባዎች ውስት አፍጠውና አግጠው የሚታዩ ግድፈቶች፣ የተዛቡ እና ሚዛን የሳቱ ዘገባዎች፣ ስሜታዊነት፣ እንዳይሰራጩ የሚታፈኑ ጉዳዮች የሉም ወይ?
የመጀመሪያውን ጥያቄ ቀደም ሲል በጻፍኩት ጽሑፌ ውስጥ የመለስኩት ቢሆንም በአጭሩ ለመመለስ እሞክራለሁ። ምንም እንኳን ኢሳት የተመሰረትኩብት አላማ በሚል ለሕዝብ በድህረ-ገጹ ላይ የገለጻቸው አላማዎቹ እና ግቡ ከላይ የጠቀስኳቸውን መርሆዎች የሚያንጸባርቅ ቢሆንም አፈጣጠሩ
ግን ከመነሻው ይህን ግቡን እንዲያሳካ በሚያስችል መልኩ አልነበረም። ምክንያቱም ኢሳት የግንቦት ሰባት ‘ሁሉ አቀፍ የትግል ስልት’ አንዱ አካል ሆኖ ነው የተፈጠረው። ግንቦት ሰባት በአስመራ ብቻ ሳይሆን የዘመናዊውን ቴክኖሎጂ በመጠቀም እያንዳንዱን ኢትዮጵያዊ በየቤቱ ለመድረስ የከፈተው እና በግንቦት ሰባት የሬዲዮ ፕሮግራም የተጀመረው የሳተላይት ዘመቻ ቀጣይ አካል ነው። ይህ ደግሞ
ኢሳት ከመነሻውም ጉዞውና መድረሻው በጠባብ የግንቦት ሰባት የፖለቲካ አጀንዳ ላይ የተወሰነ መሆኑን ነው የሚያሳየው። ግንቦት ሰባት ሲዋሽ፣ ሲሳሳት፣ አቅጣጫውን ሲስት፣ ለአገርና ለሕዝብ ዘላቂ ሰላም የማይበጅ ተግባራትና ጥፋቶችን ሲያጠፋ ኢሳትም አብሮ ይነጉዳል። ኢሳት የተመሰረተበትን ውሉን አልሳተም። የግንቦት ሰባት የቴሌቪዥን ልሳን ሆኖ ቀጥሏል። በኢሳት ውስጥ ያሉ ጋዜጠኞችም፤ ሁሉንም ለማለት አልደፍርም፤ ልክ ወያኔ በኢትቪ፣ በኢትዮጵያ ሬዲዮ እና በፋና ሬዲዮ ባሰማራቸ ‘ልማታዊ ጋዜጠኞች’ ህዝብን እያደናበር እንዲሚጓዘው ሁሉ ኢሳትም ‘የሁሉ አቀፍ ትግል’ ጋዜጠኞችን ይዞ ጉዞውን ቀጥሏል።
ሁለተኛውን ጥያቄ መመለስ በተጨባጭና በማስረጃ ኢሳት የሚነዳበት ወይም እንዲከተለው የተሰመረለትን የተሳሳት የፖለቲካ አግጣጫ ወይም ቅኝት መኖሩን ያመላክታል። ለዛሬው በተወሰኑ ትዝብቶቼ ላይ ብቻ ልወሰንና ወደፊት በዝርዝር እመለስበታለሁ።
• የኮረኔል ታደሰ ሙሉነህ ጉዳይ
በደርግ መንግስት የአየር ኃይል አብራሪ የነበሩት እና ወደ ኤርትራ ተሰደው የአርበኞች ግንባር መሪ
የነበሩት የኮረኔል ታደስ ሙሉነህ ጉዳይ የኢሳትን ተልዕኮ እና በተለይም በዚህ ጉዳይ በቀጥታ ተጠቃሽ
የሆኑውን ቀደም ሲል የግንቦት ሰባት ሬዲዮ አቅራቢና አሁን የኢሳት አምስተርዳር ቅርንጫፍ ተጠሪና
ጋዜጠኛ ፋሲል የኔአለምን ይመለከታል። ኮሎኔል ታደሰ በኤርትራ መንግስት ቁጥጥር ስር ወለው
የደረሱበት ያልታወቀ መሆኑን የተሰማው በሆላንድ አገር ነዋሪ የሆነችም ልጃቸው በ2011 ዓ.ም.
በምርጫ 97 የተገደሉ ወገኖቻችንን ለማስታወስ በአምስተርዳም ከተማ በተጠራ ሕዝባዊ መድረክ ላይ
ተገኝታ አጋጣሚውን በመጠቀም (ለምን እንዲህ እንዳልኩ አክዮ እገልጻለሁ) ባልታሰበ ሁኔታ ድምጿን
ክፍ በማድረግ “አባቴን አፋልጉኝ፣ የኤርትራ መንግስት አባቴን አፍኖብኛል፣ የኮረኔል ታደሰ ልጅ ነኝ፣
የኢትዮጵያ ሕዝብ አባቴን እንዲያፋልገኝ እና የኤርትራ መንግስት አባቴን እንዲለቅልን አብራችሁኝ
ድምጻጭሁን አሰሙልኝ” የሚል ጥሪ እያነባች ባዳራሹ ለተሰበሰበው ሕዝብ አቀረበች። የዕለቱን
ዝግጅት ሊዘግቡ የሄዱ የኢሳት ጋዜጠኞችም የልጅቷን አቤቱታ በመቅረጽ በእለቱ ዜና ስርጭታቸው
ላይ አያይዘው አቀረቡት።
የልጃቸውን አቤቱታ ተከትሎ በተለያዩ ድህረ-ገጾች የኮረኔል ታደሰ ጉዳይ መዘገብ የጀመረ ቢሆንም በቂ
ሽፋን አላገኘም ነበር። ከተወሰኑ ሳምንታት በኋላ በአምስተርዳም የተዘጋጀ የሰብአዊ መብቶች ጉዳይ
ላይ ያተኮረ ስብሰባ ለመካፈል ሄጄ በኢሳት አቤቱታ ያቀረበችውን የኮረኔል ታደሰን ልጅ ለማግኘት
እድሉ ገጥሞች ስለአባቷ ሁኔታ አንስተን ለመወያየት ችለናል። በዚህ አጋጣሚ ልጃቸው በአባቷ ላይ
ከደረሰው እና እየደረሰ ካለው ስቃይ ባልተናነሰ ስሜቷን እጅግ በሚጎዳ መልኩ በኢሳት በኩል፤
በተለይም በአቶ ፋሲል የኔአለም በኩል የደረሰባትን በደል እያነባች ሌሎች የስብሰባው ታዳሚዎች
ባሉበት አጫውታኛለች። ነገሩም እንዲህ ነው። የኮረኔል ታደሰ ልጅ የአባቷን አያያዝ እና ያሉበትን
ሁኔታ በተመለከተ ዝርዝር ማብራሪያ ለሕዝብ ለመስጠትና እግረ መንገዷንም የኢትዮጵያ ሕዝብ
ጥሪዋን አብሮ እንዲያስተጋባላትና አባቷም እንዲፈቱ ጥረት እንዲደረግ በማሰብ ወደ ኢሳት
አምስተርዳም ቢሮ በመሄድ እድል እንዲሰጣት ትጠይቃለች። ይሁንና ከኢሳት የተሰጣት መልስ አንቺን
አናቀርብም፣ የአባትሽንም ጉዳይ በኢሳት ከዚህ በኋላ አናሰናጭም የሚል ነበር። የኮረኔል ታደሰ ልጅም
ተስፋ ሳትቆርጥ ከኤርትራ ሸሽተው የመጡና የአባቷን መታሰር በአይናቸው የተመለከቱ ምስክሮችን
በመያዝ ኢሳት ማስረጃ ፈልጎ ከሆነ በሚል ግምት በድጋሚ ወደ ኢሳት አምስተርዳም ቢሮ በመሄድ
እድሉ እንዲሰጣትና ምስክሮቹም እንዲጠየቁ ላቀረበችው ጥያቄ የተሰጣት መላሽ በድጋሚ ወደ ኢሳት 4
ቢሮ እንዳትመጪ የሚል ነበር። አቶ ፋሲል አክለውም ምስክር የተባሉትንም ሰዎች ወደ ኢሳት ቢሮ
አንዳይመጡ በማስጠንቀቅ የመለሱዋቸም መሆኑን የኮረኔል ታደሰ ልጅ እያለቀሰች አውግታናለች።
ኢሳት የኮለኔል ታደሰ ጉዳይ በዝርዝር እንዳይተላለፍ በአቶ ፋሲል በኩል የከለከለው ጉዳዩ አንዴ ሽፋን
ተሰጥቶታል ወይም በፕሮግራም መጣበብ ወይም በሌሎች የአሰራር ቀደም ተከተሎች የተነሳ
አይደለም። ምክንያቱ ግልጽ እና ግልጽ ነው። በቅርቡም የግንቦት ሰባት ሊቀመንበር እንዳረጋገጡልን
ኢሳት የሚንቀሳቀሰው እና እነ አቶ ፋሲል የኔአለምም ደሞዛቸውን የሚያገኙት ከኤርትራ መንግስ
በሚሰጥ ድጎማ ነው። ከዚያም በላይ የኢሳት ባለቤት የሆነው ግንቦት ሰባት ጎጆውን የቀለሰው
በአስመራ ከተማ ነው። ስለዚህ የኤርትራን መንግስት ገበና የሚያጋልጡ ምንም አይነት ነገሮች
ከሰብአዊ መብት ወይም ከፍትህና ከዴሞክራሲ መርሆዎች ቢቃረኑ እንኳ፣ የኢትዮጵያንና
የኢትዮጵያዊያንን ክብርና መብት የሚጎዱ ቢሆኑም እንኳ በኢሳት አይዘገቡም። የኮረኔል ታደሰም ልጅ
ቀደም ሲል አጋጣሚውን ተጠቅማ ነው በኢሳት የመጀመሪያውን ድምጿን ያሰማችው። ሕዝብ
በተሰበሰበበት መድረክ ላይ ስለሆን የተናገረችው እነ አቶ ፋሲል ቆርጠው ሊያወጡት አይችሉም።
ይህንኑ ጉዳይ በተመለከተ የግንቦት ሰባት ምክትል ሊቀመንበር የሆኑት አቶ አበበ ቦጋለ በ2011 ዓ.ም.
በአንድ አጋጣሚ ተገናኝተን በቤልጂየም ኢሳትን በገንዘብ ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ስላላቸው
እቅድ አንስተው ሌሎች ሰዎችም ባሉበት አጠር ያለ ውይይት አድርገን ነበር። በውይይቱም
ኢሳታቸውን ለማጠናከር ከገንዘብ የበለጠ ለሚዲያውና በውስጥ ለሚሰሩት ጋዜጠኞች የሚያስፈልገው
ትልቁ ነገር የሚዲያው ነጻ መድረግ መሆኑን አበክሬ በመግለጽ ኢሳትን ከግንቦት ሰባት ፖለቲካ ነጻ
እንዲያደርጉት በማሳሰብ በኮረኔል ታደሰ ልጅ ላይ የደረሰውን አጋጣሚ በምሳሌነት አንስቼባቸው
ነበር። ግለሰቡም ይህንኑ ጉዳይ ወደ ኢሳት ቢሮ በመውሰድ ከአቶ ፋሲል ጋር ከተነጋገሩበት በኋላ አቶ
ፋሲል በዚያው ሳምንት ውስጥ ለኮረኔል ታደሰ ልጅ ስልክ በመደወል አርፋ የማትቀመጥ ከሆነ
ከኤርትራ አንድ ባለስልጣን በኢሳት በማቅረብ አባቷ በኤርትራ መንግስት ያልታሰሩ እና ምንም
ያልደረሰባቸው መሆኑን የሚመለከት የማስተባበያ ዘገባ የሚሰሩ መሆኑን በማሳሰብ ያስጠነቀቁዋት
መሆኑን ልጃቸው ገልጻልናለች። የሚያስገረመው ከሦስት አመት ቆይታ በኋላ አቶ ፋሲል የኔ አልም
አይናቸውን በጨው አጥበው እና አቶ አፍወርቅ አግደውን አስከትለው በኢሳት የጁላይ 18፣ 2013
“የድህረ-ገጽ ዳሰሳ” በሚል ፕሮግራማቸው ላይ አንድ ሰመረ አለሙ የተባሉ ጸሐፊ ስለ ኮረኔል ታደሰ
የሕይወት ታሪክ እና ስለሚደርስባቸ ስቃይ የጻፉትን ጽሑፍ የፕሮግራማቸው አካል በባድረግ ስለ
ኮረኔል ታደስ አቶ ፋሲል ተቆርቋሪ መስለው መቅረባቸው አስደምሞኛል። ነገር አለ ብዬ እንዳስብም
አድርጎኛል። እዚህ ላይ ለአቶ ፋሲል የማነሳንው ጥያቄ፤ ምነው እስከ ዛሬ የት ሄደው ነው? በርካታ
ግለሰቦችና ድርጅቶች፣ በተለይም የኢትዮጵያ የፖለቲካ እስረኞች አንድኘት ኮሚቴ (ኢፓኣኮ) ኦክቶበር
29፣ 2011 ያወጣውን ሪፖርት መጥቀስ ይቻላል፤ እንዲሁም በተለያዩ ድህረ-ገጾች ላይ ስለ ኮረኔል
ታደስ ሁኔታ ሲያትቱ እንዴት ሳይታይዎት ወይም ኢሳትን ሳይታየው ቀረ? ለምን ልጃቸ ለሕዝብ
ብሶቷን ባግባቡ እንዳታሰማ ማፈን አልፎም ማስፈራራት አስፈለገ? ዛሬ ምን ታየዎት? ነው ወይስ
ይህም ድርጅታዊ ሥራ ነው? ምናልባት ግንቦት ሰባት ኮረኔል ታደሰን ለሕዝባዊ ንቅናቄው አስፈላጊ
ሰው ሆነው አግኝቷቸው ከኤትርትራ መንግስት ጋር እንዲፈቱ መደራደር ጀምሮ ይሆን? ከሆነ እሰየው
መፈታታቸው ነው የሚፈለገው። ሃቁን ሰንብተን እንሰማዋለን።
ከኢሳትና የኤርትራ ጉዳይ ሳልወጣ በተደጋጋሚ ጊዜ የታዘብኩትን ጉዳይ በአጭሩ ጠቆም አድርጌ
ልለፍ። የአረብ ስፕሪን እየተባለ የሚጠራውና በርካታ የአረብ አገሮችን ሲያተራምስ የቆየም አብዮታዊ
ንቅናቄ በጀማመረበት ሰሞን ኢሳት በርካታ የትንታኔ ዘገባዎችን ያሰራጭ ነበር። በነዚያ ዘገባዎቹ ላይ
የአረቡ አልም ንቅናቄ ወደ አፍሪቃ አገሮችም ይዛመታል፤ በዚያም አምባገነናዊ ሥርዓት የሰፈነባቸው 5
የአፍሪቃ አገሮች የመጀመሪያዎቹ ሰለባዎች ናቸው የሚል ትንታኔ በተደጋጋሚ በአቶ ፋሲል ይቀርብ
ነበር። በሃሳቡ ይሁንም አይሁን ሊከሰት ይችላል በሚለው እስማማለሁ ይሁንና አቶ ፋሲል እየደጋገሙ
አደጋው ያንጃበበባቸውን እና ለበርካታ አመታት ሥልጣን ይዘው አለቅ ያሉ የአገራት መሪዎችን
ሲዘረዝሩ ከሊቢያ ተነስተው በኢትዮጵያ አድርገው ቁልቁል ወዳሉ የአፍሪቃ አገራት ሲያቀኑ ኤርትራን
በፍጹም አያነሱም። እንግዲህ በአቶ ፋሲል ወይም በኢሳት ካርታ ውስጥ ኤርትራ የለችም እንዳልል
የሱዳኑ መሪ አልበሽር አስመራ ለጉብኝት በሄዱበት ጊዜ እንደ ታላቅ ዜና ተደርጎ የተዘገበ ሲሆን
ትንታኔውም የአልበሽር ኤርትራን መጎብኘትና ከአምባገነኑ ኢሳያስ ጋር መገናኘታቸው ለኢትዮጵያ
ታጣቂ ኃይሎች ሰፊ የመፈናፈኛ ቦታን ያመቻቻል የሚል ነበር።
• የጋዜጠኛ ሲሳይ አጌና እና የዶ/ር ብርሃኑ ውይይት በኢሳት
ጋዜጠኛ ሲሳይ አጌና በቅርብ ጊዜው (ላለፉት ሃያ አመታት) የኢትዮጵያ ነጻ ጋዜጠኞች ሕዝባቸውን
ለማስተማርና የመረጃ ባለቤት ለማድረግ በከፈሉት ታላቅ መስዋዕትነት ውስጥ በግንባር ቀደምነት
የሚጠቀስ ባለሙያ ነው። ለሱ ያለኝን አክብሮትም ቀደም ሲል በጻፍኩት ጽሑፍ ውስጥ ጠቅሻለሁ።
ይሁንና ሲሳይ ከበርካታ እንግዶቹ ጋር በሚያደርገው ውይይት ውስጥ የሚያነሳቸውን በሳል እና
ደረጃቸውን የጠበቁ ጥያቄዎች ከዶ/ር ብርሃኑ ጋር ሲያደርግ አላስተውለውም። አንዳንድ
የሚያነሳቸውም ጥያቄዎች ውስጡ ምን እንደሚያስብ ቢያመላክቱም በአንጻሩ አንድ ሊጥሰው ወይም
ሊያልፈው የማይችል እና የሚጠነቀቅለት የኢሳት የውስጥ ቀይ መስመር ያለ መሆኑን ውይይቱን
በአንክሮ ለተከታተለ በግልጽ ይስተዋላል። ለዚህም ሁለት ምሳሌዎችን ልጥቀስ፦
– ጋዜጠኛ ሲሳይ የግንቦት ሰባት ሕዝባዊ ንቅናቄን መመስረት ተከትሎ በቀናት ልዩነት ውስጥ
ዶ/ር ብርሃኑን ለውይይት ጋብዧቸው ወይም እራሳቸው መድረኩን ጠይቀው ሊሆን
ይችላል አቅርቧቸው ነበር። ንቅናቄውን በተመለከተ በተደጋጋሚ ጊዜ እሳቸው ከሚመሩት
ድርጅት ጋር ያለውን ግንኙነት እንዲነግሩት ላቀረበላቸ ጥያቄ ሙሉ በሙሉ ሽምጥጥ
አድርገው ክደዋል። ከእሳቸው ድርጅት ጋር ምንም አይነት ግንኙነት እንደሌለው
ለማስረዳት ምድር ጭረዋል፣ ሰማዩንም ለመቧጠጥ ጥረዋል። ይሁንና በዚያው ወቅት
ንቅናቄው ከመመስረቱ ቀደም ብሎ የድርጅታቸው ም/ሊቀመንበር እና ሌሎች የአመራር
አባላት አስመራ መግባታቸውን፣ ሰራዊት እያደራጁ መሆኑን እና በቅርቡም ዜናውን
እንደሚያበስሩን የሚጠቁሙ ጽሁፎች በየ ድህረ-ገጹ ተበትነው የሕዝብ መወያያ ሆነው
ቆይተዋል። የወያኔ ደጋፊ የሆኑ ሚዲያዎች ሳይቀሩ ነገሩን ሲያነሱና ሲጥል ከርመው ነው
የሕዝባዊ ንቅናቄው ዜና የተበሰረው። ታዲያ ወዳጄን ሲሳይ ምን ይዞት ነው ዶ/ር ብርሃኑ
እኛ የለንበትም ብለው ሲክዱ የእርሶ ጀሌዎች ታዲያ አስመራ ምን ሊሰሩ ነው የሄዱት፣
ወይስ ሄዱ የሚባለው ውሽት ነው ወይ? ከሄዱስ ምን ሊሰሩ? የሚሉ ጥያቄዎችን እንደ
አንድ ነጻ ጋዜጠኛ ማንሳት የተሳው? መቼም የአመራሩን ወደ አስመራ ሄዶ መከተም አቶ
ሲሳል አልሰማሁም ነበር እንደማይል ተስፋ አደርጋለሁ፤ ካለያማ …
– ይህን ይሁን ብለን ባሳለፍን በጥቂት ወራት ውስጥ የዶ/ር ብርሃኑን ድምጽ የያዘ የስልክ
ንግገር መሰራጨቱን ተከትሎ በድጋሚ ጋዜጠኛ ሲሳይ አጌና እና ዶ/ር ብርሃኑ ለጥያቄና
መልስ (ድራማ) ኢሳት ቢሮ ተገናኝተው ነበር። በተሰራጨው የስልክ ንግግር ላይ የተነሱ
አንዳን አሳቦችን በመጥቀስ ዶ/ር ብርሃኑ እረዘም ያለ እና ተደጋጋሚ ሃሳቦችን እየተነተኑ
ማስተባበያ ሲሰጡ ሰምቻለሁ። ከአሁን ከአሁን ጋዜጠኛ ሲሳይ እንዲህ የሚል ጥያቄ 6
ያነሳል እያልኩ ስጠበቅ ነበር። ‘ዶ/ር ብርሃኑ በቅርቡ ባደረኩልዎት ቃለ መጠይቅ ላይ
የግንቦት ሰባት ሕዝባዊ ንቅናቄ ከእርሶ ድርጅት ጋር ግንኙነት አለው ወይ? በዮ
ብጠይቅዎት በፍጹም በለው አስተባብለዋል። አሁን ደግሞ በዚህ የስልክ ንግግርዎ ላይ
ሕዝባዊ ንቅናቄው የእናንተ መሆኑን፣ ለማደራጃም ገንዘብ መቀበልዎን፣ አንዳንድ
ንቅናቄውን አንቀበል ያሉ ድርጅቶችንም መንቀፍዎን፣ ከገንዘቡም ላይ ገሚሱ የኢሳት ሥራ
ማስኬጃዎ መሆኑን ገልጸዋል። ይህ ንግግርዎ አይጋጭም ወይ?’ ይሁንና ሲሳይ እነዚህን
ነገሮች በራሱ ፈቅዶ ይሁን ለመገደድ ወዶ ሳያነሳቸው እረዥም ሰዓት የፈጀው ትርጉም
አልባ ውይይት ተጠናቋል። ይህን ክፍተት ሲሳይ በሙያ ብቃት ማነስ ወይም በዳተኝነት
የፈጸማቸው እንዳልሆኑ አፌን ሞልቼ መናገር እችላለሁ። ሲሳይ ከነዚህ የጠነከሩ እና በሳል
ጥያቄዎችን ለማቅረብ አቅሙም ችሎታውም አለው ብዮ ነው የማምነው። እንዳልኩት ግን
ግንቦት ሰባት ለኢሳት ያሰመረለት ቀይ መስመርን ለማለፍ ብርታቱን ማጣቱ ግን ግር
አሰኝቶኛል። ‘ሁለ ገብ ጋዜጠኛ’ እንደሆኑት የእነ ፋሲል የኔአለምን መንገድ ሊያያዘው ዳር
ዳር እያለ ለመሆኑ ግን ምልክት ሊሆን ይችላል።
ይህን ዳሰሳዮን በሌላ ክፍል እመለስበታለሁ። ለማጠቃለያ ያህል ግን አንድ ኢሳት አይደለም አስር እና
ሃያ የኢሳት አይነት የመወያያ ሚዲያዎች እንኳን ቢኖሩን ተወያይተን ተነጋግረን የማንጨርሳቸው
በርካታ ሃገራዊ ጉዳዮች አሉን። የመገናኛ ብዙሃን መኖር፣ መበራከትና መጠናከር ለዘመናት ተጭነው
ያጎበጡንን ጭቆናን፣ የአንባገነናዊ ሥርዓትን፣ መገለጫ የሌለው ስር የሰደደ ድህነት፣ የሞራል ኪሳራ እና
ሌሎች ውርደትን ያከናነቡን ስንክሳሮች ከላያችን ላይ ለማራገፍ እና በሳይንሳዊ አስተሳሰብና በእውቀት
የታነጸ ማኅበረሰብ ለመገንባት መገናኛ ብዙሃን ግንባር ቀደም ተጠቃሾች ናቸው። ይሁንና በጥንቃቄ
ባልተያዙበት፣ ተጠያቂነት በጎደለው እና ለጠባብ የፖለቲካ አጀንዳ ማስፈጸሚያ እንዲውሉ
በተደረጉባት ስፍራ ሁሉ የሚጠቅሙትን ያህል ሞታችንን እና ውድቀታችንን ያፋጥኑታል። ወያኔን
በምንወቅስባቸው መሰረታዉ ጉዳዮች ሁሉ እራሳችንንም መፈተሻ፣ መጥፎውን መንቀፊያና ማረሚያ
ልናደርጋቸው ይገባል።
የግንቦት ሰባት አመራሮችም ሆኑ አንዳንድ የኢሳት ጋዜጠኞች ኢሳት የማንም ቢሆን እንደ አንድ ነጻ
ሚዲያ እያገለገለ ነው ለሚለው ሙግርታቸው ከላይ የጠቀስኳቸውን ነገሮች ብቻ ማንሳቱ በቂ ላይሆን
ይችላል። እነዚህን የመሰሉ በርካታ ምሳሌዎችን በነቂስ ለማውጣት ይቻላል። ወያኔን ስላወገዝንና
የወያኔን ገበና ስላጋለጥን ለእውነት የወገንን ነን እና የነጻ ሚዲያ ኒሻን ይሰጠን የሚለው ሙግት ግን
አያዋጣም። ለእውነት መወገን ጊዜን፣ ቦታን እና ሁኔታዎችን እየጠበቁ ወይም የፖለቲካ ሃሳብ እያሰሉ
አይደለም። ለእውነት በእውነተኝነት መቆም አዋጪ ሲሆን የምንይዘው ካላዋጣ የምንጥለው አይነት
ነገር አይደለም። ለአንድ ሚዲያ ወይም ጋዜጠኛ ትልቁ ጉልበቱ እውንነት ነች። እውነትን ይዞ መሣሪያ
ካነጋቡት፣ በሥልጣን ጡንቻቸውን ካፈረጠሙት ጋር ሁሉ እኩል መቆም፣ መሟገት ይቻላል።
ለእውነት የሚቆም ጋዜጠኛ ወይም ሚዲያ ወያኔ ላይ ያየውን እጸጽ ሌላውም ላይ ሲያይ በተመሳሳይ
ሁኔታ ያጋልጣል፤ ለሕዝብ ያሳውቃል።
ጋዜጠኛ ወይም የመገናኛ ብዙሃን የፓርቲዎች ወጥመድ ውስጥ ሲወድቁ ግን የሚታያቸውና
የማይታያቸው እውነት ይኖራል። ለሁሉም እውነቶች አኩል አይወግኑም። ለፍትሕ፣ ለሰብአዊ መብቶች
መጣስ፣ ለዲሞክራሲያዊ ሥርአት የሚኖራቸው ተቆርቋሪነት እንዲሁ የተዛባ ነው። ለዚህም ከዚህ
በፊት እንደጠቀስኩት ኢሳት የአለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች ድርጅቶች በሃገሮች ላይ የሚያወጡትን
መግለጫ ሲተነትን በተደጋጋሚ እንዳስተዋልኩት በኢትዮጵያና በሌሎች ጎረቤት አገሮች ላይ
የሚያደርጉትን ትንታኔ ያህል በሰብአዊ መብቶች የከፋ ደረጃ ላይ ስላለችው ኤርትራ በጨረፍታ ጠቆም 7
አድርገው ያልፋሉ ውይም ሳይጠቅሷት ይቀራሉ። በኢትዮጵያ ውስጥ ባለው አምባገነናዊ ሥርዓት
ተሰቃይተውና ግፍ ተፈጽሞቻቸው ከአገር የወጡ እንደ ፋሲል የኔአለም አይነት ጋዜጠኞች የሙያ
አጋሮቻቸ ለሆኑትና በኤርትራ እሥር ቤቶች ከአሥር አመት በላይ ያለፍርድ ስለሚማቅቁት ጋዜጠኞች
ድማጻቸውን ለማሰማት ብርታቱን ሲያጡና ሲቆጠቡ ማየት እጅግ ያሳዝናል። የቱጋ ነው የፍትህ
ተቆርቋሪነታችን? የቱጋ ነው ለሰብአዊ መብቶች መከበር ዘብ የምንቆመው? ወያኔ ብቻ ስፈጽመው
ከሆነ ይህ ትልቅ የሞራልክ ክስረት ነው።
እንደ እኔ እምነት ለኢሳትም ሆነ ለጋዜጠኞቹ ከየአቅጣጫው የተሰነዘሩትን አስተያየቶች ተቀብሎ
እንደሰለጠነ ሰው እራስን ማረቅ እና የጎበጠውን ማቅናት ይበጃል። ይህ ሁሉ ሙግት የተነሳው እኮ
ያልሆናችሁትን ገለልተኞች ነን ስላላችሁ እንጂ ኢሳት የግንቦት ሰባት ልሳን መሆኑን ሳይክድ ስራውን
ቢቀጥል ይህ ሁሉ አተካራ ባልተነሳ ነበር። “የግንቦት ሰባት ቢሆንስ” የሚለው የጅል ሙግት
አያዋጣም። ከላይ የዘረዘርኳቸውን ጥቂት ትዝብቶች ያስከተለው ኢሳት የግንቦት ሰባት ከመሆኑ ጋር
ተያይዞ የመጣ ነው። በቅርቡም ዘግይቶ በተለቀቀው የዶ/ር ብርሃኑ የስልክ ንግግር ላይ እንደሰማነው
ኢሳት ማስተላለፍ የማይገባውን ነገር በተመለከተ መመሪያ ሲሰጡ ሰምተናል። ሌሎችም ያፈጠጡ
እውነቶችን ለመጥቀስ ይቻላል። የቢሆንሳ ጣጣውም ይሄው ነው። ካለዚያማ ወያኔን ሚዲያዎቹን
ልቀቅ! የሕዝብ ይሁኑ! ነጻነታቸው ይከበር! ጋዜጠኞች በነጻነት ይስሩ እያልን ስንጮህ የኖርነው
ለምንድን ነው?
እን አቤ ቶክቻውም በወያኔ ባልስልጣናት ላይ እየተሳለቁ የሚያቀርቡትን ቁምነገር አዘል ምክር
በግንቦት ሰባት አመራሮች እንዲሁም በራሱ በኢሳት ላይ እንዲያደርጉ መፈቀዱንም እጠራጥራለሁ፤
አላየሁም እና።
በቀጣይ ጽሑፌ እስከምንገናኝ ቸር እንሰብት!
እግዚያብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ እኛንም ልቦና ይስጠን!
ያሬድ ኃይለማርያም
ከብራስልስ

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 11 years ago on July 22, 2013
  • By:
  • Last Modified: July 22, 2013 @ 1:17 pm
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar