www.maledatimes.com በሰማያዊ ፓርቲ ላይ የተወሰደውን ህገ-ወጥርምጃ አጥብቀን እናወግዛለን!! - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

በሰማያዊ ፓርቲ ላይ የተወሰደውን ህገ-ወጥርምጃ አጥብቀን እናወግዛለን!!

By   /   September 3, 2013  /   Comments Off on በሰማያዊ ፓርቲ ላይ የተወሰደውን ህገ-ወጥርምጃ አጥብቀን እናወግዛለን!!

    Print       Email
0 0
Read Time:3 Minute, 47 Second

 

ከአንድነትለዴሞክራሲናፍትህፓርቲ (አንድት) የተሰጠጋዜጣዊመግለጫ

አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) ነሐሴ 26 ቀን 2005 á‹“.ም ሰማያዊ ፓርቲ የጠራውን ሰላማዊ ሰልፍ አስመልክቶ የተወሰደበትን ሕገ-ወጥ ርምጃ አጥብቀን የምንቃወም ሲሆን፤ ይህንን የፈፀሙ አካላትም በአስቸኳይ ለፍርድ እንዲቀርቡ እንጠይቃለን….

እንደሚታወቀው ሰማያዊ ፓርቲ ከአንድ ወር አስቀድሞ የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ መጥራቱን እንዳሳወቀ የሚታወስ ሲሆን በተመሳሳይ ቀንም የሀይማኖቶች ጉባኤ ሰላማዊ ሰልፍ መጥራቱ መገለፁ አደናጋሪ ነበር፡፡ ይህንን የሁለት አካላት የሰላማዊ ሰልፍ ጥያቄ በሰከነ መንገድ የአዲስ አበባ መስተዳድር መፍታት ሲገባው ችግሩ እንዲከር አድርጓል፡፡ ይህም የገዥው ፓርቲ የፖለቲካ ምህዳሩን የመዝጋትና የማናለብኝነት አንዱ መገለጫ ነው፡፡

ከዚህ በተጨማሪም ቅዳሜ ምሽት በሰማያዊ ፓርቲ አመራሮችና አባላት ላይ የተፈፀመው የሰብዓዊ መብት ጥሰት በሰላማዊ ትግሉ ላይ እየተፈፀመ ያለ ርምጃ ነው፡፡ የፀጥታ ሃይሎች የወሰዱት የማገት፣ የማፈንና የመደብደብ ርምጃ አሳፋሪ ሆኖ አግኝተነዋል፡፡ ፀጥታ አስከብራለሁ የሚለው የፖሊስ አካል መብትን በድብደባ ለማስቆም የሄደበት መንገድም ህገ-ወጥ ነው፡፡ ስለዚህ ፓርቲያችን አንድነት መንግስት እያካሄደ ያለውን የአፈናና የጉልበት ርምጃ አቁሞ አሁንም ለዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታና ለሰብዓዊ መብት መጠበቅ ቅድሚያ እንዲሰጥ ጥሪ እናቀርባለን፡፡ የኢትዮጵያ ህዝብም ህገወጥነትን መቃወሙን አጠናክሮ በመቀጠል የህግ የበላይነት እንዲረጋገጥ እየተካሄደ ያለውን ሰላማዊ ትግል እንዲደግፍ ጥሪ እናቀርባለን፡፡

ዘላለማዊ ክብር ለኢትዮጵያ!!!

አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ነሐሴ 27 ቀን 2005 ዓ.ም

አዲስ አባባ

About Post Author

Abby

Internet reporter, freelancer and webmaster.
Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 11 years ago on September 3, 2013
  • By:
  • Last Modified: September 3, 2013 @ 6:39 am
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

About the author

Internet reporter, freelancer and webmaster.

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar