www.maledatimes.com “አይ ሲ ጂ”መለስ መሞታቸውን “እኔ አላልኩም ስለ ጠቅላይ ሚኒስትራችሁ ሞትም ሆነ ህይወት የማውቀው ነገር የለም” ብሏል። - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

“አይ ሲ ጂ”መለስ መሞታቸውን “እኔ አላልኩም ስለ ጠቅላይ ሚኒስትራችሁ ሞትም ሆነ ህይወት የማውቀው ነገር የለም” ብሏል።

By   /   July 31, 2012  /   Comments Off on “አይ ሲ ጂ”መለስ መሞታቸውን “እኔ አላልኩም ስለ ጠቅላይ ሚኒስትራችሁ ሞትም ሆነ ህይወት የማውቀው ነገር የለም” ብሏል።

    Print       Email
0 0
Read Time:4 Minute, 9 Second

በትላንትናው እለት ኢሳት ራዲዮ “አይ ሲ ጂ” የተባለውን ተቋም ምንጮች ጠቅሶ መለስ መሞታቸውን አረጋግጫለሁ። ብሎ የዘገበ ዚሆን ዛሬ ደግሞ “አይ ሲ ጂ” በድረ ገፁ ላይ “እኔ አላልኩም ስለ ጠቅላይ ሚኒስትራችሁ ሞትም ሆነ ህይወት የማውቀው ነገር የለም” ብሏል።

ኢሳት ከ “ኤይ ሲ ጂ” በተጨማሪ ታማኝ የዲፕሎማት ምንጮችም ነግረውኛል “ሰውዬው ከዚህ በኋላ እቃ አይሆኑም አክትሞላቸዋል የርሳቸው ነገር ከእንግዲህ ኦሮማይ ነው!” ብሎ በልዩ የዘገባ ፕሮግራሙ ሲነግረን በአንክሮ ነበር።

ያው ትላንት እኔም ይሄንን ወሬ ሳቀብላችሁ እስቲ የአቅሜን ያኽል ወሬ ፍለጋ ዞር ዞር ብዬ አካፍላችኋለሁ ባልኩት መሰረት ስለቃቅም ካገኘሁት መሀከል፤ በትላንትናው እለት በራዲዮ ፋና ላይ “የህግ ጉዳይ” በሚወራበት ፕሮግራም ስለ ጠቅላይ ሚኒስትሩን ህመም እና በእንዲህ ያለው ጊዜ ማነው የሚተካቸው? የሚለው ጉዳይ ላይ በቀጥታ ስርጭት ውይይት ሲደረግበት እንደነበር “ሶሊያና” የተባለች ወሳኝ ወዳጃችን በፌስ ቡክ ግድግዳዋ ላይ ለጥፋልን ነበር። በነገራችን ላይ ይቺው ወዳጃችን ከዚህ በፊት ሚሚ ስብሀቱ “የመነኩሴዎች ፀሎት እያለ እሳቸውማ አይሞቱብንም” ብላ በራዲዮ ፕሮግራሟ ላይ መናገሯንም ነግራን ነበር። “ሶሊን” አመስግነን “ሚሚን” ደግሞ ቆይ እንገማገማለን! እንላታለን። የሆነ ሆኖ የሁለቱ ራዲዮ ጣቢያዎች እንደዚህ መብከንከን ስንሰማ “ኢሳትማ የሆነ የደረሰበት ነገር አለ” የሚያስብል ነው።

እና ወዳጄ፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አንዴ ሲሞቱ አንዴ ሲነሱ አንዴ ህክምና ላይ ሲሆኑ ሌላ ጊዜ እረፍት ሲያደርጉ እርሳቸው ጠቅላይ ሆነው ሳለ፤ ነገራቸው ግን አሁንም ድረስ አልተጠቀለለም ማለት ነው።

ድሮ አባቴ ሲያጫውተኝ በምድር ላይ ክፉ ስራ የሰራ ሰው ቶሎ አይሞትም ብሎ ነግሮኛል። “አልጋው ላይ ሆኖ ሞተ ሲባል ሲድን፣ ዳነ ሲባል ሲሞት፤ ሰውም ያንገላታል እርሱም ይሰቃያል”። ይለኝ ነበር። አባቴ በተለይ አራጣ አበዳሪዎች እንዲህ አይነት ስቃይ እንደሚገጥማቸው ነግሮኛል። እንዴት ነው ነገሩ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር አራጣ ያበድሩ ነበር እንዴ…!?

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 12 years ago on July 31, 2012
  • By:
  • Last Modified: July 31, 2012 @ 6:31 pm
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar