www.maledatimes.com የፀረሙስና ኮሚሽን ሠራተኞች የደመወዝና የጥቅማጥቅም ጥያቄያቸው ባለመመለሱ ቅሬታ ውስጥ ናቸው - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

የፀረሙስና ኮሚሽን ሠራተኞች የደመወዝና የጥቅማጥቅም ጥያቄያቸው ባለመመለሱ ቅሬታ ውስጥ ናቸው

By   /   October 23, 2013  /   Comments Off on የፀረሙስና ኮሚሽን ሠራተኞች የደመወዝና የጥቅማጥቅም ጥያቄያቸው ባለመመለሱ ቅሬታ ውስጥ ናቸው

    Print       Email
0 0
Read Time:5 Minute, 36 Second
 
(በጋዜጣው ሪፖርተር)
የፌዴራል የሥነምግባርና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን አንዳንድ ሠራተኞች ከክፍያና ጥቅማጥቅም ማነስ ጋር በተያያዘ በሥራቸው ደስተኛ አለመሆናቸውን ጠቆሙ።
ለጉዳይ ቅርበት ያላቸው ምንጮቻችን እንዳሉት የኮሚሽኑ የደመወዝ ስኬል፣ የትራንስፖርት እና የመኖሪያ ቤት አበል ክፍያ ሥርዓት የወቅቱን የኑሮ ውድነት ያላገናዘበ፣ ከሌሎች የመንግስት ተቋማት ጋር ሲነፃፀር አነስተኛ የሚባል መሆኑንና በራሱ በኮሚሽኑ ውስጥም በተመሳሳይ ደረጃ ላይ ሆነውም ከመምሪያ መምሪያ ልዩነት የሚታይበት መሆኑን ጠቅሰዋል።
ኮምሽኑ ሙስናን ያህል ትልቅና አስቸጋሪ ወንጀሎች እንዲከታተሉ፣ እንዲመረምር፣ እንዲያጠና፣ መቋቋሙን ያስታወሱት ሠራተኞች ሌላው ቀርቶ ተጠሪነቱ ለጠ/ሚኒስትሩ የሆነው የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ደመወዝ 10ሺ ብር እንኳን የማይሞላ መሆኑን፣ በዚህች አነስተኛ ደመወዝ ሰዎችን ከባድ ኃላፊነት እንዲወጡ መመደብ የቱን ያህል አስቸጋሪ መሆኑን አስረድተዋል።
በአሁኑ ወቅት እንደገቢዎች ጉምሩክ፣ እንደስኳር ኮርፖሬሽን፣ እንደንግድ ባንክና የመሳሰሉ የመንግሥት ተቋማት፣ የሠራተኞች የደመወዝና የጥቅማጥቅም ክፍያ ሥርዓት የወቅቱን የኑሮ ውድነት ባገናዘበ መልኩ ተጠንቶ ሥራ ላይ የዋለ በመሆኑ፣ በድርጅቶቹ ሠራተኞች ላይ ትልቅ መነቃቃት መፍጠሩን፣ ያስታወሱት ምንጮቻችን የፌዴራሉ የሥነምግባርና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ከዚህ አንፃር ተወዳዳሪ ሆኖ አለመገኘቱ ቀስበቀስ በሥሩ ያለውን የሰለጠነ የሰው ኃይል እንዳያሳጣውና ያለውም ለኪራይ ሰብሳቢነት ችግር እንዳይጋለጥ ሥጋት መኖሩን ጠቁሟል።
መንግሥት ሙስናና ኪራይ ሰብሳቢነትን ለመዋጋት ቁርጠኛ አቋም እንዳለው እየገለፀ ባለበት በዚህ ሰዓት ይህን ሥራ ለማከናወን ከፍተኛ ኃላፊነት የተጣለበት የፀረ-ሙስና ተቋም ሠራተኞች በሥራቸው ደስተኛ ያለመሆን በትግሉ ላይ የራሱ የሆነ አሉታዊ ተፅእኖ እንደሚኖረው ምንጮቻችን ኀሳባቸውን ሰጥተዋል።
በጉዳዩ ላይ ያነጋገርናቸው አንዳንድ የኮሚሽኑ ሠራተኞች ጉዳዩ በርግጥም የአብዛኛው ሠራተኛ (በተለይም የሰለጠኑ ከፍተኛ ባለሙያዎች) ጥያቄ መሆኑንና ችግሩ ከዛሬ ነገ ይፈታል በሚል በትእግስት ሲጠባበቁ መቆየታቸውን አስታውሰዋል። ሆኖም በአሁኑ ወቅት ምላሹ በመዘግየቱ በርካታ ሠራተኞች ተስፋ የቆረጡበት ሁኔታ በመኖሩ ብዙዎች የሚያስቡት ኮሚሽኑን ስለመልቀቅ ብቻ ሆኗል ብለዋል። በሥራ ላይ ያሉትም ሠራተኞች ከዚሁ ጋር በተያያዘ ቅሬታ ውስጥ መግባታቸው የሥራ ተነሳሽነታቸውን እየጎዳ ነው በማለት አስረድተዋል።
በጉዳዩ ላይ ኮሚሽነር ዓሊ ሱሌይማንን ለማነጋገር ባደረግነው ሙከራ ኮሚሽነሩ በዚህ ሣምንት ውስጥ ምላሽ መስጠት እንደማይችሉ በፀሐፊያቸው በኩል ገልጸውልናል።
Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 11 years ago on October 23, 2013
  • By:
  • Last Modified: October 23, 2013 @ 9:56 am
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar