www.maledatimes.com 2019 - MALEDA TIMES - Page 41
Loading...
You are here:  Home  >  2019  -  Page 41
Latest

የአርቲስቱ ጠላቱ ቲያትር ቤቱ በጌታቸው ታረቀኝ

By   /  January 7, 2019  /  Ethiopia  /  Comments Off on የአርቲስቱ ጠላቱ ቲያትር ቤቱ በጌታቸው ታረቀኝ

የአርቲስቱ ጠላቱ ቲያትር ቤቱ የ1966ቱ አብዮት የፈጠረዉ የባሕል ምኒስቴርም ሆነ አሁን ያለዉ የቲያትር ቤቶች አደረጃጀት፤ ለአርቲስቱም ሆነ ለጥበቡ ማደግ ያበረከቱት አስዋፅኦ ብዙም የሚባልለት አይመስለኝም፡፡ ቲያትር ቤቱ በአርቲስቱ የጥበብ ሥራ፤ ኪራይ ተቀባይ ከመሆን ያለፈ፤ የዉስጥ አሰራሩን አንኳ ብዙም መቀየር ያልቻለ ደካማ ተቋም በመሆኑ፤ የመድረክ መብራት፤ አርቲስቶች የሚቀባቡት /ሜክ አፕ/ ማቅረብ የማይችል፤ መብራት አምፑል ወይ መቆጣጣሪያዉ ጠፍቶ […]

Read More →
Latest

ሜቴክ የሰወረው ሌላ ስምንት ቢሊየን ብር አልተገኘም

By   /  January 7, 2019  /  Ethiopia  /  Comments Off on ሜቴክ የሰወረው ሌላ ስምንት ቢሊየን ብር አልተገኘም

ሜቴክ ለህዳሴው ግድብና ሌሎች ግንባታዎች 8 ቢሊየን ብር ለንግድ ባንክ ሳይከፍል በገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር ተያዥነት ሰውሮታል። ገንዘቡ የት ገባ? የሚለውን የሚመልስ አልተገኘም። በጉዳዩ ላይ ያለንን መረጃ አሰናድተናል ዋዜማ ራዲዮ- ብዙው ነገር የተፈጸመው በ2008 ዓ.ም ነው።የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን የህዳሴውን ግድብ ፕሮጀክትና ሌሎች የግንባታ ውል የወሰደባቸው ፕሮጀክቶች የክፍያ አካል የሆነውን ስምንት ቢሊየን ብር ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ […]

Read More →
Latest

በጉለሌና በቦሌ የግዴታ ጋብቻ በብዛት ይፈጸማል ሲሉ የኢንሽየቲቭ አፍሪካ ዳይሬክተር አቶ ክቡር ገና ገለጹ

By   /  January 7, 2019  /  Ethiopia  /  Comments Off on በጉለሌና በቦሌ የግዴታ ጋብቻ በብዛት ይፈጸማል ሲሉ የኢንሽየቲቭ አፍሪካ ዳይሬክተር አቶ ክቡር ገና ገለጹ

በአዲስ አበባ ከሚገኙ ክፍለ ከተሞች ውስጥ ጉለሌና ቦሌ የግዴታ ጋብቻ በብዛት እንደሚፈፀምባቸው ተገለጸ፡፡  ባለፈው ሐሙስ በኢንሽየቲቭ አፍሪካ አዘጋጅነት፣ “ለውጥን በመለወጥ መተግበር” በሚል መሪ ሃሳብ በሞዛይክ ሆቴል ለአንድ ቀን በተካሄደ ስብስባ ላይ 20 የሁለተኛ ደረጃና የልዩ ፍላጐት ትምህርት ቤቶች መምህራን፣ ርዕሰ መምህራንና ሴት ተማሪዎች ተሳትፈዋል፡፡ የኢንሽየቲቭ አፍሪካ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ክቡር ገና በስብሰባው ላይ እንደገለጹት፤ድርጅታቸው ከኢትዮጵያ […]

Read More →
Latest

በጌዲኦ፣ አዋሣ እና በጉጂ አካባቢ ግጭቶች 207 ሰዎች ተገድለዋል

By   /  January 7, 2019  /  Ethiopia  /  Comments Off on በጌዲኦ፣ አዋሣ እና በጉጂ አካባቢ ግጭቶች 207 ሰዎች ተገድለዋል

በኦሮሚያ ክልል በጉጂ ዞን የተለያየ አካባቢ እንዲሁም በደቡብ ክልል ጌዲኦ ዞንና በሃዋሳ በሲዳማና በወላይታ ብሔረሰብ መካከል ተፈጥረው የነበሩ ግጭቶችን በተመለከተ ምርመራ አከናውኖ ሪፖርት ያጠናቀረው የሰብአዊ መብቶች ጉባኤ (ሰመጉ)፤ በእነዚህ ግጭቶች በጠቅላላው 207 ሰዎች መገደላቸውንና አንድ ሚሊዮን ያህል ዜጎች መፈናቀላቸውን አረጋግጫለሁ ብሏል፡፡ በጌዲኦ ዞን ከሚያዚያ 25 ቀን 2010 እስከ ሚያዚያ 28 ቀን 2010 ዓ.ም በብሔር ተኮር ግጭት […]

Read More →
Latest

ፍትህን ያጡ ፍርደኞች ስለ ፍትህ ይጮሃሉ በዘለአለም ገብሬ እንደታ

By   /  January 6, 2019  /  Ethiopia  /  Comments Off on ፍትህን ያጡ ፍርደኞች ስለ ፍትህ ይጮሃሉ በዘለአለም ገብሬ እንደታ

ለአለፉት ፳፯ አመታት በህወሃት መንግስት ብዙ የህግ ጥሰት እንደተደረገ እናስታውሳለን ፣ ብዙዎቻችን ባልሰራነው እና ባላጠፋነው ጥፋት ወንጀለኞች ተብለን ተከሰናል ፣ እንኳን እኛ ልንፈጽመው እና ሰው ሌሎች ቸካኝ ሰዎች ሲፈጽሙት የሚዘገንኑን ወንጀሎች ሲፈጸሙ እንዴት እንደሚያመን ልብ ይሏል። ለምሳሌ ሃገራችንን የምንወድ ዜጎች ሁሉ ሃገራችንን ለማንም አሳልፈን መስጠት እንደማንችል ከአያት ቅድመ አያቶቻችን ተምረናል ወርሰናል ፣ ሆኖም ግን ወያኔ […]

Read More →
Latest

ለህዳሴ ግድቡ ግንባታ 98.7 ቢሊዮን ብር ወጪ መደረጉ ተገለጸ

By   /  January 6, 2019  /  Ethiopia  /  Comments Off on ለህዳሴ ግድቡ ግንባታ 98.7 ቢሊዮን ብር ወጪ መደረጉ ተገለጸ

ለኃይድሮሊክ ስትራክቸር ሥራው የ126 ሚሊዮን ዶላር ስምምነት ተፈረመ የዛሬ ሰባት ዓመት ገደማ ግንባታው የተጀመረው ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የፕሮጀክትና የፋይናንስ አስተዳደር፣ እንዲሁም ወለድና የእርጅና ወጪ ጨምሮ በአጠቃላይ 98.7 ቢሊዮን ብር ወጪ መደረጉን የውኃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ስለሺ በቀለ (ዶ/ር) ተናገሩ። የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የህዳሴ ግድቡ ግንባታና አጠቃላይ ሁኔታዎችን የተመለከተ ሪፖርት እንዲቀርብለት ባዘዘው መሠረት፣ ሚኒስትሩና […]

Read More →
Latest

የኢትዮ ቴሌኮም የቀድሞ ዳይሬክተር የተጠረጠሩበት የ44.5 ሚሊዮን ዶላር ግዥ ውድቅ ተደረገ

By   /  January 6, 2019  /  Ethiopia  /  Comments Off on የኢትዮ ቴሌኮም የቀድሞ ዳይሬክተር የተጠረጠሩበት የ44.5 ሚሊዮን ዶላር ግዥ ውድቅ ተደረገ

የዓለም ገነት ቆርቆሮ ባለቤት የክስ መመሥረቻ ጊዜ ተራዘመ በሶማሌ ክልልና በባሌ ዞን የሞባይልና ሲዲኤምኤ (የቴሌ ታወር ሥራዎች) ግንባታን በጥቅም ተመሳጥረው ያለ ጨረታ ለሜቴክ ሰጥተዋል ተብለው በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው በእስር ላይ የሚገኙት የኢትዮ ቴሌኮም የኤንጂፒኦ የቀድሞ ዳይሬክተር፣ ከዩኒቨርሲቲዎች ኔትወርክ ግንባታ ጋር በተያያዘ ቀርቦባቸው የነበረው የ44.5 ሚሊዮን ዶላር ግዥ ውድቅ ተደረገ፡፡ የፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቡድን ተጠርጣሪው […]

Read More →
Latest

ሕወሓት ሰሞኑን የተሰበሰበው መደበኛ የሥራ አፈጻጸም ግምገማ ለማድረግ እንደሆነ ተገለጸ

By   /  January 6, 2019  /  Ethiopia  /  Comments Off on ሕወሓት ሰሞኑን የተሰበሰበው መደበኛ የሥራ አፈጻጸም ግምገማ ለማድረግ እንደሆነ ተገለጸ

የህወሃት ድክመት እምኑ ላይ እንደሆነ ማወቅ ተስኖታል!! አቶ ጌታቸው አሰፋን የተመለከተ አጀንዳ አልነበረም የሕወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ ሰሞኑን የተሰበሰበው መደበኛውን የሥራ አፈጻጸም ግምገማ ለማድረግ ሲሆን፣ በዚህም መሠረት የክልሉ መንግሥት ካለፈውሐምሌ ወር 2010 ዓ.ም. ወዲህ ባሉት ጊዜያት ያከናወናቸውን ሥራዎች እንዲሁም ፀጥታና ደኅንነትን በተመለከቱ ጉዳዮች ላይ ግምገማ ማድረጉን የድርጅቱሥራ አስፈጻሚ አባል አቶ ጌታቸው ረዳ ለሪፖርተር ገለጹ። ሕወሓት ለሁለት ቀናት ያካሄደውን ስብሰባ ባለፈው ዓርብ አጠናቋል። ይህ ስብሰባ የተለየ አለመሆኑን የተናገሩት አቶ ጌታቸው ረዳ፣ በፓርቲ ደረጃ በመገናኘትየክልሉን መንግሥት የሥራ አፈጻጸምና ወቅታዊ ሁኔታዎች ከተገመገሙ ቆየት በማለቱ የተጠራ ስብሰባ ቢሆንም የተለመደ የፓርቲ ሥነ ሥርዓት መሆኑንምአመልክተዋል። በዚህ ስብሰባ የክልሉ መንግሥት ባለፉት ወራት ያከናወናቸው የልማትና የማኅበራዊ ጉዳዮች ሲገመገሙ፣ በተጨማሪም በወቅታዊ የፀጥታና ደኅንነት ጉዳዮችላይ ውይይት መካሄዱን ተናግረዋል። አቶ ጌታቸው ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ የሕወሓት ዋነኛ መወያያ አጀንዳ ባይሆንም ከወራት በፊት የተከፈተው የኢትዮ ኤርትራ ድንበር በቅርቡ የተዘጋበት ምክንያትምን እንደሆነ የክልሉ ምክትል ፕሬዝዳንትና የሕወሓት ሊቀመንበር ደብረጽዮን ገብረ ሚካኤል (ዶ/ር) ማብራሪያ እንዲሰጡበት ጥያቄ ቀርቦላቸው ነበር። ጉዳዩ በቀጥታ የፌዴራል መንግሥትን የሚመለከት ቢሆንም፣ ጉዳዩን የክልሉ ምክትል ፕሬዚዳንት እንዲከታተሉት ማዕከላዊ ኮሚቴው መስማማቱን ገልጸዋል። በክልሉ የፀጥታና ደኅንነት ጉዳዮች እንዲሁም በአገር ደረጃ የሚስተዋለው የፀጥታ ችግርን በተመለከተ ውይይት መደረጉን የገለጹት አቶ ጌታቸው ረዳ፣ ምንምእንኳን ሕወሓት በአገር አቀፍ ደረጃ ያለው ሚና ትንሽ ቢሆንም ከፌዴራል መንግሥት ጋር በመተባበር ኃላፊነቱን እንዲወጣ መወሰኑን ተናግረዋል። የፌዴራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ በዚህ ሳምንት ለፓርላማ ባቀረበው ሪፖርት በከባድ የሰብዓዊ መብት ወንጀል የተጠረጠሩት የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት የቀድሞ ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው አሰፋ በቁጥጥር ሥር ለማዋል ለትግራይ ክልል ጥያቄ ቢቀርብም ክልሉ ለመተባበር ፈቃደኛ አለመሆኑና የክልሉ አመራር አቶጌታቸውንም ሆነ ሌሎች ተጠርጣሪዎችን ሸሽጓል በማለት ዋና ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ አቶ ብርሃኑ ጸጋዬ ተናግረው ነበር። የሕወሓት ስብሰባ ከዚህ ወቀሳ በኋላ የተካሄደ በመሆኑ የአቶ ጌታቸው ጉዳይ የውይይቱ አካል ይሆናል የሚል ግምት በበርካቶች ዘንድ ነበር። የአቶ ጌታቸው አሰፋን ጉዳይ የተመለከተ ውይይት ተካሄዶ እንደሆነ የተጠየቁት አቶ ጌታቸው ረዳ፣ በዚህ ጉዳይ ላይ ውይይት አለመደረጉንና ፓርቲው በጉዳዩላይ ሊወያይም እንደማይችል ተናግረዋል። አቶ ጌታቸው አሰፋ የሕወሓት ሥራ አስፈጻሚ አባል መሆናቸው ይታወቃል፡፡ ነገር ግን በዚህ የሕወሓት ስብሰባ ላይ አለመገኘታቸውን ሪፖርተር ከአቶ ጌታቸው ረዳለማረጋገጥ ችሏል። በኢሕአዴግ መተዳደሪያ ደንብ መሠረት የኢሕአዴግ ሥራ አስፈጻሚ በየሦስት ወሩ፣ ማዕከላዊ ኮሚቴው ደግሞ በየስድስት ወሩ መገናኘት እንዳለበት ቢደነግግም፣ አስቸኳይ ሁኔታዎች ሲኖሩ ሊጠራ እንደሚችል ይደነግጋል። ይሁን እንጂ ሥራ አስፈጻሚው ከተሰበሰበ ቆይቷል። ይህ ጉዳይ በሕወሓት የሰሞኑ ስብሰባ ተነስቶ እንደሆነ የተጠየቁት አቶ ጌታቸው፣ ‹‹አልተነሳም። ሕወሓትበዚህ ጉዳይ ለምን ይወያያል? ስብሰባውን መጥራት ያለበት የኢሕአዴግ ሊቀመንበር ነው፤›› ብለዋል። ነገር ግን የአገሪቱ ወቅታዊ የፀጥታና የደኅንነት ጉዳዮች በኢሕአዴግ ደረጃ ውይይት ሊደረግባቸው እንደሚገባ የተናገሩት አቶ ጌታቸው ረዳ፣ ‹‹ኢሕአዴግበቅርቡ ስብሰባ ካልጠራ በእኛ በኩል ስብሰባ እንዲጠራ ጥያቄ ልናቀርብ እንችላለን፤›› ብለዋል። በማኅበራዊ ትስስር ገጾች የሕወሓት ሊቀመንበር ከኃላፊነት ለመልቀቅ ጥያቄ አቅርበው እንደነበር የሚወራውንም አስተባብለዋል።

Read More →
Latest

የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ያልተለመዱ አሠራሮች ተግባራዊ ይደረጋሉ አሉ

By   /  January 6, 2019  /  Ethiopia  /  Comments Off on የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ያልተለመዱ አሠራሮች ተግባራዊ ይደረጋሉ አሉ

የአዲስ አበባ ከተማን ቁልፍ ከተረከቡ በኋላ ሪፖርታቸውን ለመጀመርያ ጊዜ ለምክር ቤት ያቀረቡት ምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ (ኢንጂነር)፣ በከተማው በ27 ዓመታት ያልተለመዱ አሠራሮች ተግባራዊ መሆናቸውንና ወደፊትም እንደሚቀጥሉ አስታወቁ፡፡ ምክትል ከንቲባው በተለይ በመታወቂያ አሰጣጥ፣ በመኖሪያ ቤት አቅርቦት፣ በመልሶ ማልማት ፕሮግራሞች፣ በገቢ አሰባሰብ፣ በውኃ አቅርቦት፣ በወጣቶችና በአረንጓዴ ልማት ሥራዎች አስተዳደሩ የሚከተለውንና እየተከተለ ያለውን አዳዲስ አሠራሮች በጥልቀት አብርተዋል፡፡ ምክትል […]

Read More →
Latest

በሃሰተኛ ክስ ልጃቸውን ገድለዋል ተብለው እድሜ ልክ የታሰሩት ታራሚ ህይወታቸው አለፈ በዘለአለም ገብሬ እንደታ

By   /  January 5, 2019  /  Ethiopia  /  Comments Off on በሃሰተኛ ክስ ልጃቸውን ገድለዋል ተብለው እድሜ ልክ የታሰሩት ታራሚ ህይወታቸው አለፈ በዘለአለም ገብሬ እንደታ

ለእረጅም ዘመናት የህይወት ጊዜአቸውን በእስር ያደረጉት እና ያለምንም ጥፋታቸው በፍትህአብሔር ክስ የተመሰረተባቸው የሰማኒያ አመቱ አዛውንት ከእረጅም የእስርቤት ስቃይ እና መከራ በኋላ በዛሬው እለት ህይወታቸው ማለፉን ከማረሚያ ቤት የደረሰን መረጃ ያመለክታል። እንደ መረጃ ዘገባው ከሆነ አዛውንቱ ምንም በማያውቁት እና በአልተረዱት ሁኔታ ልጃቸው በድንገት ሲያልፍ እርሳቸው ቀጥቅጠው እንደገደሉት አድርገው ፖሊሶች የክስ መዝገብ በማቅረባቸው ምክንያት ወንጀሉ በከፍተኛ ፍርድ […]

Read More →
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar