www.maledatimes.com 2019 - MALEDA TIMES - Page 42
Loading...
You are here:  Home  >  2019  -  Page 42
Latest

ፍርድ ቤቶች ነፃና ገለልተኛ ሆነው መሥራት አለመቻላቸውን ፕሬዚዳንቷ ተናገሩ

By   /  January 5, 2019  /  Ethiopia  /  Comments Off on ፍርድ ቤቶች ነፃና ገለልተኛ ሆነው መሥራት አለመቻላቸውን ፕሬዚዳንቷ ተናገሩ

በሶማሌ ክልል የዳኞች አስተዳደር ጉባዔ ሰብሳቢ የክልሉ ፕሬዚዳንት ነበሩ የፌዴራልም ሆኑ የክልል ዳኞች የሕግ የበላይነትን ለማስከበር በሕገ መንግሥቱ ከፍተኛ ኃላፊነት የተጣለባቸው ቢሆንም፣ የዳኝነት ነፃነታቸው በአስፈጻሚውና በሌሎች አካላት ጣልቃ ገብነት ምክንያት በመገደቡ ገለልተኛ እንዳልነበሩ፣ ዜጎችም በዳኝነት አካሉ ላይ አመኔታ እንዳይኖራቸው ማድረጉን የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ተናገሩ፡፡ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በዳኝነት ሥራ አስተዳደር የሚያጋጥሙ ውስጣዊና […]

Read More →
Latest

ሰማያዊ ፓርቲ ራሱን አከሰመ

By   /  January 5, 2019  /  Ethiopia  /  Comments Off on ሰማያዊ ፓርቲ ራሱን አከሰመ

እሑድ ታኅሳስ 21 ቀን 2011 ዓ.ም. የሰባተኛ ዓመት ምሥረታ በዓሉንና  ጠቅላላ ጉባዔውን ያከናወነው ሰማያዊ ፓርቲ ዜግነት ላይ አትኩሮት በማድረግ ለሚቋቋመው ፓርቲ ምሥረታ ይረዳ ዘንድ ራሱን በማክሰም፣ እንደ አዲስ ከሌሎች ፓርቲዎች ጋር ውህደት ለመፍጠር መወሰኑን አስታወቀ፡፡ የሰማያዊ ፓርቲ መክሰምን ውሳኔ አስመልክቶ ሰኞ ታኅሳስ 22 ቀን 2011 ዓ.ም. መግለጫ የሰጡት አመራሮቹ፣ አንድ ትልቅ አገራዊ ፓርቲ መፍጠር በማስፈለጉ […]

Read More →
Latest

ሰላም ለማስፈን ከፖለቲካ ድርጅቶች ይልቅ ሕዝቡ እንዲሳተፍ ተጠየቀ

By   /  January 5, 2019  /  Ethiopia  /  Comments Off on ሰላም ለማስፈን ከፖለቲካ ድርጅቶች ይልቅ ሕዝቡ እንዲሳተፍ ተጠየቀ

በአገሪቱ ሰላምን ለማስፈን በሚካሄደው እንቅስቃሴ ውስጥ ከፖለቲካ ድርጅቶች ይልቅ ሕዝቡን ማሳተፍ እንደሚያስፈልግ፣ ሕዝቡን ያላሳተፈ እንቅስቃሴም ወደ ውድቀት ሊያመራ እንደሚችል የአማራ ህልውና ለኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (አህኢድ) አስታወቀ፡፡ የመላው አማራ ሕዝብ ድርጅት (መአሕድ) እና የአማራ ህልውና ለኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (አህኢድ) በጋራ ለመሥራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ሰነድ ሰኞ ታኅሳስ 22 ቀን 2011 ዓ.ም. መፈረማቸውን አስመልክተው የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል […]

Read More →
Latest

የሃይማኖት መሪዎችና የአገር ሽማግሌዎች የአገሪቱ ሰላም ከምንጊዜውም በላይ አስጨንቆናል አሉ

By   /  January 5, 2019  /  Ethiopia  /  Comments Off on የሃይማኖት መሪዎችና የአገር ሽማግሌዎች የአገሪቱ ሰላም ከምንጊዜውም በላይ አስጨንቆናል አሉ

በኢትየጵያውያን ወንድማማቾች መካከል አለመከባበርና አለመተማመን የሚፈጥሩ ተጨባጭ ችግሮች እየታዩ ከመሆናቸውም ባለፈ፣ በአንዳንድ አካባቢዎች የእርስ በርስ ዕልቂት የሚያስከትሉ ግልጽ የወጡ ግጭቶች እየታዩ መሆኑንና ሁኔታው ከምንጊዜውም በላይ በአሁኑ ወቅት እያስጨነቃቸው እንደሆነ የሃይማኖት መሪዎችና የአገር ሽማግሌዎች ተናገሩ፡፡ የሃይማኖት መሪዎችና የአገር ሽማግሌዎች በአሁኑ ጊዜ በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች በተለይም በምዕራብና በምሥራቅ ኦሮሚያ፣ በጋምቤላ፣ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ፣ በሶማሌ፣ በአፋር፣ በትግራይና በአማራ ክልሎች […]

Read More →
Latest

የ48 ሺሕ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ግንባታ ሳይጀመር ግማሽ ዓመት ተጠናቀቀ

By   /  January 5, 2019  /  Ethiopia  /  Comments Off on የ48 ሺሕ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ግንባታ ሳይጀመር ግማሽ ዓመት ተጠናቀቀ

በተያዘው የበጀት ዓመት በአዲስ አበባ ከተማ 48 ሺሕ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ግንባታ እንደሚጀመር ቢታቀድም፣ ግንባታው ሳይጀመር የበጀት ዓመቱ የመጀመርያው ስድስት ወራት ተጠናቀቁ፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ የቤቶቹን ግንባታ ለማካሄድ አቅዶ የነበረው በቦሌ ክፍለ ከተማ፣ በቦሌ አራብሳ፣ በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ፣ በኮዬ ፊጬ አካባቢዎች በሚገኙ ስምንት ሳይቶች ነበር፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ ቤቶች ልማትና […]

Read More →
Latest

የትምባሆ የአልኮልና የመድኃኒት ቁጥጥር አዋጅ የበለጠ ጥብቅ እንዲሆን ጤና ጥበቃ ሚኒስትሩ ጠየቁ

By   /  January 5, 2019  /  Ethiopia  /  Comments Off on የትምባሆ የአልኮልና የመድኃኒት ቁጥጥር አዋጅ የበለጠ ጥብቅ እንዲሆን ጤና ጥበቃ ሚኒስትሩ ጠየቁ

የትምባሆ፣ የአልኮል፣ የመድኃኒትና ምግብ ነክ ምርቶችን ለመቆጣጠር ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቀረበው ረቂቅ አዋጅ የበለጠ ጥብቅ እንዲሆን የጤናጥበቃ ሚኒስትሩ ምክር ቤቱን ጠየቁ። የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሕፃናት ወጣቶችና ማኅበራዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ረቂቅ አዋጁን በዝርዝር ለመመርመር ዛሬ ረቡዕ ታኅሳስ 24 ቀን 2011 ዓ.ም. ባካሄደው ሕዝባዊ የውይይት መድረክ ላይ የጤና ጥበቃ ሚኒስትሩ ዶ/ር አሚር አማን በረቂቅ አዋጁ ላይ የተቀመጡ ክልከላዎች በቂ አለመሆናቸውንበመገንዘብ ክልከላዎቹ የበለጠ ጥብቅ እንዲሆኑ የማሻሻያ ሐሳብ ለቋሚ ኮሚቴው አቀረቡ። ካቀረቧቸው ጥብቅ የማሻሻያ ክልከላዎች መካከል እንደ ቢራ ያሉ የአልኮል ምርቶች በኤሌክትሮኒክ ሚዲያዎች ማለትም በሬዲዮና በቴሌቪዥን ከምሽቱ 3፡00ሰዓት እስከ ሌሊት 12፡00 ሰዓት ብቻ እንዲተዋወቁ በረቂቁ ላይ የተቀመጠው ድንጋጌ ተሻሽሎ፣ የአልኮል ምርቶች በተጠቀሱት ሚዲያዎች ሙሉ ለሙሉእንዳይተዋወቁ ክልከላ እንዲጣል የሚል የማሻሻያ ሐሳብ አቅርበዋል።  የአልኮል ምርቶች ማለት የአልኮል ይዘታቸው ከሁለት በመቶ በላይ መሆኑን የሚገልጸው የረቂቅ አዋጁ ትርጓሜ ተሻሽሎ የአልኮል ይዘቱ ከ0.5 በመቶ በላይበሚል እንዲሻሻልም የጠየቁ ሲሆን፣ ለዚህ ያቀረቡት ምክንያትም አልኮል የሚያመርቱ ኩባንያዎች ከሁለት በመቶ በታች የሆኑ የአልኮል ምርት ዓይነቶችንበማምረት የአልኮል መጠጦች በተጠቀሱት ሚዲያዎች እንዲተዋወቁ ዕድል የሚሰጥ በመሆኑ ነው። የአልኮል መጠጦችን ለማስተዋወቅና ገበያውን ለማስፋት ከፍተኛ ሽልማቶችን የሚያስገኙ ዕጣዎችን በቆርኪ ላይ ማያያዝ ክልከላ እንዲደረግበትም ሐሳብአቅርበዋል። ሚኒስትሩ እነዚህ ጥብቅ ማሻሻያዎች እንዲደረጉ ቋሚ ኮሚቴውን በጽሑፍ መጠየቃቸውን ተናግረዋል። ሚኒስትሩ ይህንን የተናገሩት በሕዝባዊ ውይይትመድረኩ ላይ የተገኙ የጤና ባለሙያዎች፣ ታዋቂ አርቲስቶች፣ ወጣት ተማሪዎችና ሌሎች ባለድርሻዎች ረቂቅ አዋጁ የበለጠ ጥብቅ እንዲሆንና የአልኮልማስታወቂያ እንዲቆም በተደጋጋሚ በመጠየቃቸው ነው።  የትምባሆና አልኮል ሽያጭን በተመለከተ ረቂቅ ሕጉ ላይ ሁለቱም ምርቶች ከ18 ዓመት ዕድሜ በታች እንዳይሸጡ የሚደነግገው አንቀጽ ተሻሽሎ ከ21 ዓመትበታች እንዲባል ጠይቀዋል። ይኼን ሐሳብም በሕዝባዊ የውይይት መድረኩ ላይ የተገኙት አብዛኞቹ ደግፈውታል። የኢትዮጵያ ትምባሆ ኢንተርፕራይዝ የሥራ ኃላፊዎች በውይይት መድረኩ ላይ ተገኝተው ረቂቅ የቁጥጥር ሕጉ በኩባንያው ላይ ሊያደርስ ይችላል ያሏቸውንሥጋቶች አንስተዋል። ካነሷቸውም ሥጋቶች መካከል ዋነኛው በረቂቁ የተቀመጡ የቁጥጥር ሕጎች የኮንትሮባንድ የሲጋራ ንግድን ያበረታታል የሚል ነው። ይኼም ከሥጋት ባለፈተጨባጭ መሆኑን ለማስረዳት በአሁኑ ወቅት እንኳን የአገሪቱ የሲጋራ ገበያ 44 በመቶው በኮንትሮባንድ በሚመጡ ምርቶች የተያዘ መሆኑን አንስተዋል። የጤና ጥበቃ ሚኒስትሩ በዚህ ጉዳይ ላይ በሰጡት ምላሽ አጠቃላይ የኮንትሮባንድ ንግድን በተመለከተ መንግሥት ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ መሆኑንጠቅሰው፣ የሲጋራ ኮንትሮባንድ ንግድን በተመለከተ ግን የትምባሆ አምራች ኩባንያዎች ጥብቅ የቁጥጥር ሕግ መንግሥታት እንዳያወጡባቸው ሲሉ ራሳቸውየኮንትሮባንድ የሲጋራ ንግድ እንዲስፋፋ በማድረግ አልያም መስፋፋቱን በመደገፍ መንግሥት የቁጥጥር ሕግ ቢያወጣ ኮንትሮባንድ እንዲስፋፋ ከማድረግየዘለለ ትርጉም እንደማይኖረው ለማስመሰል እንደሚሞክሩ ለመድረኩ አስረድተዋል። ከመድኃኒት አስመጪዎችም በርከት ያሉ ሥጋቶች የተነሱ ሲሆን፣ ቋሚ ኮሚቴው የተነሱትን በግብዓትነት ወስዶ ተጨማሪ የውይይት መድረክ መጥራት አስፈላጊመሆኑን ካመነበት የሚከለክለው ነገር ባለመኖሩ ሊጠራ እንደሚችል ገልጿል። ይሁን እንጂ ረቂቅ አዋጁ የንግድ ጥቅማቸውን የሚነካባቸውም ሆኑ ሌሎች ለቋሚ ኮሚቴው አመራሮችና አባሎች በግል ስልካቸው ላይ በመደወል ማስቸገርእንደሌለባቸውና ተግባሩ እንዲቆም አሳስበዋል።

Read More →
Latest

አርበኛ፣ ፀሐፊ- ተውኔት፣ ደራሲ፣ የመጀመሪያዋ ሴት የፓርላማ ተመራጭ እና ዲፕሎማት- ወይዘሮ ስንዱ ገብሩ

By   /  January 4, 2019  /  Ethiopia  /  Comments Off on አርበኛ፣ ፀሐፊ- ተውኔት፣ ደራሲ፣ የመጀመሪያዋ ሴት የፓርላማ ተመራጭ እና ዲፕሎማት- ወይዘሮ ስንዱ ገብሩ

በሸዋ ክፍለ ሀገር በመናገሻ አውራጃ በአዲስ ዓለም ከተማ ጥር 6 ቀን 1908 ዓ.ም ተወለዱ። አባታቸው ታዋቂው ዲፕሎማት፣ የመጀመሪያ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምክትል ፕሬዘደንት፤ ጣሊያኖች ከኢትዮጵያ ከወጡ በኋላ ደግሞ የምክር ቤቱ ፕሬዘደንት ፤በዳግማዊ ምኒልክ ሹመትም የመጀመሪያው የጎንደር ከተማ አስተዳዳሪ የነበሩት ከንቲባ ገብሩ ደስታ ሲሆኑ ታናሽ እህታቸው ደግሞ የውብዳር ገብሩ (እማሆይ ጽጌ ማርያም) ናቸው። ዕድሜያቸው ለትምህርት […]

Read More →
Latest

በአዲስ አበባ የመሶብ ቅርፅ ያለው ባለ 70 ወለል ሕንፃ ሊገነባ ነው

By   /  January 4, 2019  /  Ethiopia  /  Comments Off on በአዲስ አበባ የመሶብ ቅርፅ ያለው ባለ 70 ወለል ሕንፃ ሊገነባ ነው

እስከ ስድስት ዓመት ድረስ ይገነባል የተባለው ሕንፃ ባለቤት የባሕልና ቱሪዝም ሚንስቴር ሲሆን፣ የመሶብ ቅርጹ የተመረጠው የኢትዮጵያዊያንን የአብሮነት፣ የመሰባሰብ፣ የጋራ ደስታና ቃልኪዳን ምሳሌነትን ይወክላል በሚል ነው ተብሏል።ሚንስቴሩ የሚያሠራው ባለ 70 ወለል ሕንፃ 250 ሜትር ከፍታ እንደሚኖረው ተነግሯል። ይሕም በምሥራቅ አፍሪካ ረጅሙ ሕንፃ ሊያደርገው እንደሚችል ተገምቷል። ለግንባታውም ከ50 ሺሕ ካሬ ሜትር በላይ ቦታ ይፈለጋል የተባለ ሲሆን ሕንጻው […]

Read More →
Latest

የማዕድንና ነዳጅ ሥራን የሚያግዙ ‹ድሮኖች› አገልግሎት ላይ ሊውሉ ነው

By   /  January 4, 2019  /  Ethiopia  /  Comments Off on የማዕድንና ነዳጅ ሥራን የሚያግዙ ‹ድሮኖች› አገልግሎት ላይ ሊውሉ ነው

2019-01-03Author: አዲስ ማለዳ የማዕድንና ነዳጅ ሥራን የሚያግዙ ‹ድሮኖች› አገልግሎት ላይ ሊውሉ ነው የማዕድን እና ነዳጅ ሚኒስቴር ለማዕድን አሰሳ እና በቅርቡ ለሚጀምረው የኢቲዮ-ጅቡቲ የተፈጥሮ ጋዝ ቱቦ ዝርጋታ ድሮን መጠቀም እንደሚጀምር አስታወቀ።ሚንስቴሩ በአንዳንድ ቦታዎች ላይ የሚታየው አስቸጋሪ መልክዓ ምድር የማዕድን አለኝታ ቦታዎችን ለመለየት ስላስቸገረኝ የድሮን ቴክኖሊጂን ልጠቀም ነው ብሏል።በቅርቡ ለሚጀምረው የተፈጥሮ ጋዝ ቱቦ ዝርጋታም ድሮኖችን ለመጠቀም ከኢኖቬሽን […]

Read More →
Latest

ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ አዲስ መተግበሪያን ይፋ አደረገ

By   /  January 4, 2019  /  Ethiopia  /  Comments Off on ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ አዲስ መተግበሪያን ይፋ አደረገ

አዲስ ማለዳhttp://WWW.MALEDATIMES.Com ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የኅብረተሰቡን ተደራሽነትን ለማስፋት አዲስ መተግበሪያን ዓርብ፣ ታኅሣሠ 19 ይፋ አደረገ።አዲሱ የመረጃ ቋትን የያዘው መተግበሪያ በሕግና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ መረጃዎችን ለማግኘት ጉልህ አስተዋፅኦ ያደርጋል የሚል ተስፋም ተጥሎበታል። መተግበሪያው ከ1934 እስከ 2010 ድረስ ያሉ ሕጎችን፣ አዋጆችን፣ ደንቦችንና የሰበር ውሳኔዎችን አካቶ የያዘ የመረጃ ቋት ነው ተብሏል። ይህ መተግበሪያ የበይነ መረብ አገልግሎት በማይገኝባቸው ቦታዎችም […]

Read More →
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar