www.maledatimes.com ድምጻዊት መኪያ በሃይሉ አረፈች - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

ድምጻዊት መኪያ በሃይሉ አረፈች

By   /   December 24, 2013  /   Comments Off on ድምጻዊት መኪያ በሃይሉ አረፈች

    Print       Email
0 0
Read Time:4 Minute, 31 Second

ሸማመተው በሚለው ሙዚቃዋ በአጭር ጊዜ ተደማጭነትን ያተረፈችው ድምጻዊት መካያ በሃይሉ ከዚህ አለም በሞት ተለየች ።ድምፃዊ ሚካያ በሀይሉ ትናንት ማምሻውን ከዚህ ዓለም በሞት ተለይታለች። ድምፃዊቷ ለሶስት ሳምንት በህመም ላይ ቆይታ ትናንት ምሽት ህመሟ ፀንቶ ወደ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ብትወሰድም አርፋለች።

የ37 ዓመቷ ድምፃዊ ሚኪያ የአንዲት ሴት ልጅ እናት ነበረች።
የማለዳ ታይምስ መረጃ ማእከል የማጣራቱን ስራ ሲያካሂድ የቆየ ቢሆንም በኢትዮጵያ ኢትዮጵካን ሊንክ የተሰኘው መረጃ ማእከል በፌስ ቡክ ገጹ ላይ ማስፈሩን  እና እውነት መሆኑን ለህዝብ ገልጾአል ። ሙሉ መረጃውን በቅርቡ እናደርሳለን ።በማጣራት ለምታደርጉ ሁሉ በፌስ ቡክ ፔጅ ላይ ይህንን ሊንክ በመጫን መመልከት ይችላሉ::

መካያ በሃይሉ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እየተማረች ሸማመተው የሚለውን አልበሟን መስራቷ ይታወቃል ።በ2010 በደቡብ አፍሪካ በየአመቱ በሚካሄደው የኮራ አዋርድ ሽልማት ላይ ለውድድር ቀርባ እስከፍጻሜው ድረስ የባለ ጥሩ ደረጃ ተፎካካሪ ተብላ በጉጉት የአሸናፊነቱን ስፍራ ትይዛለች ተብሎ የተጠበቀላት ወጣ የነበረች ሲሆን በአጋጣሚ የሌላ አገር ዜጋ የሆኑ ሁለት ድምጻያኖች ባቀረቡት የልዩ ተሰጥኦ መበለጧ ይታወቃል ሆኖም ግን ላንተ ስል፣ ሸማመተው ፣የማነህ ቀብራራ የተሰኙት ስራዎቿ በሰው ልብ ጠልቀው የገቡ ሲሆን ከፍተኛ ተወዳጅነትንም ከማግኘት በላይ በብዙሃኑ ዘንድ ተደማጭነትንም አግኝታ የነበረች ታዳጊ ወጣት ድማጻዊ ነበረች ፣“ሸማመተው” ከሚለው አልበሟ በተጨማሪም ሌሎች ነጠላ ዜማዎች ያሏት ሲሆን፥ ግጥምና ዜማም ትደርሳለች።

ድምፃዊቷ በቤቴልሄም አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እና በአብዮት ቅርስ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ትምህርቷን የተከታተለች ሲሆን፥ የመጀመሪያ ድግሪዋን ባገኘችበት አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲም የሁለተኛ ድርጊዋን ወደ ማጠናቀቁ ተቃርባም ነበር።

ከቤተሰቦቿ እንደተረዳነው የድምፃዊቷ የቀብር ስነ ስርዓት በለቡ መካነ መቃብር ዛሬ ከቀኑ 9:00 ሰዓት ላይ ይፈፀማል።ነፍሷን በገነት ያኑርልን ለቤተሰቦቿ መጽናናትን እንመኛለን

Another Tragedy, Another Sensational Singer, Mikaya Behailu Passed Away. Rest In Peace.
Photo: Another Tragedy, Another Sensational Singer, Mikaya Behailu Passed Away. Rest In Peace.

 

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 10 years ago on December 24, 2013
  • By:
  • Last Modified: December 25, 2013 @ 12:17 am
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar