www.maledatimes.com አዲሱ 2014 አመት በዱባይ ፣ በባህሬንና በሳውዲ … ! - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

አዲሱ 2014 አመት በዱባይ ፣ በባህሬንና በሳውዲ … !

By   /   December 31, 2013  /   Comments Off on አዲሱ 2014 አመት በዱባይ ፣ በባህሬንና በሳውዲ … !

    Print       Email
0 0
Read Time:8 Minute, 0 Second
የማለዳ ወግ …

* ዱባይ በአስደናቂ 400 ሽህ ርችቶች አለምን አስደመመች!
* እፁብ ድንቅ ርችቶች የአለምን ሪኮርድ ሰብረዋልም ተብሏል
* ሳውዲና ባህሬንን በሚያገናኘው ድልድይ ተጨናንቋል
* እኛም እያዘንን ለመደሰት በመሞከር ላይ ነን

ከአመታት በፊት 828 ሜትር እርዝመት ያለው የቡርጅ ከሊፋን ሰማይ ጠቀስ ህንጻ በመገንባት የአለምን ሪኮርድ የሰበሩት ኢምሬቶች ዛሬ በጀመርነው አዲሱ አመት 400 ሽህ እፁብ ድንቅ በህብረ ቀለማት ያሸበረቁ ርችቶች ወደ ሰማይ በማጎን በኮዌት ተይዞ የነበረው 77,282 የአለም ሪኮርድ በመስበር በአዲሱ 2014 አመት አዲስ ሪኮርድ ተቀዳጅታለች። በኢምሬት አንብርት በዱባይ ሚሊዮኖች ያየነው የሰማዩን ውብና ድንቅ ርችት ብቻ አልነበረም ። በመላ ከተማዋ በሚገኙት ሰማይ ጠቀስ ፎቆቿና መዝናኛ ቦታወች እየተነሱ በምድር ለምድር በመምዘግዘግ በሰው ሰራሽ ሃይቆችና በሚያምሩት ህንጻዎች ተስፈንጥረው የሚወጡት ዘመነኛ የሌዘር ህብረ ቀለማትን የተላበሱ ርችቶች እና መብራቶች በእርግጥም አረቧ ሃገር ኢምሬት የደረሰችበትን የእድገት ደረጃ በገሃድ የሚያሳይ ነበር ማለት ይቻላል። በዘንባባ ቅርጽ በተገነባውና የአለማችን ታዋቂ ሰዎች በከተሙበት የጀማርያህ የባህር ዳርቻዎችና በደሴቶች ፣ ብረት ቀልጦ እንደ ልብስ ጥበብ በአስደናቂ ስነ ህንጻ ጥበብ የሚታይባቸው ሰማይ ጠቀሱ ቡርጅ ከሊፋ እና የቡርጅ አል አረብ ህንጻዎችም ዛሬ የአለምን አይን አማልለው ማምሸታቸው እውነት ነው። በከተማዋ ዙሪያ ገብ በተሰሩት ህንጻና ሰው ሰራሽ ባህሮች እየተስፈነጠሩ ወደ ሰማይ የሚወረወሩት ፣ ወደ ጎን ፣ወደ ላይ ወደ ታች የሚተጣጠፉት መብራቶች ብቻ አልበሩም ። ውሃው በድቅድቁ ጨለማ ከመብራት ተዋህዶ አይንን ሲያማልል ሲፈስ ፣ ሲለው ዝም ጭጭ ሲል በአረብቸኛ ባህላዊ የካልጅ ዝማሬ ቅላጼ ታጅቦ መሆኑ የሰው ልጅን መዘመን ምጥቀቱን ሲያሳብቅ ውሃና ሌዘር ተወንጫፊ መብራቶች እጥፍ ዘርጋ ሲል በዱባይ ያየነው ጉድ በአዲሱ አመት ዛሬ ነበር ። ግዑዙ ፈሳሽ ውሃ በቧንቧ እየተፈናጠረ ከመብራት ጋር ተዋህዲ እንደ ግብጽ “ረጋሳዎች “ዳንሰኞች ሲያረገርግ መመልከት በእርግጥም “ገንዘብ ካለ በሰማይ መንገድ ” አለ ያስብላል!

ከእኔ ቢጤው ደካማ ገቢ ካለው እስከ ናጠጠው ሃብታም አረቦች አዲሱን አመት ለመቀበል የኢምሬቷን እንብርት ዱባይን ከአፍ እስከ ደገፏ ጢቅ አድርገው ሞልተዋታል። ዱባይ የፈረንጆችን የዘመን መለወጫ ቀምታ ለራሷ አድርጋው ዛሬ አይተናል። እንዲህ አድርገው እንዲህ ሆነው አጅብ ተያሰኙን የዱባይ ስልጡን አረቦች ሰማይ ምድር ባህሯን በህብረ ቀለማት ርችቶች አድምቃ እና በባህላዊ የከልጅ ጣህመ ዜማ አዲስ ታሪክ ሲያስመዘግቡ የፈረንጆቹን ቴክኖሎጅን በገንዘባቸው ገዝተው ቢሆንም ዛሬ ከሸጡላት ስልጡን ሃገራት ደምቀው ፣ ተውበው ተአምርን ለአለም በማስመስከር “የአረቦች ኒዮርክ !” ተብላ በአረቦች የምትንቆለጳጰሰው ዱባይ አዲሱን አመት እንዲህ ጀመራዋለች !

በሳውዲየከተሙ ፣ ዱባይ መሄዱ ያልቀናቸው ወደ ጎረቤት ባህሬን እየጎረፉ ሲሆን ቀይ ባህርን ሰንጥቆ ሳውዲና ባህሬንን በሚያገናኘው በደማም በኩል የተዘረጋውን ድልድይ አጨናንቀውት ማምሸታቸውን የሳውዲ መገናኛ ብዙሃን ዘግበውታል ። ምክንያቱ ባህሬን ከሳውዲ በውበት ደምቃ አይደለም ! ብዙዎች ሳውዲ የሚከለከሉትን ዳንኪራ ቤትና ፈሳሿን ” ቅብአ ቅዱሷን!” እዚያ በነጻነት እየተጎነጩ ነፍሳቸውን የሚያስደስቱባት ባህሬን ብቸኛ አንጻራዊ ነጻነት የምታስተናግድ የቅርብ ጎረቤት ናትና ነው ብለን እንገምት:)

ብዙሃኑ ሃበሻም ባይሆን እኔ እና መሰሎቸ በየአቅጣጫው የወገንን ጭንቅ ፣ ስጋት ሮሮ እየሰማን ፣ ግማሽ ጎናችን ታሞ ግማሹን በአዲስ አመት ትፍስህት በተስፋ ለመቀበል እያዘንን ለመሳቅ በመሞከር ደመቅመቅ ብለን አዲሱን አመት ” እንኳን ደህና መጣህ !” ብለነዋን ! …ህይዎት እንዲህ ናት !

መልካም አዲስ አመት !

ነቢዩ ሲራክ

Nebiyu Sirak's photo.Nebiyu Sirak's photo.
Nebiyu Sirak's photo.Nebiyu Sirak's photo.
Nebiyu Sirak's photo.Nebiyu Sirak's photo.
Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 10 years ago on December 31, 2013
  • By:
  • Last Modified: December 31, 2013 @ 8:41 pm
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar