www.maledatimes.com «አፍ ሲከፈት ራስ ይታያል» - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

«አፍ ሲከፈት ራስ ይታያል»

By   /   February 12, 2014  /   Comments Off on «አፍ ሲከፈት ራስ ይታያል»

    Print       Email
0 0
Read Time:15 Minute, 7 Second

ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት ማክሰኞ የካቲት ፬ ቀን ፪ሺህ፮ ዓ.ም. ቅፅ ፪ ፣ ቁጥር ፲

በየዘመኑ ሆድ አደር ባንዳዎች አገርን እና ወገንን የጎዱ አያሌ አስፀያፊ እና አረመኔያዊ ተግባሮችን መፈጸማቸው ይታወቃል። የባንዳነት
ዋና መለያውም ባንዳ የሆነ ሰው የሚናገረው ጌታው ያለውን ብቻ ሳይሆን፣ «ጌታዬ ሊለው እና ሊያስበው ይችላል» ብሎ የገመተውን ሁሉ በመሆኑ
ነው። ባንዳ ይህን በማድረጉ ከጌታው ጠርቀም ያለ ዳረጎት (ገፈራ) ያገኛል። ስለዚህ እንዲህ ያለው የሥነምግባር እና የኅሊና ስብራት ያጠቃው ባንዳ
ግለሰብ፣ ጌታው በጠላትነት በፈረጀው ወገን ላይ እጅግ አሰቃቂ አካላዊ ጉዳቶችን እና በጤነኛ ኅሊና ሊታሰቡ የማይችሉ አሸማቃቂ ሥነ-ልቦናዊ
ጥቃቶችን ከመፈጸም አይመለስም። ባንድ ወቅት የባንዳዎቹ የአስረሱ ተሰማ እና የገብረልዑል የልጅ ልጅ የሆነው የወያኔው ራስ መለስ ዜናዊ፣
የትግራይ ሕዝብ በነቂስ ዐማራውን በጠላትነት ፈርጆ እንዲያጠፋው አዋጅ ሲጎስም «ከዐማራ ጋር መኖር አይቻልም» ብሎ ነበር። ዛሬም እርሱ
መልምሎ እና አሠልጥኖ፣ ዐማራን እንዲያጠፉለት ካሠማራቸው ሰው-መሠል አራዊት አንዱ የሆነው ዓለምነው መኮንን የተባለው የትግሬ-ወያኔ ሎሌ፣
ዐማራውን ከጌታው በከፉ ኃይለቃሎች ከመዝለፍ ወደኋላ አላለም።
ተቀብሎ መስጠት እና ሰጥቶም መቀበል ባህሉ የሆነውን፣ ከመናገሩ በፊት በቅጡ አዳምጦ እና ሲናገርም እስተውሎ፣ ፈሪሃ
እግዚአብሔርን እምነቱ እና መመሪያው ያደረገውን፣ ዘር ሳይመርጥ የሚጋባውን፣ ኢትዮጵያዊነት ዕምነቱ እና ማተቡ የሆነውን፣ ኩሩ እና ጀግና
የሆነውን የዐማራን ነገድ፣ ዓለምነው መኮንን የተባለው ዘመናዊ ባንዳ አንቋሾታል፣ ዘልፎታልም። ዓለምነው መኮንን ይህንን ዓይነቱን መረን የለቀቀ
ኃይለቃል የወረወረው፣ «እመራዋለሁ፣ እወክለዋለሁ፣ ከእርሱ አብራክ የወጣሁ ነኝ» በሚለው ሕዝብ ላይ መሆኑ ነገሩን ይበልጥ የወለፌንድ
ያደርገዋል። ይህ ባንዳ፣ ሟች ጌታው መለስ ዜናዊ ይላቸው የነበሩትን ዐማራን የማጣጣያ ቃሎች ብቻ ሳይሆን፣ «መለስ በሕይዎት ቢኖር ሊለው
ይችላል» ብሎ የገመተውን ሁሉ፣ በዕብሪት እና በማን አለብኝ ስሜት ተውጦ፣ በዐማራው ነገድ ማንነት እና ኅልውና ላይ ያነጣጠረ የስድብ
ውርጅብኝ ማውረዱን ሰምተናል፣ አዳምጠናልም። ድርጊቱ ዐማራውን ከማዋረድ እና ከመናቅ አልፎ «ምን ያመጣሉ» ዓይነት ትዕቢት ያዘለ፣ ጎልያድ
በዳዊት ላይ እንዳሳየው ንቀት መሆኑ ነው። በሌላ በኩል ከዓለምነው መኮንን የወጡት ኃይለቃሎች በትክክል ከእርሱ ኅሊና የፈለቁ አለመሆናቸውን
እርሱን የሚያውቁት ብቻ ሳይሆኑ፣ የወያኔን አካሄድ የተረዱት ሁሉ ይገነዘቡታል። በዚህ ንግግሩ እርሱ ድምፅ ማጉያ እንጂ፣ ኃሣብ እና ቃሎቹ
የትግሬ-ወያኔ መሆኑን የዐማራው ሕዝብ ጠንቅቆ ያውቃል። ባንዳነት ደግሞ ከዚህ ያለፈ ፋይዳ የለውም። ሆኖም «ናቂ ወዳቂ፣» መሆኑን ወዶ-ገባው
የትግሬ-ወያኔዎች ሎሌ ዓለምነው መኮንን ያጤነው አይመስልም። ውሎ አድሮ እርሱም ሆነ መሠል የትግሬ-ወያኔን አገልጋይ ባንዳዎች፣ የናቁት ሕዝብ
ራቁታቸውን እንደሚያስቀራቸው በተግባር ያዩታል።
ዐማራው እሰኛ፣ ያለውን እንካፈል ባይ፣ ሰላም ወዳድ እና አብሮነት መለያ ባሕሪው የሆነ በመሆኑ፣ ወዳጅ ብቻ ሳይሆን ጠላትም
የመሰከረለት ሃቅ ነው። አዎ! ዐማራው በኅልውናው፣ በአገሩ ነፃነት፣ በኃይማኖቱ እና በማንነቱ ላይ ለሚነሱ ኃይሎች እግሩን ለጠጠር፣ ደረቱን ለጦር
የሚሰጥ፤ ከሕይዎቱ በላይ ነፃነቱን የሚያስቀድም በመሆኑ ለባዕዳን ቅጥረኞች መሣሪያ አይሆንም። ዛሬም ቢሆን የቅኝ ገዥነት ፍላጎት የነበራትን፣
ኢትዮጵያን ደጋግማ ለመውረር ሞክራ ተዋርዳ የተመለሰችውን የፋሽስት ጣሊያንን ዓላማ ለማስፈጸም ከፍ ዝቅ የሚሉትን የትግሬ-ወያኔን እና
የእርሱን መሠል ፍልፍሎች ዓላማና አካሄድ የዐማራው ነገድ አልተቀበለውም። ዐማራው ይህንን ባለመቀበሉም በፈለጉት መልክ ሎሌ ለማድረግ
አልቻሉም። የዓለምነው መኮንን ጋጠወጥ ንግግርም መነሻ ምክንያቱ ሌላ ሳይሆን፣ ዐማራውን በወያኔ ፍላጎት ዙሪያ እንዲያሰልፍ በወያኔ እና «የነፍስ
አባቱ» በሆነው በሌላው የትግሬ-ወያኔ ሎሌ በደመቀ መኮንን አማካይነት የተሰጠውን የቤት ሥራ መወጣት ባለመቻሉ ነው። በመሆኑም ዐማራው«
ኢትዮጵያዊነቴ ወይ ሞቴ» ብሎ ፍንክች ባለማለቱ፣ በዓለምነው ላይ የተፈጠረበት ተስፋ መቁረጥ ያስከተለው ጭንቀት፣ የጌታውን የመለስን ቃል
ተውሶ እንደበቀቀን እንዲጮህ እንዳስገደደው ንግግሩን ያዳመጡት ይገነዘቡታል።
«አፍ ሲከፈት ራስ ይታያል» እንዲሉ ሆኖ፣ የዓለምነው መኮንን አፍ ሲከፈት በአንደበቱ ያዬነው መለስን ነው። «ባለቤቱን ካልናቁ
አጥሩን አይነቀንቁ» ይባላልና፣ ዓለምነው መኮንን ያን ያህል የዘላበደው የትግሬ-ወያኔዎችን ስሜት ተከትሎ መሆኑን ለአፍታም መጠርጠር አይቻልም።
የንግግሩ ዳራ የትግሬ-ወያኔ የዐማራውን ትዕግሥት እንደፍርሃት፣ አስተዋይነቱን እንደ ቂልነት፣ «አድሮ እንየውን» እንደ ሽንፈት ቆጥረው የሚሠሩትን
የሚያሣጣ የንቀት ደረጃ ላይ መድረሣቸውን የሚያሳይ ነው። የትግሬ-ወያኔ ራሱን እንደመንግሥት የሚቆጥር ከሆነ፣ ብአዴን የሚሉትም የምርኮኛ
ሎሌዎች ጥርቅም ራሱን እንደፖለቲካ ድርጅት የሚገምት ከሆነ፣ የሁለቱም ግምት ትክክል መሆኑን ማሳያው፣ በዓለምነው መኮንን ላይ የሚወስዱት
ርምጃ ነው። ዓለምነው መኮንን በዐማራው ነገድ ማንነት ላይ ያወረደው ፍፁም ንቀት የተሞላው የስድብ ውርጅብኝ፣ ለአንድም ቀን ቢሆን በሕዝብ
ኃላፊነት ላይ ሊያስቀምጠው ካለመቻሉም በላይ፣ በወንጀልም የሚያስጠይቀው ተግባር ነው። በመሆኑም በአስቸኳይ ለፍርድ እንዲቀርብ፣
ኢትዮጵያውያን ሁሉ፣ በተለይም የዐማራው ነገድ አባሎች የተባበረ ዘመቻ እንዲያደርጉ ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት ታላቅ ጥሪ ያቀርባል።
ዐማራው ለዚህ ዓይነቱ ውርደት የበቃው የተማሩት ልጆቹ የጠላቶቹን ማንነት ቀድመው ተረድተው፣ ሊሰነዘርበት ከሚችል ማናቸውም
ዓይነት ጥቃት ሊከላከል የሚችልበትን ዘዴ ባለመሻታቸው እንደሆነ ግልጽ ነው። «የተደራጁ ጥቂቶች ያልተደራጁ ሚሊዮኖችን ያሸንፋሉ» የሚባለው
አባባል ዕውን በመሆኑ፣ በቁጥር ጥቂት ከሆነው የትግሬ ነገድ የወጡት ወያኔዎች በመደራጀታቸው፣ ከ፵ ሚሊዮን በላይ የሆነውን የዐማራ ነገድ
ይኸው እንደምናየውና እንደምሰማው በገፍ ያስሩታል፤ ያሰድዱታል፤ ለዘመናት ከኖረበት አካባቢ ኃብት ንብረቱን ነጥቀው ያፈናቅሉታል፣ ከሥራ
ያባርሩታል፣ በየደረሰበት የውሻ ለምድ ያለብሱታል፣ አልፎ ተርፎም በጅምላ ይገድሉታል። የዓለምነው መኮንንም መረን የለቀቀ የበታችነት ስሜት
የወለደው ንግግር ያለፉት ተከታይ እንጂ፣ አዲስ አለመሆኑ ይታወቃል። ይህ ዓይነቱ ተደጋጋሚ ጥቃት በዐማራው ላይ ለወደፊትም እንዳይፈፀም፣
ብቸኛው እና አስተማማኙ መፍትሔ፣ ዐማራው እስኪመጡበት ሳይሆን ራሱን አደራጅቶ፣ ካሉበት ድረስ መሄድ ሲችል እና «አለሁ!» ሲል ነው።
ስለሆነም ዓለምነው መኮንን በዐማራው ላይ በፈጸመው መረን የለቀቀ የዘለፋ ወንጀል ለሕግ እንዲቀርብ አስፈላጊውን ጫና መፍጠር ያስፈልጋል።
ከዚህም ባሻገር፣ የዐማራው ምሁራን ለዐማራው ዙሪያ-ገብ ችግሮች መፍትሔ ለመስጠት በመንቀሳቀስ ላይ ያለውን የሞረሽ ወገኔ ዐማራ ድርጅት
በመቀላቀል ለወገናችን ችግር ፈጥነን እንድረስ ይላል።
ዐማራን ከፈጽሞ ጥፋት እንታደግ!
ፈለገ አሥራት የትውልዳችን ቃልኪዳን ነው!
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 10 years ago on February 12, 2014
  • By:
  • Last Modified: February 12, 2014 @ 8:07 am
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar