www.maledatimes.com የስድብ አፍ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

የስድብ አፍ

By   /   February 12, 2014  /   Comments Off on የስድብ አፍ

    Print       Email
0 0
Read Time:10 Minute, 54 Second

መቸም እኛ ኢትዮጵያውያን በዘመነ ወያኔ ጊዜ እዳለመታደል ሆኖ ስለ ሀገር ስለ ፍቅር ከመናገር ይልቅ
ጥላቻን የሚሰብኩ ጠብን የሚዘሩ አብሮ በመተሳሰብ የኖረውን ሕዝብ እንዲለያይ ሌት ከቀን በመባዘን
የማይሰሩት የማይፈጽሙት ምደባ የለም ለማለት እይቻልም ይህንንም እኩይ ሰራ የሚፈጽሙ ሰዎች
ደግሞ ስብና የሌላችው ተንኮለኞች ለህሰት የተጉ ስልጣን ፈላጊዎች ለከርሳችው ያደሩ ቀፎዎች
ኢትዮጵያን ለማፍረስ ከጥፋት አባታቸው ወያኔ የተሰጣቸውን ተልኮ ለመስራት ደፋ ቀና ከሚሉት
አድርባዮች አንዱ አቶ አለምነው መኮንን የተባለው ይገኝበታል ይህ አቶ አለምነው መኮንን የሚባለው
የአማራ ክልል ባለስልጣን እና የብአዴን አመራር አባል ሰሞኑን የአማራ ተወላጆችን አስመልክቶ የሰጠው
አስተያየት እጅግ በጣም የሚያሳዝን ከመሆኑም በላይ ከራሱ ከኣማራው ብሔር መገኝቱ (መውጣቱ)
ደግሞ ኣስገራሚው ነገር ነው ይህ ሰው ወያኔዎች ሲያደርጉ እንደሚሰማው እንኩዋን ነፍጠኛ እና
ትምህክተኛ በሚሉ የቃላት ጨዋታ ተጠቅሞ አማራውን ለመከፋፈል አልሞከረም ህዝቡን እንዳለ
በጅምላ እንዲህ ብሎ ተሳደበ አንጂ

“ የአማራው ህዝብ በቅድሚያ እንዳይሰደድ ለማድረግ ስራ እየተሰራ ነው፣ ነገር ግን ከተሰደደ በሁዋላም
ቢሆንም
ሰንፋጭ የሆነውን ትምክህተኝነቱን በመተው ከሌላው ጋር ለመኖር መልመድ አለበት። ”

“ የአማራው ህዝብ ሰንፋጭ የሆነ ትምክተኝነት የተጠናወተው በመሆኑ በቤንሻንጉልና በሌሎችም
ቦታዎች ለመሰደዱ ምክንያት ሆኖታል። ”

“ በባዶ እግሩ እየሄደ የሚናገረው ንጝር ግን መርዝ ነው። ይሄ መርዝ ንጝሩ አንድ የሚያደርግ አይደለም።
”

“ ከኢትዮጵያውያን ጋር አብሮ ለመኖር አማራው የትምክህት ለሃጩን ማራገፍ አለበት። ይሄ ለሃጭ
ሳይራገፍ በጋራ መኖር አይቻልም። ”

“ ማንኛውም ስም ያወጣ ሙትቻ ፓርቲ ሁሉ መንገሻው አማራ ክልል ነው። ትምክህትን እንደ ምግብ
ስለሚመገበው ነው። ያንን ምግብ እየተመገበ ያቅራራል። ”

ታዲያ ይህ ሰው ጄኖሳይድ ፓልቶክ ሩም ውስጥ አማራውን ሲሳደቡ ውለው ሲሳደቡ ከሚያድሩት ሰዎች
በምን ይለያል ???

ልብ በሉ መለስ ዜናዊ እወክለዋለሁ የሚሉትን የትግራይ ህዝብ ዕወርቅ ከሆነው ከዚህ ህዝብ በመወለዴ
እኮራለሁ እ ነበር ያሉት ፥፥ የጎሳ ፖለቲካው በግራም ሆነ በቀኝ መሪ ያደረጋቸው የኦሮሞ የደቡብ
የሶማሌ ወይም የሌሎች ጎሳ ፖለቲከኞች አንድም ቀን ህዝባቸውን እንዲህ እያዋረዱ ሲሳደቡ ተሰምተው
አይታወቅም (እኔ እስከማውቀው ድረስ )፥
ሀገራችን የምትተዳረው ሰማንያ በመቶ በግብርናና ምርት መሆኑ ሁሉም የሚያውቀው ሀቅ ነው
በመሆኑም እራፊ ጨርቅ እየለበሰ በብርድና በሀሩር እየተንገላታ ለፍሬ ያደረስውን የምርቱን ውጤት እየተመገቡ ውለታውን በመክፍፈል ፈንታ ያልተሞረደ አንደበታቸውን በደሀው ገበሬ ላይ ማላቀቃቸው
ያሳዝናል ገበሬው ሳይማር አስተምሮል እሱ በባዶ እግሩ እየሔደ በኮሸሌ እሾህ ፣በጋሬጣ እየተወጋ
ያስተማረ የሀገሩን ድንበር ከወራሪ ጠላት ለማስከበር መስዋዕት የከፈለ ይህም መስዋኣትነት በደም
በኣጥንት ውድ ህይወትን በመስጠት ወይም በመገበር ነው ገበሬው በባዶ እግሩ ኣየሄደ ዘመናዊ ጦር
መሳርያ የያዘውን የጣሊያን ወራሪ ሃይል አምበርክኮና አሳፍሮ በመመለስ ለዛሬው ነጻነት አብቅቶናል
ይሁን እንጂ ዛሬ ምኒልክ ቤተ መንግስት ያሉት የወያኔ መሪ ተብየወች ሳይማር ያስተማረውቸውን
ሕዝብ በመናቅና በመጨቆን ላይ ናቸው አማራውን ከነበረበት ቀየ እዲፈናቀል ካአቅሙ በላይ የማዳበሪያ
እዳ ክፍያ እዲከፍል በማድረግ እንዲሁም ተተኪ ትውልድ እዳይኖር ያማራ ሴቶችን ብቻ በመለየት
እዳይወልዱ የሚያመክን መርፌ በመውጋት ትውልድ እዲቁዋረጥ የዘር ማጥፋትወንጀል ፈጽመዋል
ለምን ቢባል አማራውን በተገኘው አጋጣሚ ቁጥሩን መቀነስ ብሎም ማዳከም ማጥፋት የ እረጅም ጊዜ
እቅዳቸው ስለሆነ ነው ምክንያቱም ኢትዮጵያ የምትባል አገርን ለማጥፋት ቅድሚያ አማራው
መጥፋት አለበት የሚል መርሀ ግብር ፕሮግራም ስላአላቸው ነው ባማራው ሕዝብ ላይ ያላደረጉት፤
ያላደረሱበት በደል የለም ይህም የጥፋት ዘመቻ ከምንጊዜውም በላይ አጠናክረው ቀጥለውበታል
አሁን በቅርቡ አንኩዋን አማርኛ ተናጋሪው ኤርትራዊው በረከት ስምዖን ንቀት በተሞላበት
ንግግር ገበሬውን እኛ ተኛ ካልነው ይተኛል ፤ተነስ ካልነው ይነሳል ተቀመጥ ካልነው ይቀመጣል
በቁጥጥራችን ስር ነው አድርገነዋል በማለት በድፍረት ተናግሯል አወ ለጊዜው ሊመስላቸው
ይችላል እንጂ ገበሬው እደሚሉት አይደለም አይሆንምም “ጊዜ የሰጠው ድንጋይ ቅል
ይሰብራል”እንደሚባለው ሁሉ አሁንም ጊዜ የሰጣቸው ቅጥረኞች እያዋረዱን ይገኛል ግን
አይቀጥልም ምናልባትም መውደቂያቸው ሲቃረብ የተራቀመውን መርዛቻውን አያራገፉብን
ነው ይህ ሊቆጨን ሊያንገበግበን ይገባል
ስለሆነም አነዚህ አማራውን ሳይወክሉ እንወክላለን ለሚሉ የእንግዴ ልጆች ዋጋቸውን ለመክፈል
መንቀሳቀስ ያስፈልገናል በተለይም በዘር ማጥፋት እና አንድን ሕዝብ በጅምላ በመዝለፍ
ክህደት አየሰሩ ያሉትን ዘረኞችንና ጎጠኞችን
ለፍርድ ለማቅረብ ከመችውም ጊዜ በሕብረት መነሳት አለብን ይህ የሚሆነው ወያኔና የጥፋት
ተባባሪያቸውን ሁሉ ለማስወገድ መተባበር ወቅቱ የሚጠይቀው አይነተኛ ተግባር ነው ስለዚህ እንተባበር
አንለያይ እጅ ለ እጂ ተያይዘን የድሉን ጎዳና እንስራ የስድብ አፋቸውን ዘግተን ነጻነታችንን አናስመልስ
ተድላ ጌትነት ጀርመን

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 10 years ago on February 12, 2014
  • By:
  • Last Modified: February 12, 2014 @ 8:09 am
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar