www.maledatimes.com ዋጋ ለመክፈል ፈቃደኛ የሆነ በማይገኝበት ዘመን የአገር ምጧ ብዙ ነው፡፡ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

ዋጋ ለመክፈል ፈቃደኛ የሆነ በማይገኝበት ዘመን የአገር ምጧ ብዙ ነው፡፡

By   /   February 14, 2014  /   Comments Off on ዋጋ ለመክፈል ፈቃደኛ የሆነ በማይገኝበት ዘመን የአገር ምጧ ብዙ ነው፡፡

    Print       Email
0 0
Read Time:8 Minute, 41 Second

በያዝነው ሥልጣንና ሹመት ሙጭጭ ካልን፤ በዚያውም ለተተኪው ትውልድ ቦታ ካልለቀቅን፤ የአገር- ለውጥ- ቀን እየራቀ ነው የሚሄደው፡፡ በእርግጥም ይሄ ቦታን በሰላም የመልቀቅ ባህል የዋዛ ነገር አይደለም፡፡ ፖለቲካዊ-ገፅ አለው፡፡ የኢኮኖሚ-ገፅ አለው፡፡ የግል ጥቅም-ገፅ አለው፡፡ ከፓርቲ ጋር፣ከራስ ጥቅም ጋር፣ ከራስ ህሊና ጋር መሟገትንና መታገልን ይፈልጋል፡፡ ይህን ዋጋ ለመክፈል ፈቃደኛ የሆነ በማይገኝበት ዘመን የአገር ምጧ ብዙ ነው፡፡ከፖለቲካ ባህላችን ውስጥ እጅግ ሚዛን የሚደፋ አንድ ባህል አለ፡፡ ብዙ ሊጤን ይገባል! የይቅር መባባል ባህል! ቂም፣ የወንጀለኝነት-ስሜት፣ ብድር-የመመለስ ፍላጎት፤ አጥፊ ናቸው፡፡የራሳችን ነውር ሳይታየን ስለ ሌላው አስነዋሪ ነገር መናገር ክፉ እርግማን ነው! የሌሎቹን አገሮች፤ ፓርቲዎች፣ ግለሰቦችም ሆኑ ቡድኖች ስንተች እኛስ? የእኛስ? ብለን መጠየቅን አንርሳ!“የራሱን ጭራ ሳያይ ውሻ (ወያኔ ኢሕኣዴግ) ፍየልን ጭራሽን ዝቅ አድርጊ” ይላል

አሉታዊ አመለካከትና የወንጀለኛነት ስሜት ፤በአዎንታዊ የመረዳት ስሜት፣ በመረዳዳትና በትውስታ ስሜት፤ ሊተካ ይችላል፡፡ በዚህ ስሜት ሲታይ ከዚህ ቀደም ይጠሉ የነበሩ ሰዎች ይቅርታን ሊያገኙ ይችላሉ፡፡ ከዚህ ቀደም ያስፈሩ የነበሩ ሰዎችም አሁን ሰላማዊ ሆነው ሊታዩ ይችላሉ፡፡ ዋናው ራስን ለማየትና ጥፋትን ለመቀበል ዝግጁ የመሆን ጉዳይ ነው። እርግጥ እንደኛ በፊውዳሊዝም ለተተበተበ፣ ባልለየለት ካፒታሊዝም ለታጠረና ሁሉን ጥፋት በሌሎች ላይ መላከክን ሥራዬ ብሎ ለያዘ ህብረተሰብ ፤ ከአባዜው በቀላሉ ለመገላገል አይቻልም! ሆኖም ይቻላል ብለን አዕምሮአችንንና ልቡናችንን ክፍት እናድርግ፡፡ ለዚህ ቁልፉ ነገር፤ አንዱ ከሌላው መማሩ ነው፡፡ ችግሩ ግን ያልተማረው የተማረውን ካላስተማርኩ፣ አላዋቂው አዋቂው ካላዳመጠኝ የሚልበት፤ ከሁሉም በላይ ደግሞ በአዕምሮም በአካልም ያልዳበረው ሰው፤ ልምድ ያለውንና የዳበረውን ሰው፤ ዘራፍ ሲልበት፣ ሲፎክርበት፣ ከእኔ ወዲያ ላሣር ሲለው የታየበት አገር መሆኑ ነው!

ከፖለቲካ ባህላችን ውስጥ እጅግ ሚዛን የሚደፋ አንድ ባህል አለ፡፡ ብዙ ሊጤን ይገባል! የይቅር መባባል ባህል! ቂም፣ የወንጀለኝነት-ስሜት፣ ብድር-የመመለስ ፍላጎት፤ አጥፊ ናቸው፡፡የራሳችን ነውር ሳይታየን ስለ ሌላው አስነዋሪ ነገር መናገር ክፉ እርግማን ነው! የሌሎቹን አገሮች፤ ፓርቲዎች፣ ግለሰቦችም ሆኑ ቡድኖች ስንተች እኛስ? የእኛስ? ብለን መጠየቅን አንርሳ! ልማዶቻችንን፣ በዓሎቻችንን ስብሰባዎቻችንን እንገምግም፣ እንመርምር፣ እናሻሽል፡፡ በዓላት በራሳቸው ግቦች አይደሉም፡፡ ወደፊት መራመጃ እንጂ! “ያፈረሰ ቄስ ተመልሶ አይቀድስ፣ የሸሸ ንጉሥ ተመልሶ አይነግሥ” በሚባልበት አገር የማይሻሩና በልብ ፅላት ላይ የተፃፉ ህግጋት አሉ፡፡ እነዚህ በባህልና በማህበራዊ ልምድ የዳበሩና የታመኑ ናቸው! አገር ያወቃቸውና ያመነባቸው የወል ህግጋት እንዳሉ ሁሉ፤ ሰው በግሉ በራሱ ላይ የሚወስንባቸው ግለ-ደንቦችም አሉ፡፡ እንዲህ ያሉት ህገ-ደንቦች ሲበራከቱ ስደት ልጓም ያጣል፡፡ ስደተኛው የትየለሌ ቢሆን የማይገርመው ለዚህ ነው! ውጤቱን እንደ ዛሬው በአስከፊ መልኩ ባንቀምሰውም በውሱን መልኩ የምናውቀው ስደትና አስከፊ ውጤት ነበር፡፡

በየዕለቱ ከሚገጥመን አገራዊ ችግርና አፈታቱ ጋር ለማስተያየት ብንሞክር፤ አርጅተን ጃጅተን የሠራነውንና ያልሠራነውን፣ የሄድንበትንና ያልሄድንበትን ለመለየት የማንችልበት የመርሳት ዕድሜ እስከምንደርስ ንቅንቅ አልልም ብለን፤ በያዝነው ሥልጣንና ሹመት ሙጭጭ ካልን፤ በዚያውም ለተተኪው ትውልድ ቦታ ካልለቀቅን፤ የአገር- ለውጥ- ቀን እየራቀ ነው የሚሄደው፡፡ በእርግጥም ይሄ ቦታን በሰላም የመልቀቅ ባህል የዋዛ ነገር አይደለም፡፡ ፖለቲካዊ-ገፅ አለው፡፡ የኢኮኖሚ-ገፅ አለው፡፡ የግል ጥቅም-ገፅ አለው፡፡ ከፓርቲ ጋር፣ከራስ ጥቅም ጋር፣ ከራስ ህሊና ጋር መሟገትንና መታገልን ይፈልጋል፡፡ ይህን ዋጋ ለመክፈል ፈቃደኛ የሆነ በማይገኝበት ዘመን የአገር ምጧ ብዙ ነው፡፡
ወጣቱ ላይ ዕምነት ይኑረን፡፡ ያለ ጥርጥር ወጣቱ አሸናፊ ነው፡፡ ዛሬም ይሄ ዕውነታ አይሻርም፡፡ አዲስ ኃይል መፍጠር የአገር አቅም መፍጠር ነው። ይህ ማለት ግን የግድ በፖለቲካ የሚታቀፍ ወጣት ይኑረን ማለት አይደለም፡፡

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 10 years ago on February 14, 2014
  • By:
  • Last Modified: February 14, 2014 @ 12:49 pm
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar