www.maledatimes.com ያ ትውልድ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

ያ ትውልድ

By   /   February 14, 2014  /   Comments Off on á‹« ትውልድ

    Print       Email
0 0
Read Time:26 Minute, 8 Second

የ«ያ ትውሌዴ ተቋም» ሌሳን
ያ ትውሌዴ ቅጽ 1 ቁጥር 3 የካቲት ፮ ቀን ፪ ሺህ ፮ ዓ.ም.
የካቲት 1966 እና ያ ትውሌዴ
(የካቲት 1966 ዓ.ም. 40ኛ ዓመት መታሰቢያ ምክንያት በማዴረግ)
የካቲት 1966 ዓ.ም. በኢትዮጵያ ሕዝብ የትግሌ ታሪክ ከፍተኛው ቦታ የሚሰጠው ነው። ከሦስት ሺህ
ዘመን ተያይዞ የመጣውን ንጉሳዊ አገዛዝ የነቀነቀ፣ ባሊባታዊ ፊውዲሊዊ ሥርዓትን ያናጋ ሕዝባዊ
እንቅስቃሴ በመሆኑ በታሪክ ተጠቃሽነት ከፍተኛውን ቦታ ይይዛሌ። የባሊባታዊ የመሬት ሥሪት
ያስመረረው አፈር ገፊ ጭሰኛ የተጠራቀመ ብሶት፣ የከተሜው ሊብ አዯር ቅጥ ያጣ ብዝበዛ፣ በፆታ
ሌዩነት ምክንያት በሴቶች እህቶቻችን ሊይ የሚዯርሰው በዯሌ፣ በሃይማኖት በኩሌ ያሇው አዴሌዎ
የፈጠረው ስሜት፣ የወታዯሩና የሠራተኛው ክፍሌ ዝቅተኛ የኑሮ ሕይወት፣ የተማሪዎች የየዕሇት
ሇውጥ ፍሊጎትና ሇተበዲዩ ሕዝባቸው የሚያሰሙት ጩኸት የደሊና ጥይት ምሊሽ ጥርቅም ውጤት
የካቲት 1966ን ሕዝባዊ አመጽ ወሇዯ። የበዯሌ፣ የጭቆና፣ የኋሊ ቀርነት፣ የረሃብ፣ የመብት ረገጣ
ውጤት አመጽ ጸንሶ፤ አመጽን አርግዞ፤ ሕዝባዊ ንቅናቄን በመሊ ኢትዮጵያ ተገሊገሇ። ሌክ የዛሬ 40
ዓመት የካቲት 1966 ዓ.ም.።
የካቲት 66 ሲነሳ ይበሌጡን ሇእንቅስቃሴው ከፍተኛ መጋጋሌና የሥርዓት ሇውጥ ጥያቄ እርሾ የሆነው
ከኅሉናና ከአዕምሮ የማይፋቀው የወል ረሃብ መጋሇጥ ነበር ቢባሌ ሃቅነቱ የማይካዴ ነው። ወል ተርቦ
በየዯቂቃው ሕዝብ ሲያሌቅ፣ ማንቁርታቸው ያገጠጠ፣ ዓይናቸው የሰረጎዯ፣ ቆዲቸው ከአጥንታቸው
የተጣበቀ ሕፃናት ተንዘሌዝል የዯረቀ የሟች እናቶቻቸውን ጡት ሲምጉ ማየት ሰውነትን የሚቆነጥጥ፣
ዕንባንና ሲቃን የሚያከናንብ ሰቆቃ የንጉሡን ታማኝ ኃይልች ሳይቀር ያስቆጣና ያሳመጸ ጉዲይ ነበር።
በተሇይ ከ1953 ዓ.ም. የግርማሜና መንግስቱ ነዋይ በንጉሡ ሊይ የተዯረገ መፈንቅሇ መንግስት ሙከራ
በኋሊ የተማረው ክፍሌ የነበረው ባሊባታዊ ሥርዓት ሊይ የሚያካሂዯው እንቅስቃሴ እየተጠናከረ
መምጣትና ጥያቄዎቹም ከአካባቢያዊነት አሌፈው ፖሇቲካዊ ይዘት እየያዙ መምጣት ጀመሩ። ቁጥሩ
ቢያንስም በወቅቱ አንዴ ጥሊሁን በሺህ ታጋይ ይታሰብ ነበርና ጥሊሁን ግዛው ሊይ በንጉሡ ወታዯሮች
የተወሰዯው እርምጃ ይበሌጥ ተማሪውን አነሳሳ። ከሕዝብ በሚሰበሰብ ቀረጥ የሚማረው ተሜ
ወገንተኛነቱን ሇተበዲዩ ሕዝብ ሰጠ። ትሌቁን የባሊባታዊ ሥርዓት ማናጊያ መፈክሩን ይዞ ግምባር
ቀዯም ፋና ወጊ ሆነ “መሬት ሇአራሹ!”።
ሊብ አዯሩ፣ አርሶ አዯሩ፣ ምዐሩ፣ ወታዯሩ ሁለም የኅብረተሰብ ክፍሌ ወዘተ የትግለ አጋር ይሆን
ዘንዴ ተሜ ሀገሬ ኢትዮጵያ እያሇ መቀስቀሱን ጀመረ። ያት ቅጽ 1 ቁጥር 3……………………………………………………………………….………………..የካቲት ፮ ቀን ፪ ሺህ ፮

2

«አትነሳም ወይ፤ አትነሳም ወይ፡ የግፍ አገዛዝ አይበቃህም ወይ፡ ተነስ! ተነስ!»
በዝማሬው፤ ጭንቅሊቱ የፖሉስ ደሊን አስተናግዶሌ። በቦተርና ላልች ማጎሪያ ስፍራዎች እንዱማቅቅ
ተዯርጓሌ። የጥሊሁን፣ ዋሇሌኝና ማርታ ሞት ዝማሬውን አዯመቀው፣ ትግለን አጋጋሇው።
«ጥሊሁን ሇምን ሇምን ሞተ?
ዋሇሌኝ ሇምን፤ ሇምን ሞተ?
ማርታ ሇምን፤ ሇምን ሞተች?
በሃይሌ በትግሌ ነው
ነፃነት የሚገኘው።»

ዝማሬ ሇትግለ መስዋዕትነትን እንዯሚከፍሌበት አስተማረ። የዏዴዋና የአምስት ዓመቱ የፋሽስት
ጣሌያን ወረራ ዴሌ የመቶ ሺዎች ዯምና አጥንት ውጤት መሆኑን ተገንዝቦ
«ፋኖ ተሰማራ፤ ፋኖ ተሰማራ
እንዯ ሆችሚኒ፤ እንዯ ቼኩቬራ
በደር በገዯለ፤ ትግለን እንዴትመራ»

ዝማሬዎች የየሰሌፉ ማዴመቂያና መቀስቀሻ ሆኑ። ማንነቱን ሇሕዝብ መብትና ነፃነት አሳሌፎ ሉሰጥ
የተዘጋጀ ትውሌዴ ተወሇዯ። ቅዴሚያ ጩኸቱ ሇሀገርና ሇሕዝብ ያዯረገ ትውሌዴ፤ ያ ትውሌዴ!
«ተው ስማኝ ሀገሬ፤ ኧረ ስማኝ ሀገሬ
ተው ስማኝ ሀገሬ፤ ሲከፋኝ ነው መኖሬ»

እንጉርጉሮ ትግለን አጋጋሇው። የካቲት 66 የተጠራቀመ ብሶት አምጦ፡ አምጦ የወሇዯው ሕዝባዊ
አብዮት።
«ያ ትውሌዴ ተቋም» የየካቲት 1966 ዓ.ም. መታሰቢያ 40ኛ ዓመት ስናስታውስ ሇኢትዮጵያ
ሀገራቸውና ህዝባቸው መብትና ነፃነት አኩሪ ታሪክ በዯማቸው ጽፈው ያሇፉ ወገኖቻችንን በማስታወስ
ነው።
የተማረው ያ ትውሌዴ «ዴሃ ዴሃ ምን ታየበት፤ እንዲይማር የሆነበት» ብል ትምህርት ሇሁለም ብል
የጮኸ ትውሌዴ ነው። ማንም የማንን መብት ሰጪና ነፋጊ አይዯሇም ብል «የዳሞክራሲ መብት
ያሇገዯብ ሇሁለም» በአጥንቱ ከፍ አዴርጎ ዯሙን አፍስሶበታሌ። ከሁለም የህብረተሰብ ክፍሌ
የተውጣጣ «ጊዜያዊ ሕዝባዊ መንግስት አሁኑኑ» መፈክሩ በሥሌጣን ጥመኞች ባንዲዎችና ፋሽስቶች
ጥይት ሕይወቱን ገብሮበታሌ። «የሴቶች መብት ይረጋገጥ» መፈክሩ ጀግና ሴቶችን ወዯ ትግለ
አዯባባይ አሰሌፏሌ። ሕይወታቸውን እስከ ጽንሳቸው የከፈለ ታሪክ የመዘገባቸው የትግሌ እመቤቶች
አፍርቶበታሌ። «የሃይማኖት እኩሌነት መረጋገጥ» መፈክሩ እስሊምና ክርስቲያኑን በአንዴ ዓሊማ
አሰሌፎ፡ አስተቃቅፎ፡ አታግሎሌ። «የብሔር/ብሔረሰቦች መብት ያሇገዯብ» ጩኸቱ ኦሮሞው፣
ትግሬው፣ አማራው፣ ጉራጌው፣ ወሊይታው፣ ሏዯሬው፣ ሁለም ሁለም የኅብረተሰብ ክፍሌ ሇምዬ
ኢትዮጵያ በጋራ እንዱሰሇፍ አዴርጎታሌ። «የፖሇቲካ እስረኞች በሙለ ይፈቱ» መፈክሩ፤ እስርና
ስቃይ አከናንቦታሌ። ይህ ነው እንግዱህ በየካቲት 66 ብቅ ያሇው ያ ትውሌዴ መፈክር! ይህ ነበር
ጩኸቱ !!! ያት ቅጽ 1 ቁጥር 3……………………………………………………………………….………………..የካቲት ፮ ቀን ፪ ሺህ ፮

3

የየካቲት 66 አብዮት መሪ በማጣቱ የታጠቀው ሠራዊት ክፍሌ የፖሉስና ጦር ኃይልች አስተባባሪ
ዯርግ ብል ሰኔ 21 ቀን 1966 ዓ.ም. በማወጅ ቅዴመ ዝግጅቱን ካስተካከሇ በኋሊ መስከረም 2 ቀን
1967 ዓ.ም. በሞግዚት አስተዲዯር ስም በትረ መንግስቱን ጨብጦ በሕዝብ ስም እየማሇና እየተገዘተ
የሕዝብን መፈክር ከፍ ያዯረገውን ያ ትውሌዴ በመመተር 17 ዓመት በአዋጅና በዘመቻ አቅራርቶ፣
ጥይትና ቦንብ አርከፍክፎ፣ ሀገሪቷን በዯም የወየበ ምዴር አርጎ ያሇፈ አገዛዝ ዯርግ ኢሠፓ ነበር።
የካቲት 66 ሕዝባዊ እንቅስቃሴ በፋሽስት ዯርግና አጃቢዎቹ ባንዲዎች አቅጣጫውን በመሳቱና፣ ጦረኛ
አገዛዝ በመስፈኑ ሀገሪቱ ሊይ ጥል ሇሄዯው ጠባሳ ተጠያቂ ሇሀገሩና ሇህዝብ የጮኸውን ያ ትውሌዴ
ሇማዴረግ ዛሬም ሇማዯናገሪያና ሊፈሰሱት የንጹሀን ዯም ይቅር በለን ከማሇት ይሌቅ ትክክሌ
እንዯነበሩ ሁለ “ትግሊችንና አብዮታችን” እያለ ጆሮ ሲያዯነቁሩ ይዯመጣለ። ሇነሱ “ትግሊችን”
ከማሇት ግዴያችን፤ “አብዮታችን” ከማሇት አገዲዯሊችን ብሇው መተረኩ የማንነታቸው ገሊጭ ነውና
ይመረጣሌ።
አንዴን ቤተሰብ እንዲሇ መግዯሌ እውን ጀግነት ነውን? ከ12 -16 ዓመት ያለ ታዲጊ ሕፃናትን
አሰቃይቶ በመግዯሌ፡ የየካቲትን ጎርፍ አቅጣጫውን በዯም የቀየረው ፋሽስት ዯርግ እንዯነበር የ17
ዓመቱ አገዛዝ ምስክር ነው። እናትና ሌጅን፣ አባትና ሌጅን፣ ወንዴምና እህትን አሰቃይቶ የገዯሇ
መንግስት እያሇ፤ የየካቲት 66 እንቅስቃሴ መሪ ማጣት የፈጠረው ፋሺዝም እውን በያ ትውሌዴ
ሉሊከክ ይገባዋሌን? በወራት ሌዩነት ወንዴማማቾችን መግዯሌ፣ በከሌካሻ ወራዲ ተግባራቸው በሴቶች
እህቶቻችንን አካሌ ተጫውተው መግዯሌ ነበር የነሱ አብዮት፤ የነሱ ትግሊቸው። አዎ የካቲት 66
እንቅስቃሴ ስሌጣን ሊይ ያስቀመጠው ፋሺዝም ሌጆችን በመግዯሌ እናቶችን አሳብዶሌ፤ ወሊጆችን
የአሌጋ ቁራኛ አዴርጓሌ፣ አባትና እናትን በመግዯሌ ሕፃናትን ወሊጅ አሌባ አዴርጓሌ፤ እንዯነ መሊኩ
ተፈራ ዓይነት ገዲይ ፋሽስቶችን ሽሽት በየደሩና በየበረሃው የቀረውን ቤቱ ይቁጠረውና በሺዎች
የሚቆጠር ሕፃናትና ወጣቶች ዯም ዛሬም እንዯ ጀግንነት ሲተረክ ያስተዛዝባሌ።
አዎ የካቲት 66 ሕዝባዊ አመጽ በተዯራጀና በተጠናከረ መሌኩ ሉመራውና አቅጣጫ ሉያሲዘው
ያስፈሌግ የነበረ የፖሇቲካ ዴርጅት ባሇመኖሩ ጠብመንጃ የተሸከመው ወታዯር ስሌጣን ሊይ ሉቆናጠጥ
መቻለ የእንቅስቃሴው አለታዊ አካሌ ነበርና ሉዘነጋ አይገባውም። የዯርግን አምባገነናዊና ፋሽስታዊ
አካሄዴ እየተገነዘቡ ከሕዝቡ ጋር ሆነው ትግለን ማቀናበር ሲችለ በዴጋፍና ሂስ ስም ዯርግን
አሰሌጥነው የዯርግ እሳት እራት ከመሆን ያሊመሇጡ ኃይልችም የማይዘነጉ የየካቲቱ እንቅስቃሴ
ቅሪቶች ናቸው።
ኢትዮጵያ ሀገራችንን በሌማት ጎዲና ተገቢውን ሥፍራ እንዴትይዝና ሕዝቧም ከዴህነትና ከዴንቁርና
ይሊቀቅ ዘንዴ ብርቱ ምኞት የነበረው ትውሌዴ ታሪክ በተፈሊጊው ዯረጃ የተተረከ፣ የተፃፈና፣
የተሰባሰበ ባሇመሆኑ ታሪኩን ሇማጣመም ዛሬም በሰማዕታቱ ሊይ ሉሳሇቁ የሚሞክሩ መኖራቸው
ሉዯንቀን አይገባም።
ዛሬ የካቲት 40ኛ ዓመትን ስናስታውስ ያ ትውሌዴን መቀስቀሳችን አይቀርምና ነው ያንኳኳነው። ያ
ትውሌዴን ስናነሳ ሇመብትና ሇነፃነት የከፈሇውን መስዋዕትነት መዲሰስ ግዴ ይሇናሌ። መስዋዕትነቱን
ስናነሳ አሳሪና ታሳሪ፣ ገዲይና ተገዲይ፣ አሳዲጅና ተሳዲጅ፣ አጥፊና አሌሚ የታሪኩ ተጋሪ ይሆናለና
የየካቲትን ፍሬ በሌቶ የሕዝብ ሌጆችን ዯም የጠጣው ፋሽስታዊ አገዛዝ ሀገሪቷ ሊይ ሇዯረሰው ጥፋትና
ምስቅሌቅሌ ፖሇቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ሁኔታዎች ዋናውን ኃሊፊነት እንዯሚወስዴ
በማስመር ነው። ያት ቅጽ 1 ቁጥር 3……………………………………………………………………….………………..የካቲት ፮ ቀን ፪ ሺህ ፮

4

«ያ ትውሌዴ ተቋም» የካቲት 66ን ሕዝባዊ እንቅስቃሴ 40ኛ ዓመት ስናስታውስ ዴለን ሇሕዝብ
ሇማዴረግ፣ ሕጻናት በቄያቸው ተሸማቀው ሳይሆን ቦርቀው የሚያዴጉባት ብሩህ ተስፋ ፈንጣቂ
የሚሆኑበት፣ አዛውንት እናትና አባቶች በሌጆቻቸው የት ዯረሱ የሚሳቀቁበት ሳይሆን ሇሀገር ሌማት
ሇሕዝብ ዕዴገት ዯፋ ቀና የሚሌ አኩሪ ትውሌዴ የሚያዩበት፣ ኢትዮጵያ የሁለም ብሔር/ብሔረሰቦች
ባህሌና ቋንቋ የሚፈካባት ማራኪ ሀገር ሇማዴረግ፣ የሃይማኖት አዴሌዎ ሳይኖር ሁለም እንዯ እምነቱ
ሀገሬ የሚሊት፣ የተፈጥሮ ሀብቷና የደር አራዊቶቿ ጥበቃና እንክብካቤ የሚያገኙባት፣ ታሪካዊ
ቅርሶቿ በእንክብካቤ ከትውሌዴ ትውሌዴ የሚተሊሇፉባት፣ ለዓሊዊነቷና አንዴነቷ የተጠበቀች ሀገር
ሇማየት የዛሬ አርባ ዓመት የተንቦገቦገው የአብዮት ማዕበሌ አቅጣጫውን እንዲይስት የተከፈሇው
መስዋዕትነት፣ በየቤቱ የጥይት እሳት የሆነው ያ ትውሌዴ ተጋዴል ሕዝባዊ ዴሌ አሇማስመዝገቡ
ቢቆጨንም፣ ቢሰማንም፣ ትግሊቸውና መስዋዕትነታቸው ሁላም በትውሌዴ እንዯሚታወስ፣
እንዯሚዘከር በርግጠኝነት በመናገር ነው። ከፍ አዴርጋችሁ የወዯቃችሁሇት መፈክርና ዝማሬ ዛሬም
ህያው ነው። የዴለ ተቋዲሽ ባትሆኑም/ባንሆንም ጩኸታችሁ ተጋዴሎችሁ ሇሀገርና ሇሕዝብ እንዯነበር
ታሪክ ይመሰክርሊችኋሌ። በከፈሊችሁት መስዋዕትነትና በአዯረጋችሁት ተጋዴል የኢትዮጵያንና
የኢትዮጵያዊነትን ዘሊሇማዊነት አረጋግጣችኋሌ።

የካቲት 66ና የትግሌ ሏዋርያ ያ ትውሌዴ ታሪክ ህያው ነው!!!

አባሪውን ግጥም ቀጣዩ ገጽ ሊይ ያንቡ

ያ ትውሌዴ ተቋም

ዴረ ገጽ ፡ www.yatewlid.org, www.yatewlid.com

ኢሜሌ ፡ yatewlid@yahoo.com, yatewlid@gmail.com, yatewlid@hotmail.com

ያት ቅጽ 1 ቁጥር 3……………………………………………………………………….………………..የካቲት ፮ ቀን ፪ ሺህ ፮

5

ትግላ ትዝታው

«ሇዘመናት በጭቆና ማጥ
በግፍ ሰንሰሇት ታስሬ
መብቴን ሊስከብር
ጨቋኝን ሌሽር
ተነስቻሇሁ ዛሬ
ይኸው ታጥቄሃሇሁ ዛሬ»

እየተባሇ የተዘመረው
ትግላ ትዝታው ዛሬም ህያው ነው።

«ሌቤ ቆርጦ ተነስቷሌ
የዯም አክታ ያገሳሌ
ይኸው ቆርጫሇሁ
አምጫሇሁ»

እየተባሇ የተዘመረው
ትግላ ትዝታው ዛሬም ህያው ነው።

«ማን ዯባሇቀው?
የምር ታጋዩን እኛ ስናውቀው
የምር ተኳሹን እኛ ስናውቀው
ታንክ ታቅፎ ጨረሱኝ ባዩን
ማን ዯባሇቀው?»

እየተባሇ የተገጠመው
ትግላ ትዝታው ዛሬም ህያው ነው።

«አንቺ ጭቁን ተነሽ ታገይ፤ ተነሽ ታገይ
ሇነፃነት፤ ሇዴርቡ ዕኩይ ስቃይ
ተጨቋኟ እህትዬ፤ እህትዬ
በቃሽ ተነሽ፤ አያዋጣም ሁላ ዬዬ»

እየተባሇ የተዘመረው
ትግላ ትዝታው ዛሬም ህያው ነው።

ያት ቅጽ 1 ቁጥር 3……………………………………………………………………….………………..የካቲት ፮ ቀን ፪ ሺህ ፮

6

«ጥሊሁን ሇምን ሇምን ሞተ?
ዋሇሌኝ ሇምን፤ ሇምን ሞተ?
ማርታ ሇምን፤ ሇምን ሞተች?
በሃይሌ በትግሌ ነው
ነፃነት የሚገኘው።»

እየተባሇ የተዘመረው
ትግላ ትዝታው ዛሬም ህያው ነው።

«ተው ስማኝ ሀገሬ፤ ኧረ ስማኝ ሀገሬ
ተው ስማኝ ሀገሬ፤ ሲከፋኝ ነው መኖሬ
በርከክ በርከክ አለ፤ አውሬ መስያቸው
ከሰው መፈጠሬን፤ ማን በነገራቸው
ስማኝ ያገሬ ሰው፤ በአንዴ ሊይ ተነሳ
ዴር ከተባበረ፤ ይጥሊሌ አንበሳ።»

እየተባሇ የተዘመረው
ትግላ ትዝታው ዛሬም ህያው ነው።

«አትነሳም ወይ? አትነሳም ወይ?
የግፍ አገዛዝ አይበቃህም ወይ?
ተነስ! ተነስ!»

እየተባሇ የተዘመረው
ትግላ ትዝታው ዛሬም ህያው ነው።

«ፍጹም ነው እምነቴ
ሇትግለ ነው ሕይወቴ
ሌጓዝ በዴሌ ጏዲና
በወዯቁት ጓድች ፋና»

እየተባሇ የተዘመረው
ትግላ ትዝታው ዛሬም ህያው ነው።

ተነሱ በአንዴነት
ተነሱ በሕብረት
ዛሬም በመዘመር
ክብር ሇየካቲት
ያ ትውሌዴን እንዘክር!!!

የካቲት 28 ቀን 1998 ዓ.ም (March 07, 2006) የተገጠመ።

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 10 years ago on February 14, 2014
  • By:
  • Last Modified: February 14, 2014 @ 1:10 pm
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar