www.maledatimes.com የዐፄ ምኒልክ ኅልፈት 100ኛ ዓመትና የዐድዋ ድል 118ኛ ዓመት መታሰቢያ ዝግጅት፤ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

የዐፄ ምኒልክ ኅልፈት 100ኛ ዓመትና የዐድዋ ድል 118ኛ ዓመት መታሰቢያ ዝግጅት፤

By   /   February 14, 2014  /   Comments Off on የዐፄ ምኒልክ ኅልፈት 100ኛ ዓመትና የዐድዋ ድል 118ኛ ዓመት መታሰቢያ ዝግጅት፤

    Print       Email
0 0
Read Time:240 Minute, 42 Second

1 8221 Georgia Avenue, Silver Spring, MD. 20910 www.moreshwegenie.org

ታህሳስ ፲፩፣፪ሺ፮ ዓ/ም
December 20, 2013

በዚህ ዝግጅት ፦
1 የምኒልክ ማንነትና በኢትዮጵያ ታሪክ ያላቸው ቦታ፣
2 የምኒልክ ስብዕና፣
3 ምኒልክ በውጭ ሰዎች ዕይታ፤
4 ምኒልክን የሚያወግዙ እነማን ናቸው? ለምን?
5 የዐድዋ ጦርነትና ውጤቱ፤ በተሰኙ ርዕሶች ዙሪያ ለውይይት የሚሆኑ መነሻ ሀሳቦች ይቀርባሉ።
የመነሻ ሀሳቦቹ ዝርዝር መረጃዎች የተጠናቀሩት፦
(1) ዳግማዊ ዐፄ ምኒልክ የአዲሱ ሥላጣኔ መሥራች፤ በሥርግው ሐብለሥላሴ፣
(2) አጤ ምኒልክ ፣ በጳውሎስ ኞኞ፣
(3) ዘመናዊ የኢትዮጵያ ታሪክ ፣ከፕሮፌሰር ባሕሩ ዘውዴ መጽሐፍት የተወሰዱ ናቸው።
1. የዐፄምኒልክ ማንነትና በኢትዮጵያ ታሪክ ያላቸው ቦታ፣
1.1 ትውልድና ዕድገት፣
 ምኒልክ ኃይለ-መለኮት ነሐሴ 12 ቀን 1836 ዓም አንጎለላ ልዩ ስሙ እንቁላል ኮሶ ከተባለ ቦታ ተወለዱ፣አንጎለላ በንጉሥ
ሣህለሥላሴ ዘመን የተመሠረተ ከተማ ነው። የምኒልክ ስም ምን ይልክ ነበር። ምኒልክ የተባለው ከመቅደላ መልስ
በኋላ ነው።
 እናታቸው ወ/ሮ እጅጋዬሁ አዲያቦ ይባላሉ። ምኒልክ በአባታቸውም ሆነ በእናታቸው ወገን ወንድም ሆነ እህት
እንዳላቸው የሚያመላክቱ መረጃዎች የሉም። ለዚህም ይመስላል እንዲህ ሲባል የተገጠመው፤
የመድኃኒት ጥቂት ይበቃል እያለች፣
የምኒልክ እናት አንድ ወልዳ መከነች፤ የተባለው፤
 ምኒልክ በአንጎለላ ኪዳነምህረት ክርስትና ተነሱ፤ የክርስትና ስማቸውም ሣህለ-ማርያም ተባለ።
 የክርስትና አባታቸው አለቃ ሐሤቱ የሚባሉ የሚጣቅ ዓማኑኤል አስተዳዳሪ ነበሩ፤ በመጀመሪያ የዘመኑን ትምህርትም
ያስተማሩዋቸው እኒሁ የክርስትና አባታቸው ናቸው።
 ምኒልክ በተወለዱ እስከ 11 ዓመት ከ11 ወር እስኪሆናቸው ድረስ በተወለዱበት አካባቢ በእናታቸውና ባባታቸው
እንክብካቤ እንደዘመኑ የታላላቅ ሰዎች አስተዳደግ ሥርዓት አደጉ።

MORESH WEGENIE AMARA ORGANIZATION
ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት
8221 Georgia Avenue, Silver Spring, MD. 20910
Tel: (202) 230 – 9423  Fax:  www.moreshwegenie.org
2 8221 Georgia Avenue, Silver Spring, MD. 20910 www.moreshwegenie.org

1.2 በ1848 የዐፄ ቴዎድሮስ ወደ ሸዋ መዝመት በሸዋ አስተዳደርና በምኒልክ ሕይዎት ያስከተለው ለውጥ፣
 ዐፄ ቴዎድሮስ የሰሜን ኢትዮጵያን መሣፍንቶች ተራ በተራ ድል ነስተው በ1848 የሸዋውን ንጉሥ ኃይለ-
መለኮትን ድል በመንሳት፤ለ150 ዓመታት ያህል የዘለቀውን የሸዋ መሣፍንት አስተዳደር እንዲቋረጥና
በማዕከላዊ አስተዳደር ሥር እንዲገባ አደረጉ።
 የንጉሥ ኃይለመለኮት ሥርዐተ ቀብር ኅዳር 1 ቀን 1848 ከተከናወነ በኋላ ወዲያውኑ ምኒልክ በአባታቸው
አልጋ ላይ እንዲቀመጡ ተደረገ፣
 ምኒልክ በቴዎድሮስ ተማርከው እስረኛ እስከሆኑ ድረስ ከኅዳር 1 ቀን እስከ ኅዳር 22 ቀን 1848 ድረስ ሸዋን
መርተዋል፤ ሞግዚታቸው አቶ ናደው እንዲሆኑ መኳንንቱ ወስነው ምኒልክን ሲረዱ መቆየታቸው ታውቋል፤
 የቴዎድሮስ ሸዋን ሙሉ ለሙሉ ለመቆጣጠር ምኒልክን እጅ ማድረግ አስፈላጊ ነበር፤ ይህ እንዲሆን ደግሞ
የሸዋ መኳንንቶችና የጦር መሪዎች ባለመፈለጋቸው ምኒልክን ይዘው ወደ ቡልጋ ሸሹ።
 ሆኖም የአብቹ ኦሮሞዎች የኃይለመለኮትን ሞት ሰምተው ስለነበር ምኒልክ ከቴዎድሮስ እጅ እንዳይገባ ይዘው
በመሸሽ ላይ ባሉት ሰዎች ላይ አጣብቂኝ ከተባለ ቦታ ላይ ጦርነት ገጠሟቸው፤ በዚህ ጦርነት (1) አቶ
አንዳርጋቸው፤(2) አቶ አንተን ይስጠኝ፤ (3) አቶ ባዛብህ { በኋላ ራሱን የሸዋ ንጉሥ ብሎ የሾመው} (4) አቶ
ከተማ አባ ውርጂ፣ (5) አቶ አብቱ (የምኒልክ ሞግዚት) ወዘተ ከፍተኛ የሆነ ጀግንነት ቢያሳዩም 6000(
ስድስት ሺ ) ያህል ሰንጋ በአብቹ ሰዎች ከመዘረፍ አላዳኑም።
 ቴዎድሮስ በአብቹ ኦሮሞዎችና በምኒልክ ተከታዮች መካከል ያለውን ጦርነት ከርቀት በመነፀር ይከታተሉ
ስለነበር፣ጦርነቱ የጠነከረው መሪ ቢኖረው ነው ብለው እንዲያምኑ አስገደዳቸው። በመሆኑንም
የኃይለመለኮትን መሞት በመጠራጠር መቃብራቸውን በማስከፈት አዩ፤ የኃይለመለኮትን መሞትም አረጋገጡ፤
 ምኒልክ ከአጣብቂኝ ጦርነት በኋላ ወደ ከሰምን ተሻግረው አረርቲ ላይ ሰፈሩ።
 ቴዎድሮድሮስም በመከታተል የቁር ላይ ሰፈሩ። ከዚህም ላይ ሆነው ጦራቸውን በሁለት በኩል ከፍለው
የምኒልክን እንቅስቃሴ ለመቆጣጠር አሰማሩ፤ በመሆኑም በራስ እንድዳ የሚመራው የቴዎድሮስ ጦር ምኒልክ
ወደ አንኮበር ለመመለስ እንዳይች በረከት ላይ እንዲቆርጥ ተደረገ። ይህን ምክር የሰጡ አቶ በድሉ የተባሉ
ሰው ናቸው። እንደተባለውም ምኒልክ ወደዚሁ ሥፍራ ሲያመራ በረከት ላይ ተከበቡ፤ ቀኑ ኅዳር 10 1848
ነበር, በጦርነቱም ራስ እንግዳ ተሸነፉ፤በዚህ ጦርነት በዛብህ ሲማረክ፣አቶ ሽሽጉና አቶ አብቱ ሞቱ፤ ይህን
የሰማች የዘመኑ አስለቃሽ እንዲህ ብላ ገጠመች፣

ቁርጡን ዐወቁና ያለ መኖርህን፣
በረከት አገቡት ጌታዬ ልጅህን፤
 የሸዋው ጦር ያሸነፈው የራስ እንግዳን ጦር እንጂ የቴዎድሮስ( የንጉሡን) አለመሆኑን ሲያረጋግጥ ምኒልክን
ይዞ ወደ ምንጃር አመራ፤
 ቴዎድሮስም ተከታትሎ ሸንኮራ ላይ ሰፈረ፤ የጦርነቱ ሁኔታ የማያዋጣ መሆኑን የተገነዘቡት የሸዋ የጦር
አበጋዞች ምኒልክን ለቴዎድዎስ ለማስረከብ ወሰኑ። በውሣኔአቸው መሠረትም ምኒልክን ይዘው ገቡ፤
 ቴዎድሮስ ምኒልክን እጅ ካደረጉ በኋላ ፤ለሸዋ አስተዳዳሪነት የሣህለሥላሴን ልጅ መርድ አዝማች ብለው
ሾሙት፤ አቶ አንዳርጋቸውን ደግሞ አበጋዝ አደረጉት፤
 ቴዎድሮስ ሸዋን ካደላደሉ በኋላ ምኒልክን ይዘው ጉዞ ወደ መቅደላ አደረጉ፣ ከምኒልክ ጋር የተጓዙ የምኒልክ
ረዳቶችና የቅርብ ዘመዶች (1) እናታቸው ወ/ሮ እጅጋዬሁ፣ (2) አጎታቸው አቶ በኋላ ራስ ዳርጌ፣ (3)
ሞግዚታቸው አቶ ናደው፤(4) አቶ ወልደጻድቅ፣ (5) በተለያዩ ምክንያቶች አብረው ያልሄዱትና በኋላ
የተቀላቀሉት ፣ለምኒልክም ከመቅደላ ለማምለጥ ከፍተኛ ተግባር የፈጸሙት አቶ ገርማሜ ወልደ ሐዋሪያት
ይገኙበታል,

1.3 ምኒልክ በመቅደላ፣
 ምኒልክ የመቅደላ ሕይዎታቸው የተመቻቸና ከቴዎድሮስ ጋርም የነበራቸው ግንኑኘት የአባትና የልጅ ያህል
ነበር፤
 ቴዎድሮስ አልጣሽ የተሰኘችውን ልጁን ለምኒልክ ድሮ አማቹ፣አደረገው፤የደጃዝማችነት ማዕረግም ሰጠው፣
 ምኒልክ መቅደላ በነበረ ጊዜ የፖለቲካ ሰዎች ያፈቅሩዋቸውና ያከብሯቸው እንደነበር ሄነሪ ስተርን የተባለ
ሚሲዮናዊ እንዲህ eሲል ጽፏል፤ 3 8221 Georgia Avenue, Silver Spring, MD. 20910 www.moreshwegenie.org

ነገር ቶሎ የሚገባው፣ጨዋና ግልጽ የአምባገነኑን ወዳጅነት ለማትረፍ ችሎ የንጉሣዊ ልዕልትን
የማይበገረውን የአሸናፊ ሴት ልጅ እጅን ለመጨበጥ (ለማግባት) ክብር አገኝቷል።በሀገሩ የተቀሰቀሰው ችግር
ከዚሁ ጋር ከቤተክህነትና ከወታደራዊ ኃይሎች እርዳት ለመስጠት የዋሹለት ተዳምሮ በልቡ ተቀብሮ የቆየውን
የአባቶቹን ዙፋን ለመውጣት የነበረውን ሀሳብ ቀሰቀሰው። ይኸውም የረጅም ሐረግ የኃይለኞች አያቶቹ ውርስ
ነው። (ሥርግው ሐብለ-ሥላሴ ገጽ 146)
 በሌላ በኩል ሊቀ ጠበብት ወልደ ማርያም የዐፄ ቴዎድሮስን የዘመን ታሪክ ያዘጋጁ ሰው የምኒልክን የመቅደላ
ሕይዎት እንዲህ ሲሉ ይገልጹታል፤
ንጉሥ ምን ይልክን የማይወድ አልነበረም። በመቅደላም ሲኖሩ በን ቁጣጣሽ ፣በመስቀል በፈረስ
ጉግሥ ጨዋታ ንጉሥ ምን ይልክን የሚመስል አይታይም ነበር፤(ሥርግው ሐብለ-ሥላሴ ገጽ 146)
 ምኒልክ በመቅደላ ቆይታቸው ለኋላ አስተዳደራቸው ጠቃሚ የሆኑ ዕውቀቶችን ለመሸመት ችለዋል፤ ለምሳሌ
መቅደላይ ላይ ታስረው ከነበሩት የእንግሊዝ እስረኞች ጋር በመገናኘት ስለአውሮፓ ሥልጣኔ ይጠይቃቸውና
እነርሱም ለማወቅ ያላቸውን ጉጉት በማየት የሚችሉትን ሁሉ ለጥያቄዎቹ መልስ ይሰጡት ነበር።
 ከአቡነ ሰላማና ከደጃዝማች ውቤ ጋር ወዳጅነት ከመመሥረታቸውም በላይ የቴዎድሮስ የበኩር ልጅ መሸሻ
የልብ ወዳጃቸው ነበር። በኋላ ላይ ከመቅደላ, ለማመለጥ የነዚህ ሁሉ ሰዎች ምክርና የመረጃ ልውጥጥ ወሣን
ሚና ተጫውቷል።
 ምኒልክ አብዛኛውን ጊዜአቸውን በቴዎድሮች የፍርድ አደባባይ ስለሚያሳልፉ ከፍተኛ የሆነ ዕውቀት
እንዲቀስሙ አስችሏቸዋል።

1.4 የምኒልክ ከመቅደላ አወጣጥ (ከ1857 እስከ 1870) ፤
 ምኒልክ ከመቅደላ ለማምለጥ ያደረጉት ዝግጅት የረቀቀና በከፍተኛ ደረጃ የሚጠበቅ ሚስጢር ነበር፣
 ከመቅደላ የማምለጡ ዋነኛ ተዋንያን ደጃዝማች ገርማሜ ወልደደሐዋርያት ነበሩ። እኒህ ሰው የጄኔራል
መንግሥቱ ንዋይና የገርማሜ ንዋይ አያት ናቸው።
 ገርማሜ ወልደሐዋርያት ምኒልክን ከመቅደላ ለማስመለጥ የተመረጡበት ዋና ምክንያት፣ከዐፄ ቴዎድሮስ ጋር
የሚቀራረቡ መሆኑ ነው። የቅርብርቡ መሠረትም የቴዎድሮስን ዘመድ ቀጠሮ መርሶን ማግባታቸው ነው።
 ገርማሜ ዕቅዱን ለማሳካት ከቴዎድሮስ ጋር የነበራቸውን መቀራረብ በመጠቀም፣ፍታውራሪ ሀብተሥላሴ
ደስታ የተባሉት ከወሎ ገዥቱ ከወርቂት መንገድ እንዳትዘጋባቸው የማለዘቡን ሥራ ሠርተዋል። በዚህ
ውለታም ፊታውራሪ ሀብተ ሥላሴ የገርማሜን ልጅ ወ/ሮ ዘለቃን እንዲያገቡ ሆኗል። ሀብተሥላሴ የመጓጓዣ
ፈረሶችና አጃቢዎችን በማዘጋጀት ረድተዋል።
 የአወጣጡ ዕቅድ ከተዘጋጀ በኋላ ገርማሜ በማምለጫው ቀን ታላቅ ድግስ ደገሡ። ድግሡ የተደገሠው
በተክለ ሃይማኖት ዝክር ስም ነበር።
 በጠበሉም ሁሉም ሰው ተጋበዘ፤ጠባቂዎቹ ከመብል መጠጡ ገፋ ገፋ አድርገው እንዲወስዱ ተደረገ።
 የአንባው ጠባቂዎች በመጠጥ ኃይል ተሸንፈው ሲተኙ ሀብተሥላሴ ምኒልክን እና እናቱ ይዞ ወጣ።
 ምኒልክ ከመቅደላ ያመለጡት ሰኔ 24 ቀን 1857 ነው።

1.5 ምኒልክ ከመቅደላ መውጣትና የጋዲሎ ውጊያ፣
 ምኒልክ ከመቅደላ ወጥተው 35ኪሜ ላይ ከምትገኝ መስቀላ ከምትባል ቦታ ይደርሳሉ። ይህ ቦታ በወ/ሮ
ወርቂት ቁጥጥር ሥር ስለነበር የእርሷሰዎች ምኒልክን መሣሪያቸውን ገፈው በቁጥጥር ሥር አዋሏቸው።
 ወርቂት የምኒልክን እጅ ይዛ በቴዎድሮስ ቁጥጥር ያለውን ልጇን በልዋጭ ለማስፈታት የሐይቅን መነኮሳት
ወደ ቴዎድሮስ ላከች። ሆኖም መልክተኞቹ መቅደላ ሳይደርሱ የወርቂት ልጅ አመዴ መገደሉን ሰምተው
ተመለሱ። ወርቂትም « ሰው ካዳነው እግዜር ያዳነው» ብላ ምኒልክን ከሸኝ ጋር ወደ ሸዋ ድንበር አሊ ቡኮ
ድረስ ሸኘቻቸው።
 በሌላ በኩል የሸዋ ገዥ የሆነው በዛብህ የምኒልክን ከመቅደላ ማምለጥና ቦሩ ሜዳ መድረሱን እንደሰማ፣ሁለት
ሺህ ብርና በርካታ ፈረስና በቁሎ ለወርቂት በመላክ ምኒልክን አስራ እንድታስረክበው ጠየቃት።
 ሆኖም የበዛብህ መልክተኞች ወርቂት ዘንድ ሳይደርሱ ምኒልክ ጉዞውን አፋጥኖ መንዝ ግሼ ገቡ። 4 8221 Georgia Avenue, Silver Spring, MD. 20910 www.moreshwegenie.org

 ምኒልክ ግሼ እንደገቡ፣የግሸው አስተዳዳሪ አቶ ወልዴ አሻግሬ 300 ጠብመንጃ አንጋቾች ጋር ገባላቸው።
በማከታተልም የአንጾኪያው አገረ ገዥ ከሊል ነሚ ከነሠራዊቱ ገባላቸው።
 በሌላ በኩል የይፍራታው ገዥ አቶ ሀብተየስ የበዛብህ ወዳጅ በመሆኑ በተቃዋሚነት ተሰለፈ። ምኒልክ
ሀብተየስን እንዲወጋ ጉላሽ የተባለውን የጦር መሪ ላኩ። በውጊያው ሀብተየስ ተሸነፈ። ይህም ለምኒልክ
ለመጀመሪያ ጊዜ ሸዋ ላይ ያደረገው ጦርነትና ድል መሆኑ ነው።
 ወርቂት ምኒልክን እንዲሸኙ የሰጠቻቸው ሰዎች ወደኋላ አንመለስም ብለው ለምኒልክ በማደራቸው ለኃይሉ
ጥንካሬ ተጨማሪ ድጋፍ ሆነዋቸዋል።
 የዳየርን አምባ ይጠብቅ የነበረው የቴዎድሮስ ሹም ያላንዳች ማንገራገር ለምኒልክ በመግባቱ ቁልፍ ወታደራዊ
ቦታ በምኒልክ እጅ ገባ።
 ምኒልክ ከይፍራታ ድል በኋላ ነሐሴ 13 ቀን 1857ዓም ከመቅደላ ከወጣ ከ49 ቀን በኋላ ግድም ገቡ። የግድም
ሰው ከትንሽ እስከ ትልቅ በደስታ ተቀበላቸው።
 በዛብህ ግን ምኒልክን ለመውጋት ተነሳ። የበዛብህን የመዋጋት አቋም ያያች እናት አይዋጁ የተባለች አዝማሪ
እንዲህ ብላ ገጠመች፣
ማነው ብላችሁ ነው ጋሻው መወልወሉ፣
ማነው ብላችሁ ነው ጦራችሁ መሳሉ፣
የጌታችሁ ልጅ ነው ኧረ በስማም በሉ፤

ንጉሡም ቢሰጡህ ዳር ዳሩን ተዋጋ፣
ውረድ ማለት ይቅር ልጅን ካባቱ አልጋ፤
 ይህ ሁላ ምክር ቢሰጠውም በዛብህ ምኒልክን ለመውጋት ቁርጥ ሀሳብ አድርጎ ሐምሌ 23 ቀን 1857 ጋዲሎ
ከተባለው ቦታ ላይ የምኒልክን ጦር ገጠመ። በዚህ ጦርነት በዛብህ ተሸነፈ። እርሱም ሸሽቶ አፍቀራ አምባ
ዘልቆ መሸገ።
 ምኒልክ ጋዲሎ ሳለ፣የሱባ፣ የጥሙጋ፣ የአርጡማና የከረዩ ባላባቶች ግብር አገቡለት። ከዚያም ጉዞ ወደ
አንኮበር ሲቀጥል ማፉድ ላይ የታች ይፋት አበጋዝ ወላስማ ተቀበላቸው። ነሐሴ 29 ቀን 1857 ዓም
በሐራምባ አድርገው አንኮበር ገቡ።
 ምኒልክ አንኮበር እንደገቡ የወጋቸውን የበብህን ሠራዊት በሙሉ ምረው ወደ ተለመደው መኅበራዊ ሕይዎት
እንዲገባ አደረጉ።
 ተከታትሎም የአባቶቻቸው የየደንቡ ሠራተኛ ነፍጠኛ፣ጋሼኛ፣ ገንበኛ፣ ሥራ ቤት፣ ቋሚና ለጓሚ ሁሉም
ተሰባስቦ መደበኛ ሥራውን ለማከናዎን ተዘጋጀ፤ የአዕምሮው ሥራን የሚመለከተውን ወልደመድኅን የተባለ
የጸሐፊ ትዛዝነቱን ኃላፊነት ተረከበ፣ ይህ ሰው የመጀመሪያው የምኒልክ ጸሐፊ ትዕዛዝ መሆኑ ነው። እስከ
1867 ድረስ የጸሐፊ ትዛዝነቱን ኃላፊነት የተወጣ ነው።
 በዛብህ ምኒልክን የወጋው በሰዎች ተገፋፍቶ እንጂ እርሱ የምኒልክ አፍቃሪ እንደነበርና ቀደም ሲልም ምኒልክ
በቴዎድሮስ ከመማረካቸው በፊት ከምኒልክ ጎን ሆኖ የተዋጋ ለመሆኑ የሚያመላክቱ በዘመኑ እንዲህ ተብሎ
ተገጥሞ እናገኛለን።
አባ ደክር በዙ የበረከት ለታ እሽንጡ ተወግቶ ፣
ከሻንቅላ ጋራ አብሮ ተቆራኝቶ፣
አልጋ ለምኒልክ እያለ ቆይቶ፣
ሊወጋቸው ሄደ የሰው ነገር ሰምቶ፤
አንተም አደረከኝ የመነኩሴ ፈራጅ፣
የሙት ልጅ ሲቀበል እንዲህ ነዎይ ወዳጅ፤
 በዛብ አፍቀራ ሆኖ ምኒልክ ምህረት እንዲያደርጉለት ጠየቀ። ምህረትም ተደረገለት፤ግን ተከታዮቹን አፍቀራ
ትቶ ራሱ ገባ።ሲገባ የተቀበለው የራሱ አሽከር የነበረው ጎበና ዳጨ ነበር። ለበዛብህም መተዳደሪያ ተጉለት
ውስጥ ጉልት ተሰጠው። ሆኖም በዛብህ ለጦርነት ይዘጋጃል የሚል ክስ ተመሥርቶበት ክሱ በማስረጃ
በመረጋገጡ ለፍርድ ቀረበ። በፍርዱም ሂደት(1) ምኒልክ ከመቅደላ አምልጠው ሲመጡ የአባቱን አልጋ
አለቅም ብሎ በመዋጋቱ፤(2) ምህረት ከተደረገለት በኋላ የአመጽ ሥራ ሲሢራ በመገኘቱ፣(3) የአፍቀራን
አምባ እንዲያስረክብ ቢጠየቅ የተለያዩ ምክንያቶች እየፈጠረ አላስረክብም በማለቱ ጥፋተኛ ያደርገዋል ተብሎ
በጥይት ተደብድቦ እንዲሞት ተወሰነበት።
ስለበዛብህ አሟሟት በርካታ ግጥሞች ተገጥመዋል፤ ከነዚም የሚከተሉት ይገኛሉ፤
ጋላም አርፈህ ተኛ፣አውልቀህ ጀልዶህን፣ 5 8221 Georgia Avenue, Silver Spring, MD. 20910 www.moreshwegenie.org

ያማራውም ጎበዝ ፍታ ኮርቻህን፣
በእሳት አቃጠሉት የሚያባንንህን፤
አንተም ጨካኝ ነበርክ ጨካኝ አዘዘብህ፣
እንደገና ዳቦ እሳት ነደደብህ፤
 በሌላ በኩል የበዛብህ አፍቃሪ የነበረችው እናት አይዋጁ የተሰኘችው የቡልጋ አዝማሪ እንዲህ ብላ ስለበዛብህ
ገጥማለች።
መንዝንም አየሁ፣ቡልጋንም ተጉለትም አየሁ፣
ማፉድንም ቀወትንም ይፋትንም አየሁ፣
ብፈልግም አጣሁ እንዳንተ ያለሰው፣
አመድክንም አጣሁ በእንቅብ እንዳላፍሰው።
የወንድ ወስከምቢያዬ የአክርማ ሰፌዱ፣
ምነው ተታለለ አባ ደክር ወንዱ፣
ጥንትም በቀረበት ከአፍቀራ መውረዱ።
ቢመክሩት አይሰማ እሱ የለው መላ፣
በእሳት አቃጠሉት ያንን መሳይ ገላ።

 በዚን ጊዜ በመንግሥት ላይ አድማ ሲያውጠነጥን የተደረሰበት ሰው ምህረት የለሽ ቅጣት የሚቀጣ በመሆኑ
በዛብህም ለዚህ ቅጣት በቃ። ሲፈረድም ` `አዋጅ አፍራሽ ቤተክርስቲያን ተኳሽ“ ይባል ነበር። በዚህም የተነሳ
የበዛብህ ንብረትና ጉልት ተወረሰ። አበጋዝነቱ ለአባ ወሎ ተሰጠ። ንብረቱም ለደጃዝማች ገርማሜ
ወልደሐዋርያት ተሰጠ። ሆኖም ገርማሜ በጀግንነት ከበዛብህ ጋር አቻ ባለመሆናቸው የበዛብህ ንብረት
ለገርማሜ መሰጠቱን ሕዝቡ አልወደደም። በዚህም የተነሳ እንዲህ ሲባል ተገጠመ፣
የበዙ ፈረሶች ጠለፉና ቦራ፣
በምን አገኛቸው የኋላ መከራ፣
ቂርቂሚጥ ይመስል ባንድ እግር ኩርኮራ፤
አጎቱን አልከፋው ወንድሙም አልከፋው፣
ልጁንም አልከፋው ቦራን ብቻ ከፋው፣
ገርማሜ ቢጭነው የጉንጩን ሣር ተፋው፤
የበዙ ፈረሶች ቦራና ጠለፉ እንዴት ይገርማቸው፣
ገርማሜ ባንድ እግሩ ሲኮረኩራቸው፤
ንጉሡ ሲሰጡ እርሱ መቀበሉ፣
ከነልቡ ነዎይ ከናደፋፈሩ፤

 በእናት አይዋጁ ላይ የቀረበ ክስና የምኒልክ ፍርድ፦ እናት አይዋጁ የዚያን ጊዜዋ ገጣሚና አዝማሪ ናት።
እርሷም በበዛብህ ላይ የተወሰነውን ቅጣት የሚያወግዝ የሚከተለውን ግጥም ገጠመች።
የነብርን መንጋጋ ፍየል ገብቶ ላሰው፣
እንዲህ አይደለም ወይ ጊዜ የጣለው ሰው።
 በዚህ ግጥሟ እናት አይዋጁ ተከሰሰች። ክሱ ይሙት በቃ የሚያስፈርድ ነበር። ሆኖም የክሱ ሂደት ቀጥሎ
ትችት ሲሰጥ አቶ አቦዬ፣የንጉሥ ሣህለሥላሴ አማች፤የበሻህና የንጉሥ ወልደጊዮርጊስ አባት፣ከሣሹን የማረባ
ክስ ነው ብለው ካጣጣሉ በኋላ፣«ይህች አንዲት ደሐ የዕለት ጉርሷን ለማግኘት የቀባጠረችው ስለሆነ
ሊያስከስሳት አይችልም »በማለት አስተያየት ሰጡ ። ምኒልክም በሐሳቡ ተስማምተው እናት አዋይጁ በነጻ
እንድትለቀቅ ወሰኑ።

1.6 የምኒልክ ሥልጣን መደላደል፤
 ምኒልክ ከጋዲሎ ድል በኋላ መቀመጫቸውን ሊቼ ላይ አደረጉ። ይህች መጀመሪያ የቆረቆሯት ከተማ
መሆኗ ነው። የሸዋም ሕዝብ በደህና ተቀበላቸው።
 አስተዳደራቸውን በይፋ ከመጀመራቸው በፊት ዘውድ መጫን እንዳለባቸው ወሰኑ። ለዘውድ መጫኑ
ሥርዓትም ከልቼ ይልቅ ደብረብርሃንን መረጡ። 6 8221 Georgia Avenue, Silver Spring, MD. 20910 www.moreshwegenie.org

 ዘውድ ሲጭኑም እንደሥርዓቱ በጳጳስ ወይም በእጨጌ ሳይሆን በካህን ነበር። ዘውድ የጫኑትም
ንጉሠ ነገሥት ተብለው ነው።
 ምኒልክ ንጉሠነገሥት በሚለው መዕረግ የተጠቀሙት እስከ 1870 ድርስ ነው።
 ምኒልክ በ1860 ኤደን ለሚገኘው የእንግሊዝ የቅኝ ግዛት ባለሥልጣንና ለንግሥት ቪክቶሪያ በጻፉት
ደብዳቤ ራሳቸውን ያስተዋወቁት ንጉሠ ነገስት ብለው ነው።
 ምኒልክ ለእንግሊዝ ባለሥልጣኖች የጻፉት ደብዳቤ መልዕክት ያተኮረው በሁለት ጉዳዮች ላይ
ነው።(1) ካያታቸው ሣህለሥላሴ ጋር የነበራቸውን ግንኙነት ለማደስ ።(2) በቴዎድሮስና
በእንግሊዞች መካከል ጦርነት መካሄዱ የማይቀር መሆኑን በመገንዘብ ተተኪው ንጉሥ እርሳቸው
እንደሚሆኑ እንዲያውቁላቸው ለማድረግ ነበር።
 እንግሊዞችም አጋር የሚፈልጉበት ወቅት ስለነበር ለምኒልክ ደብዳቤ ከፍተኛ ግምት በመስጠት
መልስ ሰጥተዋል። መልሱም ቴዎድሮስን ለመውጋት እየተዘጋጁ መሆኑን በመግለጽ፣ የጦርነቱም
ዓላማ፣እስረኞችን ለማስለቀቅ እንጂ፣ አገሪቱን ለመያዝ እንዳልሆነ ገልጸውላቸዋል። ምኒልክም
እንዲተባበሩዋቸው ጠይቀዋቸዋል። ለመተባበር ባይፈልጉም ገለልተኛ ሁነው እንዲቆሙ
መክረዋቸዋል። ከዚህ አልፈው ለቴዎድሮስ ቢረዱ ወይም ከለላ ቢሰጡ እርሳቸውንም
እንደሚወጉዋቸው አስጠንቅቀዋቸዋል። ከረዱዋቸውም ሲመለሱ የጦር መሣሪያ እንደሚሰጧቸው
ቃል ገብተውላቸዋል።
 ምኒልክ ግን እንደሁለተኛ አባት ሆነው ባሳደጉዋቸውና ልጃቸውን በዳሩላቸው ቴዎድሮስ ላይ
ክንዳቸውን ማንሳት አልፈለጉም።
 ምኒልክ ለሚፈልጉት ሥልጣን መደላደል የጦር መሳሪያ እጅግ አስፈላጊያቸው ስለነበር ከናፒዬር
መሣሪያውን እንዲረከብ ደጃዝማች ጎበናን ልከው ነበር፤ ሆኖም ወሎዬዎቹ መንገድ ስለዘጉበት
ሳይደርስ ቀረ። መሣሪያውን ካሣ ምርጫ ተረከቡት።
 ምኒልክም ሌላ አማራጭ በመፈለግ የጦር መሣሪያ የሚያፈላልግ ሰው ወደ ውጭ ለመላክ ቁርጥ
አደረጉ። በዚህም መሠረት አባ ሚካኤል የተባሉትን ሰው በመምረጥ መልዕክታቸውን ይዘው ወደ
ጣሊያን፣ ፈረንሳይ እና እንግሊዝ በ1863 ላኩ።
 አባ ሚክኤል ከጣሊያን ንጉሥ ኡምቤርቶ ጋር በመገናኘት ስለሸዋ የተጋነነ መግለጫ ሰጡ።
ተመሳሳይ መግለጫም ለጣሊያን የጂኦግራፊ ማኅበር አደረጉ። በዚህም የሕዝቡን ልብ ወደ ኢትዮጵያ
አማለሉት። በዚህም የተነሳ የጣሊያን የጂኦግራፊ ማኅበር በአንቲኖሪ የሚመራ የልዑካን ቡድን
ወደአንኮበር ላከ። ሆኖም ቡድኑ ለምኒልክ ያመጣው ገጸበረከት የምኒልክን ፍላጎት የሚያሟላ
ባለመሆኑ በምኒክል ዘንድ ቅሬታን አሳደረ። የምኒልክ ፍላጎት መሣሪያ ነበር፤ የንጉሡን ቅሬታ
የተገነዘበው ማሳያ ለጣሊያን ሲሰልል የኖረ ሚሲዮናዊ ለአንቲኖሪ ለራሱ መጠበቂያ ከያዘው መሣሪያ
ለምኒልክ እንዲሰጠው አሳሰበው። አንቲኖሪም በተሰጠው ማሳሰቢያ መሠረት መቶ ጠብመንጃ
ለምኒልክ ሰጠ። በዚህም የምኒልክ ቅሬታ ረገበ።
 እስክንድርያ ነዋሪ የነበረ አርኖ የተባለ ፈረንሳዊ ነጋዴ የንግድ ሥራ ከሸዋ ጋር ለመጀመር ወደ
አንኮበር ሄደ። ዘመኑም አውሮፓውያን በመብራት የሚፈለጉበት ወቅት ስለነበር፣ለአርኖ መልካም
አጋጣሚ ሆነለት። በምኒልክ ዘንድ መልካም አቀባበልን አገኘ። አርኖም የምኒልክን ፍላጎት በመረዳቱ
ወዳጅነቱን አተረፈ።
 አርኖም ባገኘው ወዳጅነት በመጠቀም የፈረንሳይ ሰዎች ወደሸዋ መጥተው የእርሻና የኢንዱስትሪ
ሥራን እንዲያሻሽሉ፣ሀሳብ አቀረበ። ሐኪሞች ከአውሮፓ አስመጥተው የሕዝቡን ጤንነት
እንዲከባከቡ፣ማተሚያ ቤትና የወረቀት ፋብሪካ እንዲያቋቁሙ፣የራሳቸውንም ገንዘብ እንዲያሳትሙ
ለምኒልክ ሀሳብ አቀረበ። በሀሳቡም ምኒልክ ተስማሙ።
 አርኖ በአንኮበር አንድ ዓመት ያህል ከቆየ በኋላ ወደ አረገሩ ሲመለስ፣ጉዞው በግብፅ በኩል ስለነበር
ምኒልክ ለእስማኤል ፓሻ ሰኔ 10 ቀን 1868 የተጻፈ ደብዳቤ እንዲያደርስ ሰጡት።
 ይህ ወቅት ኢትዮጵያና ግብፅ በጦርነት ውስጥ የነበሩበት መሆኑ ይታወቃል። በደብዳቤው ምኒልክ
ለእስማኤል ፓሻ ያስገነዘቡት ፍሬ ሀሳብ የሚከተሉት ናቸው። (1)በግብፅና በአፄ ዮሐንስ መካከል
ጦርነት የሚካሄድ መሆኑን፣ (2) የግብፅ የመስፋፋት ፍላጎት በሰሜን ብቻ ተወስኖ የማይቀር መሆኑን
እና ግብጽ በያለበት እጇን ያስገባች መሆኗን፤ምሳሌ ሐረር፣(3) ሰሜኑን ምሥራቁ የማይነጣጠሉ
የኢትዮጵያ አካሎች መሆናቸውን አስገንዝበዋል፣(4) እነዚህን ግብፅ የምትከጅላቸውን አገሮች
ካስፈለገ ከወራሪ የመከላከል መብታቸው የተጠበቀ መኖኑን አስረድተዋል፣(5) ምኒልክ ከጎረቤት
አገሮች ጋር በሰላም ለመኖር ፍላጎታቸው መሆኑንና ለዚህም የንግድ ውል ለመዋዋል አርኖን
የወከሉት መሆኑን ጠቅሰዋል። 7 8221 Georgia Avenue, Silver Spring, MD. 20910 www.moreshwegenie.org

 አርኖ ከኢትዮጵያ ከወጣ በኋላ ተመልሶ መግባት ባለመቻሉ በእርሱ ምትክ ሌዎን ሸፍኖ የተባለ
ፈረንሳዊ ጠብመንጃ ለመሸጥ ወደ አንኮበር መጣ። እርሱም አንኮበር ከገባበት ጊዜ ጀምሮ የምኒልክ
አገልጋይ ሆኖ ኖረ።
 ምኒልክ የጦር መሣሪያ ማግኘት ቅድሚ የሰጡት ጉዳይ ቢሆንም ሌሎች ጸጥታን የማስከበር
ሥራዎችንም ቸል አላሉም። በዚህም መሰረት ጸጥታን ለማስከበር የተለያዩ ዘመቻዎችን አካሂደዋል።
 1860 ላይ ቴዎድሮስ ሞተዋል፣ተክለጊዮርጊስ (ዋግሹም ገብረመድኅን) ነግሠዋል። ይም ራሳቸውን
ንጉሠነገሥት ካሉት ምኒልክ ጋር ጦር የሚያማዝዝ ነው። የምኒልክ ጉልበት ገና አልጠናም። እናም
ጊዜ መግዛት ነበረባቸው። በመሆኑም አጎታቸውን ራስ ዳርጌን ልከው ዘቢጥ ላይ ከተክለጊዮርጊስ ጋር
እንዲገናኙ በማድረግ ምኒልክ የሚከተሉትን ነገሮች ሊያሟሉ ስምምነት ተደረገ። (1)የተክለጊዮርጊስን
ንጉሠ-ነገስትነት ምኒልክ ሊያውቅ፣(2) የዓመት ግብር ምኒልክ ለተክለጊዮርጊስ ሊከፍል የሚሉ
ናቸው። ለዚህው ስምምነት ተፈጻሚነትና መጽናትም የአፄ ተክለጊዮርጊስ የእናት ልጅ ደጃዝማች
ኃይሉ ወልደ ኪሮስ የራስ ዳርጌን ልጅ ወ/ሮ ትሰሜን እንዲያገቡ ሆነ።
 በትግሬ ደጃዝማች ካሣ ፣የሹም ተንቤን ምርጫ ልጅ ከናፔየር ባገኘው የጦር መሣሪያ ተጠናክሮ
ሥላጣን ለመያዝ በዝግጅት ላይ ነበር። በመሆኑም በ1863 ዓም ዓድዋ ላይ ከንጉሥ ተክለ-ጊዮርጊስ
ጋር ባደረጉት ጦርነት ድል ቀንቷቸው ጥር 13 ቀን 1864ዓም አክሱም ፂዮን ዘውድ ጭነው IoH,ንስ
4ኛ ተብለው ነገሡ። ለካሣ ምርጫ ወይም ዮሐንስ 4ኛ ብቸኛ የሥልጣን ባለቤት ለመሆን የቀራቸው
ምኒልክን ማስገበር ነው።
 ምኒልክ በበኩላቸው የሥላጣን ባለቤት ለመሆን ኃይላቸውን ማጠናከር ይዘዋል። ለዚህም በ1859
ላይ በአንድ ጊዜ በሁለት አቅጫቻዎች፣ማለትም በሰሜን ወሎ፣በደቡብ ጉራጌ የኃይል ፍተሻ ዘመቻ
አካሄዱ። የወሎ ዘመቻ ዓላማ ከመቅደላ ሲያመልጡ ድጋፍ ለሰጠቻቸው ወ/ሮ ወርቂት ከባላጣዋ
ከወ/ሮ መስተዋት ጋር ለምታደርገው ጦርነት የመንፈስ ወይም የጉልበት እገዛ ለማድረግ ነበር።
በዚህም በሁለቱ ባላንጣሞች መካከል ይደረግ የነበረው ግብግብ ሁለቱን የሴት አበጋዞች ያዳከመ
መሆኑን ምኒልክ በመገንዘባቸው፣በዚህ አቅጣጫ ሥጋት የማይገባቸው መሆኑን አረጋገጡ።
 ምኒልክ የትኩረት አቅጣጫቸውን ወደ ሰሜን በማዞር በ1860 ወሎን አጠቃለው በግዛታቸው ሥር
አስገቡ። የወሎንም ግዛት ለመሐመድ ዓሊ ለወ/ሮ ወርቂት የእንጀራ ልጅ ሰጡ። በማከታተልም
በ1861 በጥር ወር ወረኢሉ ከተማን በመቆርቆር አሥር ሺህ ወታደር አሰፈሩባት። የዚህም ግብ
ምኒልክ ከሰሜን አቅጣጫ ለሚሰነዘርባቸው ጥቃት እርሳቸው እስኪደርሱ ለመከላከል እንዲቻል
ነበር።
 በደቡብ በኩልም ለተመሳሳይ ግብ የእንዋሪን ከተማ ቆረቆሩ። እንዋሪም የአስተዳደራቸው ማዕከል
አደረጉ።ዘውዲቱ ምኒልክ ሚያዝያ 22 ቀን 1868 በዚቺው ከተማ ተወለዱ። የዘውዲቱ እናት ወ/ሮ
አብቺው የወሎ ሴት ናቸው። ምኒልክ ከዘውዲቱ በፊት ከተለያዩ ሴቶች አንድ ሴትና አንድ ወንድ
አስወልደው ነበር። የሴቷ ስም ሸዋረጋ ሲሆን እናቷ ደስታ የሚባሉ የተጉለት ሰው ናቸው።ሸዋረጋ
የተወለደችው በ1860 ነው። የሸዋረጋ የመጀመሪያ ባል ወዳጆ ጎበና ዳጨ ነበር። ቀጥሎ ራስ
ሚካኤልን በማግባት ወሰን ሰገድና ኢያሱ ሚካኤል የሚባሉ ልጆች ወልዳለች።
 የምንሊክ ወንድ ልጅ አስፋ ወሰን የሚል ነበር።እናቱም ወ/ሮ ጌጤ የሚባሉ የሜጫ ተወላጅ ናቸው።
አስፋ ወሰን በ15 ዓመቱ በ1880 አረፈ።
 ምኒልክ በ1869 ወደ ጎንደርና ጎጃም ዘመቱ። የዘመቻውም ዓላማ ሕዝቡን በዮሐንስ ላይ
ለማስተባበር ነው። በዚህ ዘመቻ የየጁው ገዥ ደጃዝማች ወሌ ጉግሳ ገቡላቸው። የጎጃሙ ራስ አዳል
ተሰማ የምኒልክን የጦር የበላይነት መዝነው ከምኒልክ ጋር ለጊዜው ላለመጋጨት ወሰኑ።

1.7 የምኒልክና የባፈና ፍጥጫ፣
 ባፈና ምኒልክ ሸዋ ከገቡ በኋላ ያገቧቸው ሁለተኛ ሚስት ናቸው። ባፈና ምኒልክን በዕድሜ ብዙ
የሚበልጡ ብቻ ሳይሆኑ፣ ልጆቻቸው ምኒልክን የሚበልጡ ነበሩ። ባጭሩ እናታቸው ነበሩ ማለት
ይቻላል። የስምንት ልጆች እናት ነበሩ። እንደሊቀጠበብት ወልደማርያም አባባል፣የወ/ሮ ባፈናና
የምኒክል ግንኙነት የተጀመረው ፣ምኒልክ ከመቅደላ አምልጠው ወደ አንኮበር ሲያመሩ ሾላ ሜዳ ላይ
ነው። ባፈና ውብ ቆንጆ፣ነገር አዋቂ ከመሆኗም በላይ ወንዶች ዓይተው የሚወድቁላት በመሆኗ
ምኒልክም የውበቷ ምርኮኛ ሆነው አገቧት። የሁለቱ ጋብቻ በቁርባን ሳይሆን በሰማኒያ ነበር። ባፈና
ግን በቁርባን እንዲሆን ፈልጋ ነበር። ምኒልክ ግን ፈቃደኛ አልሆኑም። ፈቃደኛ ያልሆኑትም ባፈና 8 8221 Georgia Avenue, Silver Spring, MD. 20910 www.moreshwegenie.org

የማይወልዱ በመሆናቸው ነው። አልጋ ወራሽ ይፈልጉ ስለነበር፣ እርሷም በበኩሏ ልጆቿ አልጋ
ወራሽ እንዲሆኑ ትመኝ ስለነበር በምኒልክ ላይ ሴራ ማሴር ጀመረች።
 ለሴራዋም የምኒልክን ወንድም መርዕድ አዝማች ኃይለሚካኤልን ከጎኗ አሰለፈች። ይህ ሰው
መርሐቤቴ ታሞ ላይ ለረጅም ጊዜ በመታሰሩ የሪህ በሽተኛ ሆኖ ነበር። ምኒልክ ከመቅደላ እንደመጡ
ወደ ቤጌምድር ከመዝመታቸው በፊት ኃይለሚካኤልን ፈትተው በመንከባከብ ለመተዳደሪያ
እንዲሆነው ቡልጋን ሾመውት ነበር። ሆኖም ወርቅ ላበደረ ጠጠር ይሉት ሆኖ፤በባፈና ጉትጎታ
በምኒልክ ላይ የባፈና ሴራ ተባባሪ ሆነ። በዚህም መሠረት ምኒልክ ወደ ቤጌምድር ሲሄዱ እርሷም
ከነገሩ የሌለችበት ለማስመሰል አብራ እንደምትሄድና በዚህ ጊዜ ኃይለሚካኤል አመጹን አካሂዶ
ምኒልክን እንዲገለብጥ ተስማሙ።
 ምኒልክ ወደ ጎጃምን ጎንደር ሲዘምቱ እንደራሴ ያደረጋቸው ደጃዝማች ገርማሜንና አዛዥ
ወልደጻድቅን ነበር። ምኒልክ ጎጃም በገቡበት ወቅት ኃይለሚካኤል ከመሸሻ ኃይሌ ጋር በማበር
ኣንኮበርን ለመያዝ ጦርነት ከፈተ። እንደራሴዎቹ በቦታው አልነበሩም፣ሆኖም ፓቴ የተሰኘው
የምኒልክ ወዳጅ ፈረንሳዊ ጥቂት ወታደሮች አስከትሎ ጎሩ ሜዳ ላይ መርዕድ አዝማች ኃይለሚካኤል
ጦር ጋር ገጠመ። በጦርነቱም ኃልሌ ቀናው፤ ፓቴ ከሁለት ወታደሮች ጋር ሞተ። ወህኒ አዛዥ
ወልደጻድቅ ከምርኮ አምልጦ ፍቅሬ ግንብ ገባ። ይህ የተፈጥሮ ምሽግ ነው። ኃይሌም አንኮበርን ይዞ
መንገሡን አወጀ።

1.8 የባፈናና የመርዕድ አዝማች ኃይለ-ሚካኤል ፍጻሜ፣
 የኃይለሚካኤል አዋጅ እንደተሰማ የምኒልክ መልዕክተኞች ፍቼ መድረሳቸውን ኃይለሚካኤል
ሲሰማ፣አንኮበርን ለቆ ወደ ሚጣቅ ዓማኑኤል አመራ፤ የኃይሌን አንኮበርን መልቀቅ የሰሙት
ደጃዝማች ገራማሜ፣አፈንጉስ በዳኔ፣አዛዥ ወልደጻድቅ፣ አቶ አንተነህ ይስጠኝ፣ አቶ ቸርነት፣ አቶ
ድል ነሳሁና አቶ ይገዙ ተከታትለው መርሶዕድ አዝማች ኃይሌን ሚጣቅ አጠገብ ገጠሙት።
በግጥሚያውም መርዕድ አዝማች ኃይለሚካኤል ቆስሎ ተማረከ። መሸሻ ኃይሌም ተመሳሳይ እጣ
ገጠመው።
 ወ/ሮ ባፈና የኃይለሚካኤልን መሸፈት ጎጃም ላይ ከምኒልክ ጋር እንደሰማች፣ነገሩን ለማብረድ
ቀድሜ እኔ ልሂድ ብላ ምኒልክን ጠየቀች። ምኒልክም ነገሩ ሳይገባቸው ፈቀዱላትና ቀድማ ወደሸዋ
ጉዞ ጀመረች። ጉዞ ስትጀምርም በሌጣ ወረቀት ላይ የምኒልክን ማኅተም አትማ ያዘች። በወረቀቱም
ላይ እርሷን እንደራሴ አድርገው እንደሾሟት የሚገልጽ ቃል አስፍራ ለምኒልክ እንደራሴዎች
አስረከበች። በዚህ ደብዳቤ መሠረትም የምኒልክ እንደራሴዎች ሥልጣናቸውን ለባፈና አስረከቡ።
 ባፈና የእንደራሴነቱን ኃላፊነት እንደተረከበች በመጀመሪያ የወሰደችው ርምጃ የመንግሥቱን
ንብረት ለቃቅማ ወደ ታሞ አምባ አጓዘች። የዚህም ግብ ምናልባች ዕቅዷ ካልሰመረ ያን ሀብት ይዛ
ለተከታታይ ውጊያ እንዲረዳት ነበር። በሌላ በኩል አልጋ ይመኛል ብላ እንዲታሰር ምኒልክን
ትጎተጉት እንዳልነበር፣አሁን መሸሻ ሰይፉ ተባባሪዋ እንዲሆን ጠይቃው ወደ ታሞ አብረው ሄዱ።
ለፍቅራቸው መጥናትም በፊት ለምኖ እምቢ ያለችውን ልጇን እንዲያገባ ፈቀደችለት። ይህ ሁሉ
ጨዋታ ግን ታሞ እስኪገቡ ድረስ ነበር። ታሞ እንደደረሱ መሸሻን አሳሰረችው። ሆኖም ወታደሩ
ከባፈና በፊት ለመሸሻ ሰይፉ አክብሮትና ፍቅር ስለነበራቸው እርሱን ለቀው እርሷን አሰሯት። በዚህ
ጊዜ ምኒልክ ጎጃምን ለቀው ሸዋ ገብተው ነበር።
 ምኒልክ ሸዋ እንደገቡ አብረዋቸው የሄዱትን መሐመድ ዓሊን ወደ አገራቸው ወሎ እንዲሄዱ
ፈቀዱ። መሐመድ ግን ከአማቱ ከወ/ሮ ባፈና ጋር ምክር ነበረው። ከዐፄ ዮሐንስም ጋር ይጻጻፍ
ነበር። መሐመድ ዓሊ ወደ ወሎ ሲግዝ ባፈና ያደረገችውን ይሰማል። እርሱም ቀደም ሲል ካማቱ
ጋር በነበረው ግንኙነት ገስግሶ ወረይሉ በመግባት ከተማዋን አቃጥሎ ሸፈተ።
 ምኒልክ ሸዋ እንደገቡ የባፈናን ሴራ ቢሰሙም አላመኑም ነበር። ነገር ግን ባፈናም ራሷ ድርጊቱን
ማስተባበል ባለመቻሏ ድርጊቱን የፈጸመችው በቅናት ተነሳስታ መሆኑን ገልጣ ይቅርታ
እንዲደረግላት ጠየቀች። ባፈና የቀናችውም ምኒልክ አልጋ ወራሽ ልጅ አገኛለሁ በማለት ወ/ሮ
ወለተሥላሴ የተባሉ የጉራጌ ሴት አስቀምጠው ስለነበር ነው።
 ሆኖም ባፈና ያቀረበችው ምክንያት ለምኒልክ የሚዋጥ አልሆነም። በመሆኑም ባፈና ከዚህ በኋላ
ሚስታቸው ልትሆን እንደማትችል ወስነው ለታማኝ አሽከራቸው ለአፈንጉስ በዳኔ ዳሯት።
እርስቷንም እያሳረሰች እንድትኖር ፈቀዱላት። 9 8221 Georgia Avenue, Silver Spring, MD. 20910 www.moreshwegenie.org

 ምኒልክ የባፈናን ጉዳይ በዚህ ከጨረሱ በኋላ ፊታቸውን ወደ መሸሻ ሰይፉ አዞሩ። መሸሻ ሰይፉ
ምኒልክ ወደ ሰሜን ምዕርብ ኢት ዮጵያ በሄዱበት ወቅት ከመርዕድ አዝማች ኃይለሚካኤል ጋር
አብሮ አንኮበረን የወረረ ስለነበር ታስሮ ነበር። ባፈና ናት ከታሰረበት ፈትታ ታሞ የወሰደችው።
ያለበት ቦታ ለመከላከል ምቹ ከመሆኑም በላይ በቂ ምግብ ባፈና ያከማቸችበት፣እንዲሁም ባፈና
ስታስረው አሳሪዎቹ እሱን ፈትተው እሷን ያሰሩና ለእርሱ ፍቅር ያላቸው መሆን በጦርነት በቀላሉ
ድል ሊሆን እንደማይችል ምኒልክ ተገነዘቡ። ለዚህም የጋራ ዘመድ የሆኑት ራስ ዳርጌ መሸሻን
እንዲያግባቡ ተወሰነ። ራስ ዳርጌም መሸሻን አሳምነው አስገቡ። ምኒልክም ደጃዝማች ብለው
በወበሪና በጉለሌ ላይ ሶሙት።
 ምኒልክ የባፈናንና የመሸሻ ሁኔታ በዚህ መልክ ከቋጩ በኋላ ፊታቸውን ወደ መሐመድ ዓሊ
አዙረው ወደ ወረይሉ አቀኑ። መሐመድ ዓሊ ግን አልቆመም። ዐፄ ዮሐንስ እንዲደርሱለት
መልዕክት ልኮ ወደ መሐል ወሎ ሸሸ።

1.9 የምኒልክና የዐፄ ዮሐንስ የልቼ ስምምነት፣
 ዐፄ ዮሐንስ በ1864 ዘውድ እንደጨኑ በሰሜን የአገራችን ክፍል ከግብፆች ጋር ሁለት ጮርነቶች
በመግጠማቸው ምኒልክን ለማስገበር ጊዜ አልነበራቸውም። ሁለቱን ጦርነቶች በድል እንዳጠናቀቁ
ፊታቸውን ወደ ሸዋ አዞሩ። ወሎ M,ሐመድ ዓሊ ምኒልክን ከድቶ ከየሐንስ ጎን ተሰልፏል።በዚህ
በኩል ዮሐንስ ስጋት የላባቸውም። በመሆኑም ዮሐንስ በ1870 ጦሩን አስከትቶ በምኒልክ ላይ
ዘመተ።
 የሸዋ ጦርም ጎንደርና ጎጃም ባደረገው ዘመቻ ጦርነት ስላልገጠመው የትግሬ ጦር ደፍሮ ይገጥመናል
ብለው አልገመቱም። በዚህም የተነሳ በሁለቱም በኩል የዘመኑ የቀረርቶና ፉከራ የቃላት ጦርነት
ተፋፋመ። እንዲህም ተባባሉ፤
ሼዬ፦ ትግሬንም አየነው ላጨነው፣
ጎጃምንም አየነው ላጨነው፣
ቤጌምድርንም አየነው ላጨነው፣
አባ ዳኜው ብቻ ገና ቁንዳላ ነው።
ትግሬዎች፦ ትግሬም አለን አቤት አቤት፣
ቤጌምድርም አለን አቤት አቤት፣
ጎጃም፣ወሎም፣ ወልቃይትም፣ ጸገዴም ደንቢያም አለን አቤ አቤት፣
ሸዋ ብቻ ቀረን የጋላ ጎረቤት።
ሼዬ ፦ በስተ ጎጃም በኩል ገበያ ቢያስማማ፣
በስተ ቤጌምድርም በስተቋራም በኩል በስተ ትግሬም በኩል ገበያ ቢያስማማ ፣
እኛም አውቀነዋል እንዳን ገዛማ።
 ከቃላት ጦርነቱ ባሻገር ለድል አድራጊነት የሰው ኃይልና የመሣሪያ ዓይነትና መጠን ከፍተኛ ድራሻ
ስላላቸው ሁለቱ ወገኖች የሚከተለው የሰው ኃይልና መሳሪያ ታጥቀው ነበር፤
ዐፄ ዮሐንስ በሰው ኃይል፦ 1 ከትግሬ ጦር ሌላ 20 000 ከጎጃም፣
2 ከ4-5 000 ከወሎ፣ በአጠቃላይ 100 000(መቶሺ) የሚጠጋ የሰው
ኃይል አሰልፈው ነበር።
በጦር መሣሪያ ረገድ የሐንስ ከእንግሊዞች (ናፒየር) በስጦታ ካገኛቸው ዘመናዊ መሣሪያዎች
በተጨማሪ ከጉራና ከጉንደት ጦርነቶች የተማረኩ ከ20 000 በላይ መሳሪያዎች ታጥቋል።
የምኒልክ በዘመኑ ዘመናዊ የተባለየጦር መሳሪያ ያታጠቁ 8000 ብቻ ነበሩ። የሰውም ኃይል በዚያው
መጠን አነስተኛ ነበር።
 የጦርነት አሰላለፉ በዚህ ሁኔ እንዳለ፣ጉዳዩ በሰላም ለመጨረስ ሽምግልና ተጀምሮ,ነበር። በዚህም
መሰረት በምኒልክ በኩል በጅሮንድ ወርቄ፣በዮሐንስ በኩል በጅሮንድ ለውጤ ተወክለው መደራደር
ጀምረው ነበር።
 በሌላ በኩል ትግራይ ውስጥ አጽቢ ደራ ገዳም ነዋሪ የሆኑ መነኮሳት ( መናንያን) ምኒልክ ዘንድ
መጥተው ችግሩ በስምምነት እንዲፈታ፣የክርስቲያኖች ደም በከንቱ እንዳይፈስ ስሉ ሀሳብ አቀረቡ።
መናንያኑ አልታረቅም ያለ እንደሆነ መንግሥቱን እንደሚያጣ፣የታረቀ እንደሆነ እንደ አብርሃና አጽብሃ
በአንድነት አገሪቱን እንደሚገዟት ተናገሩ። በመናንያኑ ሀሳብ ምኒልክ ተስማሙ። 10 8221 Georgia Avenue, Silver Spring, MD. 20910 www.moreshwegenie.org

 መናንያኑ ወደ ዮሐንስ የምኒልክን ፈቃደኛነት ለመግለጽ ተጓዙ። እነርሱም የoH,ንስን ጋይት ውስጥ
ቀበሮ ሜዳ ከሚባለው ሥፍራ ሰፍረው አገኟቸውና ለምኒልክ የነገሩዋቸውን ለዮሐንስ መልሰው
በመንገር በስምምነት እንዲጨርሱ አሳሰቡ።
 ዐፄ ዮሐንስ ከምኒልክ የሚፈልጉት ፣ምኒልክ የዮሐንስን ንጉሠ-ነገሥትነት እንዲቀበሉ፣ የሸዋ ንጉሥ
ሆነው የዓመት ግብር እንዲገብሩላቸው ነው። ይህ ግን ለምኒልክ የከበደ ስለሆነ መልስ ሳይሰጡ
ብዙ ጊዜ ቆዩ።
 ዮሐንስ የምኒልክ መልስ በመዘግየቱ በኃይል ፍላጎታቸውን ለማሟላት ወደ ሸዋ ገፍተው
ደብረብርሃን ድንባሮ ማርያም ድረስ ዘለቁ።
 የሁለቱ ኃይሎች ጦር በሬንሳ ላይ ገጠሙ። በግጭቱ የዮሐንስ ጦር ተሸንፎ ወd ኋላ አፈገፈገ። በዚህ
ጦርነት ከፍተኛ ጀብዱ የሠሩት በሻህ አቦዬ የዮሐንስን የታወቀ ፈረሰኛ ገድሎ ነበርና እንዲህ ተባለ፣
ለአምሳ ጠብመንጃ ዋስ የጠራችሁ፣
በሻህ አቦዬ ከፈለላችሁ፤
ከፈረሰኞች ከምናውቃቸው፣
በሻህ አቦዬ ኃይሌ አንዳርጋቸው።
 ከዚድንህ ግጭት በኋላ የሽምግልናው ሁኔታ ተጠናክሮ ቀጠለ። በዚህም መሠረት ከመኳንንቱ ራስ
ጎበናና ራስ መንገሻ አቲከም፣ከካህናቱ በኩል አለቃ ኪዳነወልድ እና አለቃ ምላት ገቡበት። እነዚህ
ሰዎች ወደ ዮሐንስ ሂደው ችግሩን በሰላም እንዲፈቱ ጠየቁ። ዮሐንስም በሀሳቡ ተስማሙ። በዚህም
መሠረት ድንባሮ ( ልቼ) ሁለቱ የሥልጣን ባላንጣዎች ተገናኝተው፣በስምምነት ጦርነትን አስወገዱ።

1.10 የዐፄ ዮሐንስና የንጉሥ ምኒልክ ስምምነት ውል፣
 ምኒልክ የገቡት ግዴታ፤
(1) ምኒልክ ንጉሠ ነገሥት መባላቸው ቀርቶ ንጉሠ ሸዋ ሊባሉ፣
(2) በሸዋ የነበሩ ሚሲዮናውያን በሙሉ አግር ለቀው እንዲሄዱ( በዚያን ጊዜ 3 የካቶሊክ 2
የፕሮቴስታንት ሚሲዮንያውያን ነበሩ)
(3) መጠኑ በስምምነቱ ያልተገለጸ ግብር በያመቱ ለመገበር፣
(4) ንጉሠ ነገሥቱ ባዘዙ ጊዜ ሠራዊት አስከትተው የሐንስን ሊረዱ የሚሉ ናቸው።
 የዐፄ ዮሐንስ ግዴታ
(1) ከአባት፣ከአያት ፣ከቅድመ አያት ሲወርድ ሲዋረድ የመጣን የሸዋን መንግሥት፣ምኒልክ በሙሉ
ሥልጣን እንዲጋዙ፣
(2) ወሎ በንጉስ ምኒልክ ሥር እንዲቆይ፣ሆኖም ጥንት ክርስቲያን የነበረውን የወሎ ሕዝብ ሐዋሪያ
ልከው ወደ ጥንት ሃይማኖቱ እንዲመልሱ እንዲያደርጉ፣
(3) የሐንስ ምኒልክ በምዕራብ፣በደቡብና በምስራቅ ጥንት የኢትዮጵያ ግዛት የነበሩትን አገሮች
ለማስመለስ የሚያደርጉትን ጥረት በሙሉ ፈቃድ እንደሚደግፉ ፣የሚሉ ናቸው።
 በዚህ ስምምነት ዐፄ ዮሐንስ ከነሠራዊታቸው ተደስተው ሲመለሱ ሸዌዎች አልተደሰቱም ነበር።
ቅሬታቸውንም እንዲህ ሲሉ ገለጹ፣
ሲሆን ተከናበብ ሳይሆንም አጣፋው፣
መታጠቅ አይሆንም ለእንዳተ ያለሰው፣
እንዴት ያለ ሩቅ ነው ጭንቅ ያለ መንገድ፣
አሻቅቦ ወጥቶ አቆልቁሎ መውረድ፣
በሌላ በኩል የምኒልክ አዝማሪ ስምምነቱን ከፍራት ሳይሆን ከንግርት ጋር በማያያዝ እንዲህ ብሏል፣
ሚስቱ ጣይቱ እሱ አባ ዳኜው፣
ፈሪ ይሉታል ንግር ሲያቆየው። 11 8221 Georgia Avenue, Silver Spring, MD. 20910 www.moreshwegenie.org

1.11 የምኒልክ አገርን መልሶ ማዋሐድ (አገር) ግንባታ) ፣
 ምኒልክ የጥንቷን ኢትዮጵያ መልሶ ለመገጣጠም መሠረት የጣሉላቸው በመሀል አያታቸው
ሣህለሥላሴ፣በሰሜን ቴዎድሮስ በጣሉት መሠረት ላይ፣የዳር አገሩን ራሳቸው ምኒልክ የራሳቸውን
ድርሻ በመጨር ነው። ቴዎድሮስ ኢትዮጵያን አንድ ለማድረግ ሸዋ በገቡበት ወቅት፣ኃይለመለኮት
ካባታቸው የወረሱትን እርጎ የተባለውን በገና አንሥተው እንዲህ እንዳሉ ይነገራል፣
አገር አንድ እንዲሆን ቴዎድሮስ ማሰቡ፣
ያስመሰግነዋል ከፍ ያለነው ግቡ፤
አገርም አንድ ሆኖ ሕዝብ እንዲገዛ፣
ዘዴ ትዕግሥት ያሻዋል አይደለም የዋዛ፤

 ምኒልክ ካያታቸውና ከምኒልክ በተቀበሉት አደራና ልምድ ተነስተው አትዮጵያን አንድ የማድረጉን
ተግባር ገፉበት። ለዓላማቸው ዳር መድረስ የረዳቸው እንደ አያታቸው ሰው የመምረጥ ችሎታ
የነበራቸው መሆኑ ነው።
 ምኒልክ ኢትዮጵያን አንድ እንዲያደርጉ የገፋፏቸው ሁለት የውስጥና የውጭ ምክንያቶች ናቸው።
(1) የውስጥ፦ በዐፄ ዮሐንስና በራቸው መካከል የተደረገው የልቼ ስምምነት፣ (ዳር አገሩን
እንዲያጠቃልሉ ከዮሐንስ ፈቃድ ማግኘታቸውk በላይ ከሸዋ ብቻ የሚሰበሰበው ግብር
ምኒልክ የዮሐንስ የገቡትን የመገበር ውል ሊወጡ አለማስቻሉና ተጨማሪ አገር
ማስፈለጉ፤
(2) በውጭ ፦የአውሮጳ ቅኝ ገዥዎች አፍሪካን ለመቀራመት ያደርጉት የነበረው ዘመቻ
ኢትዮጵያንም ያሰጋት ስለነበር፣ይህን ለመቋቋም ምኒልክ የኢትዮጵያን የጥንት ወሰን
ከየት እስከየት እንደነበር የሚያመለክት ተዘዋዋሪ ደብዳቤ ለዓለም መንግሥታት ጻፉ።
ቅኝ ገዥዎቹ ለደብዳቤው ዋጋ እንደማይሰጡት በመገንዘብ፣በሰው ኃይል ዳር ድንበሩን
ማጠር እንዳለበት ምኒልክ መገንዘባቸው ነው።
 በዚህም መሠረት ምዕራብን ጎበና ዳጨ እንዲያቀና፣ ጎበና በጀግንነቱና በታማኝነቱ እንከን የለሽ
ስለነበር ምኒልክ እንዲህ ብሎ እንደገጠመለት ይነገራል።
ጎበና ጎበና ጎበና የእኔ፣
የጦር ንጉሥ አንተ ያገር ንጉሥ እኔ፤
 ምኒልክ ከጎበና ጋር በጋብቻ ለመተሳሰር ፈልጎ ልጁን ሸዋ ረጋን ለጎበና ልጅ ለወዳጆ ድረውለት ነበር፣
ጎበና ምዕራብ ኢትዮጵያን ለማጠቃለል በመጀመሪያ የጀመረው ጉድሩንና በአዋሽ ወንዝ መካከል
ያሉትን አገሮች በማስገበር ነው። እነዚህ አገሮች ቀደም ሲል በአምኃየስ፣በአስፋው ወሰንና
በሣህለሥላሴ የተጠቃለሉ ነበሩ፤
 ሁለተኛው የጎበና ጉዞ በልጁ በወዳጆ እየተረዳ የጊቤ፣የጎጀብና የዴዴሳ ወንዝ አካባቢ ያሉ አገሮችን
ተራ በተራ አሳመነ፣ በዚህ ተግባሩም እንዲህ ተብሎለታል።
ጎበና ጎበና ጎበና ፈረሱን አማን ቢያስነሳው፣
ዓባይ ላይ ገታው፤
ጎበና ፈረሱን ፋሌ ላይ ቢያስነሳው፣
ዓረብ አገር ገታው፤
ጎበና ፈረሱን ቼቼ ቢለው ፣
ሱዳን ላይ ገታው፤
 ጎበና አገር የማስተባበሩን ሥራ የጀመሩት ከ1860 እስከ 1870 ባሉት አሥርት ዓመታት ውስጥ ነው።
በነዚህ ዓመታት የሊበንን ነዋሪዎች ሙገር ጅረት፣አዋሽ ጅረት በምስራቅና ጉድሩ ጅረት በምዕራብ
የሚያዋስኑ አገሮችን አሳምነው በምኒልክ ቁጥጥር ሥር እንዲውሉ አድርገዋል። በዚህ ሂደት
አንዳንዶቹ ያለጦርነት የአንድነቱ አካል ሆኑ። ለምሳሌ የከፋው አባጅፋር፤የአባጅፋር መገበር ምኒልክ
ዋናውን የንግድ ጎዳና( መስመር) አይመለልን አልፎ ሮጌ የተባለውን ባለአራት መንታ የንግድ ኬላ
ለመቆጣጠር አስቻለው።
 ሁለተኛው የጎበና አገር የማስተባበር ሥራ የተከናወነው ከ1870 እስከ 1880 ባሉት ዓመታት ነው።
ጎበና በዚህ ዘመቻቸው ሌቃ ነቀምቴንና ሌቃ ቄለምን ያለ ጦርነት ገበሩላቸው። የሌቃ ነቀምቱ መሪ 12 8221 Georgia Avenue, Silver Spring, MD. 20910 www.moreshwegenie.org

ኩምሳ ሞረዳ ሲሆን የሌቃ ቄለሙ ደግሞ ጆቴ ቱሉ ነበር። ሁለቱም ክርስትና ተነስተዋል። የኩምሳ
ሞረዳ ክርስትና አባት ምኒልክ ሲሆኑ፣የክርስትና ስማቸውም ገብረእግዚአብሔር ተባሉ። ጎበና ከዚህ
ቀጥሎ ጊቤን በመሻገር አጠቃለሏቸው።
 በ1874 በምኒልክና በራስ አዳል መካከል የእንባቦ ጦርነት ተደረገ። የጦርነቱ መነሻ ካፋንና ወለጋን
የየግላቸው ለማድረግ ከነበረፍላጎት ነው። በጦርነቱ ምኒልክ አሸነፉ፣ራስ አዳል ቆስለው ተማረኩ፣
 ምኒልክና አዳል ካለዮሐንስ ፈቃድና እውቅና ጦርነት በማካሄዳቸው፣ ምኒልክ በወሎ ላይ የነበራቸውን
መብት አጡ፤ ወሎን ለልጃቸው ለራስ አርኣያ ሰጡ። እምባቦ ጦርነት ላይ የማረኳቸውን መሣሪያዎች
በልዩ ዘዴ ለራስ አዳል ሰጡ። ራስ አዳልም አገው ምድርን አጡ። አገው ምድር ለራስ አሉላ ተሰጡ፤
ከዚህ ሁላ በኋላ ራስ አዳልን ንጉሥ ብለው፣ የጎጃምና የከፋ ንጉሥ በማለት የምኒልክ ተፎካካሪ
እንዲሆኑ አደረጉ።
 የከፋ ንጉሥ የምኒልክን የበላይነት አልተቀበለም። ያለመቀበሉ ምክንያትም እኔም እንደሱ ከሰሎሞናዊ
ዘር እወለዳለሁ፣ሁለታችንም የአንድ ቤተሰብ አባሎች ነን፤በማለት ክብሩንና ጥቅሙን ለማስጠበቅ
ሲል ነው። ይህን ግንኙነት በተመለከተ ጀርመናዊው አይክ ሀበርላንድ የተባለው አጥኝ እንዲህ
ይላል፣« የከፋው ንጉሥ የዘርአያዕቆብ ዝርያ እንደሆነ ያምናል። ይህ የሚለው እርሱ ብቻ
ሳይሆን፣ጊሚራ፣ማጅ፣ ጉጂ፣ አርሲ፣ ዶርዜና ኡርባራግ ተመሳሳይ እምነት እንዳለ ያምናል። ለዚህም
የሚሰጠው ማስረጃ፣የክብር፣የፍትሕና የመዋዕl ንዋይ ነክ የግዕዝ -አማርኛ ቃላት እስካሁን ድረስ
የሚጠቀሙት ቃላት ተመሳሳይ ነው። ምሳሌ፦አቲዮ=ዐፄ፣ አቢቶ=አቤቶ፣ ምክሪቾ=አማካሪዎች፣ ራሳ
ወይም ኢራስ=ራስ፣ጋይቶ ወይም
ጎያታ=ጌታ፣ነጋሪታ=ነጋሪት፣አዋቾ=ዐዋጅ፣አዘዛ=አዘዘ፣ፈረዳ=ፈረዳ፣ጊፈሮ ወይም
ጊፍሮ=ግብር፣ማሬ=ማሪና ወዘተ። እነዚህ ቃላት የሚያመለክቱት የደቡብና የምዕራብ አካባቢ ነዋሪዎች
በዘር ፣በሃይማኖት እና በባህል ከሰሜኑ ነዋሪ ህዝብ ጋር በቅርብ የተሳሰሩ መሆናቸውን ይጠቁማሉ።
በሠርጸ ድንግል ዘመን ዳሞት(ወለጋ) እና እናርያ(ኢሉባቡር) የግዛቱ አካል ነበሩ።
 አርሲን በማቅናት ይገዙ የነበሩት ራስ ዳርጌ ሣህለሥላሴ ነበሩ።
 በ1879 ወደ ሐረር ምኒልክ ራሳቸው ዘምተው የሐረሩን ኢሚር አብዱላሂን ጨለንቆ ላይ ድል ነስተው
ራስ መኮንን ገዥ አድርገው ተመለሱ፣ እነዚህ በንጉሥነታቸው ዘመን የተከናወኑ ሥራዎች ናቸው።

1.12 ዐፄ ምኒልክ ንጉሠነገሥት ከሆኑ በኋላ ያዋሐዷቸው አካባቢዎች፣
 የወላይታውን ካዎ ጦና ለማስገበር ደጃዝማች በሻህ አቦዬ፣ አዛዥ ተክሌ እና ቢትወደድ መንገሻ
አቲከም ዘምተው ነበር። እነዚህ ሰዎች ግን በካዎ ጦና ድል እየተመቱ በመመለሳቸው ንጉሠ ነገሥቱ
ራሳቸው መዝመት ግድ ሆነ።
 በመሆኑም በ1887 ወደ ወላይታ ዘምቶ ቆንጦላ ላይ ሠፈሩ። ከጦና ጋር ጉዳዩን በሰላም ምኒልክ
ለመጨረስ ፍላጎት ቢኖራቸውም ካዎ ጦና ፈቃደኛ ባለበሆናቸው ጦርነቱ የማይቀር ሆነ። በጦርነቱም
ካዎ ጦና ቆስለው ተማረኩ። ምኒልክ የጦናን ተከታዮች ታላላቆቹን አዲስ አበባ በመውሰድ ክርስትና
እንዲነሱ አደረጉ። ካዎ ጦናን ምኒልክ ክርስትና አንስተው አገራቸውን እንዲያስተዳድሩ መልሰው
ላኩዋቸው።
 ምኒልክ ንጉሠ ነገሥት ከሆኑ በኋላ ያስገበሩት አገር ከፋ ነው። ይህን ያቀናው ራስ ወልደጊዮርጊስ
አቦዬ ናቸው። የከፋው የመጨረሻ ንጉሥ የሆኑት ጋኪ ሼሮኮ ከቀዳማዊ ምኒልክ ዘር እወለዳለሁ
ብለው ስለሚያምኑ ዘውዱ ለእርሳቸውም ተገቢ እንደሆነ በማመን ለምኒልክ ላለመገበር ወሰኑ።
በጦርነቱም ብዙ ሰው ካለቃባቸው በኃላ ተማርከው በግዞት በአንኮበር እንዳሉ አረፉ።
 ሌላው ከምኒልክ ንጉሠነገሥትነት በኋላ የቀናው አካባቢ ቤኒ ሻንጉል (ቤላ ሻንጉል) የተሰኘው የሸህ
ሆጄሌ አገር እና ቦረና ናቸው። ይህን አካባቢ ያስገበሩትም ዋናው ራስ መኮንን ወልደሚካኤል
ሲሆኑ፣ተባባሪዎቻቸው ሀብተጊዮርጊስ ዲነግዲ፣ደጃዝማች ጆቴና ደጃዝማች ገብረእግዚአብሔር
ነበሩ። ይህ ዘመቻ የዓረብ ዘመቻ በመባል ይታወቃል። ትርጉሙ ምዕራብ ማለት ነው። በማከታተል
ደጃዝማች ደምስ ነሲቡ ሲዳሞን አቅንቷል።
 በ1880 ላይ ሐሰን አንጃቦ የተባለሰው ሸፍቶ በምኒልክ ሹመኛ በደጃዝማች ወልዴ ላይ አመጽ
ቀሰቀሰ። ይህ አመጽ ለመግታት የአካባቢው ኃይል ባለመቻሉ ራስ ጎበና ፀጥታውን እንዲያስከብሩ
ተላኩ። ጎበናም እንደተለመደው ሐሰን አንጃሞን ድል ነስተው ተመለሱ። ይህም 19ኛው ምዕተ ዓመት
ከማለቁ በፊት ምኒልክ ኢትዮጵያን አንድ የማድረጉን ተልዕኳቸውን አጠናቀቁ።
ይህን በተመለከተም እንዲህ ተባለ፦ ተሰው ጋር ንግግር የማልወደውን፣ 13 8221 Georgia Avenue, Silver Spring, MD. 20910 www.moreshwegenie.org

አሳማኝ ምኒልክ ያራቱን ማዕዘን።

1.13 ኢትዮጵያን ለማዘመን ምኒልክ ያደረጓቸው ጥረቶች፣
1.13.1 አዲስ አበባን የአገሪቱ ማዕከል አድርገው መቆርቆራቸው፣
 ቅድመ ምኒልክ የኢትዮጵያ ነገሥታት ቋሚ መቀመጫ መዲና አልነበራቸውም። ኑሮአቸው አገር አገር
በመንከራተት በድንኳን ነበር።ነበሩ እንኳን ቢባል አክሱም፣ሮሃ እና ጎንደር ናቸው። እነዚህ ደግሞ በተለያዩ
ምክንያቶች ተዳክመው ማዕከልነታቸውን ካጡ ዘመናት ተቆጥረዋል። ስለሆነም ምኒልክ ከመቅደላ አምልጠው
እንደተመለሱ የተለያዩ ቦታዎችን ለማዕከልነት አጭተው ለተወሱኑ ጊዚያቶች ተቀምጠውባቸዋል። እነዚህም (ሀ)
አንኮበር ለተወሰነ ጊዜ ተቀምጠዋል፣ (ለ) ልቼ ፣(ሐ) በ1861 ወረኢሉን ቆረቆረሩ፣(መ) በ1867 እነዋሪን ቆረቆሩ፣
(ሠ) በ1870 አንጎለላ ከተወለዱበት ከተማ ለጥቂት ጊዜ ቆይተዋል።(ረ)ደበ ጎጆ (በከጆ) ለተወሰነጊዜ ተቀምጠዋል፣
(ሰ) ወጨጫ ላይም ለተወሰነ ጊዜ መቀመጣቸው ይነገራል።
 ምኒልክ ይህን ሁሉ ውጣ ውረድ ያደረጉት ለማዕከላቸው የሚሆን አማካኝ ቦታ ከማፈላለግ በተጨማሪ በቅድመ
አያቶቻቸው ተቆርቁሮ የነበረ የጥንት ከተማ ፍርስርሽ ፍለጋ ነበር። ይፈለግ የነበረውም የዐፄ ዳዊት ከተማ የነበረው
ነው። ይህም እንጦጦ ላይ ፍርስራሹ በመገኘቱ የእግዚአብሔር ፈቃድ መሆኑን አምነው በ1876 የከተማ ግንባታ
ጀመሩ። ሆኖም እንጦጦ ብርዱ፣ የውኃ እና የማገዶ ችግር እየበረታ ሲሄድ ከተማው ወደ አዲስ አበባ ማውረድ ግድ
ሆነ። አዲስ አበባም በ1879 ተቆረቆረች።
 ከተሞች የባህል፣የፖለቲካ፣የኢኮኖሚ፣የምኅበራዊ ሥነ-ልቦና ጎተታዎች በመሆናቸው የሕዝብን አንድነትና ውሕደት
የሚያፋጥኑ የአንድ አገር ማንነትና ምንነት መገለጫ መስተዋት ናቸው። የአዲስ አበባ መቆርቆርም ይህኑ
አንጸባርቋል።

1.13.2. የሚኒስትሮች ምክር ቤት መቋቋም፦፣ ምኒልክ በ1900 ለመጀመሪያ ጊዜ የአገሪቱን አስተዳደር የሚመሩና
የሚያስተዳድሩ ፣የዘመናዊ አስተዳደር ቅርጽ የተከተለ የሚኒስትሮችን ምክር ቤት አቋቋሙ። ሥልጣን ካንድ
ሰው እጅ ወደ ቡድን ተዛወረ። የመጀመሪያዎቹ ሚኒስትሮች የሚከተሉtr ነበሩ።
(1) ከንቲባ ወልደ ጻድቅ ጎሹ የእርሻ ሚኒቴር፣
(2) አፈንጉሥ ነሲቡ መስቀሉ የፍርድ ሚኒስቴር፣
(3) ፊታውራሪ ሀብተጊዮርጊስ ዲነግዲ የጦር ሚኒስቴር፣
(4) ጸሐፊ ትዛዝ ገብረሥላሴ ወ/አረጋይ የጽፈት ሚኒስቴር፣
(5) በጅርወንድ ሙሉጌታ የገንዘብና የጓዳ ሚኒስቴር፣
(6) ሊቀመኳስ ከተማ ያገር ግዛት ሚኒስቴር፣
(7) ነጋድራስ ኃይለጊዮርጊስ የንግድና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣
(8) አዛዥ መታፈሪያ የግቢ ሚኒስቴር፣
(9) ቀኛዝማች መኮንን ተወንድበላይ የሥራ ሚኒስቴር
(10) ልጅ በየነ ይመር የፖስታና ቴሌግራፍ ኃላፊ፣
ምኒልክ የሚኒስትሮች ምክር ቤትን ባቋቋሙበት አዋጅ እንዳብራሩት ፣ለምክር ቤቱ መቋቋም መነሻ
የሆነው የአውፓ መንግሥታት በኢትዮጵያ ውስጥ ቆንሲላዎች በመክፈታቸው፣የውጭ መንግሥታትም
የሚኒስትሮች ምክር ቤት የለለው መንግሥት ምን መንግሥት ይባላል እያሉ አገራችን በመወረፋቸው
መሆኑን ይግልጽና ስለ ተሿሚዎቹ እንዲህ ይላሉ፤
«አሁንም ምንም የቀድሞው የኢትዮጵያ ሥራት ቢኖር ከጥቂት ቀን በኋላ ቀርቷልና አገራችንን እንደ
አውሮፓ ሥራት ለማድረግ አስቤ ይሄንን ባንደኛ ወረቀት የተጻፈውን ደንብ ጽፌላችኋለሁና በዚሁ
ባስያዝኳችሁ ሥራ ሳትጣሉ፣ ሳትመቀኛኙ በዕውነት እርስ በርሳችሁ ተስማምታችሁ ጠንክራችሁ
መንግሥታችንን መርዳት ነው።
«እንዲህ ሁነን በሚገባ ሥራት ሕዝባችንን ጠብቀን ከያዝነው ለመንግሥታችንና ለሀገራችን ጥቅም
ይሆናል። አገራችንን ሌላ አይመኘውም። እኔም እስካሁን ብደክም ብደክም ሚኒስቴር መማክርት
ቆንሲል የለበት፣ባንድ ሰው ብቻ እያሉ አሙን እንጂ አላመሰገኑንም። 14 8221 Georgia Avenue, Silver Spring, MD. 20910 www.moreshwegenie.org

«አሁን እንቅልፍ ሳትወዱ፣ መጠጥ ሳታበዙ፣ ገንዘብን ጠልታችሁ ሰውን ወዳችሁ ፣ተግታችሁ ይሄንን
ሥራ እንድትፈጽሙልኝ ተስፋ አለኝ። ለዚህ ሥራ እኔ እናንተን አምኜ ስላደግሁ ፣እናንተም
የምታምኑትን፣ገንዘብ የማይወደውን፣ድሃ የማይበድለውን ፣እናንተን የሚረዳችሁን ሰው እየፈለጋችሁ
እያመለከታችሁኝ ከሥራው ማግባት ያስፈልጋችኋል።» (ጳውሎ ኞኞ 1984፤ 360)
1.13.3 የውጭ ግንኙነት ምሥረታ፦ ከዳግማዊ ዐፄ ምኒልክ በፊት የኢትዮጵያ የውጭ ግንኙነት የተመሠረተው በተናጠል
ተላላኪ ሰዎች ነበር። ምኒልክ ከታላቁ የዐድዋ ድል በኋላ ጥቅምት 15 ቀን 1889 ዓም የአዲስ አበባ ስምምነነት በመባል
የሚታወቀውን ስምምነት ከጣሊያን ጋር ካደረጉ ጊዜ ጀምሮ የውጭ ግንኙነት በቋሚ መልክተኞች መከናወን ተጀመረ። በዚህ
መሠረት ከኢትዮጵያ ጋር ሕጋዊ የሆነ የውጭ ግንኙነት መሥርተው በአዲስ አበባ ጽ/ቤት የየከፈቱት አገሮች የሚከተሉት
ናቸው።
(1) ጣሊያን ፦ጥቅምት 15ቀን 1889 ጀምሮ፣
(2) ፈረንሣይ ፦ሰኔ 8 ቀን 1889 ጀምሮ፣
(3) ሩሲያ፦ ከ1890 ጀምሮ ፣
(4) እንግሊዝ ፦ከ1891 ጀምሮ፣
(5) ጀርመን ፦ከ1897 ጀምሮ፣
(6) የተባበሩት የአሜሪካ ግዛቶች(ዩኤስኤ)፤ ከ1898 ጀምሮ፣አሜሪካ ከዚህ ቀደም ሲል በ1895
ላይ የወዳጅነትና የንግድ ስምምነት ከምኒልክ ጋር ተዋውላ ነበር።
(7) ቤልጅግ፦ ከ1898 ጀምሮ፣
(8) አውስትሪያ( ነምሳ)፦ከ1905 ጅምሮ፣

1.13.4 ከአዲስ አበባ መቆርቆር ተከትሎ ከተማዋን ዘመናዊ ለማድረግ ምኒልክ ያከናወኗቸው ተግባሮች፣
(1) ከ8 ሺህ እስከ 10 ሺህ ሊይዝ የሚችል አዳራሽ ማስገንባታቸው፤
(2) ለከተማው መሥፋፋትና ለግንባታ ሥራ የሚውል የሸክላ(ጡብ) ፋብሪካ መገንባታቸው፤
(3) ለአፈርና ለድንጋይ ማጓጓዣ የሚያገለግል ጋሪ ፣
(4) ዳግማዊ ምኒልክ ሆስፒታል፣
(5) ዳግማዊ ምኒልክ ትምህርት ቤት፣
(6) የከተማ መንገድ ቅያስ ሥራ፤ የመጀመሪያው ቅያስ መንገድ ከታላቁ ቤተመንግሥት ጀምሮ
አራዳ ገበያ ድረስ የሚዘልቀው ነው፣ ሁለተኛው ቅያስ መንገድ በ1897 የተሠራው
ከቤተመንግሥቱ እስከእንጦጦ ያለው ጎዳና ነው።
(7) ቀመሌ ወንዝ ላይ በ1896 ራስ መኮንን የሚባለው ድልድይ በራስ መኮንን የግል ገንዘብ
ተገነባ፤ ይህ በከተማይቱ 2ኛው ድልድይ ሲሆን የመጀመሪያው ቀበና ወንዝ ላይ ጀርመን
ኢምባሲ አጠገብ ያለው ነው። ለዚህ ድል ድል መሠራት ምክንያት የሆነው አንድ የሪሲያ
ተወላጅ ከሞስኮብ ቀይመስቀል(ዳግማዊ ምኒልክ ሆስፒታል) ተነስቶ ወደ ሌጋሲዮኑ ሲሻገር
ወንዙ ሞልቶ ስለነበር የሻገር ስለወሰደው ፣ይህ ዓይነቱ ተግባር እንዳይደገም የሩሲያ
ሐኪሞች ገንዘብ አዋጥተው በ1894 አሠሩት።
(8) የመንገድ ሥራው ከከተማው አልፎ ወደ ውጭም ማሠራት ምኒልክ ጀምረው ነበር።በዚህ
ረገድ የመጀመሪያው መንገድ ከአዲስ አበባ ወደ አዲስ ዓለም የሚወስደው ነው።ይህም
በ1895 መሠራት ተጀመረ። ይህ መንገድ መሠራት የተጀመረበት ዓመት« የደንጋይ ቅጥቀጣ
ዘመን »ይባል ነበር።
(9) ጓዝ የሚያጓጉዝ የሰርኪስ ባቡር የሚባል በ1895 አዲስ አበና ገባ። ሰርኪስ የአርመን ተወላጅ
ባብሩን እንግሊዝ አገር ገዝቶ የመጣ ነው። በዚህ ጊዜም እንዲህ ተገጠመ፣ ባቡሩም ሰገረ
ስልኩም ተናገረ፣ ምኒልክ ነቢይ ነው ልቤ ጠረጠረ፤ ነቢይ ለመሆንህ የተገገባህ ነህ፣
አላፊውን ትተህ መጭውን ታውቃለህ፤
(10) የመገበያያ ቦታና የሸቀጦች ማለዋወጫ ገንዘብ ብር፣ተሙን ፣አላድ፣ የመገበያያ ወጋ ተመን
አወጁ። በዚያን ጊዜ የነበሩ የእህል መስፈሪያዎች፣
 ጫን = 6ዳውላ፣
 ዳውላ = 100ኪሎ፣
 ሐረብ (ስልቻ) = ከ32 እስከ 50 ኪሎ ግራም፣
 መጋላ እንደ ከበሮ የተጠረበ ለእህል ወይም ለፈሳሽ መስፈሪያ
የሚያገለግል፣ 15 8221 Georgia Avenue, Silver Spring, MD. 20910 www.moreshwegenie.org

 ጉንዶ ከእንጨት ወይም ከቀንድ የተሠራ 4 ቁና የሚይዝ፣
 ኮርቻ = 8 ኪሎ ግራም፣
 አሞሌ = 650 ግራም፣
 ወቄት = 28 ግራም፣
 ነጥር = 16 ወቄት፣
 ኮልባ 4 ኩባያ በምኒልክ ፣
ምንዛሬ፦ 1 1 ብር = 16 ግርሽ ወይም ተሙን፣
2 1 ተሙን = 32 ቤሳ፣
4 1 ብር =10 ቱባ ጥይት፣
5 1 ብር = 20 እንደገና ታሽጎ የተተኮሰጥይት፣
6 1 ብር = 32 ቀለህ ነበር፤
(11) ሀኪም ቤት፣ ዘመናዊ ሕክምና የተጀመረው ከዐድዋ ጦርነት በኋላ ነው። ሕክምናው
የተጀመረው በጦርነቱ የሚቆስሉ ሰዎችን ለማከም እንዲቻል ምኒልክ ከጦርነቱ ቀደም ብሎ
የመስኮብ ንጉሥ ሐኪሞች እንዲልኩላቸው በጠየቁት መሠረት ፣ሐኪሞቹ ሐምሌ 28 ቀን
1888 አድስ አበባ ገቡ። ሕክምናውን የሚሰጡት ዛሬ ምኒልክ ሆስፒታል ካለበት ቦታ ላይ
ነበር። ሕክምናው የሚሰጠው በድንኳን ነበር። ከሞስኮ የመጡት ሐኪሞች ቁጥር 7
ሐኪሞች፣4 ረዳት ሐኪሞች፣ 6 የሐኪም ረዳቶች፤ 12 አስታማሚዎች ፣ 21 መኮንኖች ፣ 20
ባለሌማዕረግተኞች እና 1 ካህን ነበሩ። ለበሽተኞች ምግብ የሚመጣው ከምኒልክ ቤተ
መንግሥት ነበር። የሞስኮ ሐኪሞች በቀደዱት ፈለግ የመጀመሪው ሆስፒታል በ1900
ተሠራ። ዳግማ ዐፄ ምኒልክ ሆስፒታልም ተብሎ ተሰየመ።
(12) የመድኃኒት ቤት አገልግሎት፤ በምኒክ ዘመን የተቋቋመው የመጀመሪያው መድኃኒት
ቤት(ፋርማሲ) ዶክተር ሚራብ በሚባል የአርመን ተወላጅ ባለቤትነት ይስተዳደር የነበረው
ጊዮርጊያ መድኃኒት ቤት ነበር። ሁለተኛው መድኃኒት ቤት በ19o6 የተቋቋመውና ንብረትነቱ
ዛን የተባለው ጀርመናዊ ሲሆን፣ የመድኃኒት ቤቱ ስምም ቅዱስ ጊዮርጊስ መድኃኒት ቤት
ይባል ነበር።
(13) ምኒልክ ኢትዮጵያን ለማዘመን ሲሉ በዚያን ጊዜ በርካታ ሊባሉ የሚችሉ ሰዎችን ወደ ውጭ
በመላክ እንዲማሩ አድርገዋል። ለምሳሌ በ1886 ላይ ጉግሳ ዳርጌን፣አፈወርቅ ገብረየሱስን እና
ቅጣው ዘዓማኑኤልን ኢሊግ በተሰኘ ስውዲናዊ አማካኝነት ለትምህርት ወደ ስውዲን
ልከዋል። ለሥነጥበብብ ትምህርትም ጉጉት ስለነበራቸው አለቃ ኤልያስ ኃይሉንና አለቃ
መርዓዊን ለሥዕል ትምህርት ልከዋል።ከነዚህ ሁሉ በተጨማሪ መረጃ የተገኘላቸው 43
ወጣቶችን ወደ ውጭ ልከው አስተምረዋል።ከነዚህ ውስጥ 20 ያዎቹ ልዩ ልዩ የውጭ
ቋንቋዎች፣10ሩ ሕክምና 3ቱ ሥዕል ያጠኑ ነበሩ፣ ተሰማ እሸቴና አስታጥቄ ሀብተወልድ
የመኪና ጥገና ለመማር ጀርመን አገር ሄዱ ።ወደ ጀርመን የወሰዳቸውም ለምኒልክ መኪና
ያስመጣው ጀርመናዊው ሆልዝ ነበር። የእርሱም ፍላጎት ኢትዮጵያ የጀርመን መኪናዎች
ተጠቃሚ እንድትሆን ለማድ,ረግ ነበር። ሆሞም ሁለቱም መካኒክ ሳይሆን ሙዚቃ አጥንተው
ተመለሱ። ተሰማ እሸቴ የተወለዱ ገጣሚ እንደነበሩ ይነገራል። እንዲህ ሲሉም ገጥመዋል፣
 ከምኒልክ ይዞ እስካሁን ድረስ፣
ያልታየ ሞት ሆነ ሀብተ ጊዮርጊስ፣ (በ1919 ሀ/ጊ ሲሞቱ የተገጠመ)
 ጠጅም አላገኘን ከተለየናችሁ፣
አውራው ከተያዘ ማሩን እባካችሁ፤ (ተሰማ ከኢያሱ ጋር ባላቸው
ወዳጅነት ተግዘው በ1914 ልጅ ኢያሱ ሲያዙ የገጠሙት)
 አግብቶ ማሸከም ይህን የእኛን ቀንበር፣
ወንድም አማች ሆኖ የከዳውን ነበር፤
(14) ማተሚያ መሣሪያ መስገባት፦ ምኒልክ በአማርኛ ቋንቋ የሚያትም መሣሪያ ለሞንዶ ቪዳልዬ
በተባለ ፈረንሳዊ አማካኝነት በ1887 ወደ አገር ቤት አስገቡ። ማተሚያው በተለያዩ ችግሮች
ሳቢያ እስከ 1897 ድረስ አገልግሎት አይሰጥም ነበር። የጎደለው መሣሪያ ተሟልቶና ባለሙያ
ሰልጥኖ ሥራ የጀመረው ከዐሥር ዓመት በኋላ ነው። የማተሚያው የሥራ መሪ ቀኛዝማች
ደኅኔ ወልደማርያም ሆኖ በሥሩ 10 ሠራተኞች ነበሩት። ማተሚያው አማርኛ እና ላቲን 16 8221 Georgia Avenue, Silver Spring, MD. 20910 www.moreshwegenie.org

ፊደሎችን ያትም ነበር።ይህ ማተሚያ ቤት የኢትዮጵያ ማተሚያ ቤት ይባል ነበር። በዚህ
ማተሚያ ቤት ልዩ ልዩ መጽሐፍት፣መጽሔቶች እና በራሪ ወረቀቶች ታትመዋል።
(15) ጋዜጣ ፦ በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ጋዜጣ የሆነው አእምሮ የተሰኘው ጋዜጣ መታተም
የጀመረው በዐፄ ምኒልክ ዘመነ መንግሥት ነው። ጋዜጣ ኅትመት የጀመረውም በ1894
ነው። የጋዜጣን ጥቅምና አስፈላጊነት ለምኒልክ ያስገነዘበው እንድርያስ ካቫዲያስ የተባለ
ጀርመናዊ ነው። ጋዜጣው በየሳምንቱ ቅዳሜ ቅዳሜ ይወጣ ነበር። አእምሮ መውጣት
እንደጀመረ ፈላጊ ባለማግኘቱ ፣ይህን የተረዱት ምኒልክ ጋዜጣው በሚወጣበት ጊዜ አንድ
አንድ ቅጅ እየያዙ መታየት ሲጀምሩ ሁሉም ጋዜጣውን መያዝ ጀመረ። ይህ ጋዜጣ እስከ
ጠላት ወረራ ቆይቷል። ከእእምሮ ጋር ተያያዥ በሆነ ጊዜ ጎሕ የተሰኘ ጋዜጣ ነበር።
(16) መብራት ኃይል፦ የመጀመሪያው የመብራት ኃይል የሚሠራው በናፍጣ ሲሆን፣ለወደፊቱ
ደግሞ በዉኃ ኃይል እንደሚሠራ የታሰበ ነበር። የመጀመሪያው ዕቅድ አቃቂ ወንዝ ላይ
ሲሆን ሁለተኛው ዐባይ ፏፏቴ ላይ ነበር። የመጀመሪያው ዕቅድ በ1901 ተግባራዊ ሆነ።
አዲስ አበባ በዚህ ዘመን ከታላቁ ቤተ መንግሥት እስከ ሜክሲኮ አደባባይ ድረስ መብራት
አገኘ። ለከተማይቱ ብርሃን ለመስጠት ውሉን የተዋዋለው ስዊሳዊው መኃንዲስ አልፍሬድ
ኢሊግ ነበር።
(17) የቧንቧ ውኃ፦ አዲስ አበባ ከእንጦጦ ተስቦ ታላቁ ቤተመንግሥት የቧንቧ ውኃ የገባው
በ1887 ላይ ነው። ውኃውን ያስገባውም አልፍሬድ ኢሊግ ነው። በዚህ ጊዜ እንዲህ ተብሎ
ተገጥሟል።
 አዲስ አበባ ላይ አየነ ታሪክ፣
ውኃ ሲሰግድለት ላጤ ምኒልክ፤
 እንግዲህስ ዳኘው ምን ጥበብ ታመጣ፣
ውኃ በመዘውር ወዳየር ሲወጣ፣
ንጉሡ አባ ዳኘው እንዴት ያለ አመጣ፣
ያደፈው ሲታጠብ የጠማው ሲጠጣ፤
 እዩት በኛ ጊዜ እንዲህ ያለ መጥቷል፣
ደሞ ጥቂት ቢቆይ ከፈረንጅ ይበልጣል፤
 በኃይለመለኮት በሣህለሥላሴ ያላየነውን፣
አዲስ አበባ ላይ ጉድ ዓየ ዐይናችን፤
 ውሃ በመዘወር ወደ ላይ ሲወጣ፣
የቆሸሸው ታጥቦ የጠማው ሲጠጣ፣
ከምኒልክ ወዲያ ምንድር ንጉሥ ይምጣ፤
 ምን ንጉሥ መጣልን የንጉሥ ቂጣጣ
ውኃ ወደ ሰማይ አየር የሚያወጣ፣
ያደፈው ሲታጠብ የጠማው ሲጠጣ፤
(18) ፖስታ አገልግሎት፦
 የፖስታ አገልግሎት በ1884 ተመሠረተ። ለድርጅቱ መመሥረት
አልፍሬድ ኢልግ እና ዚመርማን አስተዋጽዖ እንዳደረጉ ይነገራል።
መሥሪያ ቤቱም እንጦጦ ነበር።
 ከፖስታ ቤቱ መቋቋም ቀጥሎ ቴምብር ተዘጋጀ። የመጀመሪያዎቹ
ቴምብሮች በዘመኑ ታዋቂ በነበረው ፈረንሣዊው ሠዓሊ ኢ ሚሺን
ተስለው ፈረንሣይ አገር ታተሙ።
 በመጀመሪያ ጊዜ ፖስታቤት የተቋቋመው አዲስ አበባና ሐረር ነበር።
 ኢትዮጵያ በዐፄ ምኒልክ ጠያቂነት በ1887 ዓም የዓለም ፖስታ
ማኅበር አባል ሆና እንድትመዘገብ ጥያቄ ለሁለተኛ ጊዜ አቀረቡ።
የመጀመሪያው ጥያቄ ያቀረቡት በ1885 ነበር።
 በ1892 ፓሪስ ላይ በተደረገው የፖስታ ኤግዚብሽን ተካፋይ ሆነች።
ይህም በዓለም መድረክ በፖስታ አገልግሎት ዘርፍ የመጀመሪያው
መሆኑ ነው። 17 8221 Georgia Avenue, Silver Spring, MD. 20910 www.moreshwegenie.org

 ኅዳር ወር 1901 ኢትዮጵያ የዓለም ፖስታ ማኅበር አባል ሆና
ተመዘገበች።
(19) ሥልክና ቴሌ ግራፍ፦
 ሥልክ ወደ ኢትዮጵያ የገባው በ1892 ነው። የሥልክ ጣቢያዎቹም
ድሬደዋ ፣ሐረር፣ ጋራ ሙለታ፣ ቁሉቢ፣ ቁኒ፣ ለገርዲን፣ ፈንታሌ፣
ገባ፣ ቡልቂ፣ ባልጭ እና እንጦጦ ነበሩ። ሁለተኛው መሥመር
የተዘረጋው ከአዲ ቋላ አዲስ አበባ ድረስ ነበር። ለሥልክ
ሙያተኞች ለማሰልጠንም ምኒልክ 12 ወጣቶች ወደጣሊያን ላኩ።
ከተላኩት ውስጥ ደስታ ምትኬ ይገንበታል።
(20) ባቡር፦
 ምኒልክ የባቡሩን ሥራ ውል ለአልፈርግ ኢልግ በሦስት ደረጃ
ከፋፍሎ እንዲያሠራ መጋቢት 1 ቀን 1886ዓም በተጻፈ ውል
ሰጡት።(1ኛ) ከጅቡቲ እስከ ሐረር፣(2ኛ) ከሐረር እስከ እንጦጦ፣
(3ኛ) ከእንጦጦ እስከ ከፋ ነጭ ዓባይ ድረስ።
 ሐዲድ የመዘርጋቱ ሥራ ጥቅምት 1888 ተጀመረ። የሐዲድ
መሥመሩ ታህሳስ 1895 ድሬደዋ ገባ።
 የባቡር መንገድ ሥራው ከብዙ ውጣ ውረድ በኋላ በ1909 አዲስ
አበባ ገባ። በዚህ ጊዜ ምኒልክ በሕይዎት አልነበሩም።
 በዚህ ጊዜ እንዲህ ሲባል ተዘፈነ።
 ወረደ ባቡር ወረደ ባቡር፣
ምጥዋና መነን ሊያመጣልን ድር፣
ወረደ ባቡር።
 ነይ እንሳፈር፣ነይ እንሳፈር
ገባሉ ባቡር፤
 ባቡር ገሠሠ ገባሉ ቦርደዴ፣
ሽንጧ የሚመስለው የሎንዶን ጎራዴ፤
 ከዚያም ገሠሠ ገባሉ ቀርጬፋ፣
እንዳቺ ያታለለኝ ያሞኘኝ ሰው ጠፋ፤
 ከዚያ ገሠሠ ገባሉ ላይ ሞጆ፣
ከቶ አይቸ አላውቅም እንዳቺ ያለቆንጆ፣
(21) አውቶሞቢል፦
 ወደ ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የገባው በ1900 ነው።
የመጀመሪያውን መኪና የመጣው ከእንግሊዝ አገር ሲሆን፣
ያስመጣው ቤንትሌይ ነው። አሽከርካሪው ደግሞ ዌልስ ይባላል።
በዚሁ ዓመተ ምህረት ሌላ መኪና ከጀርመን አገር ገብቷል።
ያስመጣው አርኖልድ ሆልዝ ሲሆን አሽከርካሪው ደግሞ አውግስት
ካውፍማን ይባላል። የጀርመኑ በገጸበከትነት የመጣ ሲሆን ሾፌር
ባለማግኘቱ ድሬደዋ ቀረ።ምኒልክ የአገሪቱ የመጀመሪያው ሾፌር
በመሆን መኪና መንዳት ጀመሩ።
(22) ብስክሌት፦ ብስክሌት በመቼ ዓመተምህረት እንደ ገባ የሚያመላክት መረጃ ባይገንም የእቴጌ
ጣይቱ ሐኪም የነበረው ቮልብረኸት ጣይቱ በብስክሊት ስፖርት እንዲሠሩ መምከሩን
ይነግረናል። ብስክሊት ከሌለ ይህን ምክር ሊሰጥ ስለማይችል በምኒልክ ጊዜ ብስክሊት
መኖሩንና ጣይቱም ብስክሊት ይነዱ እንደነበር መረዳት ይቻላል።
(23) የብር ኖት( የዐፄ ምኒልክ ብር)፦
 ኢትዮጵያ በ18ኛው ምዕተዓመት ማብቂያና በ19ኛው መግቢ
ያላይ የምተገበያየው በማር ቴሬዛ (ጠገራ) ብርና በአሞሌ
ጨው ነበር። እነዚህ ደግሞ ቅንስናሽ ገንዘቦች
ስላልነበሩዋቸው ለግብይይት አስቸጋሪዎች ነበሩ። 18 8221 Georgia Avenue, Silver Spring, MD. 20910 www.moreshwegenie.org

 በሌላም በኩል በሌላ አገር ገንዘብ መገበያየት ሉዓላዊነትን
ጥያቄ ውስጥ ስለሚጥለው ምኒልክ ከዘመኑ ጋር የሚጣጣም
መገበያያ ማስፈለጉን ተገነዘቡ።
 ለዚህም በ1881 ራስ መኮንን ወደ ሮም በላኩበት ጊዜ
በተዋዋሉት ውል ስለወረቀት ገንዘብ የማሳተም ጉዳይ
ነበረበት። ሆኖም ጣሊያን ኢትዮጵያ በቅኝ ግዛትነት ለመያዝ
ባላት ዕቅድ መሠረት ጣሊያን አገር ሊታተም የነበረው
ገንዘብ ቆመ።
 ምኒልክ ሀሳባቸውን ወደ ፈረንሣይ በማዞር የገንዘብ ለውጥ
መደረጉን የሚያረጋግጥ አዋጅ የካቲት 4 ቀን 1885 አወጁ።
የመጀመሪያዎቹ የምኒልክ ገንዘቦች በ1887 ታተሙ።ለሁለተኛ
ጊዜ በ1889 ታተመ። በተከታታይም በ1890፣ በ1891፣
በ1892 ታትመዋል።
 በአዋጁ መሠረት የሚታተመው ገንዘብ በ7 ዓይነት
እንደሚዘጋጅ ይገልጻል። እነዚህም ብር፣ አላድ፣ ሩብ፣
ተሙን፣ ግርሽ፣ ግማሽ ግርሽ እና ሩብ ግርሽ ናቸው።
የምኒልክ ብር=1 ጠገራ ብር፤1 አላድ= 2 ብር፤ 4ሩብ=1ብር፤
8ተሙን=1ብር፤ 16 ግርሽ=1ብር፤32 ግርሽ ግርሽ=1ብር፤
45ሩብ ግርሽ=1 ብር።
 ብሮቹ መታተም ከጀመሩበት ከ1887 እስከ አቆመበት 1904
ድረስ ብር፣ 1 297 830፣ አላድ 300 100፣ ሩብ 921 351፤
ግርሽ ( መሀለቅ) 16 652 857 ታትመው ሥራ ላይ
ውለዋል።

(24) የብር መቅረጫና ማተሚያ ቤት፦
 የብር መቅረጫው እና መተሚያው መቸ ሥራ እንደጀመረ
የሚያመላክት መረጃ ባይገኝም ከ1892 እስከ 1901 ባሉት
መካከል እንደሚሆን ይታመናል።የምኒልክ ብር ባገር ቤት
መታተም ሲጀምር ሕዝቡ እንደተለመደው እንዲህ ሲል
ዘፈነ።
 አጋሰስ መጋዣ አህያ እንዳልጭን፣
ፈረንጅ በጥበቡ እንዳይኮራብን፣
እምዬ ምኒልክ ሰራን ብሩን፤
ከገበያ ውጡ ጥይትና ጨው፣
የፈረንጆቹን ብር ሠራ አባ ዳኘው፤
 ዝቀህ ስጠኝና አሽከርህ ልክበር፤
ዳኘው ካስነጠርከው ካሠራኸው ብር፤

(25) ባንክ ቤት፦
 የገንዘብ መቅረጫና ማተሚያ መምጣቱ የገንዘብ
ሥርጭቱን ስላዳበረው ንግድ ባገር ውስጥና በውጭ
እየሰፋ መጣ። ፋብሪካዎችም ማቆጥቆጥ ስለጀመሩ የባንክ
አገልግሎትን አስፈላጊ አደረገው።በዚህ መሠረት ዳግማዊ
ዐፄ ምኒልክ የእንግሊዙን ሚኒስትር ሰር ጆን ሀሪንግቶን
ከመንግሥቱ ጋር ተነጋግሮ ባንክ እንዲቋቋም
እንዲረዳቸው አማከሩት። ሀርንግቶንም በጉዳዩ ተስማምቶ
የኢትዮጵያ ባንክ እንዲቋቋም ባደረገው ጥረት መጋቢት 1
ቀን 1897 ከምስር አገር ባንክ ኩባንያ ጋር ለ50 ዓመት
የሚቆይ 9 አንቀጾች የያዘ ውል ተዋዋሉ። በዚህም
መሠረት ባንክ ኦፍ አቢሲኒያ የተባለው ባንክ ነሐሴ 27 19 8221 Georgia Avenue, Silver Spring, MD. 20910 www.moreshwegenie.org

ቀን 1901 ተከፍቶ ሥራውን ጀመረ። ባንኩ ሥራው
የጀመረው በራስ መኮንን ግቢ ሲሆን፣ራሱ ባሠራው ሕንጻ
የተዛወረው በ1902 ላይ ነው።

(26) የጡብ ፋብሪካ፦
 በመጀመሪያ ለቤት መሥሪያ የሚሆን ጡብ የሚመጣው
ከውጭ አገር ነበር። ይህ ደግሞ ውድ በመሆኑ፣ምኒልክ
ፋብሪካው አገር ውስጥ እንዲቋቋም ፈለጉ። በመኑም
በ1900 የመጀመሪያው የጡብ ፋብሪካ አዲስ አበባ ላይ
ተቋቋመ። በተከታዮቹ 6 ዓመታት ውስጥ 3 ተጨማሪ
የጡብ ፋብሪካዎች ተከፈቱ። ንብረትነታቸው ግን ሁሉም
በውጭ ሰዎች የተያዙ ነበሩ።

(27) የቤት ክዳን ቆርቆሮ ከ1890ዎቹ ጀምሮ ወደኢትዮጵያ መግባት ጀምሯል።

(28) የእህል ወፍጮ፦
 የንጉሡን ግብረ በላ በእጅ እህል አስፈችቶ መቀለቡ
አስቸጋሪ እየሆነ በመምጣቱ የእህል ወፍጮ አስፈላጊ ሆነ።
በዚህም መሠረት በ1898 ለጁሴፔ ባዋጅቱ ሆለታ ወንዝ
ላይ አቋቁሞ እህል እንዲፈች ለ10 ዓመት በውል ሰጡት።
የመጀመሪያው የእህል ወፍጮ ይህ መሆኑ ነው።

(29) ኤክስሬይና የላቦራቶሪ መሣሪያ፦
 ግንቦት 25 ቀን 1900 ዓም በተጻፈ ውል ምኒልክ ለ25
ዓመት የሚቆይ አሌክሳን ታርፓንያ ከተባለሰው ጋር
ላቦራቶሪ መሣሪያና ለአምስት ዓይነት በሽታዎች
ማለትም፣(የትልቁ በሽታ፣የትልቁ ቁርጥማት በሽታ፣የከብት
መድኃኒት፣ የጨብጥ፣የቂጥኝ )መድኃኒቶች እንዲያስገባ
ውል ሰጥተዋል።

(30) የጨርቃጨርቅ ፋብሪካ፦
 ምኒልክ ሕዝቡ የዘመናዊ አልባሳት ተጠቃሚ እንዲሆን
ሰኔ 6 ቀን 1898 ዓም ሙሴ አልፎንስ ባሮን ዲሚሊዮስ
እና ዶክተር ፍሪዳሪቆስ ሸዋርድ ከተባሉ የአውስትሪያ
ተወላጆች ጋር የጨርቃጨርቅ ፋብሪካ እንዲያቋቁሙ
ተዋውለዋል። በዚህ ውል መሠረት የመጀመሪያው
ፋብሪካ ውሉ ከጸናበት ቀን ጀምሮ በ3 ዓመት ጊዜ ውስጥ
እንደሚቋቋም ይደነግጋል። በዚህ ውል መሠረት
የመጀመሪያው የጨርቃጨርቅ ፋብሪካ 1901 ተከፍቷል
ማለት ይቻላል።

(31) የእንጨት መሰንጠቂያ መኪና፦
 ምኒልክ እያደገ የሄደውን የቤት ግንባታ ፍላጎት ለማሟላት
የእንጨት መሰንጠቂያ መሣሪያ በማስፈለጉ ፋሌር ቄርሎስ
ከተባለ ሰው ጋር ሐምሌ 1 ቀን 1895 ዓም ተዋውለዋል።

(32) ባሕር ዛፍ፦
 በማገዶና በቤት ሥራ ደኑ በመመናመኑ ምክንያት አዲስ
አበባ የማገዶና የቤት መሥሪያ የሚሆን እንጨት
እየመነመነ በመምጣቱ ለምኒልክ አሳሳቢ ጉዳይ
ሆነባቸው። እንጦጦን ለቀው ወደ አዲስ አበባ ያመጣቸው 20 8221 Georgia Avenue, Silver Spring, MD. 20910 www.moreshwegenie.org

ምክንያቶች ብርድ፣ የውኃ እጥረትና የማገዶ እጥረት
ነበር። የማገዶ እጥረት የአዲስ አበባም ዋና ችግር ሆነ።
ለዚህም ችግር መፍትሔ ለመስጠት ሲያውጠነጥኑ ባጭር
ጊዜ ተተክሎ ለጥቅም የሚውል የዛፍ ዓይነት እንዳለ
ተረዱ።
 በወቅቱ የነበረውን የማገዶ እጥረት ለመግለጽ እንዲህ
ተብሎ ተዘፍኗል፤
 ይሻለኛል ብዬ ወታደር ባገባ፣
አቃቂ ሰደደኝ ፋንድያ ለቀማ፤
 ምኒልክ የማገዶ እጥረትን ለመቋቋም አዲስ ዓለምን
ለመቆርቆር ግድ ብሏቸው ነበር። ምኒልክ ባደረጉት ጥረት
በ1886 ዓም የባሕርዛፍን ፍሬ ከአውስራሊያ አስመጥተው
የአዲስ አስተከሉ።
 ባሕርዛፍ ወደ አገራችን የመጣው በታቀደ መንገድ
ሳይሆን፣ሞንዶ ቪዳልዬ የተባለ ፈረንሣዊ የኢትዮጵያ
ፖስታ አገልግሎት ድርጅት ሥራ አስኪያጅ የነበረ
ከጎርዳሜ ወንዝ (ጎላ ሚካኤል አጠገብ) ካለው መኖሪያ
ቤቱ ጓሮ የሰላጣ ተክል ፍሬ ከአውስትራሊያ አስመጥቶ
ይዘራል። የተዘራው ፍሬ ሰላጣ ሳይሆን ባሕርዛፍ
ይሆናል።ይህን የአዲስ አበባን የማገዶ እጥረት የሚያቃልል
ተክል በማግኘቱ ተደስቶ ለምኒልክ ነገረ።ምኒልክም
ፍሬው በብዛት መጥቶ እንዲተከል አደረጉ። እንጦጦ ላይ
የተተከለው የመጀመሪያው ባሕርዛፍ 1897 ላይ ነው።

(33) የቢራና የልኮል ፋብሪካ፦
 ምኒልክ በቢራና የአልኮል ፋብሪካ ለማቋቋም ግንቦት 28
ቀን 1897 በተጻፈ ውል ሙሴ ካም ኒሽድ ፣ ማብሆልዝ እና
ክሊንግ ከተባለው የጀርመን ኩባንያ ጋር ተዋዋሉ።
ፋብሪካው እንዲቋቋም የተፈለገው ሆለታ ነበር።ሆኖም
ውል ወሳጆቹ ቦታው ሩቅ ነው በማለት ሳይሠሩ ቀሩ።
በቃል ሲወርድ ሲዋረድ በደረሰ መረጃ መሠረት የአዲስ
አበባው ቅዱስ ጊዮርጊስ የቢራ ፋብሪካ የተመሠረተው
በምኒልክ ዘመን ነው ስለሚሉ፤ ይህ ዕውነት ከሆነ
ፋብሪካው ከላይ በተጠቀሰው ውል መሠረት የተሠራ ነው
ማለት ይቻላል።

(34) የጥይት ፋብሪካ፦
 የአዲስ አበባ ጥይት ፋብሪካ የተመሠረተው በ1900ዓም
ነው። ያቋቋመውም የእንግሊዝ ተወላጅ የሆነው
ሀምፍሬይስ ነው። ይህን ፋብሪካ እንደከፈቱ «
አፍሪካውያን ነፃ መውጣት አለባቸው፣ኢትዮጵያም የጥንት
ክብሯን ፣ወሰኗን በሙሉ ለማስከበር ትነሳለች» ነበር
ያሉት።

(35) የቆዳ ፋብሪካ፦
 የቆዳ ፋብሪካ የተቋቋመው በ1900 ነው። ያቋቋመውም
ባይዶ የተባለ የስዊስ ተወላጅ ነው።

(36) የሣሙናና የዘይት ፋብሪካ፦ 21 8221 Georgia Avenue, Silver Spring, MD. 20910 www.moreshwegenie.org

 የሣሙና እና የዘይት ፋብሪካ በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ
የተቋቋመው በ1899( እኤአ 1907) ነው። ባለቤቱም ቱርዬ
የተባl ፈረንሣዊ ነጋዴ ነው። መጠሪያውም የቱርዬ ፋብሪካ
የሚል ነበር።

(37) ከላይ ከተዘረዘሩት በተጨማሪ በምኒልክ ዘመነ መንግሥት ከሚከተሉት የቴክኖሎጂ
ውጤቶች ወደ አገር ውስጥ በማስገባት በሥራ ላይ እንዲውሉ ሆኗል። እነዚህም ፦
 የስፌት መኪና፣
 የጽሕፈት መኪና፣
 የሰብል ማጨጃና መውቂያ፣
 ማይክሮስኮፕ፣
 ፎቶ ግራፍ ማንሻ፣
 ቴሌስኮፕ፣
 ሰዓት፣
 ፎቶ ግራፍ፣
 የሥጋጃና የሙከሻ ሥራ፣ እና
 ሲኒማ ይገኙበታል።

እነዚህን ሁኔታዎች አሁን ካለንበት ላይ ቆመን ወደኋላ ብናይ፣ ያላንዳች ጥርጥር ምኒልክ ያሉዩትና ለኢትዮጵያ ያልተመኙት ብቻ
ሳይሆን፣ጨብጠው ያላዩት አዲስ ነገር አለመኖሩን እንረዳለን።ይህም በእርግጥም ምኒልክ የዘመናዊት ኢትዮጵያ መሥራችና አባት
መሆናቸውን ያላዳች ጥርጥር መገንዘብ እንችላለን። ምኒልክን የሚያጠቁሩ ምኒልክ በዐድዋ ድል የነሷቸው የአውሮፓ ቅኝ ገገዥዎች
ተከታዮች ብቻ ናቸው።
2 የዐፄ ምኒልክ ሰብአዊነት፤
 የኢትዮጵያ ፖለቲካዊ ባህል መቻቻልና መከባበር፣መወያየትን መደማመጥ የሌለበት፣በአጥቂና
በተጠቂ፣በአጥፊና በጠፊ ኃይሎች መካከል ተፋጥጦ የኖረና ያለ መሆኑ ዕውነት ነው። ቂም በቀልተኝነት
አውራ የፖለቲካ ባህላችን መገለጫ መሆኑም ግልጽ ነው። ይህ የረጅም ጊዜ ታሪካችን ዓይነተኛ መገለጫ
ነው። አሁንም ከዚህ በቀልተኝነት ልንወጣ ቀርቶ፣በቀልተኝነት የፖለቲካ ባህላችን መገለጫ መሆኑን ገና
የተረዳን አንመስልም። ተከታይ ትውልድ ባያገኙም ይህን ባህል ሰብረው የወጡ ብቸኛው የኢትዮጵያ
ንጉሠ ነገሥት ዳግማዊ ዐፄ ምኒልክ ብቻ ናቸው።«እምዬ » «አባዳኘው» የተሰኙት ስሞችም የተቸሩዋቸው
በሌላ በምንም ሳይሆን፣በተግባር ባሳዩዋቸው የሰብአዊነት፣የዕኩልነት፣የፍትሕና የመሐሪነት ባሕሪያቸው
ነው። በዚህ ረገድ ካሳዩዋቸውና በተግባር ካረጋገጡዋቸው የሰባዊነትና የመሐሪነት ተግባሮች የሚከተሉት
ለአብነት የሚጠቀሱ ናቸው።
 (1) ምኒልክ ከመቅደላ አምልጠው ሸዋ እንደገቡ ያገቧቸው ሁለተኛ ሚስታቸው ወ/ሮ ባፈና ከምኒልክ
ጋር በቁርባን ተጋብተው ከልጆቻቸው አንዱ የምኒልክ አልጋ ወራሽ እንዲሆን ይመኙ ነበር። ምኒልክ ግን
ባፈናን ቢወዱዋቸውም እንደማይወልዱላቸው ስለሚያውቁ ከእርሳቸው ጋር መቁረብን አልፈለጉም።
በአንፃሩ ምኒልክ አልጋ ወራሽ የሚሆን ልጅ ፍለጋ ወለተሥላሴ የሚቡሉ ሴት ቁባት አስቀምጠው ነበር።
ባፈና የፈለጉት ካለመሆኑም በላይ በመቅናታቸው በምኒልክ ላይ ማሴር ጀመሩ። በዚህም መሠረት
የምኒልክን የሥጣን ተቀናቃኝ የሆነውን መሸሻ ሰይፉን፣ መርድ አዝማች ኃይለሚካኤልን እና አማቻቸውን
መሐመድ ዓሊን በማስተባበር በምኒልክ አልጋ ላይ ጦርነት አስነሱ። ንብረት ዘረፉ። ምኒልክ ሦስቱንም ተራ
በተራ ድል ከነሱ ባኋል፤ ባፈናን ለመበቀል ሳይሹ፣ ለአፈንጉሥ በዳኔ በራሳቸው ጠያቂነት በማጋባት
ይጠቀሙበት የነበረውን መተዳደሪያቸውን ፈቅደውላቸው እስከ ጊዜ ሞታቸው ድረስ በሰላም እንዲኖሩ
አድርገዋል።
 (2) ማንም የኢትዮጵያን ታሪክ በቅጡ የሚያውቅ ሰው እንደሚገነዘበው፣አንድ ነጋሢ ሢነግሥ አስቀድሞ
የሚያሥረው የሥጋ ዘመዶቹንና ለዘውዱ ቅርበት ያላቸውን ሰዎች መሆኑ ይታወቃል። ምኒልክ ይህን
አላደረጉም። ያውም አጎታቸው የሆነውና ቴዎድሮስ እርሳቸውን አስረው ወደ መቅደላ ሲወስዱ፣ሸዋን
እንዲያስተዳድር ያደረጉት አጎታቸው መርድ አዝማች ኃይለሚካኤል፣እርሳቸው ሸዋ ሲገቡና በኋላም የወ/ሮ 22 8221 Georgia Avenue, Silver Spring, MD. 20910 www.moreshwegenie.org

ባፈና ተባባሪ ሆኖ የወጋቸውን ፣ከተማቸውን አንኮበርን ያቃጠለውን፣ ለመበቀል አልፈለጉም። ማዕረግ
ሰጥተው የሚተዳደርበት አገር በመስጠት በሰላም እንዲኖር አድርገዋል።
 (3) በተመሳሳይ መልኩ የአጎታቸው የሰይፉ ሣህለሥላሴ ልጅ የሆነው መሸሻ ሰይፉ ከወ/ሮ ባፈና ጋር
አብሮ በመንግሥታቸው ላይ ጦርነት የከፈተውን ምረው የደጃዝማችነት ቀሚስ በማልበስ በወረባና በጉለሌ
ላይ ሾመውታል።
 (4) በመጀመሪያ ከአማታቸው ከወ/ሮ ባፈና፣ቀጥሎ ከተማቸውን ወረይሉን አቃጥለው ካፄ ዮሐንስ ጋር
ያበሩትን መሐመድ ዓሊን ( በኋላ ንጉሥ ሚካኤል) ምረው ልጃቸውን ሸዋረገድን በማጋባት በወሎ ላይ
የበላይነቱን ይዘው እንዲኖሩ አድርገዋል።
 (5) በ1874 ከንጉሥ ተክለሃይማኖት ጋር እምባቦ ላይ ባደረጉት ጦርነት፣አያሌ ተከታዮቻቸው
አልቀውባቸው፣በመጨረሻ ንጉሥ ተክለሃይማኖት ቆስለው ሲማረኩ፣ምኒልክ የተማራኪውን ንጉሥ
ማዕረግና ክብር ጠብቀው፣ ደማቸውን በለበሱት ኩታ ጠርገው፣ቁስላቸውን እራሳቸው እያከሙና እያጠቡ፣
በክብር ከተከታዮቻቸው ጋር ወደ እንጦጦ በመውሰድ አሳክመው አድነው ወደ አገራቸው የሰደዱ ናቸው።
በዚህ ጊዜ ምኒልክ የተክለሃይመኖትን መኳንንቶች እናንተ ብትማርኩኝ ምን ታደርጉኝ ነበር ብለው
ቢጠይቋቸው፣«ቆራርጠን ላሞራ ነበር የምናበላዎ» ብለው እንደመለሱላቸው ታሪካችን ያስረዳናል።
 (6) የወያይታው ካዎ ጦና ምኒልክ በተደጋጋሚ በሰልም እንዲገብራና አገሩን እንዲያስተዳድር ደጋግመው
ቢጠይቁት ለክርስቲያን ንጉሥ አልገብርም በማለት እንዲያስገብሩት የተላኩትን የምኒልክ የጦር አበጋዞች
ድል በመንሳቱ ራሳቸው ምኒልክ መዝመት ግድ እንዳላቸው ይታወቃል። በምኒልክ የተመራው ጦር ካዎ
ጦናን አቁስሎ በመማረክ ለምኒልክ ይዞ ሲያቀርባቸው፣ምኒልክ አዝነው ቁስላቸውን ራሳቸው በማጠብ
አስታመው በማዳን ምኒልክ ራሳቸው ክርስትና አንስተው አገራቸውን እንዲያስተዳድሩ መልሰው
ልከዋቸዋል።
 (7) ምኒልክ በሰው ልጆች ዕኩልነት ፍጹም ዕምነት የነበራቸው መሪ ነበሩ። በዚህም የተነሳ ባርነትን
በአዋጅ የከለከሉ ከመሆናቸውም በላይ ለአባ ጅፋር የጅማው ገዥ የሚከተውን ደብዳቤ በመጻፍ ሰዎችን
ባሪያ ብለው እንዳይጠሩ ጭምር ማስጠንቀቂያ የሰጡ ናቸው።
ይድረስ ካባ ጅፋር፣
ይህንን የደንብ ወረቀት ጽፈንልሃል።
ከጃንጃሮ ወዳንተ አገር የመጣውን ጋላ እንግዲህ ከጄ ገባልኝ ብለህ ጭቡ አድርገህ
ባርያዬ ነህና አንተንም ልበድልህ ፤ልጅህንም አምጣና እንደከብት ልሽጠው
አትበል።ይህን ያህል ዘመን አባቶቻቸው ከአባቶችህ፣ልጆቹ ካንተ ጋር አብረው ኑረው
ባርያ ሊባሉ አይገባም። ባደባባይም ባርያዬ ነው እያልክ አትሟገት። የሰው ባርያ
የለውም። ሁላችንም የእግዚአብሔር ባርያዎች ነን። እግዚአብሔር መርጦ ፣ከሰው
አልቆ ሲያስገዛህ ጊዜ በሰው መጨከን አይገባም። ለሰው ቢያዝኑ ዕድሜ ይሰጣል።
ከኔም ጋር በእግዚአብሔር ቸርነት ጎንደሬ ሁሉ ተሰብስቦ እዚህ ሸዋ መጥቶ
ተቀምጧል። አገሬ ልግባ ያለ እንደሆነ ባርያ ነህ ተብሎ ሊያዝ ነውን?
ደግሞም እወደደበት እተመኘው ቦታ ላይ ይቀመጥ እንጂ ካንተ አገር ተነስቶ ወደ
ጃንጃሮ ቢሄድ ፣ወደሌላ ወደ ወደደው አገር ቢሄድ የኔ ዜጋ ነው ብለህ ልትይዝ
አይገባም። የጃንጃሮው ሰው ፣የሌላም አገር ሰው አንተን ወዶ ወዳንተ አገር ቢገባ
የጃንጃሮም ገዥ፣ሌላውም ገዥ ሁሉ የኔ ዜጋ ነው ብሎ አይያዝ። ድሀው እወደደው
እተመቸው ቦታ ይኑር።
የካቲት 8 ቀን 1902 ዓም አዲስ አበባ ከተማ ተጻፈ። (ጳውሎስ ኞኞ፣1984፤33-34)
ይህን ደብዳቤ በሚገባ ያጤነ ሰው ምኒልክ ፍጹም ሰብአዊና በሰው ልጆች ዕኩልነትና
ከቦታ ቦታ ተዘዋውሮ የመሥራት መብትን ከተባበሩት መንግሥታት በፊት የተረዱ
እንደነበሩ መገንዘብ ይቻላል።
 ምኒልክ በሃይማኖቶች ዕኩልነት የሚያምኑ በመሆናቸው እንደነገሡ« እንግዲህ ንጉሥህ እኔ ነኝ፤ዕዳ
ያለብህ ነፃ ብየሃለሁ፤በዱር በገደልም ያለህ ምሬሃለሁ፤»የሚል አዋጅ በማሳወጅ፣ በፈቃዱ ተጠምቆ
ክርስቲያን ካልሆነ በቀር፣እንደአባቱ ሃይማኖት እንዲኖር፣ እንጂ ፣በግድ እንዳይጠመቅ ከለከሉ።የትንባሆ
ነገር ሰው ሁሉ እንደልማዱና እንደወደደ እንዲያደርግ ፈቀዱ። ወታደር ተሠሪ እንዳይሆን አደረጉ።
 ሰው ሲባል ዕኩል ነውና ማንም ሰው ፣ ሰውን ባርያ እንዳይል ብለው የባርያን ነፃነት ያወጁና ሰው
እንዳከብት እንዳይሸጥ ከቴዎድሮስ ቀጥለው የታገሉ ምኒልክ ናቸው። 23 8221 Georgia Avenue, Silver Spring, MD. 20910 www.moreshwegenie.org

 ጋብቻ በሴት ወላጆች ፈቃድ ሳይሆን ፣በሴቲቱ ፈቃድና ምርጫ ፣የመረጠችውን ፣የወደደችውን እንድታገባ
ያወጁና ለሴቶች መብት መከበር የታገሉ ምኒልክ ናቸው።
 ሠራተኛ በሥራው እንዳይበደል የሠራተኛ ሕግ ያወጡ ምኒልክ ናቸው።
 በ1885 ላይ በደጃዝማች መሸሻ ወርቄና በአለቃ አድማሱ አቀነባባሪነት፣ምኒልክን አስወግዶ በቦታው
የመርድ አዝማች ኃይሌን ልጅ ፊታውራሪ ጉልላቴን ለማንገሥ ሤራ ተጠንስሶ፣ሤራው ተደርሶበት የሤራው
ተሳታፊዎች ለፍርድ ቀርበው ሞት ሲፈረድባቸው፣ምኒልክ የሞት ቅጣቱን አንስተው በእስራት እንዲቀጡ
አድርገዋል።
 ዐፄ ምኒልክ መቀሌ ተከበው የነበሩትን ጣሊያኖች በውኃ ጥም በመረታታቸው ፒየትሮ ፊልተር ለተባለው
እንዲህ አሉት፣«—–እናንተ እኛን ለማሸነፍና ድል ለማድረግ መጥታችኋል። የኢትዮጵያንም ሕዝብ
ከባርነት አገዛዝ ነፃ እናወጣሃለን ትላላችሁ። ነገር ግን እንኳን የኢትዮጵያን ሕዝብ እነኚህን በምሽጋቸው
ውስጥ የታፈኑትን ምስኪን ሰይጣን ወገኖቻችሁን ለማውጣት አልተቻላችሁም። የእኔም የደካማነት
እንደናንተ ከሆነ ፣እነኚህ ሰዎቻችሁ በውኃ ጥም እንዲሞቱ አደርጋለሁ። ይሄን ለባራቴሪ ንገረው። ቅዱሳን
መላዕክት ግን ጠላቶቻችንን እንድንወድ ይነግሩናል።እኔ ክርስቲያን ነኝ። የአረመኔ ሕዝብ ንጉሥ
አይደለሁም። ስለዚህ እኚህ ክርስቲያኖችም አይሞቱም። የሚመሩዋቸው ሰዎች ላኩና ይውስዷቸው።
ልትወጉን የምትፈልጉ ከሆነም ባንድነት ሁኑና ጠብቁኝ።እመጣለሁ—አሉኝ »ማለቱን ገልጿል።(ጳውሎስ
ኞኞ 1884፣186)
 መቀሌ ተከበው የነበሩትን ጣሊያኖች ፈቅደው ወደ አዲግራት እንዲሄዱ ሲያደርጉ ለመጓጓዣ 500 ግመልና
በቅሎች በዋጋ እየገዙ እንዲሄዱ የፈቀዱ ናቸው። ለአዛዡ ማጆር ጋሊያኖም መለፊያ መርገፍ የተጫነች
በቁሎ ሰጥተውታል።
 ዐፄ ምኒልክ ከዐድዋ ድል በኋላ ከዓለም ዙሪያ በርካታ ደብዳቤዎች ደረሱዋቸው። ከደረሱዋቸው
ደብዳቤዎች መካከል ከአውስትራሊያና ከቤኑዜላ የደረሳቸው «የእርሰዎ ወታደሮች መሆን እንፈልጋለን »
የሚሉ ነበሩ።
 ምኒልክ ስለትምህርት፦
 « —-ወንድ ልጆችና ሴት ልጆች ሁሉ ከስድስት ዓመታቸው በኋላ ወደ
ትምህርት ቤት እንጊገቡ ይሁን» በማለት ለትምህርት መሥፋፋት ብቻ
ሳይሆን፣ የፆታዎች ዕኩልነትን ያረጋገጡ ናቸው።
 « ያላስተማርህ ሰው እንደመካን ሰው ርስትህን ሹም ይወርስሃል እንጂ፣
ያልተማረ ልጅህ አይወርስህም፤ ላስተማሪውም ቀለብና ደመወዝ እኔ
እችላለሁ።» ሲሉ አዋጅ ያስነገሩ ናቸው።
 ምኒልክ አዳዲስ ነገሮችን ለሕዝብ ለማስተማር አዲሱን ነገር ራሳቸው በመሥራት ያሳዩ የነበሩ የተግባር
አራኣያ ነበሩ።
 የመጀመሪያውን አውቶሞቢል የነዱ ምኒልክ ናቸው።
 በአገሪቱ የሹፌሮች ታሪክ ውስጥ “ፐርፌክት ድራይቨር“ የሚለውን
የመጀመሪያውን የመንጃ ፈቃድ የተቀበሉ ናቸው።
 በመኪና የሚፈጨውን እህል የሚፈጨው ጋኔል ነው ተብሎ
ይታመን በነበረበት ጊዜ ጋኔል ያለመሆኑን ለማሳወቅ
የመጀመሪያውና የመጨረሻው ኢትዮጵያዊ ዱቄት አስፈጭ ንጉሥ
ምኒልክ ናቸው።
 የመጀመሪያውን ስልክ አስገብተው ጋኔሉ ከዙፋኑ አጠገብ ይውጣ
ብለው የዘመኑ ጳጳስ ጭምር ከባድ ተቃውሞ ቢያነሱባቸው
ታግለው ስልክን ያቋቋሙ ምኒልክ ናቸው።
 የመጀመሪያዋን ብስክሊት መንዳት ተምረው የነዱ ምኒልክ ናቸው።
 እቴጌ ጣይቱን ብስክሌት መንዳት አስተምረው ሴቶች ከመሸፋፈን
እንዲወጡ የታገሉ ምኒልክ ናቸው።
 ሆቴል መመገብ ነውር አለመሆኑን ለማስተማር በአዲስ አበባ
የመጀመሪያውን ሆቴል ከፍተው ባለቤታቸውን ጣይቱን ወጥ ቤት
አድርገው በገንዘባቸው መኳንንቱን እየጋበዙ ሆቴል መብላትን
ያስተማሩ ምኒልክ ናቸው።
24 8221 Georgia Avenue, Silver Spring, MD. 20910 www.moreshwegenie.org

 ምኒልክ ሹመትና ዕድገት በሥራና በችሎታ እንጂ ፣በመወለድ አይሆንም ያሉና ለሥራ ከበሬታ የሰጡ ሩቅ
አሳቢ መሪ ነበሩ።
 ምኒልክ ስለሙያ( ሥራ ዕኩልነት) ፦ ሕዝቡ በባህሉ ሙያን(ሥራን ) ያንቋሽሽ ስለነበር፣የሙያን ዕኩልነትና
ጥቅም ለማረጋገጥ እንዲህ ሲሉ አሳወጁ።« ከዚህ ቀደም ብረት ቢሠራ ጠይብ፣ ሸማ ቢሠራ ሸማኔ( ቁጢት
በጣሽ)፣ ቢጽፍ፣ ጠንቋይ፣ ቤተክርስቲያን ቢያገለግል ደብተራ፣ አራሹን አፈር ገፊ፣ ነጋዴውን መጫኛ
ነካሽ፣ እያላችሁ ትሰድባላችሁ፣ልጁ ምናምን ሥራ የማያውቀው ሰነፉ ፣ብልኁን እየተሳደበ
አስቸገረ።ቀድሞም ይህ ሁሉ ፍጥረት የተገኘው ከአዳምና ከሔዋን ነው እንጂ ሌላ ሁለተኛ ፍጥረት የለም።-
—እንግዲህ ግን እንዲህ ብሎ የተሳደበ እኔን የሰደበ ነው እንጂ ሌላውን መሳደብ አይደለም። ዳግመኛ ግን
ሲሳደብ የተገኘ ሰው መቀጫውን አንድ ዓመት ይታሰራል። ሹማምንትም አስረህ ዓመት ለማስቀመጥ
የሚቸግርህ የሆነ እንደሆነ ወዲህ ስደድልኝ » በማለት ቁርጥ ያለ አስገዳጅ ደንብ ያወጡ ናቸው።

3 ምኒልክ በውጭ ሰዎች ዕይታ፦
ï‚· ኢንስክሎፒዲያ ብሪታኒካ፦ «____ምኒልክ ዘመናዊ ኢትዮጵያን የፈጠረ ሰው ነው—-»
ï‚· ጆን ማርካኪስ፦ «—-ምኒልክ ዘመናዊ ትምህርት ቤትን በመክፈት በኢትዮጵያ ውስጥ ዘመናዊ የትምህርት
ዘር የዘሩ ናቸው።»
ï‚· እስከ ሩዶልፍ ሐይቅ ድረስ የተጓዘው ዊልቤ በ1893 ባሳተመው መጽሐፉ «—-በጠረፍ ያሉ ሰዎች ምኒልክ
ጥሩ ሰው እንደሆነ ያውቃሉ። ምኒልክ ሁሉም ሰው በሃይማኖቱ ይደር ስላለና በሕዝቡ መሀል አድሎና
የኃይል ሥራ ስለማይሠራ ይሠሩታል»ጳውሎስ ኞኞ 1984፥38»
ï‚· ማርገሪ ፐርሃም የተባለ ሰው፣«—ምኒልክ በሰላም ጊዜ የቤተክርስቲያን አባል፣ በጦር ጊዜ ፣—ተዋጊ ንጉሥ
ነው። ስለዘመናዊ ዓለምም አእምሮው ክፍት ነው» ሲል በጋዜጣ ስፏል።
ï‚· ግሊከን የተባለ አውሮፓዊ «—ምኒልክ በጥበብ ሕዝቡን ሲያስተዳድር ፣ሕዝቡ በፍቅር እንዱከተለው
እንጂ፣በፍርሓት እንዲገዛለት አይፈልግም።—–በዚህ ምክንያት በማስተዳደሩ በኩል የወጣለት ጥሩ መሪ
ነው።»
ï‚· ኡላንዶርፍ የተባለው ሌላው አውሮፓዊ፣ « —በምኒልክ ዘመን የአገሪቱ ክብር አደገ። የዘመናዊ አስተዳደር
መሠረትም ጣለ። ንጉሡም በዘመናዊ በዘዴ አስተዳደር ይመራሉ—–»
ï‚· ሮድ የተሰኘው ደግሞ ምኒልክን እንዲህ ሲል ገልጿቸዋል፤ « —-በምኒልክና በሕዝቡ መሐል ርቀት የለም።»

4 ምኒልክን የሚያወግዙ እነማን ናቸው? ለምን?
 በምንገኝበት ዘመን ምኒልክን የሚያወግዙ ፖለቲከኞች ከኢትዮጵያ ሰሜን ፣ምዕራብ፣ ደቡብና ምሥራቅ
የአገሪቱ ክፍሎች ትውልዳቸውን የሚስቡት ብሔርተኛ ፖለቲከኞች ናቸው። እነዚህም በድርጅት ሻዕቢያ፣
ሕወሓት፣ኦነግ ፣የሐረሪና የሶማሊያ ነገዶች ድርጅቶች ናቸው።
 የሁሉም የምኒልክ ተቃውሞና ውግዘት ሐረጉን የሚስበው ምኒልክ የአውሮፓውያንን ኢትዮጵያን ቅኝ
ግዛት የማድረግ ፍላጎት በታላቁ የዐድዋ ጦርነት ያመከኑባቸው በመሆኑ፣ ያንን ቂም ለመወጣት፣አፍሪካና
እስያን በፍላጎታችን ሥር ስናውል ለምን ኢትዮጵያ ድል ነሳችን? ብለው በመጠየቅ ባደረጉት
መመራመር፣ለኢትዮጵያውያን አይበገሬነት፣ነፃነት ወዳድነትና የአገር ፍቅር ሦስት ጠንካራ መሠረቶች
እንዳሉ ተረዱ።
 እነዚህም ፦ (1) የአንድነት እና የሥልጣን ምልክት የሆነ ዘውዳዊ ሥርዓት፣ (2) የዘውዱ ርዕዮታለማዊ
ክንድ እና የሕዝቡ መንፈሣዊ ሕይዎት መገለጫ የሆነ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት፣(3) በኦርቶዶክስ
ተዋሕዶ ሃይማኖት ዙሪያ ራሳቸውን ያደራጁ ፣ላገራቸው፣ለነፃነታቸውና ለሃይማኖታቸው ቀናዒ የሆኑ
ነገዶች መኖር ናቸው። እነዚህ ጠንካራ መሠረቶች ካልፈራረሱ ኢትዮጵያን በማናቸውም የውጭ ኃይል
ሥር ማዋል እንደማይቻል ተረዱ። ስለሆነም ኢትዮጵያን በምዕራባውያን ፍላጎት ሥር ለማዋል በቅድሚያ
እነዚህ ተቋሞች መፍረስ እንዳለባቸው አመኑ።
 ተከታዩ ጥያቄ አቸው እነዚህን ተቋሞች እንዴት ማፍረስ ይቻላል ? የሚለው ሆነ። ለዚህ ጥያቄአቸው
ያገኙት መልስ በኢትዮጵያ ተማሪዎች እንቅስቃሴ ወቅት ኤርትራ በኢትዮጵያ ቅኝ ግዛት ተይዛለች።
በመሆኑም ኤርትራ ከኢትዮጵያ መገንጠል አለባት የሚለው ሻዕቢያና ጀብሃ፤ እንዲሁም የኢትዮጵያ ችግር
ብሔራዊ ጭቆና ነው ፣ ስለሆነም ተጨቋኝ ብሔሮች ጨቋኙን ብሔር ታግለው መበጣል የራሳቸውን ዕድል 25 8221 Georgia Avenue, Silver Spring, MD. 20910 www.moreshwegenie.org

በራሳቸው መወሰን አለባቸው ያሉ እንደ ሕወሓት፣ኦነግ፣ የሶማሊያ አቦና፣ እስላሚያ ኦሮሚያ የመሳሰሉ
ድርጅቶችን አገኙ። ምዕራባውያኑም «ቅቤ ሲያምርበት ተንከባሎ ከገንፎ ማሰሮ ይገባል» ሆኖላቸው
የኢትዮጵያዊነት ምሰሶና ማገር የሆኑት ጥንታዊ ተቋሞች ሊፈርሱ የሚችሉበት መንገድ የተመቻቸላቸው
መሆኑን በማመን፣ እነዚህን ድርጅቶች በሚፈልጉበት መልኩ መርዳት ብቻ ሳይሆን፣ ተቋሞቹ በፍጥነት
ሊፈራርሱ የሚችሉበትን መረጃ፣ገንዘብ፣ ዕውቀት፣ሎጂስቲክ ወዘተርፈ በመስጠት ፍላጎታቸውን እንዳሳኩ
እያየን ነው።
 ሽዕቢያ ምኒልክ በዐድዋ ጦርነት ለጣሊያን አሳልፈው ሰጡን( ሸጡን) በማለት ይከሷቸዋል፣ ይህ ግን ጠላት
ይቀባል ጠላት ነው፣ የሸጣቸው ዮሐንስ እንጂ ምኒልክ አይደሉም። ምኒልክማ ተሟገቱላቸው።
 ሕወሓት ምኒልክ የሚያወግዙት ሥልጣናችን በኃይል ከዮሐንስ ወራሾች በመውሰዳቸው ለትግራይ ሕዝብ
መራብ፣መቸገርና መሰደድ ተጠያቂ ናቸው ይላል፤
 ኦነግና መሰል ብሔርተኛ ድርጅቶች ምኒልክን የሚያወግዙት ፣ምኒልክ በአገር ግንባታው ወቅት እልቂት
አድርሰውብናል።«ጡት ቆርጠዋል» የሚል ነው። በዚህም በባህላችንና በቋንቋችን እንዳንጠቀም ተደርገናል
የሚል ነው።
 የአንድነት ኃይሉ በግራው ዘመም ርዕዮተ ዓለም ተጭበርብሮ የብሔርተኞቹንና የተገንጣዮቹ ፍላጎት ተገዥ
በመሆኑ ፣ ይኸውና ዘውዳዊ ሥርዓቱን በትብብር አፈረስን። ከዘውዱ ጋር የተዋህዶ ኦርቶዶክስ ሃይማኖት
ታሪካዊ ቦታዋን እንድታጣ ሆነ። የቀረው ዐማራ የተሰኘው ነገድ ሆነ። ይህንም ከመታሰር፣ከመገደል
፣ከሥራ ከመፈናቀል አልፎ በኢትዮጵያ ምድር እንዳይኖር እየተደረገ ነው።
 ዛሬ ምኒልክን ስም አጥብቀው የሚጠሉ ሰዎች በመጀመሪያ ደረጃ ሁሉም የባንዳ ልጆች ናቸው። ሁለተኛ
ሁሉም በምዕራባውያን ፍላጎት ሥር የዋሉ ናቸው። አብዛኞቹ በፀረ ኢትዮጵያ ሚሽነሪዎች ተኮትኩተው
ያደጉ ኢትዮጵያዊነትን አውልቀው የጣሉ ናቸው።
 እነዚህን ኃይሎች ለመታገል ብቸኛው መንገድ በኢትዮጵያዊነቱ የሚያምነው ኃልይ መደራጀት ነው።

6 ማጠቃለያ፦

ተወደደም ተጠላ፣ ምኒልክ የዘመናዊት ኢትዮጵያ መሥራች፣ የኢትዮጵያ ሥልጣኔ ጎሕ ቀዳጅ፣ የቅኝ ገዥዎች ቅስም ሰባሪ፣
የጥቁር ሕዝብ ኩራት፣ የኢትዮጵያውያን አባት መሆናቸውን ማስተባበል አይቻልም።

7 የጦርነቱ መነሻ ምክንያቶች፡-
7.1 የዐድዋ ጦርነት መነሻ ምክንያቱ እ.ኤ.አ መስከረም 26 ቀን 1885 የአውሮጳ ኃያላን መንግሥታት አፍሪካን እንደገና
ለመቀራመት በርሊን ላይ ያደረጉት ስብሰባና በስብሰባው የተላለፈው ውሣኔ ነው፡፡
በዚህ ስብሰባ አፍሪካን በመቀራመቱ ሂደት ወደኋላ የመጣችው ጣሊያን
ኢትዮጵያን ቀደም ሲል ከያዘቻቸው ኤርትራ (1881/1889) እና 1905
ከያዘቸው የጣሊያን -ሶማሊያ ላንድ ጋር ቀላቅላ የመያዝ መብት ሰጣት፡፡
7.2 በዚህ መሠረታዊ ምክንያት ኢትዮጵን ለመውረር ጣሊያን ሲያወጣ ሲያወርድ እ.ኤ.አ ግንቦት 2 ቀነ 1889 በጣሊያንና
በንጉሥ ምኒልክ መካከል በታሪክ የውጫሌ ውል በመባል የሚታወቀው ስምምነት አንቀጽ 17 ያስከተለው የትርጉም
መዛበት የፈጠረው አለመግባባት ወደ ዐድዋ ጦርነት ሁለቱ አገሮች እንዲገቡ ስበብ ሆኗል፤
የአንቀጹ የአማርኛ ትርጉም፡-
“የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት ከሌሎች መንግሥታትና መስተዳድሮች
ጋር ለሚኖረው ጉዳይ ሁሉ የኢጣሊያ ንጉሣዊ መንግሥት አጋዥነት መጠቀም 26 8221 Georgia Avenue, Silver Spring, MD. 20910 www.moreshwegenie.org

ይችላል፡፡”
በጣሊያንኛው………. “ይችላል” የሚለው “ተስማምቷል” ይላል፡፡
ይኸን ተከትሎ፣ እ.ኤ.አ ጥቅምት 11 ቀን 1889 የጣሊያን የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር በውጫሌ ውል አንቀጽ 17 መሠረት
፣ኢጣሊያ ከውጪ መንግሥታት ጋር በኢትዮጵያ ስም ለመነጋገር ውክልና መረከቧን የሚያመለክት ሰርኩላር(ተዘዋዋሪ
ደብዳቤ) ለመንግሥታት ሁሉ አስተላለፈ፡፡ ይህም ኢትዮጵያ በጣሊያን ጥበቃ ሥር እንደሆነች የሚያረጋግጥ ነበር፡፡
ይህን ኢትዮጵያ በጣሊያን ጥበቃ ሥር ናት ሚለውን ደብዳቤ አሜሪካና ሩሲያ ሲቃወሙ፣ የቀሩት መንግሥታት ተቀበሉት፡፡
ከሁሉም በላይ ጀርመን፣
 እ.ኤ.አ በታህሳስ 1889 ምኒልክ የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት ሆነው ዘውድ መጫናቸውን ለአውሮጳ ለዘመኑ ኃያላን
መንግሥታት አሳወቁ፡፡ ይህም በተዘዋዋሪ መንገድ የጣሊያንን የጠባቂነት መብት የሚቃረን ነበር፡፡
 ቀጥሎ እ.ኤአ መስከረም 27 ቀን 1890 ዳግማዊ ዐፄ ምኒልክ ለጣሊያን ንጉሥ ቀዳማዊ ዑምቤርቶ የውጫሌ ውል
አንቀጽ 17ን የትርጉም መፋለስ የሚያመላክት ደብዳቤ ጻፉ፡፡
 ምኒልክ ከአውሮፓውያን ጋር ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ለማጠናከር እ.ኤአ በ1890 የእንግሊዝ፣ የፈረንሣይና
የሩሲያን ተወካዮች በቤተመንግሥታቸው ጠርተው አነጋገሩ፡፡
 እ.ኤ.አ ሚያዝያ 10 ቀን 1891 የኢትጵያን ዳር ድንበር ከየት እስከየት እንደሆነ የሚያመለክተውን ታዋቂና ዝነኛ
የተባለውን ተዘዋዋሪ ደብዳቤ ለዓለም መንግሥታት በተኑ፡፡
 ጣሊያኖች በምኒልክና በዮሐንስ ላይ እንዳደረጉት ሁሉ፣ራስ መንገሻ በምኒልክ ላይ እንዲያምጽ ጥረት አደረጉ፤
በዚህም የተነሳ ራስ መንገሻ በጣሊያኖች እርዳታ ምኒልክን እጥላለሁ ብሎ ገመተ፡፡ በዚህ ግምቱ መሠረትም እ.ኤ.አ
ታህሳስ 7 ቀን 1891 ከጣሊያኖች ጋር የሚስጢር ውል ተዋዋለ፡፡ ውሉና ስምምነቱ ግን ብዙም ሳይቆይ ፈረሰ፡፡
 ጣሊያን ምኒልክ ጥገኝነቱን ይቀበላል፤ካልተቀበለ በኃይል እንወረዋለን በሚል አስተሳሰብ ኤርትራ ላይ ሆኖ
የጦርነት ዝግጅቱን ቀጠለ፤
 እ.ኤ.አ በየካቲት ወር 1893 ጣልያን በኢትዮጵያ ላይ ያላትን የበላይነት በዓለም ማኅበረሰብ ዘንድ ዕውቅና
ለማግኘት ዲፕሎማሲያዊ ጥረቷን አጠናክራ ቀጠለች፤
 በመሆኑም ሳሊምቤኒ የጣሊያን መንግሥት ተወካይ ሆኖ፣ሸዋ እንዲቀመጥና የምኒልክ አማካሪ እንዲሆን አደረገች፡፡
 በሐረር የፖለቲካ ተወካይ እንዲሆን የታሰበው ቼላሬ ኔራዚኒ እና በሸዋ ለፖለቲካ አማካሪነት የታጨው
ሌዎፖልድ ትራቨርሲ፣ሳሊምቤኒን ተከትለው ምኒልክ ቤተመንግሥት ውስጥ ገቡ፤
ሳሊምቤኒ አዲስ አበባ እንደደረሰ የሚከተሉትን ጠየቀ፡፤
1) በፍርድ ጉዳዮች አማካሪ ሆኖ ከንጉሠ ነገሥቱ ግቢ ለመግባትና ለመውጣት እንዲችል ፈቃድ
እንዲሰጠው፤
2) በጣሊያንና በኢትዮጵያኖች መካከል ለሚነሱ አከራካሪ ጉዳዮች በኤርትራው ገዥ በጄኔራል ባራቴየሪ
እንዲታዩ የሚሉ ነበሩ፡፡
የኢጣሊያኑ መልዕክተኞች ዓላማ የተረዳው የዳግማዊ ምኒልክ አስተዳደር በሳሊምቤኒ የቀረቡትን ጥያቄዎች ባለመቀበል
ውድቅ አደረገበት፡፡
ሳሊምቤኒ አከታትሎ የምጠይቃቸው ጥያቄዎች ከውጫሌ ውል የሚመነጩ ስለሆነ ንጉሡ ማብራሪያ እንዲሰጡኝ እሻለሁ
በማለት ጠየቀ፤
ዐፄ ምኒልክም ከሳሊምቤኒ ለቀረበላቸው ጥያቄ፣በኢትዮጵያና በጣሊያን መካከል የወዳጅነት ግንኙነት እንጂ፣ የጥገኝነት ውል
ወይም ስምምነት አልገባንም ሲሉ መለሱለት፡፡ 27 8221 Georgia Avenue, Silver Spring, MD. 20910 www.moreshwegenie.org

በዚህን ጊዜ የውጫሌን ውል የተዋዋለው የታወቀው የጣሊያን ዲፕሎማት ፒየትሮ አንቶኔሊ እንዲመጣና ጉዳዩን እንዲነጋገር
በጣሊያን በኩል ታምኖበት አንቶኔሊ መጥቶ ሳሊምቤኒን ተቀላቀለ፡፡ ቢሆንም ለውጥ አላመጣም፡፡
ዳግማዊ ዐፄ ምኒልክ ዲፕሎማሲያዊ ጥረታቸውን በመቀጠል እ.ኤ.አ የካቲት 27 ቀን 1893 በተጻፈ ደብዳቤ ጣሊያን
ኢትጵያን በሚመለከት የበላይነት መብት የሌላት መሆኑን የሚያረጋግጥና የውጫሌን ውል ውድቅ ያደረጉት መሆኑን
የሚያስረዳ ደብዳቤ ለዓለም አሰራጩ፡፡
ምኒልክ ላሰራጩት ደብዳቤ አጸፋ እንዲሆን ዘንድ ጣሊያን የሚከተሉትን ተግባሮች አከናወነ፤
1) በትግሬ ወሰን ላይ ወታደራዊ ኃይል አከማቸ፤
2) የኢትዮጵያን የንግድ እንቅስቃሴ ለመግታት በሱዳን ጠረፍ በመሐዲስቶች እጅ የነበሩ
አካባቢዎችን ተቆጣጠረ፣
3) እ.ኤ.አ በ1893 መሐዲስቶችን ድል ነስቶ አቆርደትን ያዘ፣
4) እ.ኤ.አ በ1894 ጄኔራል ባራቲየሪ ከሰላን ይዞ መሐዲስቶችን ከአካባቢው አስወጣ፤
የጣልያን ዲፕሎማቶች ሆነው ምኒልክ አንቀጽ 17ን እንዲቀበሉ ሊያግባቡ የመጡት አንቶኔሊ፣ሳሊምቤኒ፣ትራቬርሲ እና
ኔራዚኒ ጥረታቸው ሳይሳካላቸው ሲቀር፣ የጣሊያን መንግሥት ሌላ ሙከራ አደረገ፡፡ በመሆኑም እ.ኤ.አ በ1894 አጋማሽ
ሻለቃ ፒያኖ ወደ ምኒልክቤተ መንግሥት ዘልቆ በትዕዛዝ መልክ ንጉሡ ከጣሊያን ጋር ስላለው ግንኙነት ማብራሪያ
እንዲሰጡት ጠየቀ፡፡ የሚሰጠው ማብራሪያ አጥጋቢ ካልመሰለው ጦርነት ሊከተል እንደሚችል አስጠነቀቀ፡፡
ንጉሠ ነገሥቱም የኢጣሊያ መንግሥት የውጫሌን ውል አንቀጽ 17 የአማርኛውን ትርጉም ቢቀበል ለግራ ቀኙ ጠቃሚ ሊሆን
እንደሚችል ገለጹ፡፡ ይህ ካልሆነ ኢትዮጵያም ለጦርነት ዝግጁ መሆኗን አረጋገጡ፡፡
ይህም የጦርነቱን አይቀሬነት አረጋገጠ፡፡ ተከትሎም የጣልያን ጦር ደንበር እያቋረጠ ትግራይ መግባት ያዘ፡፡

7.3 የጦርነቱ አጀማመር፤ (የጣሊያኖች ትንኮሳ)
 እ.ኤ.አ ታህሳስ ወር 1894 የጣልያን ወታደሮች የኢትዮጵያን ወሰን አልፈው ገቡ፤
 እ.ኤ.አ ጥር 14 ቀን 1895 ጣልያኖች ኩአቲት ላይ ከራስ መንገሻ ሠራዊት ጋር የመጀመሪያውን ታላቅ
ውጊያ አደረጉ፡፡ መንገሻ ቀናቸው፡፡ ሆኖም በጄኔራል ኦሪሞንዲ የሚመራ የማጠናከሪያ ጦር ተልኮ
የመንገሻን ድል ቀለበሰው፡፡
 ራስ መንገሻ ወደ ሰንዓፌ አፈገፈጉ፣ ሰንዓፌ ላይ በተደረገው ጦርነት መንገሻ ተሸነፉ፤ሕይዎታቸውን ግን
አተረፉ፡፡
 ዳግማዊ ዐፄ ምኒልክ የጣልያን መንግሥት ጦሩን ከኢትዮጵያ ግዛት እንዲያስወጣ በኦፊሴል ጠየቁ፤
ሆኖም የጄኔራል ባራቲየሪ ሠራዊት ወደ መሀል ኢትዮጵያ ግስጋሴውን ቀጠለ፡፡ አዲግራትን ያዘ፤ ሚያዝያ
10 ቀን 1895 ዐድዋን ለሁለተኛ ጊዜ ያዘ፡፡
 በዐፄ ምኒልክ ዕውቅና ራስ መኮንን ወደ ጣሊያን ለመግባት ከጣሊያኑ ተወካይ ከሆነው ፌልተር ጋር
በሐረር የተለያዩ ስብሰባዎችን አደረጉ፡፡
 በዚሁ ጊዜ ንጉሥ ተክለሃይማኖት ከጣልያን ጋር አብረው ምኒልክን ለመውጋት ፍላጎት እንዳላቸውና
ይህም በምኒልክ ዘንድ በመታወቁ፣ምኒልክ ለተክለሃይማኖት የሚከተለቀውን ማስጠንቀቂያ በመጻፍ
ከድርጊታቸው እንዲታቀቡ አደረጉዋቸው፡፡ ምኒልክ ለተክለሃይማኖት የጻፉት ማስጠንቀቂያ “ ላንተ
ምንም አላንስም፤ግን ብዙ አድባራት የሚገኙበት አገርህ በእጅጉ ያሳዝነኛል፡፡ በቅርቡ መጥቸ አመድ
አደርገዋለሁ፡፡” ተክለሃማኖት ይህ መልዕክት እንደደረሳቸው ከጣሊያን ጋር ያደርጉት የነበረውን ግንኙነት
አቋረጡ፡፡ 28 8221 Georgia Avenue, Silver Spring, MD. 20910 www.moreshwegenie.org

 ጣሊያኖች ከምኒልክ በመነጠል አጋራቸው ለማድረግ ያዘጋጁት የአውሳውን ሡልጣን (ጧላ) ነበር፡፡
በመሆኑም እ.ኤ.አ 1894 አጋማሽ ላይ ሻምበል ፔሪሲኮ ወደ አውሳው ሡልጣን ተልኮ ተገናኘ፡፡ እርሱም
በጣሊያን መንግሥት ስም በርከት ያለ ገንዘብና ብዙ የጦር መሣሪያ ሰጠው፡፡ በለውጡም ምኒልክን
የሚወጉና የሚዘምቱ 20000 ጦር መልምሎ እንዲያዘጋጅ ጠየቀው፡፡ ሡልጣኑ ገንዘቡንም
መሣሪያውንም ከተቀበለ በኋላ ሁኔታውን ለምኒልክ እንዳሳወቀ አንድርዜይ ባርትኒስኪ፣ዮዓና ማንቴል-
ኒየችኮ ሲያረጋግጡ፣ጳውሎስ ኞኞ በበኩሉ አጤ ምኒልክ በተሰኘ መጽሐፉ እንዲህ ይለናል፡፡ “ዋግሹም
ብሩ የላስታው ከጣሊያን ጋር ተዋዋለ፤ይህድርጊት ታውቆባቸው በምኒልክ ታሰሩ፤ ራስ ሚካኤልም
በጣሊያን ተባብለው ነበር፤የአውሣው ባላባት ሼክ ጧላ ለጣሊያን አደረ፤ሆኖም በምኒልክ ጦር
ተደበደበ፤አላጌ ላይ በተደረገው ጦርነት ሼክ ጧላ 350 ዘመናዊ መሣሪያ የታጠቁ ወታደሮችን አሰልፎ
ኢትዮጵያን እንደወጋ ነግሮናል፡፤ሌላው የአውሣ ባላባት መሐመድ አንፋሪ ከጣሊያን ጎን በመሰለፍ
ኢትዮጵያን ሊወጋ እንደተዘጋጀ በሰሙ ጊዜ ራስ ወልደጊዮርገስ፣ደጃዝማች ተሰማ ናደውንና አዛዥ
ወልደጻዴቅን አዘው እንዲወጉት አደረጉ በማለት ጳውሎስ ኞኞ ገልጾታል፡፡
 ከአንዳንድ የፖለቲካ ክብደት ከሌላቸው ሰዎች በስተቀር፣ከታላላቅ ባላባቶች ውስጥ ጣልያን ያገኘው
ተባባሪ ጥቂቶች ብቻ እንደነበሩ እነአንድርዜይ ሲጠቅሱ በጳዎሎስ ኞኞ ከራስ ስብሓትና ራስ ሐጎስ
በተጨማሪ ሁለቱ ከላይ ስማቸው የተጠቀሱት የአውሳ ባላባቶች፣የወላይታው ካዎ ጦና ፣የሌቃውና
የለቀምቱ ባላባቶች ጆቴና ሞረዳ ወደ አድዋ እንዳልዘመቱ ይግረናል፡፡
 ለጣሊያን ከተባበሩት ባላባቶች መካከል፡-
1) የላስታው ገዥ ዋግሹም ብሩ፣
2) ራስ ሥብሃት የትግሬው፣
3) ራስ ሐጎስ የትግሬው ፣
4) የአውሣው ባላባቶች ሼክ ጧሊ እና መሐመድ አንፍሪ ይገኙበታል፡፡
ዋግ ሹም ብሩ ከጣሊያን ጋር መምከራቸው ለምኒልክ ጀሮ ይደርሳል፡፡ ምኒልክም ብሩ ሳያስቡት ተጠርው እንዲቀርቡ
ይደረጋል፡፡ ብሩ ከምኒልክ ግቢ እንደገቡ እንዲያዙና እንዲታሰሩ በማድረግ፣ ልጃቸውን ጓንጉልን የላስታ ዋግሹም አድርገው
ሾሙት፡፡
ሥብሃትና ሐጎስ ለጣሊያን ካገለገሉ በኋላ ተመልሰው ለምኒልክ እጃቸውን ሰጥተዋል፡፡
7.4. የጦርነት ዝግጅት፡-
7.4.1 በጣሊያን በኩል፣
 በኤርትራ የጣሊያን ጦር ኃይሎች አዛዥ ባራቲየሪ ፣ጣሊያን ድል አድራጊ እንደምትሆን ሙሉ እምነት
ነበረው፡፡ ኢትዮጵያን ድል ለመንሳትም 20 000 ሺ ወታደር በቂ እንደሚሆን አመነ፡፤
 ባራቲየሪ ከኢትጵያ ጋር የሚደረገው ጦርነት ናፒየር ከቴዎድሮስ ጋር ያደረገው ጦርነት ዓይነት
እንደሚሆን ሙሉ እምነት አድርጓል፡፡
 ባራቲየሪ የዳግማዊ ምኒልክን ፖለቲካዊና ወታደራዊ ችሎት እጅግ ዝቅ አድርጎ ገምቷል፡፡
7.4.2 በኢትዮጵያ በኩል፣
 አውሮፓውያን አገር ጎብኝዎች ስለምኒልክ ያላቸው አስተያየት እንዲህ የሚል ነበር፤ “ዳግማዊ ምኒልክ
ያለጥርጥር የላቀ ብቃት ያለው ፖለቲከኛ፣ታላቅ አርቆ አስተዋይና አቻ የሌለው ፖለቲካን የማሽተት
ተሰጥዖ የታደለው፣የጣሊያንን መስፋፋት በዝምታ ይቀበላል የማይባል ሰው፤” በማለት ይገልጧቸው
ነበር፤
 ምኒልክ ከጣሊያን ጋር ሲያደርጉት የነበረው መለሳለስ ለታክቲክ ነበር፤
 ምኒልክ ሥልጣን ከጨበጡ በኋላ የጣልያን ዕርዳታ አላስፈለጋቸውም፤ 29 8221 Georgia Avenue, Silver Spring, MD. 20910 www.moreshwegenie.org

 የጣልያን በሀገሪቱ ሰሜናዊ ክፍል ተጨማሪ መሬት የመያዝ ፍላጎት፣ምኒልክ የተማከለ ታላቅ መንግሥት
ለመመሥረት ካላቸው ዓላማ ጋር የሚጋጭ ነበር፤
 በውጫሌ ውል አተረጓጎም ላይ ድርድሮች በተደረጉ ወቅት ከኢጣሊያ በኩል ጥቃት ሊሰነዘር
እንደሚችል ምኒልክ ተገንዝበዋል፤ በመሆኑም የበኩላቸውን ዝግጅት አድርገዋል፡፡ ዝግጅቱም በውስጥና
በውጭ ነበር፡፡

7.4.3 በአገር ውስጥ የነበረው ዝግጅት፡,
1) ለመሣሪያ መግዣ የሚውል ልዩ ቀረጥ ተጥሎ እንዲሰበሰብ አደረጉ፣ በዚህም በአጭር ጊዜ ውስጥ
ሁለት ሚሊዮን ጠገራ ብር ተሰበሰበ፤
2) ለሠራዊቱ የምግብ እህል እንዲከማች አደረጉ፤
3) አገሪቱን ለመከላከል አስፈላጊ የሆነው መስዋዕትነት ሁሉ እንዲከፈል የሚለው የንጉሡ ጥሪ በመላ
አገሪቱ ተናኘ፡፡

7.4.4. የውጭ ዝግጅት፡-
1) ከውጭ አገር መሣሪያና ጥይት የሚገዛበት ሁኔታ ተመቻቸ፣
2) በጥቃቱ ዋዜማ ከመቶ ሺ በላይ ካራቢነር ጠብመንጃ ገቢ ተደርጓል፤ ይህም ቀደም ሲል ከጣልያን
በስጦታ ካገኙት ጋር ተዳምሮ ከሁለት መቶ ሺ በላይ ካራቢነር ጠብመንጃ ሠራዊታቸው ታጥቋል፡፡
3) ከወታደራዊ ዝግጅት በተጨማሪ በዓለም አቀፍ ደረጃ ዲፕሊማሲያዊ ዘመቻ ከፍተዋል፤
4) ከጅቡቲ እስከ አዲስ አበባ ያለውን የባቡር ሐዲድ ግንባታ ሥራ ፈረንሣዮች እንዲሠሩት ስምምነት
ፈጽመዋል፡፡
5) ወደ ፒተርስበርግ አንድ ልዩ መልዕክተኛ ልከዋል፡፡
ይህ የምኒልክ ዝግጅት ግን በባራቲየሪ በኩል ከቁምነገር የተቆጠረ አልነበረም፡፡ በመሆኑም ባራቲየሪ እ.ኤ.አ በሰኔ ወር 1894
ሮም ላይ ከፓርላማው ፊት ቀርቦ ያሰማው ንግግር ምኒልክን ለማሸነፍ ብዙ እርዳታ እንደማያስፈልገው ነበር፡፡

7.4.5 የጦርነቱ መጀመር፡-
እ.ኤ.አ በጥር ወር 1895 የራስ መንገሻን ጦር ድል ካደረገ በኋላ የጣልያን ወታደሮች ወደ ትግሬ ግዛት ጠልቀው መግባት
ጀመሩ፡፡ መቀሌንም ያዙ፡፡ የደቡብ ግንባር አዛዥ ሆኖ የተመደበው ሻለቃ ቶሴሊ አምባላጌን ያዘ፡፡
እ.ኤ.አ መስከረም ወር 1895 ዐፄ ምኒልክ የክተት አዋጅ አወጁ፡፡ በአዋጁም ወንድ የሆነ ሁሉ ወደ ኋላ ሳይል ከእኔ ጋር
ይዝመት ብለው አዘዙ፡፡
የዐፄ ምኒልክ የዐድዋ ጦርነት የክትት አዋጅ፡-
“ሀገርና ሃይማኖት የሚያጠፋ፣ጠላት ባሕር ተሻግሮ መጥቷል፡፡ እኔም ያገሬ ሰው መድከሙን አይቼ እስካሁን
ብታገስም፣እያለፈ እንደ ፍልፈል መሬት ይቆፍር ጀመር፤አሁን ግን በእግዚአብሔር እርዳታ አገሬን አሳልፌ
አልሰጠውም፡፡ ያገሬ ሰው ጉልበት ያለህ ተከተለኝ፡፡ ጉልበት የሌለህ በጸሎትህ እርዳኝ፡፡” የሚል ነው፡፡
ከዚህ አዋጅ በኋላ ንጉሠ ነገሥቱ እ.ኤ.አ ጥቅምት 2 ቀን 1895 25 000 እግረኛ፣3 000 ፈረሰኛ ጦር አስከትለው ከአዲስ
አበባ ወደ ትግራይ ጉዞ ጀመሩ፡፡ 30 8221 Georgia Avenue, Silver Spring, MD. 20910 www.moreshwegenie.org

ራስ ዳርጌን( አጎታቸውን) በእንደራሴነት ሸዋ እንዲቆዩ ተደረገ፡፡
ከክተት አዋጁ ቀደም ሲል፣የደንከል (አፋር) ነገዶች በምኒልክ ላይ ያመጹ መሆኑ ተሰማ፡፡ በጣሊያኖች የተገዙ ሰዎች
ምኒልክን በመንገድ ለመውጋት መዘጋጀታቸው ተነገረ፡፡
ወሬው እንደተሰማም የጠቅላይ ግዛቱ ገዥ ራስ መኮንን የአድማውን መሪዎች ተከታትሎ በመያዝ ያለምሕረት እንዲቀጣ
ታዘዙ፡፡ ራስ መኮንንም በክህደት የተነሱትን የጎሣ መሪዎች በዘመቻው ላይ ለመምከር በሚል ስበብ እንዲሰበሰቡ ጥሪ
አደረጉ፡፡ የጎሣው መሪዎችም በተደረገላቸው ጥሪ መሠረት ሳይጠራጠሩ ከተው መጡ፡፡ እንደገቡም በራስ መኮንን
ወታደሮች ተከበው በጥይት ተደብድበው አለቁ፡፡ ድርጊቱ የደንከልን ቀበሌ ቢያስቆጣም ፣በምኒልክ ላይ የተጠነሰሰውን ሤራ
አክሽፏል፡፡
እ.ኤ.አ ጥቅምት 27 ቀን 1895 ምኒልክ ደሴ ገቡ፡፡ ለወሳኙ ጦርነትም የመጨረሻ ዝግጅት ማድረግ ጀመሩ፡፡
ንጉሠ ነገሥቱን ተከትለው የዘመቱ የጦር መሪዎች፡-
o ራስ መኮንን ከሐረር፣
o ራስ ሚካኤል ከወሎ፣
o ራስ ወሌ ከየጁ፣
o መንገሻ አቲከም ከጎንደር፣
o ንጉሥ ተክለሃይማኖት ከጎጃም፣
o ራስ መንገሻ እና ራስ አሉላ ከትግሬ ናቸው፡፡

7.4.6 የአምባላጌ (ውጊያ)ጦርነት፡-
በጥቅምት መጀመሪያ 1895 ክረመረቱ እንደወጣ ጄኔራል ባራቲየሪ ሠራዊቱ ወደ መሀል ትግራይ እንዲንቀሳቀስ ትዕዛዝ
ሰጠ፡፡
 ሻለቃ ቶሴሊ የጄኔራል ኦሪሞንዲ ጦር እስኪደርስ ቀደም ሲል የተያዙትን ቦታዎች አጠናከረ፡፡
 ዐፄ ምኒልክ ጦርነቱ ከመጀመሩ በፊት እንደገና ለመደራደር ሙከራ አደረጉ፡፡ ጄኔራል ባራቲየሪ የኢትዮጵያን ግዛት
ለቆ እንዲወጣ ጠየቁት፡፡ ካልሆነ ጦርነት አይቀሬ እንደሚሆን አስጠነቀቁት፡፡ በዚህ ጊዜ ግን ከሞላ ጎደል ትግራይ
በጣሊያን ተይዟል፡፡
 ጣሊያን የምኒልክን ሀሳብ አልተቀበለም፡፡ በመሆኑም ባራቲየሪ ከምኒልክ ለቀረበለት የድንበር ለቀህ ውጣና
የድርድር ጥያቄ የሚከተለውን መልስ ሰጠ፡፡
“የኢትዮጵያ ሠራዊት ትጥቁን እንዲፈታ፣ራስ መንገሻ እንዲታሰር፣መላውን ትግራይና አጋመን
እንዲያስረክብ፣ጣሊያን በኢትዮጵያ ላይ ያለውን የበላይነት እንዲቀበል፡፡” የሚል፤
 ምኒልክ ይህ መልዕክት ሲደርሳቸው ጦርነቱ አይቀሬ መሆኑን በማመን፣ ሠራዊቱ ወደ ሰሜን እንዲንቀሳቀስ ትዕዛዝ
ሰጡ፡፡ በዚህም መሠረት፡-
 በታህሳስ መጀመሪያ 1895 ላይ የራስ መኮንን ሠራዊት በሻለቃ ቶሴሊ በሚመራው ሠራዊት ከተያዘው ቦታ
ተጠጋ፡፡ በአምባላጌ ጦርነት 15 ሺህ ከሚሆነው ከራስ መኮንን ጦር በተጨማሪ 11ሺህ የራስ ሚካኤል፣ 10 ሺህ
የራስ ወሌ 6 ሺህ የመንገሻ አቲከም እና 5 ሺህ የራስ አሉላና ሌሎች አነስተኛ ኃይሎች የሚንቀሳቀሱ የጦር
አበጋዞች በግንባሩ ተሰልፈዋል፡፡
 በአጠቃላይ በራስ መኮንን የሚመራው ጦር 50 ሺህ ያህል ነበር፡፡ 31 8221 Georgia Avenue, Silver Spring, MD. 20910 www.moreshwegenie.org

 በግንባሩ በሻለቃ ቶሴሊ የሚመራው የጣሊያን ጦር ብዛት 2450 ያህል ነበር፡፡ የአምባላጌው ጦርነት ሁለት
ሰዓት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ በኢትዮጵያ አሸናፊነት ተጠናቀቀ፡፡
 በአምባላጌ ከተሰለፉት 34 የጣሊያን መኮንኖች 31 ተገድለዋል፡፡ ከተራው ተዋጊ ውስጥ የተረፉት 200 ብቻ
ናቸው፡፡ መሪው ቶሴሊ በዚሁ ጦርነት ተገድሏል፡፡
 የአምባላጌ ድል ኢትዮጵያ በጣሊያን ላይ የተቀዳጀችው የመጀመሪያው ታላቅ ድል ነው፡፡ ድሉን ታላቅና
ወሣኝ የሚያሰኘው በወታደራዊ መልኩ ሳይሆን፣ በኢትዮጵያውያን ላይ ያሳደረው ጠንካራ ፖለቲካዊና ሥነ-
ልቦናዊ ትጥቅ ነው፡፡ ኢትዮጵያውያን አውሮፓን ቅኝ ገዥ ኃይል ማሸነፍ እንደሚቻል ተመክሮ ሰጣቸው፡፡
ድሉ የምኒልክንና የሠራዊቱን ሞራል ገነባ፡፡ ዜናው በዓለም ናኜ፡፡
 በሀገር ውስጥ በምኒልክ ላይ ይቃጣ የነበረውን ተቃውሞ ሁሉ አረገበ፡፡
 የራስ መኮንን ጦር ወደ አምባላጌ በተንቀሳቀሰበት ወቅት ከሌላው የጣሊያን ጦር ተነጥሎ ወደ ደቡብ ትግራይ
ጠልቆ ገብቶ የነበረው በጄኔራል ኦሪሞንዲ የሚመራው ሠራዊት፣የጠላት ኃይል እየተቃረበ መሆኑን ለዋናው
አዛዥ ባራቲየሪ መረጃ ሰጥቶ ነበር፡፡ ነገር ግን ባራቲየሪ የምኒልክ ጦር በአጭር ጊዜ ውስጥ ይደርሳል ብሎ
ባለመገመቱ ለመረጃው ዋጋ አልሰጠውም ነበር፡፡ ሆኖም፣የምኒልክ ጦር በደቡብ በኩል መትመሙን ባራቲየሪ
ሲያረጋግጥ ታህሳስ 2 ቀን 1895 መላ ሠራዊቱን አዲግራት እንዲከት አዘዘ፡፡ ትዕዛዙ ለጄኔራል ኦሪሞንዲ
ሲደርሰው የሻለቃ ቶሴሊ ምሽግ መደምሰሱን ባንድነት ሰማ፡፡

7.4.7. የመቀሌ (ውጊያ) ጦርነት፡-
 በተሰጠው ትዕዛዝ መሠረት ኦሪሞንዲ ጦሩን ወደ አዲግራት ሲመልስ ፣መቀሌ ላይ የተወሰነ ኃይል ትቶ ነበር፡፡
መቀሌ እንዳኢየሱስ ላይ የተጠናከረ ምሽግ ተሠርቷል፡፡ የምግብ ክምችት አለ፡፡ ሆኖም ብዙ ቀን ለመቆየት
የሚያስችል አልነበረም፡፡ በቂ ውኃ አልነበረም፡፡ ለ10 ቀኖች ብቻ የሚበቃ 200 000 ሊትር ያህል ውኃ ነበር
የነበረው፡፡
 መቀሌ ላይ የተመደቡት ወታደሮች ቁጥር 1500 ሲሆኑ፣አዛዣቸው ሻለቃ ጋሊያኖ ነበር፡፡ የጣሊያኑ ጦር አዛዥ ይህ
ምሽግ እንደማይሰበር እምነት ነበረው፡፡
 እ.ኤ.አ ታህሳስ 8 ቀን 1895 የራስ መኮንን ቃፊር ጦር መቀሌን ከበበ፡፡ የውኃ ኩሬዎችን ቀድመው በመያዝ
የጋሊያኖን ምሽግ ተቆጣጠሩ፡፡
 እ.ኤ.አ ጥር 7 ቀን 1896 ምኒልክ መቀሌ ገቡ፡፡ በዚሁ ዕለት ምሽጉን ማጥቃት ተጀመረ፡፡ ምሽጉ የተጠናከረ
በመሆኑ ጣሊያኖቹ ጉዳት ሳይደርስባቸው በራስ መኮንን ሠራዊት ላይ ጉዳቱ እየበረከተ ሄደ፡፡ ይኸም ሆኖ
የጋሊያኖ ሠራዊት ውኃ አልነበረውም፡፡ ይህም ለጋሊያኖ ሠራዊት ከፍተኛ ችግር በመፍጠሩ ባራቲየሪ የጋሊያኖ
ወታደሮች ምሽጉን ለቀው እንዲወጡ ምኒልክን ጠየቀ፡፡ በለውጡም መቀሌን ሊለቅና ገንዘብ ለመክፈል ተስማማ፡፡
መቀሌ የተሰለፈው ወታደርም በሌላ ጦርነት እንደማይሳተፍ ባራቲየሪ ቃል ገባ፡፡
 ዳግማዊ ዐፄ ምኒልክም የባራቲየሪን ሀሳብ ተቀበሉ፡፡ በመሆኑም እ.ኤ.አ ጥር 24 ቀን 1896 የጋሊያኖ ክፍለ ጦር
ከነሙሉ ትጥቁ ከመቀሌ ተነስቶ ወደ አዲግራት ተጓዘ፡፡
 ዐፄ ምኒልክ መቀሌን ከተቆጣጠሩ በኋላ ለጄኔራል ባራቲየሪ የሚከተለውን መልዕክት ላኩ፡፡
1) የኢትዮጵያና የኤርትራ ወሰን ለዘለቄታው መረብና በለስ እንዲሆን፣
2) እርቅ እንዲፈጠር፣
3) የውጫሌ ውል አንቀጽ 17 የተሰረዘ መሆኑን እንዲቀበል የሚሉ ነበሩ፡፡
ይሁን እንጂ ባራቲየሪ የምኒልክን ሀሳብ አልተቀበለም፡፡ በሌላ በኩል የመቀሌ መለቀቅ ምኒልክን ከድተው ለጣሊያን ያደሩት
የትግራይ ባላባቶች ራስ ሥብሃትና ራስ ሐጎስ ጣሊያንን እንዲከዱ ምክንያት ሆነ፡፡
32 8221 Georgia Avenue, Silver Spring, MD. 20910 www.moreshwegenie.org

7.4.8 ዋናው ውጊያ በዐድዋ ፡-
የካቲት አጋማሽ 1896(እ.ኤ.አ) የምኒልክ ጦር በዐድዋ ከተማ አካባቢ የመጨረሻ ጦርነት የሚፋለምበትን ቦታ ያዘ፡፡ የጄኔራል
ባራቲየሪ ጦርም ከአዲግራት የመጣው የምኒልክ ሠራዊት በያዘው አካባቢ ነበር፡፡
የካቲት 23 ቀን 1888 ሁለቱ ተፋላሚዎች ዐድዋ ላይ ተፋጠጡ፡፡ የጣሊያን ተዋጊ ሠራዊት ቁጥር 17 700 ያህል
ሲሆን፣ከዚህ ውስጥ 10596ቱ ጣሊያኖች ሲሆኑ፣የቀረው 7104 ቱ ኤርትራውያን ነበሩ፡፡
የጄኔራል ባራቲየሪ ጦር አሰላለፍ፡-
ባራቲየሪ ጦሩን በአራት መደበ፡፡
1) ምድብ 1 በጄኔራል አልበርቶኔ የሚመራ ሆኖ፣4076 የሰው ኃልና 14 መድፎች፣
2) ምድብ 2 በጄኔራል ኦሪሞንዲ የሚመራ ሆኖ፣2493 የሰው ኃይልና 12 መድፎች፣
3) ምድብ 3 በጄኔራል ዳቦርሚዳ የሚመራ ሆኖ፣3800 የሰው ኃይልና 16 መድፎች፣
4) ምድብ 4 4150 የሰው ኃይልና 14 መድፎች ያሉት፣ በተጠባባቂነት ተዘጋጀ፡፡ የጦሩ ጠቅላይ አዛዥም
ጄኔራል ኤሌና ሆኖ ተመደበ፡፡
የዐፄ ምኒልክ የጦር አሰላለፍ፡-
i. ዐፄ ምኒልክ 30 000፣
ii. እቴጌ ጣይቱ 3 000፣
iii. ፊታውራሪ ገበየሁ 6 000፣
iv. ንጉሥ ተክለሃይማኖት 3 000፣
v. ራስ ወሌ 3 000፣
vi. ራስ ሚካኤል 8 000፣
vii. ራስ መኮንን 8 000፣
viii. ራስ መንገሻ፣ራስ አሉላ እና ራስ ሐጎስ 3000፣
ix. ዋግሹም ጎበዜ(ጓንጉል ብሩ) 6000፣
x. ራስ መንገሻ አቲከም 3000፣
በጠቅላላው የዐፄ ምኒልክ ጦር 73 000 በላይ ነበር፡፡ አውሮፓውያኑ የምኒልክ ጦር 100000 እንደሆነ ይናገራሉ፡፡(
በዓለማየሁ አበበ ከተተረጎመውና በነአንድርዜይ በተጻፈው መጽሐፍ የተገኘው መረጃ ነው)
ጰውሎስ ኞኞ አጤ ምኒልክ በሚለው መጽሐፉ የምኒልክ የኃይል አሰላለፍ እንደሚከተለው ያቀርበዋል፡፡
1) ዐፄ ምኒልክ 30 ሺ እግረኛ 12 ሽ ፈረሰኛ፣
2) ዕቴጌ ጣይቱ 3 ሺ እግረኛ 6 ሺ ፈረሸኛ፣
3) ራስ መኮንን 15 ሺ እግረኛ፣
4) ራስ መንገሻ ዮሐንስ 12 ሺ እግረኛ፣
5) ራስ አሉላ 3 ሺ እግረኛ፣
6) ራስ ሚካኤል 6 ሺ እግረኛ 10 ሺ ፈረሸኛ፣
7) ራስ መንገሻ አቲከም 6 ሺ እግረኛ፣
8) ራስ ወሌ ብጡል 10 ሺ እግረኛ፣
9) ራስ ወልደጊዮርጊስ 8 ሺ እግረኛ፣
10) አዛዝ ወልደ ጻድቅ 3 ሺ እግረኛ፣ 33 8221 Georgia Avenue, Silver Spring, MD. 20910 www.moreshwegenie.org

11) ደጃዝማች ተሰማ ናደው 4 ሺ እግረኛ ፣
12) ራስ ዳርጌ፣ቀኛዝማች መኮንንና ግራዝማች በንቲ 20 ሺ እግረኛ ጦር በድምሩ 120 ሺ እግረኛና 28
ሺ ፈረሰኛ እንዳሰለፉ ጳውሎስ ኞኞ ጽፏል፡፡ ይህም በርካታ ታሪክ ተመራማሪዎች የተስማሙበት
እንደሆነ ጨምሮ ገልጧል፡፡
በኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን፣በዓለም ዝነኛና እጅግ ታዋቂ የሆነው የአድዋ ጦርነት እኤአ መጋቢት 1 ቀን 1896 ማለዳ ከጥዋቱ
11፡32 ሰዓት ( እንደ ኢትዮጵያ አቆጣጠር የካቲት 23 ቀን 1888 5፡32 ሰዓት) የጄኔራል አልቤርቶኔ ክፍለ ጦር በፊታውራሪ
ገበየሁ፣በዋግሹም ጓንጉል፣በራስ ሚካኤልና በራስ መንገሻ ጦር ላይ በከፈተው የማጥቃት እርምጃ ጦርነቱ ተጀመረ፡፡
የምኒልክ የመሀል ጦር አዛዥ ፊታውራሪ ገበየሁ ተክሌ በጦርነቱ ተሰው፡፡ ወታደሮቹ የመሪያቸውን ሬሣ ይዘው ወደ ኋላ
አፈገፈጉ፡፡ በዚህ ግንባር አልቤርቶኔ ድል የቀናው መስሎ ነበር፡፡ ያቀረበው የተጨማሪ ኃይል በወቅቱ ቢደርስለት ኖሮ
ምናልባትም ድሉ የጣሊያን ይሆን ነበር፡፡
የአልቤርቶኔና ዳቦርሚዳ ጦሮች የተራራቁ ስለነበሩ ለመተጋጋዝ አልቻሉም፡፡የመሬቱ አቀማመጥም ለፈጣን እንቅስቃሴ
አመች አልሆነም፡፡ የጦሩ በአራት መከፈልና ተራርቆ መመደብ የሥልት ችግር ነበር፡፡
በገበየሁ ሞት ተደናግጦ የነበረው የምኒልክ ጦር በፍጥነት ተረጋግቶ ወደ ውጊያው ገባ፡፡ በአራት ሰዓት አካባቢ የአልቤርቶኔ
መኮንኖች አብዛኛዎቹ ተሰው፡፡ አልቤርቶኔ የጋለበው በቁሎ በጥይት ሲመታ አብሮ ወደቀ፡፡ የጄኔራሉን መውደቅ ያዩ
ኢትዮጵያውያን ፈጥነው በመክበብ ማረኩታል፡፡ የዋናው ጦር አዛዥ መማረክም ጦርነቱን ወደ ፍጻሜ መራው፡፡
አቡነ ማቲዎስ መስቀላቸውን ይዘው ወታደሮቹን ያደፋፍሩ ነበር፡፡ ምኒልክም እንደተራ ተዋጊ ጦር ግንባር ገብተው ያዋጉ
ነበር፡፡
ኦርሞንዲ ተመትቶ ወደቀ፡፡ ይመራው የነበረው ወታደር ጥሎት ሸሸ፡፡ ከጄኔራል ኤሌና ጦር ጋር ተቀላቅሎ ፈረጠጠ፡፡
ቁስለኛው ጄኔራል ኤሌና እና ጄኔራል ባራቲየሪ ሸሹ፡፡
የኢትዮጵያን ጦር መክቶ የያዘው በጄኔራል ዳቦርሚዳ የሚመራው ጦር ብቻ ሆነ፡፡ የተጋጠመውም 30 ሺ ያህል ኃይል
ከያዘው ከራስ መኮንን ጦር ጋር ነበር፡፡ በዚህ ግንባር ጦርነቱ ከአንድ ሰዓት እስከ አስራ ሁለት ሰዓት ቆየ፡፡ የጣሊያን ወታደር
ጥይት ሲያልቅበት ጄኔራል ዳቦርሚዳ የማፈግፈግ ትዕዛዝ ሰጠ፡፡ ሆኖም ጄኔራል ዳቦርሚዳ በሽሽት ላይ እንዳለ ተመትቶ
ሞተ፡፡
መጋቢት 1 ቀን 1896 ( ካቲት 23 ቀን 1888) ምሽት ላይ የጄኔራል ባራቲየሪ ወራሪ ጦር ድርሻው ጠፋ፡፡ ድሉም
የኢትዮጵያውያን ሆነ፡፡
በጦርነቱ የደረሰ ጉዳት፡-
በጣሊያን በኩል፣
 11000 የሰው ኃይል የሞተና የቆሰለ፣
 4000 የተማረከ፣
 2 ጄኔራል የተገደሉ፣
 1 ጄኔራል ተማረከ፣
 ያሰለፉት 56 መድፎች ተማረከ፣
 11000 ጠብመንጃ ፣መጠኑ የበዛ ጥይት ተማርኳል፣

34 8221 Georgia Avenue, Silver Spring, MD. 20910 www.moreshwegenie.org

በኢትዮጵያ በኩል፣
 4000 የሞት፣
 6000 የቆሰለ፣
 ፊታውራሪ ገበየሁ፣ ልዑል ዳምጠው(የሩሲያ አምባሳደር የነበረ)፣ ደጃዝማች መሸሻ፣ ደጀዝማች ጫጫ፣
ቀኛዝማች ታፈሰ፣ ቀኛዝማች ገለሜ፣ ስም ካላቸውና ከታዋቂዎቹ መካከል በጦርነቱ የተሰው ናቸው፡፡

7.4.9 የዐድዋ ጦርነት ያስከተለው ለውጥ፡-
7.4.9.1 በጣሊያን በኩል፣
 በጣሊያን ሕዝብ ላይ ከፍተኛ የሆነ የኅሊና ስብራት ፈጠረ፣
 የጣሊያን ሕዝብ በመንግሥቱ የአፍሪካ ፖሊሲ ላይ በየከተሞቹ የተቃውሞ ሰልፍ አደረገ፣
 ጠቅላይ ሚኒስቴር ክሪስፒ ከሥልጣኑ ተነሳ፣
 የኤርትራው አገረገዥ ጄኔራል ባራቲየሪ ተነስቶ በጄኔራል አንቶንዮ ባልዲሴራ ተተካ፤

7.4.9.2 በኢትዮጵያ በኩል፣
 ኢትዮጵያውያን ታሪካዊ አይበገሬነታቸውንና ነፃ ነታቸውን በዘመነ ቅኝ አገዛዝ ዳግም አረጋገጡ፣
 ኢትዮጵያ የበለጠ በዓለም ላይ እንድትታወቅ ሠፊ አጋጣሚ ፈጠረ፣
 የኢትዮጵያ ፖለቲካዊ ካርታ በቅጡ ተለይቶ እንዲታወቅ አደረገ፣
 ከበዋት የነበሩት የአውሮፓ ቅኝ ገዥዎች ማለትም እንግሊዝ፣ፈረንሣይና ጣሊያን ጋር ወሰኗን
እንድትካለል አስገደደ፣
 በሱዳንና በኬንያ በኩል ከእንግሊዝ ጋር፣
 በእንግሊዝ ሶማሊያ ላንድ በኩል ከእንግሊዝ ጋር፣
 በጅቡቲ ከፈረንሣይ ጋር፣
 በኤርትራና በጣሊያን ሶማሊያላንድ በኩል ከጣሊያን ጋር፣ ድንበሯን ተካለለች፣
 ኢትዮጵያ ነፃና የተከበረች አገር መሆኗን ዓለም እንዲያውቅ ሆነ፣
 ከዘመኑ የአውሮፓ ኃያላን መንግሥታት ጋር ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት እንዲመሠረት አስገደደ፡፡
በዚህም መሠረት፣ጣሊያን፣ፈረንሣይ፣ እንግሊዝ፣አሜሪካና ቤልጄየም የመጀመሪያዎቹ አገሮች
በመሆን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት በመመሥረት ኢምባሲዎቻቸውን በአዲስ አበባ ከፈቱ፡፡
 የዐፄ ምኒልክ ዝናና ስም በዓለም ላይ ናኘ፣
 የውጫሌ ውል ተሻረ፣
 የኢትዮጵያ ነፃ አገርነት በውል ተረጋገጠ፣
 የኤርትራና የኢትዮጵያ ደንበር መረብና በለሳስ እንዲሆን በውል እንዲጠና አደረገ፣
 ጣሊያን በሚቆጣጠረው የኤርትራን መሬት ለሌላ ወገን አሳልፎ እንዳይሰጥና ጣሊያንም ከለቀቀ
ለኢትዮጵያ ማስረከብ እንዳለበት ውል ገባ፣

35 8221 Georgia Avenue, Silver Spring, MD. 20910 www.moreshwegenie.org

7.4.9.3 በዓለም ዙሪያ፣
 ኢትዮጵያ በጥቁር አፍሪካ የነፃነት ቀንዲልና ምሳሌ ሆና እንድትታይ አደረገ፣
 የነጮችን አንገት አስደፋ፣ነጮች በጥቁሮች ሊሸነፉ የሚችሉ መሆኑን አሳዬ፣
 የአውሮፓ ቅኝ ገዥዎች አፍሪካን በተመለከት ይከተሉት የነበረውን ፖሊሲ ቆም ብለው
እንዲመረምሩ አስገደደ፣
 ምኒልክ ፣ዐድዋና ኢትዮጵያ የሚባሉ ስሞች በዓለም ላይ በተደጋጋሚ መሰማት ያዙ፣
 የዐድዋ ድል ኢትዮጵያ በዓለም አቀፋዊ መድረክ ከፍ ብላ እንድትታይ አደረገ፤

7.4.9 ከዐድዋ ድል ኢትዮጵያዊው ትውልድ ያተረፈው መልካም ነገር፡-
 ነፃነትና ድል አድራጊነትን፣
 የኢትዮጵያ ታሪክ፣ባህልና ሃይማኖት ተከታታይነቱን ጠብቆ እንዲዘልቅ ያደረገ መሆኑን፣
 ለዘመናዊ የተማከለ አስተዳደር በር የከፈተ መሆኑን፣
 ኢትዮጵያ በዓለም ላይ ሁለንተናዊ ዕውቅና እንድታገኝ ማድረጉን፤
 ኢትጵዮጵያ ለጥቁር አፍሪካ ሕዝቦች የነፃነት ምሳሌ ሆና እንድትታይ ማድረጉን፤

7.4.10 በዐድዋ ጦርነት ከፍተኛ የሆነ ተዋጊ ኃይል የተገኘው ከየትኛው ነገድ ነው;
የመሪዎቹን ማንነት በመመልከት ብቻ ከአምባላጌ እስከ ዐድዋ ድረስ ከሦስት ወር በላይ በቆየው ጦርነት ከየትኛው ነገድ
ከፍተኛው ተዋጊ የሰው ኃይል እንደተገኘ መገንዘብ ይቻላላ፡፡
አለቃ ገብረሥላሴ የተባሉ ባልታተመ መጽሐፋቸው በዐድዋ ጦርነት ጣሊያን እንዴት እንደሸሸ እንዲህ ሲሉ የገለጹት
አገላለጽ በጦርነቱ ወሳኙን ሚና የተጫወተው የዐማራው ነገድ እንደሆነ ያስረዳል፡፡
“እግረኛው እሮጣለሁ ሲል፣ ጫማው እየከበደው፣ አውልቆ እንዳይሮጥ አቀበትና ቁልቁለቱ፣ ጠጠር
እየወጋው፣የኋሊት እየተኮሰ እሮጣለሁ ሲል፣ከእንዝርት የቀለለ የጁዬ፣ከነብር የፈጠነ ቤጌምድሬ፣ከቋንጣ የደረቀ
ትግሬ፣ከአሞራ የረበበ ሸዌ፣ ከንብ የባሰ ጎጃሜ እየበረረ በየጎዳናው ዘለሰው፡፡….ያን ቀን ከዐማራውም
ከኢጣሊያውም እየቆሰለ እሚያነሳው እየታጣ ሐሩር እየያዘው በውሃ ጥም ሲጨነቅ ከየደገላው እሳት እየተነሳ
አቃጥሎ ፈጀው፡፡ያን ጊዜ መንገዱ ባይከፋ ፣ሠራዊቱ በርሃብ ባይጎዳ፣ዐማራ ጨክኖ ቢከተል ኖሮ ጣሊያን አንድ
ለዘር አይተርፍም ነበር አስመራን አስለቅቆ ከጥንት ሀገሩ ይሰደው ነበር፡፡”(ጳውሎስ ኞኞ 1984፣209)
በሌላ በኩል ይኸኑ ጦርነት ፕሮፌሰር አፈወርቅ ገብረየሱስ እንዲህ ሲሉ ገልጸውታል፡፡ “….የሸዋ ፈረሰኛ፣ የጎጃም እግረኛ፣
የትግሬ ነፍጠኛ፣ ያማራ ስልተኛ ከቦ ያናፋው፣ ይቀላው፣ ያንደገድገው ጀመር፡፡ …ከእንዝርት የቀለለ የጁዬ፣ ተነብር የፈጠነ
ቤጌምድሬ፣ ተቋንጣ የደረቀ ትግሬ …ፈጀው፣ አሰጣው፣ ዘለሰው፡፡” (ጳውሎስ ኞኞ 1984፣210)
“ለብልህ አይመክሩም፣ ለአንበሣ አይመትሩም” ነውና የነዚህን የዐይን ምስክሮች አገላለጽ ከመሪዎቹ ማንነት ጋር ማገናዘብ
የቻለ ሰው፣ ማን በዐድዋ ጦርነት ወሳኙን ሚና እንደተጫወተ መገንዘብ ይገደዋል አይባልም፡፡

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 10 years ago on February 14, 2014
  • By:
  • Last Modified: February 14, 2014 @ 1:08 pm
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar