www.maledatimes.com የቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትር መለስ የአገዛዝ ዘመን እና የኢትዮጵያ የሰባዊ መብቶች ሁኔታ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

የቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትር መለስ የአገዛዝ ዘመን እና የኢትዮጵያ የሰባዊ መብቶች ሁኔታ

By   /   September 3, 2012  /   Comments Off on የቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትር መለስ የአገዛዝ ዘመን እና የኢትዮጵያ የሰባዊ መብቶች ሁኔታ

    Print       Email
0 0
Read Time:66 Minute, 35 Second

1
የኢትዮጵያ ሕዝብ እያለቀሰ ያለው ለጠ/ሚ መለስ ዜናዊ “ብቻ” ወይስ
ላለፉት ሃያ አንድ አመታት እርሳቸው በሚመሩት መንግስት በግፍ ለተገደሉት ከ3 ሺ በላይ
የሚሆኑ ንጹሃን ዜጎች እና አመራራቸው ባስከተለው የኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ሳቢያ ላለቀው
ከ70 ሺ በላይ ሕዝብ?

the former pm meles zenawi watching tv

ከያሬድ ኃይለማሪያም
የቀድሞ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ጉባኄ (ኢሰመጉ) የምርመራ ሠራተኛ
ነሐሴ 2004 ዓ.ም.
yhailema@gmail.com

መግቢያ
በመጀመሪያ አገራችን ኢትዮጵያን ፈቅደንም ይሁን በአፈሙዝ ተገደን ለ21 አመታት ኢትዮጵያን በመጀመሪያ በፕሬዚደንትነት፤
ከዚያም ረዘም ላለ ጊዜ በጠቅላይ ሚኒስትርነት ሲያስተዳድሯት ቆይተው ባደረባቸው ሕመም ከዚህ አለም በሞት ለተለዩት ጠ/ሚ
መለስ ዜናዊ ቤተሰቦች፣ ዘመድ አዝማድና ወዳጆች ሁሉ እግዚያብሄር መጽናናቱን እንዲሰጣቸው ከልብ እመኛለሁ። ለሰው ልጆች
ሁሉ የማይቀረው ሞት ትቢያ ለብሶ፣ ከስቶና ገርጥቶ፣ የረሃብ አለንጋ እየሸነቆጠው በጠኔ ከሚያልቀው እና በየሜዳውና በየአውራ
ጎዳናው የሰውነት ክብሩ ተገፎ፣ ተዋርዶና ተንቆ፣ ሰው መሆኑ ምር ተረስቶ ከእንስሳ ያነሰ ህይወት ከሚኖረው የአገሬ ድሃ የኔ-ቢጤ
አንስቶ በተመቻቸ እና ለመግለጽ በሚያስቸግር የድሎት ሕይወት ውስጥ ቆይቶ ወይም እንደ ጠ/ሚ መለስ በታንኮች፣ በብዙ ሺህ
ወታደሮች፣ በታጠቁ የደህንነት ኃይሎች ዙሪያውን ታጥሮ የሚኖር ሰውን፤ ሞት የሚባል ጠላት ከመካከላችን መን ቆ ሲወስድ ማየት2
እንደ አንድ የሰብአዊ ፍጡራን ሕይወት የሚያሳስበውና የሚያስጨንቀው ግለሰብ እኔም ሃዘኔ ብርቱ ነው። ካደኩበት ባህልና
ማኅበረሰብም የተማርኩት ይህንኑ ወግና ሥርዓት ነውና እግዚያብሔር የጠ/ሚ መለስን ነፍስ ይማር እላለሁ።
ይሁንና ጠ/ሚ መለስ ዜናዊም ሆኑ ልክ እንደ እሳቸው በየታሪክ አጋጣሚው ከራሳቸው ሕይወት አልፈው ሕዝባዊና አገራዊ በሆኑ
ጉዳዮች ላይ በአንድ ወይም በሌላ መንገድ፤ ላ ር ጊዜም ይሁን ለረዥም፣ አወንታዊም ይሁን አሉታዊ አስተዋጽኦ የነበራቸው ሰዎች
ሕልፈተ ህይወት “በነፍስ ይማር” ጽሎት፣ በደመቀ የለቅሶና ሃዘን ሥርዓት ብቻ የሚደመደም አይደለም። በተለይም እጅግ የከፋ ደረጃ
ላይ የደረሰና ስር የሰደደ ድህነት በተንሰራፋበት አገር፣ በኑሮ ዋስትና ማጣት የተነሳ ሰብአዊ ክብሩ ተዋርዶ፣ መንፈሳዊምና አካላዊ
ቅስሙ እጅግ ተንኮታኩቶ በደቀቀ ሕዝብ፣ ሰብአዊ መብቶች በገፍ በሚጣሱበት፣ ፍትህ እና ዴሞክራሲ በብዙ ሺህ ማይልስ በራቁት፣
እርሃብ እና ጠኔ በሚፈራረቁበት፣ በሽታና ድህነት በነገሱበት ማኅበረስብ ውስጥ፤ እንኳን የጠ/ሚ መለስ ይቅርና በቀበሌና በወረዳ
ደረጃ በኃላፊነት ላይ የቆየና በሕዝብና አገራዊ ጉዳዮች ላይ በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ እጁን ሲያስገባ የቆየ ሰው ህልፈተ ሕይወት
ዜና ሲሰማ ሁለት ገጽታዎች ይኖሩታል።
የመጀመሪያው ከላይ እንደገለጽኩት በሰብአዊ ፍጡርነታችን ሁላችንም የምንጋራውና በልባችን ውስጥ የሚሰነቀረው የሃዘን ስሜት
ነው። ሁለተኛው ደግሞ ግለሰቡ በሕዝባዊ እና አገራዊ ጉዳዮች ላይ በነበረው ድርሻ ትቷቸው ያለፋቸውን በጎና መጥፎ ነገሮች
የሚፈትሸው አዕምሯችን የሚያነሳው ጥያቄ ነው። እነኚህ ግለሰቦች እንደ ሰው ቢሞቱም በሕዝብ ህይወት ውስት በነበራቸው ሚና
የተነሳ ትተዋቸ የሚያልፉት ነገሮች ከህልፈታቸውም በኋላ የሕዝብ ሆኖ ይቀራል። የክፋታቸውም ሆን የበጎነታቸው ቀጥተኛ ወራሽ
ሕዝቡ ነው። ስለዚህም አዕምሮዋችን እነዚህ ግለሰቦች ብቻቸውን ነው የሞቱት ወይስ ይዘውን ሞተዋል? ወይስ ከትውልድ ትውልድ
የሚተላለፍ እና በእያንዳንዱ ሰው ልብ ውስጥ ታትሞ የሚቀር መልካም ውርስ ትተውልናል? የሚሉ ጥያቄዎችን ያነሳል። በዚህም
የተነሳ እንዲህ ያሉት ግለሰቦች በሚሞቱ ጊዜ በሕዝብ ከመወቀስ፣ ከመታማት፣ ከመወንጀል እና ለሠሯቸው ተግባራት በጥሩም ይሁን
በመጥፎ ከመነሳትና ተጠያቂ ከመሆን አይድኑም። “ሟች አይወቀስም” የሚለው የቆየው የአገራችን የጨዋነት አነጋገር እንዲህ ያሉትን
ሰዎች፤ ጠ/ሚ መለስን ጨምሮ አይመለከትም፤ ከወቀሳ እንዲድኑም የመከላከያ ምብል ሊሆን አይችልም።
ይህንን መሰረታዊ አስተሳሰብ መነሻ በማድረግ የእዚህን ጽሑፍ አላማ ላስተዋውቅ። የዚህ ጽሑፍ አላማ ጠ/ሚ መለስ ዜናዊ
የሚመሩት የኢህአዴግ መንግስት አምባገነኑን የደርግ ሥርዓት ገርስሶ ስልጣን ከያዘበት ጊዜ አንስቶ በአገሪቱ ወስጥ የነበረው የሰብአዊ
መብቶች አያያዝ ምን ይመስል እንደነበር በከፊል ለማሳየት ነው። ለስምንት አመታት በአንጋፋውና በኢትዮጵያም ውስጥ ብቸኛው
የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶችን አጣሪ በሆነው የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ጉባኤ (ኢሰመጉ) ውስጥ በአቤቱታ መርማሪነትና አጣሪነት
ባገለገልኩበት ዘመን ካገኘሁት ልምድ፣ እውቀትና መረጃቾች በመነሳት እንዲሁም ከዚህ ጽሑፉ ጋር በአባሪነት የተያያዙትን የሰነድ
ማጣቀሻዎች መነሻ በማድረግ አንባቢዎች በቂ ግንዛቤ እንዲኖራቸው ለማድረግ ነው። ጽሑፉ በዋናነት የኢሰመጉን መግለጫዎች
መሰረት ያደረገ መሆኑን ለማሳሰብ እወዳለሁ።
ኢሰመጉ በነበረበት ከፍተኛ የመንግስት ጫና የተነሳ አቅሙ በብዙ መልኩ እጅግ የተወሰነ ነበር። ዛሬ ደግሞ ከዛም በከፋ ደረጃ ላይ
ይገኛል። በመሆኑም የኢሰመጉ መግለጫዎች እጅግ ሰፊ በሆነው የኢትዮጵያ ግዛት እና ሕዝብ ላይ ይደርስ ከነበረው እና እየደረሰም
ካለው የሰብአዊ መብቶች እረገጣ ውስጥ እሩቡን እንኳን ይሸፍናል የሚል እምነት የለኝም። ይህን ስል የኢሰመጉን የ20 አመት የትግል
ጉዞ እና ያደረገውን ከፍተኛ ተጋድሎ ለማንኳሰስ አይደለም። በተቃራኒው ኢሰመጉ ብቻውን የተጋፈጠውን አገራዊ ጉዳይ ለማመላከት
ነው። እንዲሁም በዚህ ጽሑፍ እንደ ማጣቀሻ የምጠቅሳቸው የኢሰመጉ መግለጫዎች በአገሪቱ ውስጥ የተፈጸፈውን የሰብአዊ
መብቶች ጥሰቶችን እና በሰው ዘር ላይ የተፈጸሙትን ወንጀሎች “crime against humanity” በከፊል ብቻ የሚያሳዩ
መሆናቸውን ለማስገንዘብ እወዳለሁ። እንደኔ እምነት በጠ/ሚ መለስ ዜናዊ የ21 አመት አመራር ዘመን ውስጥ የደረሰው ሰብአዊ፣
ቁሳዊ እና ፖለቲካዊ ጉዳት እጅግ ሰፊ እና በርካታ በመሆኑ እንደዚህ ባለ ውስን ጽሑፍ ሳይሆን ሰፊ የሆነ ጥናት እና ምርምር
ተደርጎበት በርካታ ሰነዶች ታክለውበት የሚቀርብ ነው።
በዚህ ጽሑፍ ግን የአቶ መለስ መንግሥት ከፈጸማቸው ዋና ዋና የሰብአዊ መብት ጥሰቶች ከፊሉን በሁለት ንዑስ ክፍሎች ከዚህ
እንደሚከተለው አቀርባለሁ።
ከ1983 – 2004 ዓ.ም. የተፈጸሙ ዋና ዋና የሰብአዊ መብቶች ጥሰት በአሃዝ
ከ3 ሺ በላይ ኢትዮጵያዊያን በመንግስት ታጣቂዎችና የጸጥታ ኃይሎች ተገድለዋል
በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ማሰቃየት (Torture) እና ድብደባ ተፈጽሞባቸዋል (ኢሰመጉ 997 ስዎች የማሰቃየት ተግባር የተፈጸመባቸ
መሆኑ በመግለጫዎቹ ገልጿል)፣
በአሥር ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ለሕገ ወጥ እስር እና እንግልት ተዳርገዋል (ኢሰመጉ 14፣308 ሰዎችን እስር የገለጸ ሲሆን የ
1997ቱን ምርጫ ተከትሎ የታሰሩትን ከ20 ሺ በላይ ሰዎች ቁጥር አይጨምርም)፣
ከ 300 እስከ 500 የሚጠጉ ሰዎች በመንግስት ታጣቂዎችና የደኅንነት ኃይሎች ታፍነው ተውስደው ለበርካታ አመታት የደረሱበት
ሳይታወቅ ቀርቷል (ከእነዚህ መካከል ኢሰመጉ የ 273 ሰዎችን ታፍኖ የድረሱበት አለመታወቅ በስም ጠቅሶ ይፋ አድርጓል)፣3
እጅግ በተደጋጋሚ ጊዜያት በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች በተቀሰቀሱ የጎሳና የኃይማኖት ግ ቶች ሳቢያ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች
ከቀያቸው ተፈናቅለዋል፣ በሺቆች የሚቆጠሩ ተገድለዋል፣ በ10 ሺዎች የሚቆጠሩ ለከባድና ቀላል የአካል ጉዳት ተዳርገዋል፣ በአስር
ሺዎች የሚቆጠሩ ቤቶች በቃጠሎ ወድመዋል፣ በሚሊዎኖች ገንዘብ የሚገመት የሕዝብና የመንግስት ንብረቶች ወድመዋል። ለዚህም
በተደጋጋሚ ጊዜያት በጋምቤላ፣ በደቡብ ብ/ብ/ሕ/ክ፣ በኦሮሚያ፣ በሶማሌ እና ሌሎች ክልሎች የተከሰቱትን ግ ቶች ማስታወስ
ይቻላል፣
በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ከመንግስት ታጣቂዎች በተተኮሰባቸው ጥይት ተመተው ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል
(ኢሰመጉ 1057 ሰዎችን ስም እና የድረሰባቸውን የጉዳት አይነት ጠቅሶ ገልጿል)፣
መቶ ሺህ የሚጠጉ ዜጎች በፖለቲካ አመለካከታቸ ሳቢያ እና ሕግና ሥረዓትን ባልተከተለ መልኩ ከሥራ ገበታቸው ተባረውና ፍትህን
ተነፍገው ራሳቸውና ቤተሰቦቻቸው ለረሃብና ችግር ተዳርገዋል፣ ገሚሶችም ከቤተሰቦቻቸው ተነጥለውና በቅጣት መልክ ከአንድ
የአገሪቱ ጫፍ ወደሌላ በግዳጅ ተዛውረው እንዲሰሩ ተደርገዋል። ለዚህም በዋነኝነት የተቃዋሚ ፓርቲዎች አባላት የሆኑ እና
የቀድሞው የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር አባላት ተጠቃሾች ናቸው።
ጋዜጠኞች ለተደጋሚ ክስ እና እንግልት ከመዳረጋቸውም በላይ በርካቶች ለአመታት ያህልም በእስር እንዲማቅቁ ተደረገዋል፣ አሁንም
በሽብርተኝነት ምር እየተከሰሱ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ፣ ርዮት አለሙ፣ ውብሸት ታዬ፣ ተመስጌን ደሳለን፣ እና ሌሎችም በእስር
እየማቀቁ ይገኛሉ፣
ጥቂት የማይባሉ ሴቶችም በመንግስት ታጣቂ ኃይሎች ተገደው ተደፍረዋል፣
የመብት ጥያቄ ያነሱ የከፍተኛ ተቋማት እና የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች በተደጋጋሚ ጊዜያት ተገድለዋል፣ ታፍነው ተሰውረዋል፣
በጥይት ቆስለዋል፣ ካኔ በተሞላበት መልኩ ተደብድበዋል፣ ታስረዋል፣ በርካቶችም ከነ አካቴው ከትምህርት ገበታቸው ተባረዋል፣
አገሪቱ በድሃ አቅሟ አስተምራ ያበቃቻቸውም ምሁራን ገሚሶቹ ለሞት ተዳርገዋል (ክቡር ፕ/ር አስራት ወልደየስ፣ አቶ አሰፋ ማሩ፣
እና ሌሎች)፣ በርካቶች ለእስር ተዳርገዋል (ዶ/ር ታዬ ወልደሰማያት፣ አቶ አበራ የማነአብ፣ ፕ/ር መስፍን ወልደማርያም፣ ዶ/ር
ብርሃኑ ነጋ፣ ኢንጂነር ኃይሉ ሻወል፣ ዶ/ር ኃይሉ አርአያ፣ ዶ/ር ያቆብ ኃይለማርያም፣ ለሎች በርካቶች ምሁራን) እንዲሁም በሺዎች
የሚቆጠሩ አገራቸውን ለቀው እንዲሰደዱ ተደርገዋል፣
በአግባቡ ባልተጠና የመንግስት ፖሊሲ ሳቢያ በርካታ ገበሬዎች ከመሬታቸው ተፈናቅለው ከነቤተሰቦቻቸ ለልመና ተዳርገዋል፣
ለሃገራቸው ደፋ ቀና ሲሉ የኖሩና የላቀ አገልግሎት ለሕዝባቸው ያበረከቱ ዜጎች ሳይቀሩ የጡረታ መብታቸውን ተነፍገው ለርሃብ እና
ችግር ተዳርገዋል፣
አገሪቷ በተጋረጡባት ተደጋጋሚ ጦርነቶች፣ እንደ ሰደድ እሳት በተዛመተም የኤድስ በሽታ፣ ሌሎች ማኅበራዊ ቀውሶች ሳቢያ
ወላጆቻቸውን ያጡ ህፃናትን ጨምሮ በርካታ የአካል ጉዳተኞች፣ የገበሬ ልጆች፣ በልመና የሚተዳደሩ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ድሆች
ውሎ አዳራቸውን በአዲስ አበባና በሌሎች የአገሪቱ ከተሞች ጎዳናዎች ላይ አድርገዋል። ከአንዴም በተደጋጋሚ ጊዜ እነዚህ የጎዳና ላይ
ተዳዳሪዎች በመንግስት ታጣቂ ኃይሎች ታፍሰው በመኪና እየተጫኑ በሌሊት ከአዲስ አበባ ው ተወስደው በየጫካው ውስጥ
ተጥለዋል። ገሚሶቹም የአውሬ ቀለብ ሆነዋል። የዚህ ሪፖርት አቅራቢ ይህ ድርጊት ሲፈጸም፤ ማለትም የጎዳና ተዳዳሪዎቹ ታፍሰው
ሲወሰዱ በአይኔ ተመልክቻለሁ። ጉዳዩንም ከተከታተሉት የኢሰመጉ መራሪዎች መካከል አንዱ ነኝ። ኢሰመጉም የጉዳዩን አሳሳቢነት
በመግለጽ ድሃን በማጥፋት ድህነትን ማጥፋት እንደማይቻል በመግለጽ መንግስት ከድርጊቱ እንዲታቀብ በተደጋጋሚ አሳስቧል፣
የተበዳዮችንም ስም ዝርዝሮ አውጥቷ፣
በአገሪቱ ወስጥ ያለውን ሕግና ሥርዓት በመተማመን ለዘመናት ያፈሩትን ቅርስና ሃብት ይዘው ነግደው ለማትረፍ ውድድር ውስጥ
የገቡ ነጋዴዎች መንግስት በየጊዜ በሚያወጣቸው ደንቦችና የውስጥ መመሪያዎች፣ ባለስልጣናት በሚወስዷቸው ሕገ-ወጥ እርምጃዎች
የተነሳ ንብረቶቻቸውን ተነጥቀውና ከውድድር ው እንዲሆኑ ተደርገዋል፣
ጠ/ሚ መለስ ሳይቀሩ ባደባባይ እንደገለጹት በሙስና የተዘፈቁ የመንግስቱ የበላይና የበታች ሹማምንት በጫንቃው ላይ ተሸክሞ
ለሚያኖራቸው ድሃ ሕዝብ ክብር ሳይሰጡ በባዶ ፕሮፓጋንዳ፣ በማያቋርጡ አታካች ስብሰባዎችና ግምገማ፣ አሁን ደግሞ የግዳጅ
“የህዳሴ ግድብ” መዋጮ እያዋከቡት ይገኛል፣
የሙያ ማኅበራት፣ የሲቪክ ማህበራት፣ የሰብአዊ መብት ድርጅቶች፣ እና ለሎች ማህበራት አባላት፣ አመራሮችና ደጋፊዎች ይደርስባቸ
የነበረውን ሕገ-ውጥ አፈና እና ጫና ተቋቁመው በርካታ አገራዊ ተግባራትን ያከናወኑ ቢሆንም መንግስት በተከተለው የተሳሳት
የፖለቲካ ምሪት የተነሳ ገሚሶች ላይ ተለጣፊ ድርጅት በማቋቋም፣ አመራርና ሠራተኞቻቸውን በማሰር እና በማዋከብ ሲያዳክም
ቆይቷል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ መንግስት የበጎ አድራጎት ድርጅቶችንና የሲቪክ ማሕበራትን ለመቆጣጠር ባወጣው አዋጅ ሳቢያ
ብዙዎቹ ማኅበራት ህልውናቸው የሚያከትምበት አፋፍ ላይ ይገኛሉ።
በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያን በአገራቸው ውስጥ በሚደርስባቸው ፓለቲካዊ፣ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጫናዎች የተነሳ
ስደትን ብቸኛ አማራ አድርገዋል። በኢትዮጵያ ታሪክ ሆኖ በማይታወቅ ሁኔታ ኢትዮጵያዊያን ከትንሿ አገር ጅቡቲ አንስቶ
በኤርትራ፣ የመን፣ በበርካታ አረብ አገራት፣ በሱዳን፣ ኬኒያ፣ ኡጋንዳ እና በመንግስት እጦት በምትታመሰው ሱማሊያ እንኳን ሳይቀር4
ሰብአዊ ክብራቸው ተዋርዶ በየሰዉ ቤት በባሪነት አገልጋይ ለመሆን ተገደዋል። በሺዎች የሚቆጠሩም ሰሃራ በርሃን ለማቋረጥ ሲሞክሩ
አሸዋ በልቷቸዋል፣ የዚያኑ ያህል ሰውም ለቀይ ባህር አሳዎች ሲሳይ ሆነዋል። ዛሬ በሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያን ወጣቶች
በጅቡቲ፣ በሲማሌ፣ በሳውዳረቢያ፣ በሊቢያ እና ሱዳን እስር ቤቶች ውስጥ ታጉረው የሕዝብ ያለህ፣ የወገን ያለህ፣ የመንግስት ያለህ
እያሉ በቪ.ኦ.ኤ፣ በጀርመን ድምጽ እና በሌሎች ሚዲያዎች ድምጻቸውን ቢያሰሙም ምላሽ ተነፍገዋል። ከፊሎቹ እራሳቸውን ሲገሉ፣
ቀሪዎቹም ለአዕምሮ መታወክና በርካታ ችግሮች ተዳርገዋል። ይሁንና ዛሬም መንግስት ይህን የክፍለ ዘመኑን የባርነት ንግድን ለዜጎች
በው አገር የስራ እድል መፍጠር በሚል ሽፋን በይፋ ዜጎችን ለአረቡ አለም ባርነት የማመቻቸት ተግባሩን ቀጥሎበታል።
የ1997ቱ ምርጫ እና ያስከተለው መዘዝ
የ1997 ዓ.ም. ምርጫ ተከተሎ “የተሰረቀው ድምጻችን ይመለስ” በሚል የተቀሰቀሰውን ሕዝባዊ አመጽ ለመቀልበስ መንግስት
በንጹሃን ዜጎች ላይ የወሰደው ያልተመጣተነ እርምጃ በሁላችንም አእምሮ ውስጥ ክፉ ጠባሳን ትቶ አልፏል። ጠ/ሚ መለስ የፖሊስ፣
የመከላከያ እና የደኅንነት ክፍሉን ጠቅለው በአንድ ዕዝ ስር በማድረግ ሁሉም ተጠሪነታቸውም ሆነ በቀጥታ ታዛዥነታቸው
ለእርሳቸው መሆኑን በአዋጅ አስነግረዋል። ሠራዊቱንም አፍንጫው ድረስ በማስታጠቀ የገዛ ወገኑን እንዲገድልና እንዲጨፈ ፍ
በይፋ “ከእንግዲህ ወዲህ ጣቱን (የቅንጅትን መለያ ምልክትን) የሚያሳየውን እንቆርጠዋለን” በማለት ለሕዝቡ ማስፈራሪያን፣
ለሠራዊቱ ደግሞ ጠአት ከመቁረጥ አንስቶ ያሻውን እንዲያደርግ ተእዛዝ አስተላልፈዋል። ቃላቸውም መሬት ጠብ አላለም። ጠአቶች
ተቆርጠዋል፣ ታዳጊ ወጣቶች፣ እናቶች እና ሕፃናት ሳይቀሩ በጠራራ ፀሃይ በአዲስ አበባ ጎዳናዎች በአልሞ ተኳሽ የአጋዚ ሠራዊት
አባላት ግንባርና ደረታቸውን እየተመቱ ወድቀዋል። ይህን አሰቃቂ የሆን የግድያ ተግባር የሚያሳዩ ፎቶዎች ከዚህ በታች በአባሪነት
ስለቀረቡ መመልከት ይቻላል። ይህ ክስተት ወላጆች እንደገና ወደ ኋላ ዞር ብለው በደርግ ዘመን በአገሪቷ ውድ ልጆች ላይ
የተፈጸመውን አሰቃቂ ድርጊት እንዲያስታውሱ አድርጓቸዋል። ከአስርት አመታት በኋላም በተመሳሳይ መልኩ በአደባባይ
በልጆቻቸው እና የልጅ ልጆቻቸው ላይ የጥይት ናዳ ሲወርድ በማየታቸውም ክፉኛ ደንግጠዋል። እናቶች ወደ አምላካቸው አንጋጠው
ተሟግተዋል፣ አማረዋል። እዚህ ላይ አንዲት በሰኔው እልቂት ልጃቸው በጥይት የተገደለባቸው እናት ቤተክርስቲያን ደጃፍ ቆመው
ወደ ሰማይ በማንጋጠጥ እግዚያብሔርን “ወዴት ነው ያለኸው? ወይ ፍረድ ወይ ውረድ” እያሉ ተስፋ በቆረጠ ስሜት ከአምላካቸው
ሲሟገቱ በአይኔ ተመልክቻለሁ።
ወጣቶችም በተፈጠረው እና ባረፈባቸው የ ካኔ በትር ደንግጠው በአገራቸው ላይ፣ በሥርዓቱ ላይ እና ድርጊቱን በፈጸሙባቸውና
ባስፈጻሚዎቹ ላይ ቂም አርግዘው ደማቸውን እያበሱ ገሚሶች ተሰደዋል፤ ቀሪዎቹም ተሸማቀውና ደንግጠው አገራዊ በሆኑ ጉዳዮች
ላይ መሳተፍ፣ መብትን መጠየቅ እና ለእውነት ባደባባይ ወጥቶ መሟገት የማያዋጣና የተሳሳተ መንገድ አድርገው ደምድመው ጎመን
በጤና ብለዋል። የምርጫውን ሂደት በታዛቢነት፤ በሰኔ ወር 1997 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ከተማ የተከሰተውን ግ ት ደግሞ በኢሰመጉ
የምርመራ ሥራ ላይ በመሆን ለመታዘብ ችያለሁ። ምንም እንኳን በዚህ ወቅት ስለተፈጸሙት ክስተቶች እና ስለምርጫው ሂደት ብዙ
የተጻፈና የተነገረ ቢሆንም ከታዘብኩዋቸው ዋና ዋና የሰብአዊ መብት ጥሰቶች መካከል የተወሰኑትን ለመጥቀስ እወዳለሁ።
በሰኔ 1997ቱ እና በጥቅምት 1998 ዓ.ም. በአዲስ አበባ እና በሌሎች የአገሪቱ ክፍሎች በተከሰተው ግ ት የበርካቶች ህይወት
አልፏል። በመቶዎች በጥይት እሩምታ ቆሳስለዋል፤ የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል። መንግስት እራሱ የሰየመው አጣሪ ኮሚሽን
የነበሩበትን በርካታ ጫናዎችና ወከባዎች ተቋቁሞ ባከናወነው ምርመራ 193 ሰዎች በግፍ መገደላቸውን፣ ከ700 በላይ በጥይት
መቁሰላቸውን አረጋግጧል። በእኔ ትዝብት የሟቾቹ ቁጥር በአጣሪ ኮሚሽኑ ከተገለጸው ቁጥርም አጅግ ከፍ ያለ ይሆናል የሚል ነው።
ለዚህም እንደ ግምቴ እንደ ማረጋገጫ የምጠቅሰው ቁጥራቸው በርካታ የሆኑ ሰዎች በፖሊስ ሆስፒታል እና በጦር ኃይሎች ሆስፒታል
የአስከሬን ማቆያ ክፍሎች ታ ቀው እንዲቆዩ የተደረገ መሆኑን። ከዚያም ማንነታቸውን የሚገልጽ ምንም አይነት ሰነድ (መታወቂያ)
በኪሳቸው ውስጥ ያልተገኘውን እና በቀጣዮቹ ቀናት ውስጥ አስከሬናቸው እንዲሰጠው ጠያቂ የሌላቸውን በርካታ ሰዎች በጥቁር
ላስቲክ እየተጠቀለሉ ከአዲስ አበባ ወጣ ብሎ ወደ ሰበታ በሚወስደው መንገድ ዳርቻ በአንድ ትልቅ ጉድጓድ ውስጥ በሌሊት በጅምላ
የተቀበሩ ስለመሆኑ በወቅቱ መረጃዎች ደርሰውናል። በእኔ እምነት እኒዚህ ግለሰቦች በአዲስ አበባ አውራ መንገዶች ላይ የሚኖሩ
የጎዳና ተዳዳሪዎች ናቸው። በተደጋጋሚ ጊዜያት ለምርመራ ሥራ በተለያዩ የአዲስ አበባ ሆስፒታሎች በመዘዋወር የአስከሬን
ክፍሎቻቸውን የመጎብኘት እድል ነበረኝ። በነዚህ ክፍሎች ውስጥ በማናቸውም አጋጣሚ ይሁን ሞተው አስከሬናቸው የሚመጣ
የጎዳና ላይ ተዳዳሪዎ እና በልመና የሚተዳደሩ ሰዎች ፈላጊ ስለሌላቸው ለተወሰኑ ቀናት አስከሬናቸው እንዲቆይ ከተደረገ በኋላ
በማዘጋጃ ቤት ተወስደው ይቀበራሉ።
በጥቅምት ወር 1998 ዓ.ም. በተከሰተው እልቂት ደግሞ በመንገድ ላይ ከተፈጁት ሰዎች በተጨማሪ 60 ሰዎች በቃሊቲ ማረሚያ ቤት
ውስጥ በጥይት ተደብድበው ተገለዋል። በወቅቱ መንግስት 13 እስረኞች ብቻ ሊያመልጡ ሲሞክሩ የተገደሉ መሆኑን መግለጫ
መስጠቱ ይታወሳል። ይሁንና በበቂ ማስረጃ ለማረጋገጥ እንደተቻለው ግለሰቦቹ የተገደሉት ሊያመልጡ ሲሞክሩ ሳይሆን የተወሰኑ
ታሳሪዎች ከእስር ቤቱ ጠባቂዎች ጋር መጋ ታቸውን ተከትሎ ነው። ታሳሪዎቹ ዙሪያው በቆርቆሮ በተሰራ ክፍላቸው ውስጥ እንዲገቡ
ከተደረገ በኋላ በሩን ከው እንዳይወጡ በመቆለፍ የጥይት ናዳ አውርደውባቸዋል። በክፍሉ ውስጥ ከነበሩት መካከል ስልሳዎቹ
ሲሞቱ የተወሰኑት የመቁሰል አደጋ ደርሶባቸዋል። የሟቾቹን ስም እና ዝርዝር የአሟሟታቸውን መግለጫ በሜይ 15፣ 2006 ዓ.ም.
ለአውሮፓ ፓርላማ ባቀረብኩት የምስክርነት ቃል ላይ አካትቼዋለሁ።
1

1
http://www.powershow.com/view/48caNTA4O/Testimony_by_Yared_Hailemariam_Human_Rights_Defender_Ethiopia_to_flash_ppt_presentation5
እንግዲህ ለእነኚህ ሁሉ ወንጀሎች እና አሰቃቂ ተግባራት ተጥያቂው ማን ነው?
እነኚህና ሌሎች በርካታ የሰብአዊ መብቶች ረገጣዎች የተፈጸሙት ዛሬ ታላቅነታቸውና ኃያልነታቸው፤ እንዲሁም ባለ ህራዕይ እየተባለ
የሚዘፈንላቸው፣ የሚገጠምላቸው፣ ሙሾ የሚወርድላቸው ጠ/ሚ መለስ ዜናዊ አገሪቱን ሲያስተዳድሩ በቆዩበት 21 አመታት ውስጥ
ነው። እርግጥ ነው አቶ መለስ በቆዩበት የሥልጣን ዘመን ውስጥ ያበረከቷቸው በጎ እርምጃዎች ይኖራሉ። ሆኖም በሥልጣን የቆዩበትን
ጊዜ ጨምሮ ሕልፈተ ሕይወታቸው ለሕዝብ ከተገለጸበት ጊዜ ጀምሮ የመንግሥት ልሳን በሆኑት የመገናኛ ብዙሃን እና ለሥርዓቱ
ቅርበት ያላቸው የዜና ማሰራጫዎች በጠቅላላ ማባሪያ በሌለው መልኩ ጠ/ሚኒስትሩ ያደረጉትንም ሆነ እንዲያደርጉ
የተመኙላቸውንም ምር እያጋነኑና እየደጋገሙ ሕዝብ እስኪማረር ድረስ እየዘገቡ ስለሆነ ጊዜዬኝ በዚህ ጉዳይ አላጠፋም። የዚህ
ጽሑፍ አላማም አይደለም። ይህን ባለማድረጌም በአንባቢዎቼ ዘንድም ላስተላልፍ የፈለኩትን መልዕክት ሚዛናዊነት የጎደለው
እንደማያድርግብኝ ተስፋ አደርጋለሁ።
ከላይ የዘረዘርኩትን በአሃዞች የተደገፈ ጥቅል መረጃ የበለጠ ተአማኒ ለማድረግ ከዚህ የሚከተሉቱን ሰነዶች በአባሪነት፦ በኢሰመጉ
መግለጫዎች የተካተቱትን ዋና ዋና የሰብአዊ መብት ጥሰቶች በአ ሩ የሚያመላክት ሠንጠረዥ እና መናልባት ከዚይ ቀደም ሰነዱን
ለማየት እድሉ ያልገጠማችሁ ሰዎች ካላችሁም በሜይ 15፣ 2006 በአውሮፓ ፓርላማ ኢትዮጵያን በሚመለከት ተዘጋጅቶ በነበረው
የምስክርነት መድረክ ላይ ተገኝቼ የግንቦት 1997 ዓ.ም. ምርጫን ተከትሉ በአዲስ አበባ በሰኔ እና ጥቅምት ወራት በአዲስ አበባ
ከተማ ውስጥ በጠ/ሚ መለስ ዜናዊ ቀጥተኛ ትእዛዝ የአጋዚ ጦር በንጹሃን ዜጎች ላይ ያደረሰውን አሰቃቂ ፍጨፋ የሚያሳዩ
ፎቶግራፎችን ከዚህ በታች በአባሪነት አያይዣለሁ። ከጉዳዩ አጣዳፊነት የተነሳ፤ ማለትም ጠ/ሚ መለስ ዜናዊን ቅዱስ መሪ፣ እንኳን
ይህን ያህል ሰብአዊ ቀውስና ጉዳት ያደረሱ ይቅርና አንድም ግድፈት እንደ ሰው እንኳን ያልፈጸሙ አድርጎ ለማቅረብ እየተደረገ ያለው
ዘመቻ በፈጠረብኝ ግፊት የተነሳ ማካተት የሚገቡኝን ሰነዶች እና መረጃዎች ያላካተትኩ መሆኑ ለመግለጽ እወዳለሁ። ይሁንና በዚህ
ጽሑፍ የተካተቱት መረጃዎች ለሚተረከው ገድላቸውም ይሁን በቀብራቸው እለት የሚነገረው የሥልጣን ዘመን ታሪካቸው ተጓድሎና
ተንሻፎ ለሕዝብ እንዳይቀርብ፤ እንዲሁም ባሰለጠኑዋቸው ካድሬዎቻቸውም የሚነገረው ውሸትና እጅግ የተጋነነ የጠ/ሚኒስትሩ በጎ
ስብዕ ብቻ ተደጋግሞ ሲነገር በብዙ የዋህ እና ወጣት ኢትዮጵያዊያን ዘንድ እውነት ተደርጎ እንዳይወሰድ በማሰብ ሰብአዊ መብቶችን
በማስከብር፣ ዴሞክራሲያዊ ሥርአትን በመገንባር እና የሕግ የበላይነት በማረጋገጥ እረገድ ጠ/ሚ መለስ ያልተሳካላቸ መሪ ብቻ
ሳይሆን የታሪክ ተወቃሽ መሆናቸውን ምር ለማስገንዘብ ይረዳል የሚል እምነት አለኝ።
ማጠቃለያ
ከላይ በአ ሩ የዘረዘርኳቸውን ጥቂት እና ሌሎች ከዚህ ጽሑፍ መነሻ አላማ ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት የላቸውም በሚል ያልጠቀስኳቸው
በርካታ አገራዊ ጉዳዮችን እና ክስተቶችን መሰረት በማድረግ የአቶ መለስ ዜናዊን ኢሕአዲግዊ የአገዛዝ ዘመን በአግባቡ መገምገም
ተገቢ ነው ብዬ አምናለሁ። ከላይ የተጠቀሱት የሰብአዊ መብት ጥሰቶች፣ በዘር ላይ ያነጣጠሩት ጥቃቶች፣ በሰው ዘር ላይ የተፈጸሙት
ወንጀሎች ፍትህ በተጓደለባት፣ ኃያላና አገሮች በጸረ-ሽብር ዘመቻ ስም በሚያካሂዱት የራሳቸውን ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ጥቅም
ለማስከበር ሲሉ ለአምባገነኖች መሸሸጊያ ዋሻ የሆኑበት አለምና ጊዜ ላይ ስላለን ነው እንጂ ጠ/ሚ መልስ በሕይወት በነበሩበት ዘመን፣
ቀሪዎቹ አጋር የኢሕአዴግ ባለሥልጣናት እስካሁን በቆዩበትም ዘመን ይሁን ወደፊ በአለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ቀርበው
በተፈረደባቸው ነበር። ይሁኝና ይህ ሁኔታ ቢያንስ በጠ/ሚ መልስ ላይ አልሆነም። ባልንጀሮቻቸውም ሆኑ ሌሎች ከሳቸው ስህተት
ለመማር እድል አላገኙም። እንዳያያዛቸውም ከሆን የሚማሩ አይመስሉም። ለዚህም የጠ/ሚትሩ ሞት በተነገረበት ሳምንት ውስጥ
የፍትሕ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ የሆነው ወጣት ተመስጌን ላይ የተፈጸመው ተግባር ጥሩ ማሳያ ነው።
አለም ለእውነት፣ ለፍትሕ፣ ለዴሞክራሲ፣ ለሕግ-የበላይነት፣ ለተገፉ ሰዎች የምትቆምበት ዘመን እሩቅ ነው ብዮ አላምንም። ያ ቀን
እስከመጣ ግን ቢያንስ አጥፊዎቻችንን፣ ሰብአዊ መብቶቻችንን፣ ነጻነታችንን፣ ሰብአዊ ክብራችንን፣ ኢትዮጵያዊነታችንን አደጋ ላይ
የሚጥሉ ሰዎችን በቅጡ ለይተን ማወቅ የገባናል። ፍጹም ሰላማዊ በሆነ መንገድም ልንቃወማቸውን እና ልንታገላቸው ይገባል። ይህ
ባይሆንል እንኳ ቢያንስ አብረናቸው ላንሰለፍ እና ለጥፋታቸው ኃይል ወይም በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ተባባሪ ላለመሆን መወሰን
ይኖርብናል። የጠ/ሚ መለስ ዜናዊን ፍጹምነት አንዳንዴም ቅዱስ አድርጎ የማቅረብ አዝማሚያ በአገዛዛቸው ዘመን በተገደሉት፣
በታሰሩት፣ ታፍነው የደረሱበት ባልታወቀ እና ለስቃይና እንግልት በተዳራጉት ንጹሃ የአገሪቱ ዜጎች ላይ መፍረድ ነው የሚሆነው።
እንግዲህ ማቅ ለብሰን፣ እራሳችንን ጎድተን ካለቀስን እና ካዘንን አይቀር ለጠ/ሚ መለስ ብቻ ሳይሆን፤
በግፍ ሕይወታቸ ለተቀጠፈ በሺዎች የሚቆጠሩ የአገሪቷ ብርቅ ልጆችም እናልቀስ፣
ከሕግ አግባብ ውጪ በኢሕአዴግ ወታደሮችና የጸጥታ ኃይሎች ታፍነው ተወስደው እምጥ ይግቡ ስምጥ ሳይታወቅ አመታትን
ላስቆጠሩት ኢትዮጵያዊያን እና ደጅ ደጁ እያዩ ታፍኖ የተሰወረባቸው የቤተሰብ አባል አንድ ቀን በሕይወት ይመጣ ይሆናል እያሉ
ለሚጠባበቁት ልጆቻቸው፣ የትዳር አጋሮቻቸውና ቤተሰቦቻቸም እናልቅስ፣
በኢሕአዴግ ታጣቂዎች ተወስደው በየእስር ቤት ለተጣሉት፣ አሰቃቂ የሆነ ድብደባ ተፈጽሞባቸው ለሕልፈተ ሕይወት ለተዳረጉት፣
እርጉዝ ሴቶች በዱላ ብዛት ደም አማቷቸው ስንሳቸውን እስር ቤት ላስወረዱት፣ ለአመታት በጨለማ ክፍል እንዲቆዩ በመደረጉ
የአይናቸውን ብርሃን ላጡት፣ በዱላ ብዛት ለአካለ ጎዶሎነትና ከባድና ቀላይ የአጋል ጉዳል ለደረሰባቸው ንጹ ወገኖቻችንም እናልቀስ፣
ከወያኔ ሲሺሹ ሰሃራ በርሃ እና ቀይ ባህር፤ እንዲሁም በየሜዳው ለቀሩት ወገኖቻችንም እናልቀስ፣6
በድህነት ለሚኖረው፣ ቁራሽ አጥቶ በየቄየው ለሚደፋት፣ ባለፉት አርባ አመታት በእርስ በርስ ጦርነት እና በኤድስ ላለቁት ወገኖቻችን
ሁሉ እናልቀስ!
እንግዲህ ማዘን እና ሐዘናችንን፣ ቁ ታችንን፣ ብሶታችንን በለቅሶ የምንወጣው ከሆን አብረን ብሔራዊ ለቅሶ እናድርግ። ምናልባት
ብሶት የፈነቀለው የእምባችን ጎርፍ ድህነትን፣ ቆናን፣ አምባገነንነትን፣ የሰብአዊ መብት እረገጣዎችን፣ ዘረኝነትን፣ ሙስናን፣
ፍርሃትን፣ ግለኝነትን እና ለሎች ጎጂ ስንክሳሮቻችንን ሁሉ ጠራርጎ ይወስድልን ይሆናል። ህዳሴያችንም ይቃረብ ይሆናል። ያኔ አባይን
ብቻ ሳይሆን ዜጎቿ በእኩልነት ተከብረውና ኮርተው የሚኖሩባት፣ ዜጎቿ ሸሽተው የሚሰደዱባት ሳትሆን የተከፉ የው ስደተኞችን
ተቀብላ የምታስተናግድ፣ በርሃብ፣ በጦርነት፣ በስደት እና በሰባዊ መብት እረገጣ ሳይሆን በልማት፣ በእድገትና ብልጽግባ የምትታወቅ
ታላቅ ኢትዮጵያን መገንባት እንችላለን።

እግዚያብሄር ጽናቱን ይስጠን!
ኢትዮጵያ ለዘለአለም ትኑር!
“ሁሉም ሰብአዊ መብቶች ለሁሉም!”
ያሬድ ኃይለማርያም
የቀድሞ የኢሰመጉ የምርመራ ክፍል ባልደረባ
ነሐሴ 24 ቀን 2004 ዓ.ም.

ኢትዮሚድያ – Ethiomedia.com pls click here full report     http://www.ethiomedia.com/2012_report/ethiopia_human_rights_violations_1991_2012.pdf
August 31, 20127
Figures of Human Rights Violation in Ethiopia from 1991 – 2012:
Reported by EHRCO and other HR organizations
Table No. 1:
Source Extrajudicial Killings Beating and Torture Unlawful detention Disappearance Shot and Wounded
EHRCO 2632 997 14,308 273 1057
Human Rights Watch,
March 2005 Vol.17, No.3
(A)
2
424 – – – –
Ethiopian Inquiry
Commission (2005)
193 – 20,000 – 760
Table No. 2: EHRO’s Regular and Special reports
EHRO’s Regular and Special reports and their date
of released
Extrajudicial
killings (2632)
Beating and
Torture (997)
Unlawful
detention
(14,308)
Disappearance
(273)
Shot and
Wounded
(1057 )
1sr Regular Report (December 12, 1991) – – 1106 2 –
2
nd
Regular Report (February 13, 1992) – – 1720 – –
3
rd
Regular Report (July 16, 1992) 345 11 2147 24 60
4
th
Regular Report (January 21, 1993) 32 8 461 32 10
5
th
Regular Report (June 3, 1993) 13 8 66 7
6
th
Regular Report (January 4, 1994) 106 7 2154 13 3
7
th
Regular Report (August 1994) 68 – 42 30
8
th
Regular Report (June 1995) 15 6 450 25
9
th
Regular Report (January 1996) – 15 – –

2
HRW’s report : Targeting the Anuak: Human Rights Violations and crimes against humanity in Ethiopia’s Gambella Region8
10
th
Regular Report (September 1996) 24 18 2 6 10
11
th
Regular Report (December 10, 1996) 1 2 43 – 1
Special Report 12th (March 27, 1997) – (A.A.U.
Students)
3
212
– – –
Special Report 14th (May 13,1997) (Assefa Maru)
1
– – – –
Special Report 19
th
(December 1, 1997) 3 – 16 5 –
12
th
Regular Report (November 1997) 22 2 125 14 –
Special Report 20th (May 16, 1998)
4
– (Husband and
wife) 2
– –
13
th
Regular Report (November 1998) 2 + 150
5
– 3 4
14
th
Regular Report (March 1999) 7 17 3 19 4
Special Report 26
th
(June 11, 1999)
6
1 8 107 – 2
Special Report 27th (December 13, 1999)
7
7 10 78 2 11
15
th
Regular Report (December 16, 1999) 6 3 11 12
Special Report 29th (February , 2000) – – 70 – –

3
Addis Ababa University students attempted to hold a peaceful demonstration on March 21, 1997 to protest against the discriminatory land redistribution that is being
implemented by the Amhara Regional State as well as the illegal detention of farmers in connection with the redistribution.
4
At 5:00 AM. on September 18, 1997, Mrs. Menbere Abebe and her husband Mr. Qale’ab Tesfahun* were taken away from their home in Woreda 9, Qebele 11, House no.
641 by seven policemen in uniform and plainclothes. The policemen also searched their house and took away cassettes recorded with songs, a tape recorder, two Citizenbrand female wrist watches, and two photo albums containing photographs. The couple were then shoved into a Land Cruiser and driven to Woreda 20 Police Station, where
Mrs. Menbere was asked to produce the Mercury that her husband had allegedly hidden. She replied that she didn’t know what Mercury was. Then in the presence of other
policemen the chief of Zone 2 Police Station, Tagay Agazi, threatened to have her whipped until her back grew maggots unless she confessed about the secret Mercury. He
then ordered that she be detained. … Furthermore, after making her stand for hours facing the wall with her hands raised, they whipped her back. During this torture she
began to bleed and suffered a miscarriage. After her miscarriage, Mrs. Menbere had been bleeding for 23 days while under detention and without getting any medical aid.
5
More than 150 people killed on July 22, 1998, following the conflict occured between the Guji Oromo and the Gedo tribes in Borena Zone, Hageremariam Wereda
6
On May 25, 26 and 28, 1999 armed, government agents committed cruel and inhuman beatings, torture, illegal detentions, and extra-judicial killing on peaceful citizens that
had gathered to mourn the death of Professor Asrat Woldeyes, founder and leader of the All Amhara People’s Organisation (AAPO) and a person who had served the
Ethiopian people in various ways and, especially, as a medical practitioner for more than half his life.
7
Human Rights Violation in North Omo 9
Special Report 31
st
(April 20, 2000)
8
1 9 18 –
Special Report 33
rd
(March 2000)
9
– 8 48 3 2
Special Report 34th (September 18, 2000)
10
8 – – – –
16
th
Regular Report (September 18, 2000) 8 8 87 5 1
Special Report 35th (November 2, 2000) 75 33
Special Report 37
th
(January 23, 2001) 4 13 53 – 3
Special Report 38th (February 23, 2001)
11
103 35 3 (2 EHRCO’s
investigators and
one EHRCO’s
supporter)
4 22
Special Reporter 39th (February 2001)
12
– – 1 – –
Special Reporter 41st (April 30, 2001)
13
– 45 – – –
Special Reporter 43rd (May 9, 2001)
14
2
Special Report 45
th
, (June 15,, 2001) 67 Many of the
detainee were
234 – 253

8
Human Rights Violation that occured durring and after the clashes between security force and students of Ambo comprehensive Secondary school on March 9, 2000.
9
Human rights violation in Nekemte
10
Beginning in March 2000, council members as well as administrative officials in Eastern Wellega in general and especially in Seredeno, Abidengero, Ghida
Kiramo, and Awaro weredas, caused the burning of houses and churches, the looting of household and church property, including cattle and other domestic
animals, the illegal detention, beating and wounding of people whose exact number is unknown at present as well as the death of eight Amhara peasants who
had been either displaced from their original region or brought for resettlement purposes. Eight persons were also killed in the conflict. These wereda and
regional officials were direct participants in the illegal actions taken against the Amhara peasants. In doing so, they are responsible for leading toward ethnic
conflict and the disruption of the culture of respect and tolerance that had characterised the historical relationship of the Oromo and Amhara living in the area.
11
Ethinic and religious conflict in Eastern Wellega and Harar town.
12
Illegal arrest of the editor of Tomar
13
Children who are less than 10 years of age and without parents, parents who have lost their houses due to different reasons, shoeshine boys, news paper venders and others
who are forced to make the street their home have been victims of this illegal and inhuman action of the government. Since February 2001, the government is taking similar
measures in Addis Ababa against street children.
14
Prof. Mesfin Woldemariam and Dr. Berhanu Nega have been detained in the morning of 8
th
May 2001, claiming that Federal Police had evidence that they had incited the
A.A.U. Students to riot.10
tortured
17th Regular Report ( 2001) 18 – 769 3 7
Special Reporter 48th (April 2002)
15
5 – 18 10
Special Report 49
th
(2 May 2002)
16
24 – 25 – 6
Special Report 51
st
(June 4, 2002)
17
25 – 36 – 26
Special Report 52
nd
(July 1, 2002)
18
– 200 – – –
18th Regular Report (August, 2002) 229 – 239 3 17
Special Report 54
th
(September 6, 2002) 5 2 – – 1
Special Report 55
th
(September 6, 2002)
19
60 – – – 41
Special Report 57th (December 3, 2002)
20
– – 73 – –
19
th
Regular Report (May 19, 2003)
21
494 – 14 1 67

15
Human rights violation committed in Oromiya region against students
16
Conflict resulted in many deaths in Tepi, Shekicho zone, in March 2002.
17
Serious human rights violations in Awassa and its environs on May 24, 2002.
18
People in the street who take shelter in verandahs and lying by the roadsides in various localities in Addis Ababa were rounded as of June 11, by the Federal Police Special
Security forces, whisked off to the outskirts of the city and dumped in forests. …. On June 11/2002 the police rounded nearly 200 people in the street, loaded them into police
trucks, and dumped them at 1:00 a.m. in a forest called “Gorfu”, located at a distance of 55 kms from Addis Ababa. The ages of the people in the street that were dumped in
the forest ranged from 11 to 65. These included, blind people, pregnant women, physically handicapped people who either crawl or use crutches, and demobilized EPRDF
soldiers.
19
Great destruction caused in conflict between Agnuak and Nu-er Tribes, on July 7/2002.
20
Members of the Federal Special Police Force have on November 18/2002, severely beaten up and highly inconvenienced the clergy and monks who were rendering
spiritual services as well as the laity and Sunday School students who had congregated in the sacred pre-cincts of Mahdere Sibhat Holy Lideta Mariam and Debre Medhanit
Medhanealem Church. Many people have been clobbered and received light and serious physical injuries as a result of the forceful action that was taken by members of
the Federal special police force. On that very date, many people were rounded up in the church’s premises, crammed in trucks and whisked off to Wereda 22 Police
Station. According
21
From the total number of killed 484 of them were refugees who died because of lack of medical treatment. 11
Special Report 62
nd
(June 23, 2003)
22
1 – – – –
Special Report 66th (October 15, 2003)
23
39 – – – –
Special Report 67th (October 23, 2003)
24
– 1 – – –
20th Regular Report (December 24, 2003) 34 5 244 1 28
Special Report 71th (December 30, 2003)
25
18 – – – 21
Special Report 72nd (January 5, 2004)
26
102 – – – 42
Special Report 73rd (January 24, 2004)
27
14 – – – 20
Special Report 74th (February 2004)
28
– – 357 – –
Special Report 75th (25 March 2004) – – – 5 –
Special Report 76th (5 April, 2004) 1 1 48 – –
Special Report 77th (19 April, 2004) – – 4 – –
21st Regular Report (May 8, 2004) 2 36 140 6 3
22nd Regular Report (September 3, 2004) 20 10 9 – 20

22
This report describes EHRCO’s investigation and findings regarding the illegal detention and death of Ato Abera Hey while under the custody of the Addis Ababa police
criminal investigation.
23
Another Ethinic conflict in Bench-Maji Zone. As a result of the conflicts that kept flaring up now and then, many farmers were displaced from their homes in
Toom and Jebba weredas since July 2002.
24
Ato Araya Tesfa Mariam (the victim) is a resident of Yeka sub-municipality, kebele 06; house number 404.He is 28 years old and is father of a 9-year-old girl. He had
been a reporter for The Reporter newspaper from1996-1998. … three men in Federal Police uniform came out of their hiding place in the dark and hit him twice on the head
by a ball-pointed iron rod. When he fell to the ground, the men continued to hit him with the iron rod. While laying on the ground, Ato Araya heard one of the men ordering
in Tigrigna, to kill him and the other one responding that he was dead. Then, the attackers went to their car and, put the car’s lights on and watched the situation of their
victim. Then, they lifted him up, took him to the Abo Bridge and threw him into the riverbed under the bridge. He fell on a rocky ground in the river. The bridge is 5-6 meters
high.
25
An Ethnic Conflict Flared up in West Harrarge Zone between Oromos and Somalis.
26
A ferocious attack committed in Gambella region, in attacks launched against the Anuaks in the Gambella Region on 12 and 13 December 2003,many were killed and
wounded and a considerable amount of property was damaged. Thousands have fled their homes to the jungles. Children and older people who could not flee the attacks were
also killed and wounded. HRW on March 2005 Vol.17, No.3 (A), reported that 424 Anuaks have been killed in Gambella.
27
Another round of Ethinic conflict flared up in West Harrarghe Zone
28
Human rights violation committed against oromo students of Addis Ababa University.12
Special Report 79th (September 21st, 2004)
29
6 – – – 19
Special Report 80th (October 19, 2004) 32 14 – –
Special Report 83rd (June 9, 2005)
30
– – 1 – –
Special Report 84th (July 5, 2005)
31
36 12 97 17 35
24th Regular Report (March 20, 2006) 5 54 284 – –
Special Report 90th (December 6, 2005) 34 – 358 28 62
Special Report 94th (June 30, 2006) 3 – 184 – 8
25th Regular Report (August 2006) 19 14 237 – 6
Special Report 95th (December 2006)
32
– 4 – – –
26th Regular Report (September 2006) 8 54 81 – –
Special Report 96th (October 31st, 2006) 1 – – – 14
Special Report 97th (November 30, 2006) 19 8
27th Regular Report (May 2007) 9 11 43 5 19
Special Report 101st (June 8, 2007) 13 33
28th Regular Report (September 20, 2007) 17 13 201 3 25
Special Report 103rd (October 2007) – – 26 – –
Special Report 104th (November 26, 2007)
29th Regular Report (January 2008) 17 16 244 3 –
30th Regular Report (May 2008) 18 69 176 – 16
31st Regular Report (July 2008) 147 7 18 1 –
Special Report 106th (January 31, 2008) 4 5
Special Report 107th (February 28, 2008) 33 – – – 49

29
Human rights violations vomited by government security forces in Dire Dawa Town.
30
One of EHRCO’s investigators arrested following the June 8, 2005 clash between students and security force in Addis Ababa.
31
Human rights violations committed by the government against citizens following issues of rights raised by the Addis Ababa University students.
32
Mistreatment of prisoners and their visitors: in the case of journalist Eskindir Nega, opsition leader Andualem Arage and others. 13
Special Report 109th (May 7, 2008) 23 8
Special Report 110th (June 10, 2008) 46 – – – 25
Regular Report 34th (November 17, 2010) 2 5 24 2
Special Report 114th (February 2011) 1 – 13 – 1
Special Report 116th (July 2011)
33
10 – 89 – –
Special Report 117th (July 2011) 1 – 6 – –
Regular Report 35th (December 2011) 1 10 18 1
Special Report 118th (December 2011)
34
– – 20 – –
Special Report 119th (December 2011)
35
35
Special Report 120th (March 2011)
36
– – 120 – –

33
Continuous conflic in Kenba Woreda, Konso Zone, Southern Nations, Nationalities and Pooples’ Regional State demands a lasting solution.
34
Aribitrary detention and the denial of the right to cultural self-determination in Kaffo Zone, SNNP Region.
35
Illegal dispossession of land and arbitrary detention in the Southern Nations, Nationalities and People’s Region.
36
Harasments and unlawful detentions committed against the AEUP members in SNNP Regional state.

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 12 years ago on September 3, 2012
  • By:
  • Last Modified: September 3, 2012 @ 6:40 pm
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar